ተአምርየቅዱስ ገብርኤል ተአምር 3 ኪሎ እጢ በጸበሉ ምክንያት የወጣላቸው እናት

(አንድ አድርገን ታህሳስ 21 2007 ዓ.ም)፡- በየዓመቱ ታህሳስ እና ሀምሌ 19 በሚከበረው በዓለ ንግሥ ላይ የተለያዩ ሰዎች ከለተያዩ ቦታዎች የሚመጡ የተደረገላቸው ተዓምራትን ለመናገር አውደ ምህረቶችን ሲያጨናንቁ ፤ መርሀ ግብር መሪዎች  አንዱን ሰምተው አንዱን መተው እስኪያቅታቸው ድረስ ለማስተናገድ እስኪቸገሩ ድረስ አውደ ምህረትን ሲያጣብቡ ይስተዋላል፡፡ በዚህኛው ዓመት ከቀናት በፊት ታህሣስ 19 ቀን 2007 ዓ/ም በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን (ግቢ ገብርኤል 4 ኪሎ) አንድ እናት በአውደምህረት የተደረገላቸውን ተዓምር ሲናገሩ  ‹‹በመጀመሪያ ከማህፀኔ ቀይ ደም ለብዙ ጊዜ ይፈሰኝ ነበር ቀጥሎ ግን ነጭ የሚመስል ነገር ከማህፀኔ መፍሰስ ቀጠለ ፤ በዚህ ምክንያት ህይወቴና ኑሮዬ መበጥበጥ ጀመረ ፤ የረጅም ጊዜ የትዳር አጋሬ የልጆቼ አባት ትዳሩን ትቶ በበሽታዬ ምክንያት ጥሎኝ ሄደ ፤ በዚህም ማዘኔ ሳይበቃኝ የረጅም ጊዜ ጓደኞቼ ሸሹኝ አገለሉኝ፡፡ ከሰው የሚቆጥረኝ ሰው ጠፋ ፤ በበሽታዬ ምክንያት ከሰው ተገለልኩኝ፡፡››
እኔም አምላኬንና ፈጣሪዬን እንዲህ ብዬ መማፀን ጀመርኩ ‹‹የእዛችን  ለ12 ዓመታት ደም ሲፈሳት የነበረችው ምስኪኗን ሴት እንደማርክ እኔንም ማረኝ ›› እያልኩ መፀለይ ጀመርኩ።መንበረ መንግሥት ግቢ ገብርኤል በመምጣት ፀሎት አድርጌ ፀበል ጠጣሁኝ ፤ ፀበሉን በጠጣሁ በአስረኛው ቀን ከባድ ምጥ ያዘኝ አምጬ 3 ኪሎ የሚመዝን እጢ ተገላገልኩኝ።
ይኸው ዛሬ እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን ከዛ ሁሉ ችግር ተላቅቄ ከፊታቹ ቆሜያለሁ ፤ ወንዶች በጭብጨባ ሴቶች በእልልታ ፈጣሪያችሁን እና መልአኩ ገብርኤልን አመስግኑልኝ በማለት ሲናገሩ በቦታው በአሉን ለማክበር የተገኝ ምዕመን በተደረገው ተዓምር በመገረም እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
ምህረቱን ከእኛ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን
-------------------------------------------
  የዘብር ገብርኤል ድንቅ ተአምር

(ኅዳር 19 2007 ዓ.ም)፡-አንድ እናት ናቸው ልጅ ሳይወልዱ እንደ ኤልሳቤጥ እድሜያቸው የገፋ ወገባቸው የታሰረ ናቸው፡፡ የአብራካቸውን ክፋይ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔርን አብዝተው ይለምኑት ነበር፡፡ ጸሎታቸው ሰምሮ በእግዚአብሔር ፈቃድ ልጅ ይወልዳሉ፡፡ ልጅ ጐበዝ ተማሪ ሆኖ ያድግና የትምህርት እድል አግኝቶ ወደ ውጭ ሀገር ይሄዳል፤ እዛው ስራ ይጀምራል፡፡ በየወ ለእናቱ ገንዘብ ይልካል እናቱም አሁን የሚጦራቸውን ልጅ አግኝተዋልና ዘብር ገብረኤል ድረስ ሁሌ በመሄድ ይሳለማሉ፡፡ ከጊዜ ቡኋላ ግን ይህ ልጃቸው ገንዘቡን መላክ አቆመ፤ ስልክም ሳይደውል 8 ወር ሙሉ ድምጹ ጠፋ፡፡ የልጃቸው የውሃ ሽታ መሆን ያሳሰባቸው እናትም ዘወትርብቻ ልጄ ባለበት ደህና ይሁንልኝይሉ ነበር፡፡ እርሳቸውም ቀና ብሎ ከነበረው ኑሮአቸው ወደቀድሞው ድህነታቸው ተመልሰው እንደምንም አቅራቢያ ያሉትን ቤተክርስትያን እየተሳለሙ ችግራቸውን ለእግዚአብሔር እየነገሩ 8 ወር ቆዩ፡፡ 8ኛው ወር ይኸው ልጃቸው ስልክ ይደውላልሄሎ እናቴ ደናነሽ ? የምልከውንም ገንዘብ አቋርጬ ስልክም ሳልደውል ጠፋሁ አይደልይላቸዋል፡፡ እርሳቸው ግን ልጄ ባለህበት ደህና ሁንልኝ እንጂ ምንም ችግር የለውም ይሉታል፡፡ ልጃቸውም መልሶ እናቴ የጠፋሁት የምልከው ገንዘብ ስላጣሁ አይደለም ነገር ግን 8 ወር ሙሉ በየሆስፒታሉ እየተንከራተትኩ ስለነበረ ነው፤ ብዙ ቦታ ተመረመርኩ ሁሉም ዶክተሮች የእግዚአብሔርን አናውቅም በእኛ በኩል ግን ከዚህ ቡኋላ 72 ሰአት ብቻ ነው የቀረህ ብለውኛል፡፡ አሁን ለመጨረሻ ጊዜ ኦፕራሲዮን ሊያረጉኝ ነጫጭ ጓንት ያደረጉ ዶክተሮች በዙሪያዬ ቆመዋል፤ እናቴ አሁን የደወልኩት ሌሎች ደውለው መርዶዬን ከሚነግሩሽ ወይም አስከሬኔ ሲላክልሽ እንዳትደነግጪ ከመሞቴ በፊት ልሰናበትሽ ብዬ ነው አላቸው፡፡ 

በእድሜያቸው አመሻሽ ላይ የተስፋ ብርሃን ይሆን ዘንድ የወለዱት ልጃቸው ይሄን ሲነግራቸው ለራሱ ሳይኖር ለእኔ ብቻ ኖሮ ሳይወልድ ሳይከብድ በአይኔ ሳላየው በሰው ሀገር ሊሞት ነውን ብለው አለቀሱ፡፡ በቤታቸው ውስጥ በመስታወት ፍሬም ተደርጐ የተሰቀለውን የልጃቸውን ፎቶ ይዘው የገብርኤል ታቦት ደባል የሆነበት በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቤተክርስትያን ሄዱ፡፡ ብዙ አልቅሰው ጸለዩ፤ ረዳቴ ባለሟሌ የዘብሩ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ባይሞላልኝ እንጂ ከቤትህ መች ጠፍቼ አውቅ ነበር አሁንም በሰው ሀገር የሚንከራተተውን ልጄን ማርልኝ በሰው ሀገር አታስቀረው ለቤቱ ለእናቱ አብቃው እያሉ አይናቸው የእንባ ምንጭ ጉንጫቸው የእንባ ቦይ እስኪሆኑ ድረስ መሪር ልቅሶን አለቀሱ፡፡ ጸልየው ሲጨርሱ ከለቅሶአቸው ብዛት ጭቃ ከሆነው አፈር አንስተው ፎቶው ከውስጥ እንዳለ መስታወቱ ላይ ግንባሩን ቀቡት፡፡ ወደቤታቸው ሲገቡ ስልኩ ይጮሀል እርሳቸው ግን ለማንሳት ፈሩ፤ ልጄ 72 ሰአት እንኳን ሳይደርስ ሞትክን? እያሉ አለቀሱ፤ ኋላ ላይ  መርዶ ልሰማ ነው ብለው እያዘኑ ስልኩን አነሱት፤ ልጃቸው ነበር፡፡ እናቴ ምንድነው ያደረክሽው? አላቸው እሳቸውም ሁሉነም ነገር ዘርዝረው ነገሩት፤ ልጃቸው መልሶ እስከዛሬ ላንቺ ብነግርሽ ኖሮ ሆስፒታል ለሆስፒታል ባልተንከራተትኩ ነበር አላቸው፡፡ ነገር ሁሉ ተቀየረና የደስታ እንባ ሳያስቡት ከአይናቸው ይፈስ ጀመር፡፡


እንግዲህ አለም እንዲህ ናት ተስፋ የለውም ብላ የሞት ሪፈር ስትጽፍ እግዚአብሔር ደግሞ የተስፋ ሪፈር ይጽፍልናል፤ አብቅቶለታል ያልነውን ህይወት እርሱ ደግሞ ይቀጥለዋል፡፡ የተማመንባቸው የአለም ሰዎች ተስፋ የላችሁም ሲሉን ደጉ እግዚአብሔር ደርሶ ተስፋችንን ሲቀጥል ከእንባ ሌላ ምን ስጦታ ልናቀርብ እንችላለን ? ልጃቸው ለቤቱ በቅቶ ወልዶ ከብዶ ታሪኩ ተቀይሮ ይህን ላደረገለት ለባለውለታው ምስጋና ለማቅረብ በቃ፤ በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ያለጥርጥር በእምነት የልጃቸውን ፎቶ እምነት ቀብተው ድንቅ ተአምር ያሳያቸውም እናት ድንቅ ስራውን አወሩ ተአምሩንም መሰከሩ እኛም ይኸው ሰማነው፤ በቅዱሳኖቹ ላይ አድሮ እግዚአብሔር ድንቅ ነገርን ያደርጋል የችግረኛን እንባ ያብሳል የእግዚአብሔር የማዳኑ ስራ ግሩም ነው ብለን መሰከርን፡፡ እስመ አልቦ ነገር ዘይሰሀኑ ለእግዚአብሄር። አንትሙ ሀዝበ ክርስቲያን በልዎ ለእግዚአብሄር ግሩም ግብርከ።ይህን ላደረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን፡፡
-------------------------------------------

(ከደቂቀ ናቡቴ)፡-የካቲት 16/2004 ዓ.ም የቃል ኪዳኗ ታቦት ለእመቤታችን ቃል ኪዳን በተገባበት ቀን ለማክበር ከህናት ወደ ዋሻው ገብተው ታቦቷን ተሸክመው ወደ ድንኳን መጡ፡፡ እልልታው ቀለጠ ግማሹ በደስታ የለቅሳል ቀድሞ የፈረሰው የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ጋር የተጣለው ድንኳን ደረሱ ታቦት ተሸካሚው ካህን ምልክት አሳዩ ታቦትን መሸከም አልቻልኩም አቃጠለኝ ካህን ይቀየርልኝ አሉ፡፡ በሌላ ካህን ተቀየሩ ሕዝቡም እንዲረጋጋ ተነገረው፡፡ ወረብ ስብከት ወደፊት ለሚሰራው መቃኞ ቤተ ክርስቲያን እርዳታ ተሰበሰበ ስርዓት ቅዳሴ በድንኳን ውስጥ ተከነወነ፡፡ ከዚያም ታቦተ ቅድስት ኪዳነምህረትን ይዘው ከድንኳን ጉዞ ተጀመረ፡፡ ለወንጌል መስፋፋት ዘወትር የሚደክሙት ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉት የለገዳዲ ወጣቶች ቀይ ቲሸርት ለብሰው ቀይ ምንጣፍ የሚያነጥፉ ተቦቷን ወደ መጣችበት ዋሻ ለመመለስ ይዘምራሉ፡፡ ድንገት ድምፅ ተሰማ አልቅሱ ምዕመናን አልቅሱ እግዚአብሔር እንዲታረቀን አልቅሱ የሚል በሞንታርቦ ድምጽ ተሰማ ምዕመናን ሁሉ ተደናገጡ ታቦተ ኪዳነ ምህረትን የተሸከሙትን ሁለኛው ካህን እያለቀሱ ድምጽ አሰሙ፡፡ ተቃጠልኩ አንሱልኝ አልቻኩም እግዚኦ በሉ ብለው በወደቁበት ይጮኃሉ ግን ማን ታቦቷን ያንሳላቸው፡፡ እሳትን ማን ይደፍራል፡፡ ጩኽቱ ምህላው ለቅሶው እግዚኦታው ቀጠለ ግን ማንም ታቦቷን ማንሳት አልቻለም ሕዝበ ክርስቲያን እንደ ሻሽ ተነጥፈው አለቀሱ መነኮሳት እና ካህናት አነቡ በብዙ ለቅሶና እግዚኦታ ቆሞሱ አባታችን በወደቁበት ቦታ ሆነው ወደ ዋሻ አትመልሱኝ ክብሬ መገለጫው ደርሷል ወደ ድንኳን አስገቡኝ ብላለች ሲሉ በቀላሉ ብድግ አለችና ወደ ድንኳን ገባች፡፡ ሁለተኛው ታቦት ተሸካሚው ካህን ከወደቁበት ለማንሳት ተሞከረ እራሳቸውን ስተው በሕይወትና በሞት መካከል ሳሉ ወጣቶች ካህኑን ከካህን ጋር ይዘው ወደ ፀበሉ ሮጡ ታቦት ተሸካሚው ካህን ሲጠመቁ በእሳት የጋለ ብረት ምጣድ ውሃ ሲፈስበት የሚያወጣውን ድምጽ እና ጭስ እሰቸውም ላይ ታየ ከብዙ ሰዓታት ቆይተ በኋላ እራሳቸውን አወቁ፡፡ ካህናቱ የወደቁት ኃጢያተኛ ስለሆኑ ሳይሆን የቅድስት ኪዳነ ምህረት ዕለት ወደ ዋሻ አልገባም ብላ በተዓምቷ ቦታውን ስአስከበረች ነው፡፡

የወረዳው ምክር ቤት ፍልፍል ቤተክስቲያን ኃይማኖታዊ እና ታሪከዊ ቦታነቱን የታቦቷን ሃያልነት አምነው ተቀበሉ፡፡ ግን ቦታውን እስካሁን ለቤተክስቲያኗ አልሰጡም ጠንካራው የለገዳዲ ምዕመናን ግን በጥቂት ቀን ውስጥ መቃኞ ቤተክስቲያን ስርቶ አጠናቆ እሁድ መጋቢት 16/2004 ዓ.ም ፅላቷን ከድንኳን ወደ መቃኞ በሰላም ገብታለች ሕዝበ ክርስቲያኑም ከተለያየ ቦታ እየመጡ እየተፈወሱ ናቸው በቀጣይ የተሸለ ቤተ ክርስቲያን ሰርቶ በቅርብ ማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው ሁላችንም የራሳችንን ድርሻ እንድንወጣ ይገባል መልክታችን ነው ፡፡ 

አምላክ ቤተክርስቲያናችንን ከጠላት ይጠብቅልን
-------------------------------------------

የወላዲተ አምላክ ድንቅ ተአምር

(አንድ አድርገን ፤ ህዳር 21 2004 ዓ.ም)፡- ዛሬ ፃድቃኔ ማርያም ሄጄ በአይኔ ያየሁትን ተአምር ልፅፍላችሁ ወደድኩኝ፡፡ ቀኑ ቅዳሜ ነው ፤ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ወደ ፃድቃኔ ለመሄድ የሚነሱበት ቀን ስለሆነ መጀመሪያ የሚወጣው አውቶቡስ እንዳያመልጠን ከባለቤቴ ጋር በጠዋት ነበር አውቶቡስ ተራ የደረስነው ፤ ነገር ግን ሰው እዛ ያደረ ይመስል 12፡00 ላይ አውቶቡሱ ሞልቶ መንቀሳቀስ ጀምሮ ነበር፡፡ ባለቤቴም ‹‹አይ በዚህም ሰዓት ደርሰን አመለጠን ይገርማል ተወው ባክህ እመቤቴ እንደፈቀደች›› አለችኝና ሁለተኛው አውቶቡስ ላይ ገባን፡፡ ይህኛው ደግሞ ቀጥታ ዘላቂ ሰው ስላጣ የመንገድ ሰዎችንም በመጫን ነበር የሞላው፡፡ ጉዞ ወደ ፃድቃኔ ማርያም ፤ ውዳሴዋን ደግመን ጉዞ ጀመርን፡፡ መኪናው ሲያወርድ ፤ ሲጭን 9፡00 አካባቢ  ደብረ ምጥማቅ ደረስን ፤ እዚህ እንውረድና በአቋራጭ እንሂድ ተባብለን ሰላ ድንጋይ ሳንደርስ ወረድን ፡፡ እቃችንን ለአንድ የሀገሬው ሰው አሸክመን አቋራጩን ተያያዝነው ፡፡ ልጁ እንዲህ አለን ‹‹ ዛሬ ግን ማደሪያ የምታገኙ አይመስለኝም በጣም ብዙ ሰው ነው የመጣው አለን›› :: ‹‹ችግር የለውም ውጪ አንጥፈን እናርፋለን ለመተኛት መች መጣን››አልነው፡፡
----------------------------------------------------

ይህ የቅዱስ ገብርኤል ድንቅ ተዓምር ነው

(አንድ አድርገን ፤ ጥቅምት 28 2004 ዓ.ም):- የመጀመሪያውን ተዓምር ስፅፍ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሁለተኛውን ለመፃፍ ያብቃኝ ብዬ ነበር፡፡ እነሆ ዛሬ የምነግራችሁ ተዓምር እዛው ኮራ ገብርኤል ላይ የተደረገ ነው ፡፡ ይህ ሁለተኛው ተዓምር ሲሆን የመጀመሪያውን እዚህ ቦታ ላይ የተደረገውን የቅዱስ ገብርኤልን ተአምር ካላነበቡ ለሁለተኛው መንደርደሪያ ይሆኖታልና ቢያነቡት መልካም ነው፡፡

የመጀመሪያውን ተአምር ለማንበብ ይህን ይጫኑ
እነሆ እንደ እርሱ ፍቃድ የኮራውን የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተአምር ለመፃፍ በቅቻለሁ አስተውለው ያንብቡት ፡፡
----------------------------------------------------


‹‹ይህ ድንቅ ነገር ነው ›› የዮሐንስ ወንጌል 9፤30


 • ‹‹የቤተክርስትያን ፍቅር ለካስ እንዲህ ያስለቅስ ኖሯል ? ፍቅሯ ለካ አጥንት አልፎ ይሰማል››
 • ‹‹ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ›› ትንቢተ ዳንኤል 9፤21 
(አንድ አድርገን ፤ ጥቅምት 2 2004 ዓ.ም) ጊዜው ከጥቂት ወራት በፊት ሲሆን የአሰቦት ገዳም ጉዞ ከሚሄዱ ምዕመና አንዱ ነበርኩኝ የጉዞ ፕሮግራሙ ቀጥታ ከአዲስ አበባ አሰቦት ገዳም ገብቶ ማደርና  ጠዋት ኪዳን ካደረስን ፤ ቅዳሴ ካስቀደስን በኋላ ቀጥታ በቅርብ ርቀት ላይ ወደሚገኙት ቅዱስ ገብርኤል ፤ ቅዱስ ሚካኤል እና የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስቤተክርስትያን ተሳልሞ ቦታውን ተመልክተን ፤ በቦታ ላይ የተደረገውን ገቢረ ተዓምራት ሰምተንና አይተን  በቀጣዩ ቀን ወደ አዲስ አበባ መመለስ ነበር::
አሰቦት ገዳምን ሐረር-ድሬደዋ ስመላለስ መግቢያ መንገዱንና ጠቋሚ ታፔላውን እንጂ ቦታው ላይ ቀደም ሲል ስላልሄድኩ ቦታውን ለመርገጥ በጣም ጓጉቼ ነበር፡፡ ‹‹ሰው ያስባል እግዚአብሄር ይፈፅማል›› ነውና እንደእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ በሰላም ተነስተን በሰላም አሰቦት ገዳም ደርሰናል ፡፡መኪናው የሚያደርሰን ቦታ ካደረሰን በኋላ የአንድ ሰዓቷን ዳገት ግን እኛ ደክመን በረከት እንድንቀበልበት የዳገቱን መንገድ ጀምረን በመሐል የሚገኝውን የአባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግን ቤተክርስትያን ተሳልመን ያሰብንበት ቦታ ስንደርስ ፀሐይ ለመግባት አጋድላ ነበር፡፡

Click here to read more   
----------------------------------------------------
ቅድስት ድንግል ማርያም በዘይቱን - ግብጽ ከ500,000 በላይ ለሆነ ሕዝብ የመታየቷ ተዓምር!!ከላይ ያለውን ፊልም ከተመለከቱ በዃላ ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃ http://www.zeitun-eg.org/stmaridx.htm*----------------------------------------------------
ድንቅ ተአምር
ይህ የእመቤታችንን ድንቅ ተአምር የተነገረው  ነሐሴ 19/2003 በግቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የማታ ጉባኤ ሲሆን ነገሩም እንዲህ ነው::
 • “እማየ” ብሎ ጠራኝ እኔም “አቤት” አልኩት “ጆሮወቼ ሰሙልኝ” አለኝ፡፡ እኔም “ልብህ ቢሰማ ነውንጅ የሚሻለው” አልኩት፡
ይህ የእመቤታችንን ድንቅ ተአምር የተነገረው ትናንት ነሃሴ 19/2003 በግቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የማታ ጉባኤ ሲሆን ነገሩም እንዲህ ነው ፦ ተአምሩን የመሰከሩት አንዲት እናት ሲሆኑ “የእመቤቴን ስም እየጠራሁ ያለአባት ያሳደግኩት ልጅ ነበርኝ ፡ እኔም ልጄም እመቤታችንን በጣም እንወድ ነበረ ፡ ያለአባት በእመቤቴ ስም ያሳደኩት ልጄ ተምሮልኝ ጥሩ ስራ ያዘልኝ ፡ በዚህ ደስ ብሎኝ ሳለ ልጄ በስራ ቦታ ካልሆኑ ልጆች ጋር ገጥሞ አዲስ ነገርን ተማረብኝ ፡ አንድ ቀን ማታ ሲመጣ “ እናቴ ሆይ ጌታን ተቀበይ” አለኝ ይህን ሲለኝ ደነገጥኩ “እመቤታችንስ” ስለው “ዙሪያ ጥምጥም መሄዱ ይበቃናል አንቺም እኔም ጌታን መቀበል አለብን” አለኝ ፡ እኔም ጧት ማታ አለቅስ ጀመር ፡ ለልጄም ይህ የነፍስ በሽታ ለስጋውም ተርፎ ሁለቱ ጆሮወቹ አልሰማም አሉት፡፡ በዚህም የተነሳ ጴንጤወች እንፀልይልህ ብለው በአዳራሻቸው ወሰዱት ፡ ጆሮወቼ ይድኑ ይሆን ብሎ ተስፋ ያደረገው ልጄም ይባስ ብሎ ሁለቱም አይኖቹ ጠፉ ፡ ከዚህ በኅላ እቤት ተኛ ፡ እኔም እያለቀስኩ እኖር ነበር፡፡ አስቡት ጆሮውንኳ ባይሰማ አይን ቢኖረው በምልክት እንግባባ ነበር ፡ ወይንም አይኑ ባይኖርና ጆሮው ቢሰማ በድምፅ እንግባባ ነበር አሁን ግን እጅግ ችግር ሆነብኝ፡፡ ከሁሉ የሚያስጨንቀኝ ግን እመቤቴን መክዳቱ ነበር፡፡ 
አንድ ቀን ቤተክርስቲያን ምስክርነት ሲሰጥ ሰምቼ እኔም በሃይላንድ ፀበል ይዜ ወደቤት ሄድኩኝ፡፡ በሁለቱ ጆሮወቹ ፀበሉን አፈሰስኩበት፡፡ የእመቤቴ ስእል ፊትም ተንበርክኬ “እመቤቴ ሆይ ጆሮውም አይስማ ፡ አይኑም አይይ ፡ ነገር ግን ልቡን መልሺልኝ” እያልኩ አልቅሼ ፀልየ ወደ መኝታየ ሄድኩኝ ሌሊት 10፡00 ላይ ልጄ “እማየ” ብሎ ጠራኝ እኔም “አቤት” አልኩት “ጆሮወቼ ሰሙልኝ” አለኝ፡፡ እኔም “ልብህ ቢሰማ ነውንጅ የሚሻለው” አልኩት፡፡ አሁንም ትንሽ ቆይቶ 11፡00 ላይ “ እማየ የእመቤታችንን ስእሏን ስጭኝ” አለኝ ፡ እኔም ሰጠሁት እሱም ስእሏን አቅፎ ለአንድ ሰአት ያክል አለቀሰ፡፡ ትንሽ ቆይቶም “እማየ” አለኝ ፡ እኔም “አቤት ልጄ” አልኩት ፡ እርሱም ”ሁለቱም አይኖቼ በሩልኝ” አለኝ፡፡ ደስታየን እንዴት እንደምገልፀው አላውቅም ፡ የኔ እመቤት የልጄን የነፍሱንም የስጋውንም ህመም ፈወሰችልኝ፡፡ አሁንም ልጄ እዚሁ ቤተክርስቲያን ከእመቤቴ ስእል ፊት ተንበርክኮ እየፀለየ ነው፡፡ እኔን የሰማች እናንተንም ትስማልኝ” ይህ ታአምር እንዴት ደስ ይላል፡፡ እመቤታችን ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን ፡ ከፍ ከፍ እናደርግሻለን ፡ በልጅሽ አምነው በአማላጅነሽ ተማምነው ስምሽን የሚጠሩትን እንደማትተያቸው እናውቃለን፡፡ ድንግል ሆይ ስለዚህ ክብር ምስጋና ይገባሻል፡፡ አንቺን ለእናትነትና ለአማላጅነት የሰጠን ጌታችን አምላካችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፍቅሩ ነገር ምን ይረቅ?


Source:- Mahlet Girma's post on Mehal zege Giorgis rebulding committee face book pagehttp://www.facebook.com/groups/giorgis/. (It is inactive to share. )

14 comments:

 1. ልባችን ደነደነ እንጂ እርሳስ ያውነች ሁሌም ፍቅር በእውነት ምልጃዋ ኣይለየን በእውነት ለእውነት እንድንቆም ኣሜን

  ReplyDelete
 2. በመጨረሻው ዘመን ማስታወል ይጠፋል
  ሰው ለገንዘብና ለጥቅም ይኖራል ተብሎ የለ፡፡ የአምላክን
  መምጣት በማሰብ ልብ ይስጣቸው እንበል፡፡

  የወርቅውሃ

  ReplyDelete
 3. በመጨረሻው ዘመን ማስታወል ይጠፋል
  ሰው ለገንዘብና ለጥቅም ይኖራል ተብሎ የለ፡፡ የአምላክን
  መምጣት በማሰብ ልብ ይስጣቸው እንበል፡፡

  የወርቅውሃ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hi Yeworkwoha, I was just wondering - it's be such a LONG time, but in case you are the same person, please let me know. Did you ever attend at a computer teaching center in 4 kilo may be about some 20 years ago?

   Thanks,
   Fikerte

   Delete
 4. seytanimko kezihe belay liyaderg yichilalina bizu ayasdenikim yilik kalun enastewul!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰይጣንማ ቤመቤታችን ስም የሚያስመስልበት ድፍረቱም አቅሙም የለውም:: በጭራሽ:: አንተና መሰሎችህ ግን ክሰይጣን ያነሳችሁበት ዘመን ላይ ደርሰናል:: እባክህ የማይነካውን አትንካ ... እዚያው ዝም ብለህ ከሚርመሰመሱ አጋንንት ጋር ዳንኪራ ክምትጨፍርበት አዳራሽህ ውስጥ አርፈህ ብትቀመጥ ይሻልሃል:: የንጉሱን እናት ለመሳደብ ከመንጠራራትህ በፊት አረፋ እያስደፈቀ የሚያንፈራግጥህን የዲያቢሎስን የዛር መንፈስ ማንነቱ አውቀህ ተረዳ ?????

   Delete
  2. that is absolutely true...There is only ONE religion..
   ORTHODOX TEWAHEDO.

   Delete
 5. Amen yamelak enat natko!!! k fetoran belay hona amelaken lejwan yhonwen hulem lftrtate hulo dehenten meherten telemenalch !!! k amlakachen k amelakewme talaqe tsega tstewatalena!!! LZIHE HULO EGEZIABEHER YEKEBRE YEMSEGNE +++

  ReplyDelete
 6. Amen !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 7. Howlong the Devil can play on the life of our people in the name of Saints and Angels? You 'Andadrigden' could you please stop and think over and over. God is not only mercy, but He is also Consuming fire. Please! please!! leave our innocent people!!!!

  Selam

  ReplyDelete
  Replies
  1. off course but why u deny the way of mercy of the almighty God, God heal the world in many ways; from that let me remember u a man get heal from Selihom holly water(or metemekia)

   Delete
 8. God always shows us miracles.Since the day our country was created Very many
  miracles have been seen.The previous generation saw, the current is seeing,
  and the coming will see more than before.But the hearts of some does not show changes.why? Fabricating false narratives and lying before God is the day to day activities of many people.What is to be done? Some are not the sons of God in their deeds.Who is their father then? Devil? The father of lies..../

  ReplyDelete