Monday, July 6, 2015

የመንበረ ፓትርያርክ ቅ/ማርያም ገዳም ሰበካ ጉባኤ “ለሕይወት የሚያሰጋ የአድማ እንቅስቃሴ እየተደረገብኝ ነው” አለhttp://www.addisadmassnews.com
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መቀመጫ የኾነችው የቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፥ ጥፋቶች ታርመው ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር እንዳይሰፍን በሚሹ ጥቂት የአስተዳደር ሰራተኞች፣ በህይወት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ከአድማ ያልተናነሰ እንቅስቃሴ እየተደረገበት መኾኑን አስታወቀ፡፡ የመልካም አስተዳደር ጅምሩን ከፍጻሜ ለማድረስ የቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የአስተዳደር ክፍሎች እገዛ እንዲያደርጉለትም ጠይቋል፡፡

ለብክነት፣ ለዘረፋ እና ለሙስና ከተመቻቸ አሰራር እንዲሁም በገዳሟ ቀደም ሲል ከመልካም አስተዳደር ዕጦት የተነሳ የተከሰቱ ጥፋቶችን ለማረም ልዩ ልዩ መመሪያዎችንና የውስጥ ደንብ ረቂቆችን ማዘጋጀቱን ሰበካ ጉባኤው ለሀገረ ስብከቱ የዋና ሥራ አስኪያጅ /ቤት ባቀረበው ሪፖርት ገልጿል፡፡ ይኹንና ለቁጥጥር የሚያመች ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበትን አሰራር ለማስቀጠልና ለማስፈጸም እንዳይቻል ጥቂት የአስተዳደር ሰራተኞች ማኅበረ ካህናቱን በመከፋፈል፣ከሰበካ ጉባኤው ጋር ተባብራችኋልበሚል ከሥራና ከደመወዝ በማገድ፣ በማስጠንቀቂያዎች በማሸማቀቅ፣ መረጃዎችን በማዛባት የሚፈጥሩት ግጭት ኹኔታውን አስቸጋሪ አድርጎብኛል ብሏል፡፡

Friday, July 3, 2015

ቤተክርስትያኗ በአይ ኤስ ለተገደሉ ወገኖች ቤተሰቦች ድጋፍ አደረገች
 አዲስ አበባ ሰኔ 25 2007 (ኤፍ ) በስዊዘርላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን በአይ ኤስ ለተገደሉ ወገኖች ቤተሰቦች 400 ሺህ ብር በላይ ስጦታ አበረከቱ። ድጋፉ የተደረገው 11 ተጎጂ ቤተሰቦች ሲሆን፥ ለእያንዳንዳቸው 27 ሺህ 500 ብር በአጠቃላይ 400 ሺህ ብር በላይ ተብርክቶላቸዋል። እጅግ ችግረኛና በእድሜ ለገፉ ስድስት ቤተሰቦችንም ለመደገፍ ቃል ገብተዋል። የቤተክርስትያኗ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባስተላለፉት መልዕክት ቤተክርስትያኗ ይሄን አሰቃቂ ድርጊት ከሰማችበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ተግባራት አከናውናለች።

የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ምንም ዋስትና ወደ ሌለበት አገራት እንዳይሰዳዱ ትልቅ ትምህርት ነው ያሉት ብፁእነታቸው በቀጣይም ቤተክርስትያኗ ዜጎች በአገራቸው ሰርተው እንዲለወጡ ትሰራለች ብለዋል።ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተወከሉት አምባሳደር ሙሌ ታረቀኝ በበኩላቸው መንግስት ችግሩን ከምንጩ ለመድረቅ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ነው ብለዋል።

ምንጭ:-ኢዜአ