አብዝተን እናጭድ ዘንድ አብዝተን እንዝራ! (በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!! አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከ347 እስከ407 ዓ.ም. የነበረና ከ398 እስከ 404ዓ.ም. የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ሆኖ ያገለገለ ታላቅ የቤተክርስቲያንአባት ነው፡፡ ይህ አባት ከሚያስተምረው የትምህርቱ ጣዕም የተነሣ “አፈወርቅ፣ ጥዑመ ልሳን” ተብሏል፡፡በእርግጥም በትምህርቱ ሁሉንም መማረክ የሚችል፤ ለማንም የማያዳላ ይልቁንም ለድሆች ጠበቃየሚሆንላቸው የፍትሕ አባት ነው፡፡ ትምህርቶቹም ዘመን ተሻጋሪና ክርስቲያናዊ ሕይወቱን መመዘን ለሚፈቅድሰው የማያዳሉ ሚዛኖች ናቸው፡፡ እስኪ ዛሬም በዚያ አንደበቱ ይናገረን፤ እኛም እንደ ሊድያ ልቦናችንንከፍተን እንስማው፤ ከዚያም ራሳችንን እንመርምር፡፡
To Read more clock here
--------------------------------------------------
የሴት ራስ - ወንድ
(by Birhanu Admass Anleye )እንደምን ሰነበታችሁ፡፡ ረዘም ላለ ጊዜ በመጥፋቴ ይቅርታ እየጠየቅሁ ለጊዜዉ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የሃይማኖት ዐምድ ‹‹ሃይማኖት እና ሴቶች›› በሚለዉ የመወያያ ርእሰ ጉዳይ ላይ ከእኛ እምነት አንጻር ያቀረብኳትን ትንሽ መጣጥፍ እነሆ ብያለሁ፡፡
ቤልጄየም ዉስጥ በምትገኘዉ የአንትወርፕ ከተማ አይሁድ ይበዙባታል፡፡ በዚሁ ምክንያት በዚያ ሀገር ሱቆች እንኳ ሳይቀር በብዛት የሚይዙት ለአይሁድ የሚሆኑትን ልብሶችና ሌሎች የእነርሱን ፍላጎት የሚያሟሉ ነገሮች ነዉ፡፡ ምክንያቱም በዚያ ለሁለት ሺሕ ዐመታት በተሰደዱባቸዉ ቦታዎችም ባሕላቸዉንንና ዕሴቶቻቸዉን ጠብቀዉ የሚኖሩ በመሆናቸዉ ነዉ፡፡ የተማሩት ትምህርትና የደረሱበት ሥልጣኔና ዘመናዊነት ምንም ያህል ተጽእኖ እንዳያመጣ አድርገዉ መቛቛማቸዉም ሥልጣኔና ዕሴትን አንዴት አስታርቆ መሔድ እንደሚቻልም ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡
ቤልጄየም ዉስጥ በምትገኘዉ የአንትወርፕ ከተማ አይሁድ ይበዙባታል፡፡ በዚሁ ምክንያት በዚያ ሀገር ሱቆች እንኳ ሳይቀር በብዛት የሚይዙት ለአይሁድ የሚሆኑትን ልብሶችና ሌሎች የእነርሱን ፍላጎት የሚያሟሉ ነገሮች ነዉ፡፡ ምክንያቱም በዚያ ለሁለት ሺሕ ዐመታት በተሰደዱባቸዉ ቦታዎችም ባሕላቸዉንንና ዕሴቶቻቸዉን ጠብቀዉ የሚኖሩ በመሆናቸዉ ነዉ፡፡ የተማሩት ትምህርትና የደረሱበት ሥልጣኔና ዘመናዊነት ምንም ያህል ተጽእኖ እንዳያመጣ አድርገዉ መቛቛማቸዉም ሥልጣኔና ዕሴትን አንዴት አስታርቆ መሔድ እንደሚቻልም ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡
--------------------------------------------------
የጌታችን ክህነትና የመልከ ፄዴቅ ክህነት
ቅዱስ ጳውሎስ ለምን ጠቀሰው? - - - ዕብ.3:1 “ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ” ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ በእብራውያን መልእክቱ ያተኮረው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ማስረዳት ነው፡፡ ይህንንም የሚያስረዳው ደግሞ በንፅፅር ነው፡፡ ከነቢያት ስለመብለጡ የእነሱን ንግግርና የእሱን ንግግር በማነፃፀር አስረዳ፡፡ ከዚያም በኅላ ደግሞ ከመላእክት መብለጡን አስረድቷል፡፡ አሁን ደግሞ ከካህናት መብለጡን ለማስረዳት ያመጣል፡፡ ከካህናት መብለጡንም ሲያስረዳ ዋናወቹ ምክንያቶች 1) በክህነቱ 2) በመስዋእቱ 3) መስዋእቱ በቀረበበት ድንኳን መሆኑን ያስረዳል፡፡ ስለክህነቱም በ ዕብ.5፡1-10 ፣ በዕብ. 6፡20 ፣ 7፡1-28 ፣ 8፡1-3 ባሉት አስረድቷል፡፡
እመቤታችን በእናት አባቷ ቤት ሦስት ዓመት፣ አሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ /ዘጠኝ ወር በቤተ ዮሴፍ/፣ ከመድኃኒታችን ጋር ሰላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ፣ በቤተ ዮሐንስ አሥራ አምስት ዓመት፤ ጠቅላላ ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ምድር ኑራለች::
ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ለአገልግሎት ወደ ኤፌሶን በሄደበት ወቅት የቤተ መቅደስ አለቆች ልጆች የነበሩ ደናግል እግሯን እያጠቡ እየተላላኩ ያገለግሏት ነበር:: እመቤታችን ጐልጐታ በሚገኝው የመቃብር ቦታ እየሄደችም አዘውትራ ትጸልይ ነበር:: መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም በመቃብሩ በምትጸልይበት ጊዜ ከዚህ ዓለም በሥጋ ስለምታርፍበት ሁኔታ ከነገራት በኋላ ታመመች:: ያን ጊዜ አገልጋዮቿና ጎረቤቶቿ ሁሉ በአንድነት ተሰበሰቡ ብዙ ድውያንም ወደእርስዋ እየመጡ ያመሰግኗትና ይፈወሱም ነበር:: እመቤታችንም ደስ ብሏት ትባርካቸዋለች::
«ወዮልኝ፣»
To read more click here
To read more click here
ክህነት ምንድን ነው? - - - አገልግሎት ሲሆን መሾምን መመረጥን ያመለክታል፡፡ በመፅሃፍ ቅዱስም ከአዳም ጀምሮ የተለያዩ ሰወች ለዚህ ክህነት በሰውም በእግዚአብሄርም ሲመረጡ ያሳየናል፡፡
--------------------------------------------------
ያለፈው ዘመን ይበቃል ... 1ጴጥ.4፡3፡፡
- «የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁ በት፡ በመዳራት እና በሥጋ ምኞት፣ በስካርም፣ በዘፈንም ፣ያለልክም በመጠጣት፣ ነውርም ባለበት፣ በጣዎት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና»1ጴጥ.4፡3፡፡
- «ሰውስ ዘመኑ እንደ ሣር ነው እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል፡፡ ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋል» መዝ.102/103፡ 15፡16
- በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘን ሁላችን በስካርና በዝሙት፣በስርቆት እና በቅሚያ፣ በመግደልና በምቀኝነት በቅንዓትና በቂመኛነት ያሳለፍነውን ሕይወት ትተን አዲስ ሰው የምንሆንበት ዘመን ሊሆን ይገባል
-----------------------------------------------
እመቤታችን ከማረፏ ከሰዓታት በፊትና በኋላ ምን ሆነ?
ማርያም ስጋኪ ዘተመሰለ ባሕርየ
ተሓፍረ ሞት አኮኑ ሶበ ነጸረ ወርእየ
እንዘ በደመና ብሩህ የዐርግ ሰማየ
እንኳን አደረሰን
ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ለአገልግሎት ወደ ኤፌሶን በሄደበት ወቅት የቤተ መቅደስ አለቆች ልጆች የነበሩ ደናግል እግሯን እያጠቡ እየተላላኩ ያገለግሏት ነበር:: እመቤታችን ጐልጐታ በሚገኝው የመቃብር ቦታ እየሄደችም አዘውትራ ትጸልይ ነበር:: መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም በመቃብሩ በምትጸልይበት ጊዜ ከዚህ ዓለም በሥጋ ስለምታርፍበት ሁኔታ ከነገራት በኋላ ታመመች:: ያን ጊዜ አገልጋዮቿና ጎረቤቶቿ ሁሉ በአንድነት ተሰበሰቡ ብዙ ድውያንም ወደእርስዋ እየመጡ ያመሰግኗትና ይፈወሱም ነበር:: እመቤታችንም ደስ ብሏት ትባርካቸዋለች::
----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ድካማቸውን አይተው፥ ጉድለታቸውን አስተውለው፥ ራሳቸውን የሚገሥጹ፥ በራሳቸው የሚፈርዱ ሰዎች ብፁዓን (ንዑዳን፥ ክቡራን) ናቸው። ያለፈውን ዞር ብሎ በማየት፥ የቆሙበትን በማስተዋል፥ ወደፊት ሊመጣ የሚችለውንም አሻግሮ በ መመልከት፦ «ወዮልኝ፤» ብሎ ራስን ማስጠንቀቅ መንፈሳዊነት ነው። በተሰጣቸው ጸጋ ሳይኰፈሱ ፥ በአገልገሎት ብዛት ሳይጋረዱ፥ ወደ ውስጥ ማየት የአእምሮ መከ ፈት ነው። «አይገባኝም ፥ ሳይገባኝ ነው፤» ማለት የእግዚአብሔርን ቸርነት መግለጥ፥ ለጋስነቱን መመስከር ነው። በምድርም በሰማይም (በሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ) ትሑት ሰብእና፥ ቅን ልቡና ይዞ መገኘት ነው። «ወዮልኝ፤» ያለ ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስ ነው። እርሱም ከዓበይት ነቢያት አንዱ
-------------------------------------
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ፦ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት፤ (ክፍል ፩)
ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት፤ ምክንያቱም የአንድ የክርስቶስ አካል ናትና። ይህች የክርስቶስ አካል የሆነች ቤተ ክርስርስቲያን መሠረቷም ጉልላቷም ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህንንም ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ፦ «እርሱም (ክርስቶስ)ከሁሉ በፊት ነው፤ (ለዘመኑ ጥንት የሌለው ቀዳማዊ ነው)፤. . . እርሱም የአካሉ ማለትም የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤. . . እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት፤» ሲል ገልጦአታል። ኤፌ ፩፥፳፫፣ ቈላ ፩፥፲፰። በተጨማሪም በቆሮንቶስ መልእክቱ ላይ «የእግዚአብሔር ጸጋ እንደተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ። ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ ሊመሠርት አይችልምና፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።» ብሎአል። ፩ኛ ቆሮ ፫፥፲-፲፩። በክርስቶስ ደም ላይ የተመሠረተችው ይህች ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያዪቱ ቤተ ክርስቲያን ናት። የሐዋ ፳፥፳፰፣ ዕብ ፫፥፲፬።
-----------------------------------
To read more here
‹‹የኢትዮጵያ ድኳኖች ሲጨነቁ ዐየሁ›› ዕንባ 3.7
ኢትዮጵያ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአሥራት አገር ናት፡፡ ሊቃውንትም ነቢያት የተነበዩትን ትንቢት የቆጠሩትን ሱባዔ መሠረት በማድረግ ቅድስት ድንግል ማርያም በኪደተ እግሯ ኢትዮጵያን መባረኳን ያስተምራሉ፡፡ ነቢዩ ዕንባቆም «የኢትዮጵያ ድኳኖች ሲጨነቁ ዐየሁ፤» ዕንባ. 3፡7 ብሎ የተናገረው ቃለ ትንቢት እመቤታችን የኢትዮጵያን አውራጃዎች ለመባረኳ ማስረጃ መሆኑን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይተረጉማሉ፤ ያመሠጥራሉ፡፡
----------------------------------
No comments:
Post a Comment