ከክርስቶስ ልደት በፊት በ800 ዓመተ አለም እንደተገነባ የሚነገርለት ጥንታዊው የይሓ ቤተ መቅደስ ጥገና ተደርጎለት ዛሬ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ። ቤተ መቅደሱን መጠገን ያስፈለገው በዕድሜ ብዛት የመሰንጠቅና ሌላም ጉዳት ስለደረሰበት መሆኑን በአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት የአርኪዮሎጂ ባለሙያ የሆኑት አቶ አላይ ገብረስላሴ ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል ከአደዋ ከተማ 32ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የይሓ ቤተ መቅደስ ጥገናው የተደረገለት ባለፉት ስምንት ዓመታት በጀርመናዊያን ባለሙያዎች እንደሆነም አመልክተዋል፡፡ባለሙያው እንዳሉት ቤተ መቅደሱ ጥንታዊ ይዘቱ ሳይለቅ የተሰነጠቁ ድንጋዮችን መሙላት፣ የበሰበሱ ድንጋዮችን ደግሞ በሌላ የመተካት ስራው በጥንቃቄ ተከናውኗል፡፡
የቤተ መቅደሱን የጥገና ስራ መጠናቀቁን ይፋ በማድረግ መርቀው ለጎብኚዎች ክፍት ያደረጉት የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ እና የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ዳዊት ሃይሌ ናቸው፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
(ከምሕረተሥላሴ መኰንን)
ከአክሱም ከተማ በስተሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ 56 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ጥንታዊቷ ይሓ ከተማ ትገኛለች፡፡ የይሓ ከተማ
መግቢያ ላይ ከተማዋ
የምትታወቅባቸው ሁለት
ታላላቅ ሕንጻዎች ይገኛሉ፡፡
አንደኛው ግራት በዓል
ግብሪ በሚባለው ቦታ
የነበረው ቤተ መንግሥት
ነው፡፡ ይህ ሥፍራ
አሁን የአርኪዮሎጂ ስፍራ
(ሳይት) ሲሆን፣ በተመራማሪዎች
ተከልሎ ይታያል፡፡ የጀርመን
አርኪዮሎጂካል ኢንስቲትዩት
ባለሙያዎች በሚያደርጉት ቁፋሮ
ከክርስቶስ ልደት በፊት
ወደ 8ኛውና 9ኛው
መቶ ክፍለ ዘመን
የሚጠጉ ግኝቶች ይፋ
መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡
አንዳንድ ጥናቶች በአካባቢው
ቁፋሮ ከተጀመረ ዓመታት
ቢቆጠሩም በደርግ ወቅት
ተቋርጦ በ1985 ዓ.ም.
ዳግም መጀመሩን ያሳያሉ፡፡
ኢትዮጵያን ኢንስቲትዩት ኦፍ
አርኪዮሎጂና የፈረንሳይ የአርኪዮሎጂ
ቡድንን ጨምሮ የብዙ
ተመራማሪዎች መዳረሻ ነው፡፡