EBC መጋቢት 03፣2009
በድንገት ተቀስቅሶ የዝቋላ ተራራን ደን ያቃጠለው የእሣት አደጋ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉ ተገለፀ፡፡ የ3ሺህ ሜትር ከፍታ ያለው በዚሁ የዝቋላ ተራራ ከዚህ በፊት ሙሉ ለሙሉ በደን የተሸፈነ እንደነበር ይነገራል፡፡

ይሁንእንጂ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሰራዊት አባላት ፣የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የገዳሙ ነዋሪዎች ባደረጉት ርብርብ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡ስለደኑ የቃጠሎ መንስኤ ግን እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ ደኑ ከቅርብ አመታት ወዲህ በተደጋጋሚ የመቃጠል አደጋ እያጋጠመው በመሆኑ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትና ደኑን መልሶ ለመተካት ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም ጥሪ ቀርቧል፡፡
No comments:
Post a Comment