Thursday, May 31, 2012

በዋልድባ ከሶስት ሺህ ሰው በላይ ለተቃውሞ መንግስት ላይ ተነሳስቷል

 •   ስብሰባው ላይ ለመገኝት በመኪና ሲመጡ የነበሩ የመንግስት ባለስልጣናት መኪናቸው መንገድ ላይ ተገልብጧል
 • “እኛ ምንም ኮሚቴ ማቋቋም አያስፈልገንም የምንፈልገው ስራውን እንድታቆሙ ብቻ ነው ፤ የህዝቡን ጥያቄ ረግጣችሁ ስራውን ብትቀጥሉ ግን ሌላ ነገር ውስጥ እየገባን መሆኑን እወቁት” የአካባቢው ነዋሪዎች
 •    ከአምስት በላይ ጎጆዎች ከ60 ኩንታል በላይ እጣን በእሳት ተቃትሏል
(አንድ አድርገን ፤ ግንቦት ተክለኃይማኖት ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ዋልድባ የሀዘን ድባብ ከጣለበት ሰንበትበት ብሏል ፤ መንግስተ በጉዳዩ ላይ የቤተክርስትያኒቱን አባቶች ለማወያየት የተስማማ ቢመስልም አሁንም ዋልድባን ማረሱን ተያይዞታል ፤ ትላንትና በቪኦኤ ላይ ባገኝነው መረጃ መሰረት ለትንሽ ጊዜያት ስራውን ካቋረጠ በኋላ ከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ  በሰፊው ማረሱን ጀምሯል ፤ ይህን የተመለከተ ትላንት የአድርቃይ እና አካባቢው ከሶስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች  የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት ወደ ቦታው እንደወረዱ ቃላቸውን ለቪኦኤ ከቦታው ሆነው ያስተላለፉት አንድ መነኩሴ ተናግረዋል ፤ አሁንም በግሬደር ሬሳዎችን እየፈነቃቀለ ይገኛል ፤ “ መንግስት አይከሰስ መሬት አይታረስ” እንደሚባለው ተረት መንግስትን የቤተክርስትያኒቱን ገዳም ከማፈራረስ እረፍ የሚለው አካል አልተገኝም፡፡

“መቻቻልን የማያውቅና ለዲሞክራሲ ፀር የሆነ ሃይማኖትን መቻል አይጠበቅብንም” መጋቢ ዘሪሁን

 • ይህ በልዩነታችሁ ያጌጠ የመቻቻል ባህል ሁሌም ከእናንተ ጋር የሚቀጥል እንደይመስላችሁ ፤ ኢትዮጵያ ገና አልተፈተነችም፡፡” / አብዱላህ

(አንድ አድርገን ግንቦት ጊዮርጊስ 2004 ዓ.ም)፡- ባለፈው ሰኞ ከሰዓት ለሀገሪቱ ከጥቂት ዓመታ በፊት የእግር እሳት የሆነባት መንግስም ለመቆጣጠርና ለማስቆም ያልቻላቸው ጉዳዮች አንዱ በሀይማኖት አካባቢ ያለን ችግር ነው ፤ በመሰረቱ ቤተክርስያናች የዚህን ችግር ገፈት ቀማሽ እንጂ ችግሩን ካመጡት ጎራ የምትመደብ አይደለችም ፤ በፊት በፊት ከአክራሪ ሙስሊሞች የሚደርሰው ጉዳት ነበር አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰው ፤ አሁን ባለንበት ጊዜ ግን መንግስት የሚያካሂደው የልማት ስራ የቤተክርስያኒቱ የነገ ህልውና ላይ የሚታይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን እያስተዋልን እንገኛለን ፤ በጊዜው ከኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር / ሽፈራው ተክለ ማርያምና ሌሎች ጥቂት ባለሥልጣናት  በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን አዲሱ ትልቁ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሃይማኖት መቻቻል ዙሪያ  ዙርያ ለመምከር  ኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር እና ከተለያዩ ሀገራት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር ተሰብስበው ነበር፡፡

Wednesday, May 30, 2012

1500 ዓመት ያስቆጠረው የአቡነ ገሪማ ገዳም ሙዚየም ተመረቀ

(Reporter ):- አንድ ሺሕ አምስት መቶ ዓመታት ባስቆጠረው የአቡነ ገሪማ ገዳም የተሠራው አዲስ ሙዚየም ግንቦት 18 ቀን 2004 .. ተመረቀ፡፡ በትግራይ ክልል በዓድዋ ወረዳ የሚገኘውና ከገዳሙ እኩል ዕድሜ 1500 ዓመታትን ያስቆጠረ የወንጌል መጻሕፍትና ጥንታውያን ቅርሶች ላሉበት ገዳም ዘመናዊ ሙዚየሙ የተገነባለት 400 ሺሕ ብር በላይ ወጪ ነው፡፡

መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቱያን የቅርስ ጥበቃና ምዝገባ የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምርያ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የፈረንሣይ መንግሥት በሰጠው 400 ሺሕ ብር በላይ ዕርዳታ መሠረት ጥንታዊው ሕንፃ ታድሶና ተዘጋጅቶ ለቤተ መዘክር አገልግሎት እንዲውል ተደርጓል፡፡

Tuesday, May 29, 2012

“ሙስሊም መሆን ይሻል ነበር” ያስባለ የሀሰት ምስክርነት


 (አንድ አድርገን ግንቦት 22 ፤ 2004 ዓ.ም)፡-የባቦጋያ ምስራቀፀሐይ መድሀኒዓለም የመሬት ጉዳይ አሁን አሁን ድራማ እያስተናገደ ይገኛል ፤ እነ ጌታቸው ዶኒ ህዝብ የወከላቸውን የአካባቢው ክርስትያኖችን ነጣጥሎ የማዳከም ስራቸውን ተያይዘውታል ፤ ፍርድ ቤቱ ቦታው ያለ አግባብ ለሪዞርት ባለቤቱ እንደተሰጠ በመቃወም ላቀረቡት ጥያቄ “ቤተክርስትያኒቱ ራሷ ትጠይቅ ፤ እናንተ የቤተክርስትያን ህጋዊ ወኪል አይደላችሁም”  የሚል ድፍን ያለ መልስ ከፍርድ ቤት  በጊዜው  እንደተሰጣቸው ገልጸን ነበር ፡፡ ይህ ጉዳዩ ፍርድ ቤቱ እንዲህ ቢልም  ክርስትያኖቹ  እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ በህገወጥ መንገድ የተወሰደውን ከ10ሺህ ካሬ በላይ  የመድሀኒዓለምን ቦታ ለማስመለስ የቻሉትን ያህል እየጣሩ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡


አቶ ጌታቸው ዶኒ የመሬቱን ጉዳይ ወጥረው የያዙትን የቤተክርስትያን የቁርጥ ቀን ልጆች ላይ ከአዲሱ የቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ጋር በመመሳጠር “አስፈራርተው ዛቻ አድርሰውብናል ፤ ለህይወታችን እንሰጋለን እና ሙዳየ ምጽዋት ገልብጠው ዘርፈዋል” በሚል የሀሰት ክስ አቅርበውባቸው ነበር ፤ የባቦጋያ መድሀኒአለም ጉዳይ ላይ “አስፈራተው ሙዳይ ምጽዋት ዘርፈዋል” የተባሉትን ግለሰቦች ፍርድ ቤት 16/09/2004 ዓ.ም ቀርበው ነበር ፤ አንደኛ ምስክር ሆነ የቀረቡት አዲሱ ቤተክርስትያኒቱ አስተዳዳሪ ቀሲስ መስፍን ፤ ሁለተኛ ምስክር አቶ ጌታቸው ዶኒ ፤ ሶስተኛ ምስክር የደብሩ ሰበካ ወንጌል ፤ ሲሆን አራተኛ ምስክር ደግሞ በብር የተገዛና አቶ ጌታቸው ዶኒ የመከረው ሰው ነበር፡፡

አባቶች ስለ ዋልድባ ዝምታን ለምን መረጡ ?

(አንድ አድርገን ግንቦት 21 2004 ዓ.ም)፡- ከቀናት በፊት ተጀምሮ ፍጻሜውን በአስር ነጥብ የአቋም መግለጫ የተጠናቀቀው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በርካታ መስተካከል የሚገባቸውን ነገሮች ለህዝበ ክርስትያን እና ለቤተክርስትያኒቱ በሚጠቅሙ አጀንዳዎች ላይ ተነጋግሮ መጠናቀቁ ይታወቃል ፤ ስብሰባው ሲጀመር የቅዱስ ሲኖዶስ 20 አጀንዳዎችን ከተቀረጹ በኋላ የዋልድባ ጉዳይ እንደ አጀንዳ አለመያዙን እያነጋገረ መሆኑን ገልጸን ጽፈን ነበር ፤ እኛ እንዳልነው ስብሰባው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ በዋልድባ ጉዳይ ላይ ምንም የተባለ ነገር አለመኖሩ ምዕመኑን አስደምሞታል ፤ ለምን አባቶች አቋማቸውን መግለጽ አልፈለጉም ? ከዚህ በላይ ችግርስ አሁን በቤተክርስትያኒቱ ላይ አለን ? ምዕመኑ የተቃወመውን ያህል አባቶች ምን እንደሚሉ መስማት የብዙዎች ፍላጎት ነበር ፤ ነገር ግን ይህ ሲሆን መመልከት አልቻልንም ፤

ማኅበረ ቅዱሳን ያቀረበው ሪፖርት ላይ የ‹‹አንድ አድርገን›› ሐሳብ

(አንድ አድርገን ግንቦት 21 2004.)- ባሳለፍነው ሳምንት ማኅበረ ቅዱሳን በዋልድባ ገዳምና በወልቃይት  የስኳር ልማት ፕሮጀክት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት አስመልክቶ አምስት  አባላት ያሉት  ልኡካን ቡድን የጥናት ዘገባ አስነብቦናል፡፡

ገዳማትና የአብነት ት/ቤቶች የቤተክርስቲያኗ ህልውና መሰረት እንደሆኑ በመገንዘብ ማኅበረ ቅዱሳን ከ100 በላ የሚሆኑ የአብነት ት/ቤቶችና ገዳማት ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ ፕሮጀክት አጥንቶ ምእመናን በማስተባበር እየተገበረ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ገዳማት ውስጥ የዋልድባ ገዳም አንዱ ነው፡፡ ማኅበሩ ፕሮጀክት አየተገበረበት የሚገኘው የዋልድባ ገዳምና የስኳር ልማት ፕሮጀክት ውዝግብን እንደ   ቤተክርስቲያኒቱ አካል ጉዳዩን በሰከነና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንደተመለከተው ከጥናቱ ዘገባ መረዳት ይቻላል፡፡

Friday, May 25, 2012

ቅዱስ ሲኖዶስ ‹በቦታው› የተገኘበት ስብሰባ እና መግለጫ ማጠቃለያ ሪፖርታዥ


·   የመግለጫው የመጀመሪያ ረቂቅ ምልአተጉባኤው ያልመከረባቸውን ዐበይት ጉዳዮችያካተተ እንደነበር ተጠቁሟል፤ የዋልድባ እና የነ አባ ፋኑኤል የሐሰት ስኬት በሥርዋጽገብቶበት ነበር
·     አባ ጳውሎስ ምልአተ ጉባኤው ስለ ማኅበረቅዱሳን ውሳኔ ባስተላለፈበት ቃለ ጉባኤላይ አልፈርምም ብለዋል፤ ስለማኅበሩ በመግለጫው ላይ የሰፈረውን አንቀጽምአላነብም” የሚል አተካራ ውስጥገብተው ነበር
·     ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን ከኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስነት አንሥቶ ወደ ጉጂና ቦረና ሊበን ዞኖች ሀ/ስብከት ለማዛወር በፓትርያ የቀረበው ሐሳብ ውድቅ ተደርጎ ብፁዕ አቡነ ገብርኤልደርበው እንዲመሩ ተወስኗል
·      አገር ዓቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መሥራች ጉባኤ ከግንቦት 26 - 27 ቀን 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
  ሙሉ ዘገባው ደጀ ሰላም ብሎግ ነው::  

Thursday, May 24, 2012

አባቶች ከባለፈ ስህተት የተማሩ ይመስላሉ

 (አንድ አድርገን ግንቦት 16 2004 ዓ.ም)፡-አባቶች ከባለፈ ስህተታቸው የተማሩ ይመስላሉ ፤ የባለፈው ዓመት የቃለ ጉባኤ ማጭበርበር ብዙዎችን አባቶች በጣም አበሳጭቶ ነበር ፤ ለቀናት የተነጋገሩበት ሳይሆን በሰዓታት በአቡነ ገሪማ አማካኝነት የተጻፈውን  መግለጫ ብዙዎችን አስከፍቶ ነበር ፤  በዚህ ጉባኤ ላይ ግን የባለፈው ሁኔታ ሊደገም አልቻለም ፤ ቃለ ጉባኤ የሚጽፉት አባቶች ያልተነጋገሩባቸውን 3 ነገሮች አካተው እንደባለፈው ሸፍጥ ለመስራ አስበው ነበር ፤ ከመፈራረማቸው በፊት እያንዳንዱ አጀንዳ ተነቦላቸው ያመኑበትን እና ያላመኑበትን ነገር ለይተው በማስቀመጥ ያልተነጋገሩባቸውን ጉዳይ  ቃለ ጉባኤው ላይ የተጨመሩትን ነገሮች በማስወጣት በከባድ ጥንቃቄ ቃለ ጉባኤውን ሊፈርሙ ችለዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ባለ አሥር ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ


ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የተሰጠ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ ፤ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 164 በተደነገገው መሰረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የዘንድሮውን መደበኛ የርክበ ካህናት ስብሰባ ከግንቦት 1 2004 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሔድ ሰንብቷል፡፡ በዚሁ መሰረት የመክፈቻ ስርዓት ጸሎት ከተፈጸመ ከበዓሉ ዋዜማ ከሚያዚያ 30 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 15 2004 ዓ.ም ድረስ ለ16 ቀናት ያህል ባደረገው ጉባኤ ጠቀሜታ ባላቸው የአጀንዳ ነጥቦች ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡ ከተላለፉት ውሳኔዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

Wednesday, May 23, 2012

አቶ በጋሻውን ለማውገዝ 4 ወር ተጠይቆበታል

  የቆቅ ለማዳ የለውም፤ እባብንም ቆዳው ለሰለሰ ብለህ ቀበቶ አርገህ አትታጠቀውም
 • በሙስና ካገኝው ‹‹መጋቢ አዲስ›› መዓረግ ወደሚመጥነው ‹‹አቶ›› ማዕረግ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ስም የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟት ባላቸው እቅድ መሰረት ቀጥተኛ የሆነውን ትምህርት ሃይማኖትና ነባር ስርዓቷን በማዛባት የኑፋቄ ትምህርት ሲያስተላልፉ የተገኙት መናፍቃን ጉዳይ በልዩ አጥኒ ኮሚቴ ሲጠና ከቆየ በኋላ አድራጎታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሚፈታተን ሆኖ በመገኝቱ ከቤተክርስትያናችን እንዲለዩ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተወግዘዋል ፤ በቤተክርስትያኑ ላይ ላሳዩት ክብረ ነክ ጉዳይም በህግ እንድጠየቁ ተወስኗ፡፡ ህብረተሰቡ ይህን በመረዳት ብርቱ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እያሳሰብን አጥፊዎች በጥፋታቸው ተጸጽተው ወደ እናት ቤተክርስትያናቸው ከተመለሱ ግን ቤተክርሰትያኒቱ በሮቿን ከፍታ ትጠብቃቸዋለች( ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያይቶ አቋም የያዘበት ነጥብ)


ማክሰኞ ከቀትር በኋላ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሎ


በኢንተርኔት ችግር መረጃ በጊዜው ባለማውጣታችን ይቅርታ እጠይቃለን

አርእስተ ጉዳይ
 • የተሃድሶ መናፍቃን መሪዎችና አስተባባበሪ የሆኑትን ግለሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ አወገዘ፡፡
 • ቃለውግዘቱ ከመደበኛው የሲኖዶስ ቃለጉባዔ በተለየ መልኩ በመገናኛ ብዙኅን እንዲነገር የውግዘቱን ጽሑፍ የሚያዘጋጁ አራት ሊቀነጳጳሰት ተመርጠዋል፡፡
 • በጋሻው ደሳለኝ ኮሚቴው አጣርቶ ያቀረባቸው ሁለት መረጃዎች የሚያስወግዙት ቢሆንም፣ ለገቢያ ያዋላቸው ስምንቱ የስብከት ካሴቶች፣ በአውደ ምህረት ያሰተማራቸው ትምህርቶች የድምጽወምስል መረጃዎች ኮሚቴው አብሮ አይቶ እንዲያቀርባቸውና የጥቅምቱ ሲኖዶስ ላይ በጋሻው ከነትምህርቱ እንዲወገዝ ተወስኗል፡፡ ኮሚቴ ወደ አስር የሚጠጉትን የድምጽወምስል መረጃዎች ያላያቸው በፓትሪያሪኩና በእጅግአየሁ በየነ ተጽእኖ ስለተደረገበት መሆኑን ተነግሯል፡፡
 • ለሊቃውንት ጉባዔ ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት መናፍቃኑ ላስተማሩት ኑፋቄ በቃልም በጽሁፍ መልስ እንዲሰጥ ታዟል፡፡

(አንድ አድርገን ግንቦት 15 ፤ 2004ዓ.ም )፡- ቅዱስ ሲኖዶስ ማክሰኞ በጠዋቱ ውሎ የተሃድሶ አራማጅ ድርጅቶችን በተመለከተ በማሕበረቅዱሳን በኩል መረጃዎች ቀርበው፣ የሊቃውንት ጉባኤ አጣርቶ፣ ለሊቃነ ጳጳሳት ኮሜቴ ባቀረበው ሪፖርት መሰረት ቅዱስ ሲኖዶስ ማኅበራቱን አውግዟል፡፡በህግ እንዲጠየቁም ትእዛዝ ማስተላለፉን ገልጸን ነበር፡፡

ማክሰኞ ጠዋት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሎ


• (ሰበር ዜና) ማኅበረቅዱሳን ከሠንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መመረያ ሰር መመራቱ ቀርቶ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ቤተክህነቱ ሥራአስኪያጅ እንዲሆን ተወሰነ፡፡
• የተሃድሶ አራማጅ ድርጅቶች ተወገዙ፡፡በህግም ይጠየቃሉ፡፡
• መ/ር እንቁ ባህርይ ተከስተ ጉዳይ እንደባለፈው ጥቅምቱ ሲኖዶስ ተደባብሶ ታለፈ፡፡


(አንድ አድርገን ግንቦት 15 ፤ 2004ዓ.ም )፡- በዛሬ ጠዋት በትናንቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በተወሰነው መሰረት በማኅረቅዱሳንና በማደራጃ መምሪያው ስለተፈጠረው ችግር መላእከ ጽዮን ቆሞስ አባ ሕሩይ ወንድይፍራውና የማኅበሩ አመራሮች ምልዓተ ጉባኤ ቀርበው እንደሚያስረዱ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም ምልዓተ ጉባኤው የማኅበሩን አገልግሎት እያደናቀፈው ያለው የመምሪያው ማኅበሩን የመምራት አቅም ማነስ በመሆኑ ማህበሩ ለጠቅላይ ሥራአስከያጁ ተጠሪ እንዲሆን ወስኗል፡፡ 

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዘጠነኛ ቀን ውሎ
ቅዱስ ሲኖዶስ የማኅበራት መተዳደርያ ደንብ ጥናት ዳግመኛ ተጠንቶ እንዲቀርብ አዘዘ
አርእስተ ጉዳይ-
·             በማኅበራት መተዳደሪያ ደንብ ዝግጅት ላይ የቀረበው ጥናት የጽዋ፣ የጉዞና የስብከተ ወንጌል ማኅበራት፤ የጽርሐ ጽዮን አንድነት ማኅበር፣ የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበረና የማኅበረ ቅዱሳን ህልውና እንዲከስም የሚጠይቅ ነው
·             የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበዋል
·             የሰንበት /ቤቶች / ሊቀ ጳጳስ ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተና ጸሐፊውለመሪያው የማይመጥኑበሚል ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ጠይቀዋል
·             ዕንቍ ባሕርይ በማ/ ላይ ተጨማሪ የክስ ደብዳቤ ለምልአተ ጉባኤው አሰራጭቷል፤ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ እና የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት ቀርበው ያስረዳሉ

·             ብፁዕ አቡነ አብርሃም አቡነ ፋኑኤልን ቋቋሙ - “እኔ ወጪውን እችላለኹ፤ ከእኔና ከአንተ ማናችን ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም ሥራ እንደ ሠራ አጣሪ ተልኮ ይጣራ?”
§  ·የጨለማው ቡድን በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ በኮሚቴው የቀረበውን የጥናት መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ ለማስገልበጥ እየተንቀሳቀሰ ነው
§  ·አባ ጳውሎስ የቀሲስ / መስፍንን አቤቱታመዋቅሩን ጠብቆ አልመጣምበሚል ለማዘግየት እየሞከሩ ነው፤ የዋሽንግተን ዲሲ ሀገረ ስብከት ልኡካንንበነገር አቀጣጣይነትከሰዋል
§  ·የዕርቀ ሰላም ንግግሩ በሐምሌ ወር ይቀጥላል፤ አባ ጳውሎስና አባ ፋኑኤል አባ መልከ ጼዴቅን በፖሊቲከኛነት ከሰዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ በበኩላቸውበውጭ ያሉት አባቶች ዕርቀ ሰላሙን ከልብ የሚፈልጉ ናቸው፤ ችግር ያለው እዚህ ቤት ነውበማለት ለፓትርያርኩ ወቀሳ ምላሽ ሰጥተዋል