Wednesday, May 2, 2012

የዋልድባ ገዳም የስኳር ልማት ቁጣ ቀሰቀሰ

  •       ሰዎች በብዛት ወደ ገዳሙ እንደተጓዙ የዓይን ምስክሮች ገለጹ 
  • (VOA NEWS):- ለስኳር ልማት ሊውል ወደታቀደበት የዋልድባ ገዳም አካባቢ፤ ህዝብ ከተለያዩ አካባቢዎች እንዳቀና ምስክሮች ገለጹ። ከተለያዩ የጎንደር ከተሞች የተውጣጡ በርካታ ነዋሪዎች፣ ዋልድባ ገዳም አካባቢ ይሠራል የተባለውን የስካር ፋፍሪካ በመቃወም፤ ወደ ግድቡ መሥሪያ ስፍራ እንደሄዱ ተሰምቷል።በዚህም የተነሳ አንዳንድ ውዝግብ እንደተቀሰቀሰ ከአካባቢው ለአሜሪካ ድምጽ አስተያየታቸውን የሰጡ ግለሰቦች ገልጸዋል።


በሃያም፣ በሃምሳም፣ በመቶም እየሆነ የተመመው ሕዝብ ማንም ያላሰባሰበውና ያላስተባበረው፣ ነገር ግን በራሱ ፈቃድ ጥሩምባ ነፍቶና ብሎ እንደሆነየአይን ምስርክር ገልጸዋል። እንደምስክሩ አገላለጽ ጦር  ያለው ጦሩን፣ መሣሪያ ያለው መሣሪያውን፣ ዶማና አካፋ ያለውም ያንኑ እየያዘ ነው ግድቡ ይሠራል ወደተባለበት ስፍራ የተጓዘው። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን፣ ወታደሮች ወደ ሕዝብ ለመተኮስ እንዳይሞክሩ መንግሥት ማስጠንቀቁንም እኒሁ ምንጭ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አንድ ከዚያው ከገዳሙ አካቢ ያሉ ቄስ «ከወልቃኢትም፣ ከጠገዴም፣ ከአድርቃይም፣ ከማይፀብሪም ባለሥልጣናት ተጠርተው ሥራው ሊቆም ተደራድረዋል፤ ለዚህም ቀጠሮ ለሚያዝያ ፳፱ ተይዟል» ሲሉ ለቪኦኤ ገልጸዋል። በመንግሥት በኩል ላለው ምላሽ ከዚህ ቀደም አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ በመስጠት ወደተባበሩን፣ የማይፀብሪ አስተዳዳሪ ወደሆኑት ወደ አቶ ሲሳይ መረሣ ዘንድ ደውለን ለጊዜው ስብሰባ ላይ ስለነበሩ ማግኘት አልተቻለም።

3 comments:

  1. Gena bizu tiru neger enesemalen! Gena! Egziabher yeabatochin tselot eyemelese new.

    ReplyDelete
  2. Gudayu beselamawi menged endifeta hulum yebekulun astewatsio endiaderg egziabher yirdan. Tsihufochin endezih betiniqaqe bitayuachew melkam new.Mengist tekus endaynor mazezun adenqalehu. Egziabher kehulachin gar yihun.

    ReplyDelete
  3. ክርስቶስ ያለውን ማንም አያስፈራውም። ማነንም መፍራት የለብንም። የእስራኤል አምላክ ከኛ ጋር ነው። ከሀይማኖት በላይ ማን አለ? ለሰማያዊው ቤታችን ወይንስ ለዚህ የጥላ ስር ህይወታችን መጨነቅ ያለብን? ከነ ዮዲት ጉዲት፣ ከግራኝ አህመድ፣ከግብጾችና ከደርግ ጠላቶቻችን የጠበቀን አምላክ ዛሬም ከኛ ጋር ነው። የማያቆም ከሆነ ምን እስክንሆን እንጠብቃለን? የአስቴር አምላክ ይርዳን!!!!
    የአባቶቻችን አምላክ ይጠብቅን!!!!!!!!!

    ReplyDelete