Monday, May 7, 2012

ዋልድባን ማን ዘረፈው?



(አንድ አድርገን ሚያዚያ 29 ፤ 2004ዓ.ም)፡-በቅርቡ ዋልድባ ገዳም ባልታወቁ ሰዎች መዘረፉን ሰምተናል ፤ ይህ ነገር ግን ማነው የፈጸመው? የሚለው ጥያቄ መልስ የሚያሻ ይመስለናል ፤ ምዝበራው በተከናወነበት እለት የገዳሙ አባቶችን በማስገደድ በአንድ ቦታ በመሰብሰብ ፊታቸውን ጭንብል በለበሱ ሰዎች አማካኝነት በማስፈራራት ዝርፊያው እንደተከሰተ ለማወቅ ችለኛል ፤ በወቅቱ የገዳሙ አባቶች በአካባቢው ለሚገኝው የፖሊስ ጣቢያ የደረሰባቸውን ነገር ለሊት በስልክ ዝርፊያው ከተከናወነ በኋላ ደግሞ በጠዋት ለሚመለከታቸው የፖሊስ አካላት ሪፖርት አድርገዋል፡፡ አባቶች ከእነርሱ የሚጠበቀውን ነገር አከናውነዋል የሚል እምነት አለን ፤ በዚች አንድ ቀን ከዚህ በፊት ተከናውኖ በማይታወቅ መልኩ ከለሊቱ 6፡00 ሰዓት በኋላ ጭንብል በለበሱ ሰዎች አማካኝነት ለዓመት ቀለብ ብለው ያጠራቀሟት 66 ሺህ ብር በዘራፊዎች ከንብረቶቻቸው ጋር ተወስደዋል ፡፡ ገዳም ንግድ ተነግዶ ብር የሚተረፍበት ቦታ አይደለም ፤ ቦታው የጾምና የጸሎት ነው ፤ ዓለምን ንቀው ራሳቸውን ለአምላካቸው አሳልፈው የሰጡ አባቶችን ነው የምታገኙት ፤ ይህ ሁኔታ ከተከሰተ በኋላ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ስለ ጉዳዩ የአካባቢውን የፖሊስ ኋላፊ ማነጋገር ችለው ነበር ፤ ያገኙት መልስ አጥጋቢ ባይሆንም ፤ በጊዜው አባቶቻችን የሆነው ነገር ለአካባቢው ፖሊስ ሁኔታው ከተፈጸመ ከደቂቃዎች በኋላ በስልክ ፤ በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ደግሞ በአካል ፖሊስ ማዘዣው ድረስ በማምራት የሆነውን ነገር ለአዛዡ ማስረዳት ችለው ነበር፡፡ የተሰጣቸው መልስ እናጣራለን የሚል ነበር ፤ ሁሉንም ነገር ታስቦ የተደረገ እ የሚጣራ ነገር በይኖርም ፤ የዚያን ቀን ማታ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ላይ ጉዳዩን አንስተው አቤቱታውን የተቀበሉትን የፖሊስ አዛዥ ሲያናግሯቸው ፤ ‹‹ምንም የሰማውት ነገር የለም ፤ አሁን በአካባቢው አይደለውም›› በማለት ‹‹አይኔን ግንባር ያድርገው››  አልሰማውም አላየውም የሚል መልስ ሰጥተዋል ፤ ነገር ግን ከእሳቸው የተሰወረ ነገር ኖሮ አይደለም ፤እሳቸውም ሳያውቁት የተከናወነ ነገርም የለም::

አቶ አዲሱም(የቪኦኤ ጋዜጠኛ) የገዳሙ አባቶች ‹‹የተደረገውን ነገር ለአካባቢው ፖሊሶች አሳውቀናል›› ብለው ነግረውኛል ሲላቸው ፤ የአካባቢው የፖሊስ አዛዥ ደግሞ ‹‹ አልሰማው ›› በማለት ክደዋል ፤  ከላይ ያለው አመራር ከታች ላሉት አመራሮች ያስተማራቸው አንዱ ነገር ቢኖር ‹‹አይኔን ግንባር ያድርገው ›› የሚለውን ነገር ይመስለናል ፡፡ እኛ ግን  ‹‹ አይንን የሰራ አምላክ አይናቸውን ግንባር ማድረግ ይችላል ብለን እናምናለን›› መጽሐፈ ምሳሌ 2012 ላይ ‹‹የሚሰማ ጆሮንና የሚያይ ዓይንን፥ ሁለቱን እግዚአብሔር ፈጠራቸው። ›› ይላል ፤ እኛም ሆንን እነርሱ የምናይበት አይን እና እና የምንሰማበትን ጆሮ ባለቤቱ እንደፈጠረው ማወቅ መቻል አለብን ፤ ለዛሬ እነርሱ አይተው እንዳላዩ ፤ ሰምተው እንዳልሰሙ ቢሆኑ አትፍረዱባቸው ፤ እነርሱ አልማር ብለው እንጂ በቴሌቪዥን መስኮት ስትመለከቷቸው በሬዲዮ ስትሰሟቸው  የነበሩትን ባለስልጣናት  ዛሬ አንደበታቸው የተያዙትንና አልጋ ላይም የወደቁትን ብታውቁ ጉድ ነበር የምትሉት !! የአባቶቻችንን ድምጽ ባትሰሙ አምላክ ይሰማቸዋል ፤ ለእነርሱ መልስም ባትሰጧው እርሱ ይሰጣቸዋል ፤ አሁን የምታደርጉት ነገር ግን ለራሳችሁም ህሊና ተቀባይነት ያለው አይመስለንም ፤ ህሊና ያለው ሰው እየሆነ ያለውን ነገር ማመዛዘን ይችላል ፤ ህሊና የሌለው ሰው ግን የሚያመዛዝንበት ሚዛን የለውም ፤ እኛ ገዳም በታጣቂ ራሳቸውን በሸፈኑ ሰዎች ተዘረፈ ሲባል አሁን ነው  የሰማነው ፤ በአሁኑ ሰዓት እኛ ገርሞን ሊሆን ይችላል ወደፊት ከዚህም የባሰ ነገር ሊሰሙ ይችላሉ ፡፡

መቼስ ዋልድባን እንደ ጻድቃኔ ማርያርም 180 ኪሎ ሜትር በመሄድ ጸሎት የምናደርስበትና በረከትም ይምንካፈልበት ገዳም አይደለም ፤ በቅርብ ርቀትም የሚገኝ አይደለም ፤ የገዳሙን በረከት እነርሱ ከእኛ ይልቅ ያውቁታል ፤ ግን ለምን ? አይተው እንዳላዩ ሰምተው እንዳልሰሙ በመሆን ተነሱበት ? ገዳሙ ላይ የወረወራችሁት ጦር ፊቱን እንዳያዞር ለራሳችሁ ስጉ ፤ የገዳሙ አባቶች ‹‹ተዘረፍን›› ሲሉ እናንተ ለምን ለማስተባበል ሞከራችሁ ? በአሁኑ ሰዓት በገዳሙ ላይ እየተካሄደ ያለው ነገር ‹‹ሀገር ያወቀው ጸሀይ የሞቀው ነገር ነው›› ታዲያ ለምን ስህተታችሁን ትሸፍናላችሁ ፤ ሁሉም ሰው ሊያጠፋ እና ሊሳሳት ይችላል  ፤ መሳሳት እና ማጥፋ ምንም ነገር ማለት አይደለም ፤ ዋናው መሰረታዊ ችግር ስህተትን አለማመን  ነው ፤ ስህተትን ማመን ሞት የሚመስለው መንግስት መሀል መኖራችን ስናስበው ለራሳችን እናፍራለን ፤ ነገ መኖሩን የማያውቀው ሰው(በረከት ስምኦን) ‹‹ይችን ሀገር 40 ዓመት መግዛት አለብኝ ብሎ በአደባባይ ተናግሯል›› ፤ በዚህ አካሄድ ለ40 ቀን ስጋት ይግባ እንላለን ፤ ሰው ዝም ቢል እግዚአብሔር ይነቅላል፡፡
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ‹‹ማነው ገዳሙን የዘረፈው ?›› ሁሉም ሰው ያወቀውን ነገር ግን ለመናገር ድፍረት ያጣውን ነገር እኛ እንናገራል፤ ገዳሙን የዘረፈው መንግስት ነው ፤ በቦታው ላይ በአሁኑ ወቅት በታጠቁ የመከላከያ እና የፌደራል ፖሊሶች አማካኝነት ወደ ቦታው ለማለፍ ኩላሊትና የውስጥ አካል በሚመረመርበት ጊዜ የትኛው ዘራፊ ከየት መጣ ማለት እንችላለን ? እንዴ ! እኛም የምናስብበት ጭንቅላት እንዳለን አትርሱ ፤ አይደለም የሰራችሁት ያሰባችሁትን ራሱ መረጃ ይደርሰናል ፤የገዳሙ አባቶች ስም ጠርተው መናገር እንዳይችሉ ፊታቸውን ጥቁር ጨርቅ ሸፍነው ገዳሙ አለኝ የሚለውን ነገር በመበርበር የሚፈልጉትን ነገር ጠራርገው ሲወሰወዱ ተመልክተዋል ፤ እና የትኛው ሌባ ነው ገዳም 65ሺህ ብር ለመመዝበር የሚንቀሳቀሰው ?  እኛ ግን እርግጠኛ ሆነን መናገር እንችላለን ይህ ነገር የተከናወነው መንግስት በላካቸው ጀሌዎቹ አማካኝነት መሆኑን ሳንጠራጠር እንናገራለን ፡፡

አሁንም ደግመን መናገር እንችላለን ይህ ምዝበራ የተካሄደው በጀሌዎቻቸው አማካኝነት ነው ፤ እኛ ይጠብቀናል ከመሰል ዘራፊዎች ይከላከልልናል ብለን ከደሞዛችን ላይ ግብር ቆርጠን የምሰጠው መንግስት ራሱ ዘራፊ ከሆነ ምን እንላለን ? ‹‹አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ ›› ከማለትስ ውጪ ምን ይባላል ፤ ይህን ነገር መንግስት ያደረገው መረጃ ለማግኝት እንጂ ፍቅረ ነዋይ ኖሮበት እንዳልሆነ እናውቃለን ፤ ግን ይህም ቢሆን ህገ ወጥ ነው በማለት እንቃወማለን ፤ የገዳሙ መነኮሳት ያነሱትን ጥያቄ በአግባቡ መስማት ፤ ምዕመኑን በማወያየትና ተገቢ መልስ መስጠት አግባብ ነው ብለን እናምናለን ፡፡ ትልቁ ችግር አልሸነፍ ባይነት አጉል ነገር መሆኑን እናውቃለን ፤ ከላይ ሲቆጧቸው ኮስተር የሚሉ ፤ ህዝቡ ሲናገራቸው ደግሞ በሰሩት ስራ የሚያፍሩ ሰዎች መሀል መኖራችንን አንዘነጋም ፤ 80 ቢሊየን ብር የወጣበትን የአባይ ግድብን ደግፈናል ፤ 8 ቢሊየን ብር የሚወጣበትን የሸንኮራ ልማት ግን ተቃውመናል፡፡  ነገ ጥያቄ እንደሚኖር አንዘንጋ ፤

በመሰረቱ መንግስትንም ቢሆን ያለ ስራው መወንጀል አግባብ እንዳልሆነ እናምናለን ፤ ነገር ግን ያለ መረጃ ብናወራ የራሳችን ህሊና ይቃወመናል ፤ አስኪ ዋልድባን የምታውቁ ሰዎች ለማያውቁት የቦታውን ርቀት አስረዱልን ፤ ታዲያ ይህን ያህል መንገድ 65ሺህ ብር ለመዝረፍ  ዘራፊ መጣ ብለን እንመን ? እኛ ግን አናምንም ፤ ለምን ብትሉን በአሁኑ ሰዓት አይደለም የተደራጀ ዘራፊ አካባቢውን ሊረግጥ ቀርቶ አንድ የኔ ቢጤ ተራ ሰው እንኳን የውስጥ አካሉን በcity scan እስከሚመለከቱት ድረስ ፍተሸ በሚደረግበት ቦታ ላይ የታጠቁ ዘራፊዎች ጭንብል ለብሰው በገዳሙ ላይ የዝርፊያ ሙከራ አደረጉ ቢባል ለነጋሪም ሆነ ለሰሚ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው ፤ ዘራፊው መንግስት ነው ፤ 65ሺህ ብር የወሰደውም እርሱ ነው ፤ መረጃ ፈልጋችሁ በላካችኋቸው ሰዎች ብሩንም ጠራርገው ወስደውላችኋል ደስ ይበላችሁ ፤ ብሩ ብዙ ሆኖ አይደለም ምግባራችሁ ግን በጣም ያሳፍራል ፤ በጣምም ያሳዝናል ፤ ለአንድ መጽሄትና ጋዜጣ ብዙ ሰላይ በመላክ የኮምፒዩተር ፤ የኢሜል መረጃ ከህግ ውጪ የመዘበራሁ ሰዎች ይህን አታደርጉም ብለን ማሰብ ይከብደናል ፡፡ አደራ እውነቱን ስለተናገርኩኝ አትቀየሙኝ ፤ በየዋህነት ከስህተት ጎዳናችሁ ብትመለሱ ብዬ ነው ይህን የጻፍኩት ፡፡

ታዲያ ይህን ብር እና መሰል ንብረቶችን ማን ዘረፋቸው ? ዘራፊዎቹ ለምን ዝቋላ ፤ አሰቦት ፤ ደብረሊባኖስ አላመሩም ? ዋልድባ ያለው ሀብት ከዚህ በልጦባቸው ይሆን ?  በ8 ቢሊየን ብር የማይጠቅማችሁን ነገር ፤ የምትወቀሱበትን ነገር እየሰራችሁ መሆኑን አትርሱ ፤  ጉልበትም እኮ ይደክማል ፤ ኃይልም ይዝላል ፤ ነፍስም ወደ ፈጣሪዋ ትመለሳለች ፤ ሁሉም ነገር ያልፋል ፡፡  እናንተ ግን የዋልድባ ገዳም የዓመት ቀለባቸውን ብትወስዱባቸውም የማይተዋቸውና የማይረሳቸው አምላካቸው ምንም ሳይጎልባቸው ያኖራቸዋል ፤ የወሰዳችሁት ብር ምንም እንደማይጠቅማችሁ እናውቃለን ፤ የምትፈልጉትንም መረጃ እንዳላገኛችሁ መጽሀፍ ይዘን እንምላለን ፤ የዛሬ 20 ዓመት በዚች ቤተክርስትያን ላይ ያላችሁን አላማ በአባላችሁ በተጻፈ መጽሀፍ ሰዎች ቢያነቡም እውነት ነው ብለው ለመቀበል ሲያቅታቸው አስተውለናል፡፡ ገዳም የሚያዘርፍ ተግባራችሁ ግን ነገ እናንተ ለራሳችሁ እንደምታፍሩበት አንጠራጠርም ፤ ለምን ቢባል ፤ እግዚአብሔር ወደ ፈጠረላችሁ ህሊናችሁ ትመለሳላችሁ ብለን ስለምናስብ ነው ፤ ሰው እግዚአብሔር ከፈቀደለት መጀመሪያ ላይ ፤ ያለበለዚያ በህይወቱ አጋማሽ ላይ ፤ ወይም ደግሞ መጨረሻ ላይ ልቦናው ይመልሰዋል ብለን ስለምናምንም ይሆናል ፤ ካልተመለሰ ደግሞ…..

ይህን የምታነቡ ሰዎች ፡- ‹‹ ማነው ይህን ዝርፊያ ያደረገው ብላችሁ ታምናላችሁ? ህግም ቢኖር ከህጉ ጀርባ ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅመው መንግስት አለመሆኑን በምን እርግጠኛ ሆነን መናገር እንችላለን ? አሁን አሁን እኛ ስናስበው መፍትሄ ከሰው  ዘንድ አንጠብቅም ፤ ለምን ፈተና መጣ አንልም ፤ መሹለኪያ መንገዱን የሚያሳይ አምላክ ስላለን ምንም አንልም ፤ ‹‹ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።››1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች10፤13 ፤ ከእኛ የሚጠበቀው ዘወትር ሳንሰለች መጸለይ ብቻ ነው ፤ እስራኤላውያንን ከ400 ዓመት በኋላ ታግሶ ነጻ ያወጣ አምላክ አሁንም ከእኛ ጋር መሆኑን አንርሳ ፤ ‹‹ቢዘገይም የሚቀድመው የለም›› ይህን እንመን ፡፡

በሆነ ወቅት ያነበብኩትን ላካፍላችሁ ፤ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በ1818 አካባቢ በአሌክሳንደር ፑሽኪን በጊዜው የነበረው መንግስት በመቃወም ፤ የወደፊቱን ጊዜ ከማመላከት አኳያ እንዲህ ሲል ቋጠረላቸው



The will rise , believe me comrade
A star of captivating bliss,
When Russian wakes up from her sleep
And when our names will both be written
Ohh the ruins of despotism


እመኑኝ ወንድም እህቶቼ ..እመኑኝ
የደስታችን አብሳሪ ኮከቦች
የምስራቾቻችን ነጋሪዎች መብራ የጀመሩ እለት
ሩሲያ ከእንቅልፏ ትነቃለች
ያን ጊዜ……..ያን ጊዜ…..
ስማችን በገዥዎቻችን መቃብር ላይ ይጻፋል
በአምባገነን ቅሪት ላይ ይነሳል ……   እያለ ፑሽኪን ይቀጥላል ፤ እኔ ግን ለኢትዮጵያ እና ለቤተክርስትያናችን  ይችን ያህል ወሰድኩ ፤
አዎን ወንድም እህቶቼ እመኑኝ
ኢትዮጵያም ከእንቅልፏ ትነቃለች
ቤተክርስትያናችንም ትነሳለች
ያን ጊዜ..ያን ጊዜ ….
የገፏት ከፊቷ ይቆማሉ
ስማችንን እንደ አሌክሳንደር ፑሽኪን በገፉን ሰዎች ቅሪት ላይ ከመጻፍ ይልቅ ይቅር የምንልበት ጊዜ ይመጣል ………..
   

14 comments:

  1. E/R yistachihu!!! ewonet yeminager betefabet giz endih ewonet silawotachu lebetkirstian bemekomachum des belognal!!!! bertu E/R yirdachihu!!!!!

    ReplyDelete
  2. Dhugaasaa BaasaaMay 7, 2012 at 4:04 AM

    I have no doubt....about...no doubt Oh GOD forgive for they do not know what they are doing.

    ReplyDelete
  3. ስማችንን እንደ አሌክሳንደር ፑሽኪን በገፉን ሰዎች ቅሪት ላይ ከመጻፍ ይልቅ ይቅር የምንልበት ጊዜ ይመጣል ………..

    ReplyDelete
  4. really thank you due to you are writing about the reallity! none does not stole our maney rather than the govt. Our GOD will give as more than that this is because he can do any thing as he want. so gest praying is our response for those un believable govt.

    ReplyDelete
  5. ''...ይህን ነገር መንግስት ያደረገው መረጃ ለማግኝት እንጂ ፍቅረ ነዋይ ኖሮበት እንዳልሆነ እናውቃለን...'' ብላችሁ ጽፋችኋል:: ፍቅረ ንዋይ እንዳለበት ግን አላወቃችሁም:: ፍቅረ ንዋይ ባይኖርበት ኖሮማ ትንሽ ዶላር ለማግኘት ብሎ የምእራባውያን ውሻ በመሆን በአለም ግርማ ሞገስ ያላትንና የምትፈራዋን የሀገራችንን ማንነት ለማጥፋት ባልተነሳ ነበር:: በርግጥ የዋልድባን ብር የዘረፈው የፍቅረ-ንዋይ ጥማቱን ለማርካት ሳይሆን መረጃ ፍለጋና በVOA ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸውን መነኩሴ ፍለጋ ነው:: መንግስት ግን ከማናችንም በላይ ሃይለኛ የገንዘብ ጥማት አለበት አትጠራጠር:: በርግጥ የተዘረፈው 65,000 ብር ወደ መንግስት ካዝና ወይም ወደነ መለስና በረከት ስምኦን ኪስ አልገባም:: በዘራፊዎቹና በቅርብ አዛዦቻቸው እጅ ነው የቀረው:: እረ እስኪ ተውን 'ማወቁንስ እናውቀዋለን....' አለ ያገሬ ሰው:: ማን ዘረፈ በማለት ጊዜ አታቃጥሉ ይሔ ምንም analysis የሚያስፈልገው ነገር አይደለም:: የፖሊስ አዛዡ ደግሞ ለVOA መጨረሻ ላይ የመለሰውን የሰማኸው አለመሰለኝም:: እንደ ፖሊስ አዛዥ ማወቅ ያለበትን ጉዳይ 'እኔ አላውቅም ሄደህ እነሱኑ (መነኮሳቱን) መጠየቅ ትችላለህ' ነበር ያለው:: ሌባ መንግስት ባለበት ሃገር እየተሰራ ያለው ስራ ሁሉ እንዴት ያቃጥላል መሰላችሁ:: እስኪ ተውኝ:: እኔ VOA ስሰማ እንዴት ተቃጠልኩ መሰላችሁ:: ያ የፖሊስ አዛዥ ጋ አጠገቡ ብሆን ኣጥፍቼው ይህ አረመኔና ሌባ መንግስት በጁ እንዳያስገባኝ እራሴን አጠፋ ነበር:: እስኪ ይሁን አሁንም ከዚህ በላይ እየተቃጠልኩ የምኖር አይመስለኝም ኢትዮጵያን ለማጥፋት ታጥቀው ከተነሱት አንዱን ሳላጠፋ እድሜዬን እንዳያሳጥረው ጽኑ ምኞቴ ነው::

    Biruh

    ReplyDelete
    Replies
    1. አሜን እግዚአብሄር መልካም ጊዜ ያምጣልን፡፡

      Delete
  6. ''...ይህን ነገር መንግስት ያደረገው መረጃ ለማግኝት እንጂ ፍቅረ ነዋይ ኖሮበት እንዳልሆነ እናውቃለን...'' ብላችሁ ጽፋችኋል:: ፍቅረ ንዋይ እንዳለበት ግን አላወቃችሁም:: ፍቅረ ንዋይ ባይኖርበት ኖሮማ ትንሽ ዶላር ለማግኘት ብሎ የምእራባውያን ውሻ በመሆን በአለም ግርማ ሞገስ ያላትንና የምትፈራዋን የሀገራችንን ማንነት ለማጥፋት ባልተነሳ ነበር:: በርግጥ የዋልድባን ብር የዘረፈው የፍቅረ-ንዋይ ጥማቱን ለማርካት ሳይሆን መረጃ ፍለጋና በVOA ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸውን መነኩሴ ፍለጋ ነው:: መንግስት ግን ከማናችንም በላይ ሃይለኛ የገንዘብ ጥማት አለበት አትጠራጠር:: በርግጥ የተዘረፈው 65,000 ብር ወደ መንግስት ካዝና ወይም ወደነ መለስና በረከት ስምኦን ኪስ አልገባም:: በዘራፊዎቹና በቅርብ አዛዦቻቸው እጅ ነው የቀረው:: እረ እስኪ ተውን 'ማወቁንስ እናውቀዋለን....' አለ ያገሬ ሰው:: ማን ዘረፈ በማለት ጊዜ አታቃጥሉ ይሔ ምንም analysis የሚያስፈልገው ነገር አይደለም:: የፖሊስ አዛዡ ደግሞ ለVOA መጨረሻ ላይ የመለሰውን የሰማኸው አለመሰለኝም:: እንደ ፖሊስ አዛዥ ማወቅ ያለበትን ጉዳይ 'እኔ አላውቅም ሄደህ እነሱኑ (መነኮሳቱን) መጠየቅ ትችላለህ' ነበር ያለው:: ሌባ መንግስት ባለበት ሃገር እየተሰራ ያለው ስራ ሁሉ እንዴት ያቃጥላል መሰላችሁ:: እስኪ ተውኝ:: እኔ VOA ስሰማ እንዴት ተቃጠልኩ መሰላችሁ:: ያ የፖሊስ አዛዥ ጋ አጠገቡ ብሆን ኣጥፍቼው ይህ አረመኔና ሌባ መንግስት በጁ እንዳያስገባኝ እራሴን አጠፋ ነበር:: እስኪ ይሁን አሁንም ከዚህ በላይ እየተቃጠልኩ የምኖር አይመስለኝም ኢትዮጵያን ለማጥፋት ታጥቀው ከተነሱት አንዱን ሳላጠፋ እድሜዬን እንዳያሳጥረው ጽኑ ምኞቴ ነው::
    Biruh

    ReplyDelete
  7. What about the people who went to Waldba with different types if firearms? Sewu gejera, tor, mesaria, akafa.... Minamn yizo bebudn bebudn eyehone tememe sitlun alneber ende?
    Kenesu wist bihonus zerafiwoch?
    Yaweqn eyemeselen hizbun Gira banagabana ke-mengist gar banatala tiru new. Esun le-poletikegnoch enitewilachew....

    ReplyDelete
  8. What about the people who went to Waldba with different types if firearms? Sewu gejera, tor, mesaria, akafa.... Minamn yizo bebudn bebudn eyehone tememe sitlun alneber ende?
    Kenesu wist bihonus zerafiwoch?
    Yaweqn eyemeselen hizbun Gira banagabana ke-mengist gar banatala tiru new. Esun le-poletikegnoch enitewilachew....

    ReplyDelete
  9. egzihabehire gize alewe!

    ReplyDelete
  10. I was WALDEBA IN 1996E.C the road takes more than 28 hr. I don't know how i'm talken about from ADERKAY to WALDEBA so defintely the GOVERNMENT did it this dam thing EMBARACING.

    ReplyDelete
  11. May God bless u Andadgren
    ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ‹‹ማነው ገዳሙን የዘረፈው ?›› ሁሉም ሰው ያወቀውን ነገር ግን ለመናገር ድፍረት ያጣውን ነገር እኛ እንናገራል፤ ገዳሙን የዘረፈው መንግስት ነው ፤

    Awo tikikil the government who does all this.

    ReplyDelete
  12. are ebakachu be haymanot sem ye enante yal awaki sami poletica selechen!le men andegnawen tekelelachu ategbubetem chenbelachehun awelekachu?

    ReplyDelete