Thursday, May 31, 2012

በዋልድባ ከሶስት ሺህ ሰው በላይ ለተቃውሞ መንግስት ላይ ተነሳስቷል

  •   ስብሰባው ላይ ለመገኝት በመኪና ሲመጡ የነበሩ የመንግስት ባለስልጣናት መኪናቸው መንገድ ላይ ተገልብጧል
  • “እኛ ምንም ኮሚቴ ማቋቋም አያስፈልገንም የምንፈልገው ስራውን እንድታቆሙ ብቻ ነው ፤ የህዝቡን ጥያቄ ረግጣችሁ ስራውን ብትቀጥሉ ግን ሌላ ነገር ውስጥ እየገባን መሆኑን እወቁት” የአካባቢው ነዋሪዎች
  •    ከአምስት በላይ ጎጆዎች ከ60 ኩንታል በላይ እጣን በእሳት ተቃትሏል
(አንድ አድርገን ፤ ግንቦት ተክለኃይማኖት ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ዋልድባ የሀዘን ድባብ ከጣለበት ሰንበትበት ብሏል ፤ መንግስተ በጉዳዩ ላይ የቤተክርስትያኒቱን አባቶች ለማወያየት የተስማማ ቢመስልም አሁንም ዋልድባን ማረሱን ተያይዞታል ፤ ትላንትና በቪኦኤ ላይ ባገኝነው መረጃ መሰረት ለትንሽ ጊዜያት ስራውን ካቋረጠ በኋላ ከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ  በሰፊው ማረሱን ጀምሯል ፤ ይህን የተመለከተ ትላንት የአድርቃይ እና አካባቢው ከሶስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች  የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት ወደ ቦታው እንደወረዱ ቃላቸውን ለቪኦኤ ከቦታው ሆነው ያስተላለፉት አንድ መነኩሴ ተናግረዋል ፤ አሁንም በግሬደር ሬሳዎችን እየፈነቃቀለ ይገኛል ፤ “ መንግስት አይከሰስ መሬት አይታረስ” እንደሚባለው ተረት መንግስትን የቤተክርስትያኒቱን ገዳም ከማፈራረስ እረፍ የሚለው አካል አልተገኝም፡፡


የገዳሙ መነኩሴም እንደተናገሩት በተከዜ አካባቢ የሚገኙ እጣን አምራቾች እጣናቸውን የሚያስቀምጡበት 5 ጎጆ ቤቶች ከነሙሉ ንብረታቸው በእሳት መውደማቸውንና እሳቱን ለማጥፋት ከአካባቢው የመጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማጥፋት እደተሳናቸው ጎጆዎቹም የዶግ አመድ እንደሆኑ ጨምረው ገልጸዋል ፤ በሌላ በኩል ግንቦት 3 ፤ 2004 ዓ.ም ሌሎች እጣን ለቃሚዎች የለቀሙት 60 ኩንታል እጣን በእሳት እንደተቃጠለ አክለው ገልጸዋል ፤ ይህን የማቃጠል ስራ ማን እንዳከናወነው ሆን ተብሎ ይሁን ወይም በአጋጣሚ ለማወቅ አልተቻለም ፤ “ዋልድባ ገዳም በዚህ አጋጣሚ እጣን እጣን ሸታለች” በማለት በቀልድ መልክ ሁኔታውን አስረድተዋል፡፡

ገዳሙን በአሁኑ ሰዓት ለጸጥታ እንዲያመች በማለት በጎንደርና በትግራይ ክልል የሚገኝውን አካባቢ በከፍተኛ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ  እና በመከላከያ ሰራዊት በመጠበቅ ላይ ይገኛል ፤ መንግስት ይህን ስራ ሲሰራ 27 አስከሬኖች በክብር አንስቼ በተገቢው ቦታ አሳርፌአለሁ ቢልም የገዳሙ መነኮሳት ግን የተነሳው የአስከሬን ብዛትም በውል አይታወቅም ፤ ይሁን እንጂ ገለልተኛ አጣሪ አካል ከመጣ እና ማጣራት ከቻለ በአግባቡ ሁሉን ነገር ለማሳየት እንችላለን ብለዋል ፤ መንግስት የገዳሙን አባቶች እንደ ድኩላ ማሳደዱን እንዲያቆምና የገዳሙን የወደፊት ህልውና የሚፈታተን ስረ-መሰረቱን የሚንደውን የስኳር ልማት ከወዲሁ እንዲያቆም  አሳስበዋል ፤ 

የዛሬ ወር አካባቢ ገዳሙን መንግስት በላካቸው የጨለማ ሰዎች አማካኝነት ከ60 ሺህ ብር በላይ ገዳሙ መዘረፉን እናታውሳለን ፤ ይህን የሰሙ ምዕመና ባሳለፍነው ሳምንት ከተለያዩ ቦታዎች ገዳሙን ሊረዱ ሲመጡ በእጃቸው ለገዳማውያን አቡጀዴ ፤ ሙዳይ ምጽዋት ሳጥንና መሰል የመነኮሳት መገልገያዎችን ይዘው ነበር ፤ ነገር ግን እነዚህ ምዕመናን በሰላም ገዳሙ ጋር ቢደርሱም በሰላም ወደ መጡበት ቦታ መመለስ አልቻሉም ፤ ማይጸብሪ ሳይደርሱ በፖሊስ ታግተው እስከ ለሊቱ 3 ሰዓት ድረስ በአካባቢው ፖሊስ ምርመራ እና ፍተሻ ሲካሄድባቸው ነበር ፤ ምን ይዛችሁ ነው የሄዳችሁት ? ፤ ለምን መጣችሁ ? ፤ ሙዳይ ምጽዋት ውስጥ ምን አለ ? ፤ ከየት ከየት አካባቢ ነው የመጣችሁት ? ፤ ፕሮጀክቱ የሚካሄድበት ስፍራ ሄዳችኋል ወይ ? በማለትና የተለያዩ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ሊለቀቁ ችለዋል  ፤ ከወራት በፊት አቶ ሲሳይ መሬሳ የተባሉት የአካባቢው አስተዳዳሪ ማንም ምዕመን ቦታው ድረስ በመምጣት እየተሰራ ያለውን ነገር መመልከት እንደሚችልና እየተወራ ያለው ነገር ከእውነት የራቀ መሆኑን ገልጸው ነበር ፤ ነገር ግን የመንግስታችን አንዱ ባህሪው “በአደባባይ ፈቅዶ በጀርባ ማባረር” ስለሆነ እነዚህን ሰዎች በሰላም ገዳም ወርደው እንዳይመለሱ እንቅፋት ሆኖባቸዋል፡፡

መንግስት የማረስ ስራውን በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠሉን የተመለከቱ ከአድርቃይና በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ቁጥራቸው ከ3000 ሺህ እንደሚበልጥ ለማወቅ ተችሏል ፤ “በዚህ ጉዳይ አንስማማም ገዳማችን ሲታረስብን ዝም ብለን አናይም  ፤ ይህ የስኳር ልማት አሁኑኑ መቆም አለበት” በሚል አቋም ሰብሳቢ ሳያስፈልጋቸው በአንድ ቀን አንድ ቦታ ላይ መንግስትን ተቃውመው ወጥተዋል ፤ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በጸጥታ ሀላፊው አቶ ሙሉጌታ አስናቀ በተገኙበት ስለ ስኳር ልማቱ ሁኔታ ቀኑን ሙሉ መወያየት ችለዋል ፤ ስብሰባውንም አቶ ማሩ የተባሉ ሰው በሚገባ ሲመሩ ቆይተዋል ፤ በውይይቱ ላይ “ ይህን ጉዳይ የሚያጣራ ገዳሙ ላይ ልማቱ ጉዳት ያድርስ አያድርስ የሚያጣራ ኮሚቴ እናቋቁም” የሚል ሀሳብ ከወደ ሰብሳቢዎቹ ቢመጣም ተሰሚነትንና ተቀባይነትን አላገኝም ፤ “እኛ ምንም ኮሚቴ ማቋቋም አያስፈልገን የምንፈልገው ስራውን እንድታቆሙ ብቻ ነው ፤ የህዝቡን ጥያቄ ረግጣችሁ ስራውን ብትቀጥሉ ግን ሌላ ነገር ውስጥ እየገባን መሆኑን እወቁት” የሚል መልስ ከተሰብሳቢዎቹ አግኝተዋል ፡፡ በስተመጨረሻም ሰብሳቢዎቹ “ከመንግስት ጋር ተነጋግረን ስራውን እናስቆማለን” የሚል መልስ ሰጥተዋቸው አመሻሽ ላይ ስብሰባው ሊጠናቀቅ ችሏል ፡፡ይህን ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑን ያወቁት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ስብሰባው ላይ ለመገኝት በመኪና እየከነፉ ወደ ዋልድባ እየመጡ ሳለ መኪናው መገልበጡን ለማወቅ ተችሏል ፤ የደረሰውም አደጋ ለጊዜው በውል አልታወቀም፡፡

አሁንም ጊዜው አልረፈደም ከእኩይ ስራችሁ ተመለሱ ፤ ገዳሙን የማፍራረስ ተልዕኳችሁን አቁሙ ፤ ባለፈው ከጎንደር የነጎደውን ምዕመን አባብላችሁ በሰላም የሚፈታ ጉዳይ ነው በማለት አዘናግታችሁታል ፤ ቃላችሁን ግን ልትጠብቁ አልቻላችሁም ፤ ህዝብን አንዴ ሁለቴ ማታለል ይቻላል ለዘለቄታው ማታለል ማሰብ ግን ሞኝነት ነው አይቻልም ፤ እንደ ግብጽ ያሉ 90 በመቶ ሙስሊሞች ባሉበት ሀገር የኦርቶዶክሶችን ገዳም የሀገር ቅርስና ሀብት ስለሆነ 14ሚሊየን ዶላር እስላማዊ መንግስቱ በጅቶ ሲያሳድስ እናንተ ግን 45 በመቶ ኦርቶዶክሳውያን ባለንበት በዚች ሀገር የዋድባን ገዳም መሬት ለማረስ 8 ቢሊየን ብር መድባችኋል ፤ ይህ የዝቅጠታችሁ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ጎንደርና አድርቃይ አካባቢው ላይ ያለ ክርስትያን ዋልድባ ሲታረስ እያየ ዝም እንደማይላችሁ እወቁ ፤ በ16ተኛው ክፍለ ዘመን በሱስንዮስ ዘመነ መንግስት የተፈጠረውን የሀይማኖት ወረራ ለመመከት ምዕመኑ እንዴት በእምነቱ እንደቆመ ታሪክን ወደ ኋላ ብትመለከቱ ኖሮ ከታሪክ መማር ብልህነት መሆኑን ትረዱ ነበር ፤ የፍርሀታችንን ቆብ የምንጥልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ፤ የዛኔ ለማንም የማይጠቅም ነገር ሊፈጠር አለመቻሉን እርግጠኞች ሆነን መናገር አንችልም ፤ በዋልድባ ጉዳይ 1000 ሺህ ጊዜ ጥናት ቢካሄድ ሪፖርት ቢቀርብ መደምደሚያው ግን የስኳር ፕሮጀክቱን ማቆም ብቻ ሊሆን ይገባዋል ፤  ከ1000 ዓመታ በላይ በሰላም የቆየን ገዳም ዛሬ ምን ተገኝ እና ነው አይናችሁን ያሳረፋችሁበት? በተጨማሪም ከዚህ በፊት ስራ ከጀመራችሁበት ጊዜ አንስቶ በቦታው ላይ የተከናወኑትን ገቢረ ተዓምራት ባታምኑበት እንኳን መለስ ብላችሁ ተመልከቱ ፤ የትላንትናው የመኪና አደጋም ትምህርት ይሁናችሁ ፤ እስከ አሁን እግዚአብሔር ዝም ያላችሁ ትእግስቱ የበዛ አምላክ በመሆኑ እንጂ በሌላ አይምሰላችሁ ፤ መሬት አፏን እንደማትከፍት የዘራችሁት ሸንኮራ እባብ እንደማይሆንባችሁ እርግጠኛ ሆናችሁ መናገር አትችሉም ፤ አባቶች አገልግሎታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አካባቢው ላይ ያሰፈራችሁትን የመከላከያ ሀይል ዞር አድርጉላቸው ፤ መሳሪያ ፈርቶ ገዳም ለቆ የሚሂድ መነኮሴ ያለ አይምሰላችሁ ፤

<><><><><><> <><><><><><><><><><><><> <><><><><><> <><><><><><> <><><><><><><><><><><><> <><><><><><><><><><><><> <><><><><><> <><><><><><> <><><><><><><><><><><><> <><><><><><><><><><><><> <><><><><><> <><><><><><> <><><><><><>
የእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከተማይቱ ዙሪያ ጭፍራና ፈረሶች ሰረገሎችም ነበሩ። ሎሌውም። ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እናደርጋለን? አለው።

እርሱም፦ ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው።

ኤልሳዕም። አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ፥ አየም እነሆም፥ በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ተራራውን ሞልተውት ነበር።

ወደ እርሱም በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ። ይህን ሕዝብ ዕውር ታደርገው ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ቃል ዕውር አደረጋቸው።”መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6፤15-18

 ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ” መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6፤16 ይላል የእግዚአብሔር ቃል ፤ እናንተ ጋር በአይን ከሚታዩት የታጠቁ ሰራዊቶቻችሁ ይልቅ አባቶቻችን ጋር ያለው እግዚአብሔር አስር እጥፍ ይበልጣል ፤ ከመነኮሳቱ ጋር ያሉት ጻድቃን ሰማእታት በእጥፍ እንደሚበልጡ እናምናለን፡፡ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ነው ፤ የኤልሳን ጸሎት የሰማ እግዚአብሔር ነው ፤ ሰራዊቱን እውር ያደረገው በኤልሳ ላይ ያደረው እግዚአብሔር ነው ፤ አሁንም በኦሪት ዘመን ነገሮችን ሲያከናው የነበረው እግዚአብሔር ፤ የያእቆብ አምላክ ፤ የይስሃቅ አምላክ የአብርሀም አምላክ አሁንም ከአባቶቻን ዛሬም ወደፊትም  እንዳለ እወቁ ፡፡ ቦታው ላይ የሚደረገውን ነገር እየተመለከታችሁ ልቦናችሁ ደንድኖ በስራችሁ ከገፋችሁ ከባለቤቱ ከመድሀኒዓለም ጋር እንደምትገዳደሩ እወቁ ፤ እርሱን ታግሎ  በታሪክ ያሸነፈ ማንም የለም ወደፊትም አይኖርምም ፤ 


9 comments:

  1. ይደልዎ! ይደልዎ! ይደልዎ!

    ReplyDelete
  2. በዚህ ጉዳይ ላይ አፍ የሌለው ቅዱስ ሲኖዶስ መፍትሔ ቢያፈላልግ ምን አለበት; እኔ የምለው ነቀሩን ከመሸፋፈን ይልቅ ወሳኝ የሆኑ የቤ/ክህነት እና የመንግስት አካላት ከህዝብ ከተወከሉ ወሳኝ መዕናንን ጋር በመወያየት መፍትሄ ማምጣት አይሻልም; ምነው ነገሩ ጫፍ ደርሶ ቤተ ክርስቲያኑትን፣ አባቶችንም አገሪቱንም ከመጉዳቱ በፊት ቢታሰብበት፡፡ የደናቁርት አስተሳሰብ ቢወገድ ምን አለበት;

    ReplyDelete
  3. የሃውዜንን ህዝብ በስውር ሆኖ እያስጨፈጨፈ ፣ ፊልም ሲያሰናዳልን የነበረ ድርጅት ፣ ገዳምን ለመመዝበር ፤ ዕጣን ለማጋየት ብዙ ጥበብ አያሻውም ፡፡ የተንኰል ክህነታቸው ከዚህ በላይ ሌላ ረቂቅ ወንጀልም ሊያሠራቸው ይችላል ፡፡ በዚህ ሁሉ የተንኰል መረብ ውስጥ እያለፈ ድምጹን የሚያሰማውን ህዝብና እንቅስቃሴውን ግን እንደ ወዳጄ ይበል ፣ ይደልዎ! ይደልዎ! ይደልዎ! ብያለሁ ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን በቁንጮነት የሚመሩት አባታችን ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ የዚህን ሁሉ ህዝብ ድምጽና አቤቱታ ተቀብለው መከራከር ይጠበቅባቸው ነበር ፡፡ ዕቅዳቸው ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን ቅርስ ፣ ገዳማቱን ጭምር ጠቅልለው ሙዚየም ለማስገባት የወሰኑ ይመስለኛል ፤ ደፋ ቀና የሚሉትና ፣ እርዳታም የሚጠይቁት ሙዚየም ለማስገንባት ነው ፡፡ ገዳምንና ገዳማዊ ህይወትን የሚቃወማት ፣ ፈተናው የከበደውና የወደቀው ሉተር ነበረ ፡፡ በዚህ ዘመን ደግሞ መፍቀረ ሉተር የሆኑ ግለሰቦች ልብሳችንን ለብሰው ፣ ማዕረጋችንን ተጐናጽፈው ፣ እኛኑ መስለው ወረውናል ፤ ገዳምን ለስኳርና ለከረሜላ ማምረቻ ይሆን ዘንድ የታቀደውም በነዚህ የቤተክርስቲያን ተቀናቃኞች ግፊት ይመስላል እንጅ መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን ለመድፈር በራሱ የልብ ልብ አይሰማውም ነበር ፡፡ በአንድ ዓመት ውስጥ በተከታታይ በእሳት የጋዩትን ገዳማትና ቤተ ክርስቲያንም እናስብ ፤ መንስኤውንም እንመርምር ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. የሃውዜንን ህዝብ በስውር ሆኖ እያስጨፈጨፈ ፣ ፊልም ሲያሰናዳልን የነበረ ድርጅት ፣ ገዳምን ለመመዝበር ፤ ዕጣን ለማጋየት ብዙ ጥበብ አያሻውም ፡፡ የተንኰል ክህነታቸው ከዚህ በላይ ሌላ ረቂቅ ወንጀልም ሊያሠራቸው ይችላል ፡፡ በዚህ ሁሉ የተንኰል መረብ ውስጥ እያለፈ ድምጹን የሚያሰማውን ህዝብና እንቅስቃሴውን ግን እንደ ወዳጄ ይበል ፣ ይደልዎ! ይደልዎ! ይደልዎ! ብያለሁ ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን በቁንጮነት የሚመሩት አባታችን ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ የዚህን ሁሉ ህዝብ ድምጽና አቤቱታ ተቀብለው መከራከር ይጠበቅባቸው ነበር ፡፡ ዕቅዳቸው ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን ቅርስ ፣ ገዳማቱን ጭምር ጠቅልለው ሙዚየም ለማስገባት የወሰኑ ይመስለኛል ፤ ደፋ ቀና የሚሉትና ፣ እርዳታም የሚጠይቁት ሙዚየም ለማስገንባት ነው ፡፡ ገዳምንና ገዳማዊ ህይወትን የሚቃወማት ፣ ፈተናው የከበደውና የወደቀው ሉተር ነበረ ፡፡ በዚህ ዘመን ደግሞ መፍቀረ ሉተር የሆኑ ግለሰቦች ልብሳችንን ለብሰው ፣ ማዕረጋችንን ተጐናጽፈው ፣ እኛኑ መስለው ወረውናል ፤ ገዳምን ለስኳርና ለከረሜላ ማምረቻ ይሆን ዘንድ የታቀደውም በነዚህ የቤተክርስቲያን ተቀናቃኞች ግፊት ይመስላል እንጅ መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን ለመድፈር በራሱ የልብ ልብ አይሰማውም ነበር ፡፡ በአንድ ዓመት ውስጥ በተከታታይ በእሳት የጋዩትን ገዳማትና ቤተ ክርስቲያንም እናስብ ፤ መንስኤውንም እንመርምር ፡


      egiziabeheare yebarkihe

      Delete
  4. Even those responsible persons who has been silent will get what they deserve. Not from people but from God!

    ReplyDelete
  5. እርሱን ታግሎ በታሪክ ያሸነፈ ማንም የለም ወደፊትም አይኖርምም
    Dear brothers thank you for your report.
    Can you post the address of Walidiba Gedam Bank Account. I will share some amount for their coming summer! This summer it will be the most challenge-full season for the monasteries due to financial problem and instabilities of the place.
    The head is corrupted the body is useless; both the church and the government heads are thinking to their stupid bench but God will ruin it! We should pray for our poor home; time will give the tangible judgments for all. Look the poor farmers are brave to face the challenge but the so called inland Pseudo-Holy Synods panic to rise at least the issue of Walidiba together with other agendas. God always has a man to confront like Loti. We Orthodox have a believe God save Walidiba for His Holy Words give to Holy Virgin St. Mother Marry.

    Instead of sugar we need Walidiba badly! Respect the Church and monks, they are Ethiopians like you! We need all the good news and the growth of Ethiopia but not in the fences of Church or Mosques! These are our identities that make us the existing Ethiopia and Ethiopians.

    Don’t give up God always with us!

    ReplyDelete
  6. Egziabher mechereshawun yasamirilin.

    ReplyDelete
  7. በመጀምርያ ፖለቲካና ሃይማኖት ለዩ አግዚአብሔር ዋልድባን ሀይማኖታቺንን ሀገራችንን ይጠብቅልን

    ReplyDelete