Friday, May 4, 2012

"ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ" እና ጥቂት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በዝቋላ ታሪክ እየሰሩ ነው



(አንድ አድርገን ሚያዚያ 26 ፤ 2004ዓ.ም )፡- ባለፈው ወር በዝቋላ በተነሳው እሳት ያላዘነ ሰው አልነበረም ፤ ሁሉም  ከሀገር ውስጥም ይሁን ከሀገር ውጪ የሚገኝ ምዕመን መረጃውን በቅርበት እየተከታተለ ለእሳት ማጥፋት ዘመቻው የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረጉ አይዘነጋም ፤ እኛ በጊዜው የአቅማችንን ያህል መረጃ ማድረሳችን ይታወቃ ፤ አሁን ከገዳሙ ምንጮች እንዳገኝነው አንድ አስደሳች ዜና ሰምተናል ፤ ይህንም እናንተው ዘንድ ለማድረስ ወደናል፡፡

 ፈተና ያለአንዳች በጎ ነገር አይመጣምና እሳቱ በተነሳበት ወቅት ገዳሙ ከቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ (የከተማ አውቶቡስ መገጣጠሚያ) ጋር የሚተዋወቅበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ለገዳሙ በራሱ መኪና (ኡራል) በጊዜው ውሃ አቀብሎ ነበር፡፡ እናም በዚህ አጋጣሚ ገዳሙ  ኢንዱስትሪው የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እንዳለውና ለደንበኞቹ አሰልጥኖ እንደሚሸጥ ስለተረዳ የማሽነሪዎቹን ብቃት ለማስመስከር እና እንደ ሃገራዊ ጉዳይ ለሃገሪቱ ቅርስ ከመሆኑ አንጻር ለረጅም አመታት በማንም ያልተደፈረውን በኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ተሰርቶ ከስምንት አመት በፊት ለማደስ ተሞክሮ ያቃተውን የዝቋላ ተራራ ጥርጊያ መንገድ ቢሰሩልን ተብለው በተጠየቁት መሰረት በሙሉ ፈቃደኝነት የመስክ ስራን  በቦታው በቦታው በመገኝት የተጠየቁትን አገልግሎት በመስጠት ታሪክ ለመስራት የቻሉ ከመሆኑም በላይ በወቅቱ ተልከው በነበሩት ውስን ማሽን ኦፕሬተሮች እና አስተባባሪዎች ጋር በአስገራሚ ሁኔታ ከረቡዕ ምሽት እስከ እሁድ ለሰኞ ጠዋት ፀሀይ ወጥታ እስክትገባ ደረስ ሰርተው ሲደክማቸው መስክ  ላይ ለተወሰነ ደቂቃ ብቻ በተራ እያንቀላፉ ገድል ፈፅመዋል፡፡

 ባለሞያዎቹ ባላቸው መንፈሳዊ ፍቅር ያለአንዳች አበል በአባቶች ቡራኬ እና አባታዊ እንክብካቤ ብቻ ምግብ ተራራ ላይ እየወጣላቸው ስራቸውን ከተጠበቀው በላይ  ሰርተዋል፡፡በዚህ ጊዜም ማኀበረ ቅዱሳንም ነዳጅ እጥረት እንዳለ ሲነገረው ያላንዳች ማንገራገር ሃያ አምስት ሺህ ብር ይውሰዱ በማለት የበኩሉን አስተዋጽኦ አድጓል፡፡ ባለሞያዎቹ እና የገዳሙ ማህበረ መነኮሳት በሙሉ አሁን ትልቅ ስጋት የሆነባቸው ነገር ቢኖር ይህ ሁሉ የተለፋበት ተራራ ቀይ አሸዋ ካልፈሰሰበት ክረምት ሲመጣ ወይም አሁን ዝናብ ቢዘንብ አፈሩ ተጠራርጎ ስለሚሄድ ልፋታቸው ሁሉ ውሃ በላው ማለት ነው በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል ፡፡ ቅስማቸው የሚሰበር መሆኑን በአንደበታቸው የገለፁልን ሲሆን ምክንያቱንም ሲጠየቁ  ‹‹ተስፋ በአይናችን አይተን መልሶ ሲጨልምብን ከማየት በላይ ሌላ ቅስም የሚሰብር ነገር ምን አለ›› በማለት ተናግረዋል፡፡

 ታዲያ አሁን ታሪክ ለመድገም የሚነሳ ሌላ ትውልድ ጠፍቶ አባቶች ባለሞያዎቹ እና ታላቅ ተጋድሎ የፈጸመው "ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ" ድርጅት ልፋታቸው ከንቱ ሆኖ መቅረት የለበትም ፤ ታዲያ ከኛ ምን ይጠበቃል? ለምትሉ፡- ገንዘብ ያለው በገንዘቡ የሚችለውን ያህል መኪና አሸዋ የነዳጅ ዋጋ በመሸፈን  ፤ ገልባጭ መኪና ወይም አይሱዙ ያለው መኪናውን በማቅረብ መንገዱ በሙሉ ጤንነት ለብዙ ዘመን ሳይጎዳ የሚያገለግልበትን ስራ አብራችሁ ትሰሩ ዘንድ መልዕክታችን እናስተላልፋለን፡፡

ከጻዲቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ በረከት ለመቀበል ግሬደር፤ ሩሎ(መሬት መደምደሚያ) ሎደር(አሸዋውን መኪና ላይ መጫኛ) ያለው ወይም ማሽኑ ያለውን የሚያውቅ የተቻለውን ሁሉ አስተዋጾ ቢያያደርግ እና እውቀት ያለው በእውቀቱ ፤ ገንዘብ ያለው በገንዘቡ ቢራዳ መልካም ነው፡፡  የተጀመረው ስራ ፍጻሜ አግኝቶ መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የሚረኩበት በታሪክም በዚህ ገድል ላይ የተሰማሩት ሁሉ በየዘመኑ በስፍራው ባእት አድርገው ለመላው አለም በሚማልዱ አባቶች ሲባረኩ ከመኖር በላይ ገዳማችንም አደጋ ቢደርስበት ፈጥኖ ለመድረስ የመንገዱ ማለቅ ወሳኝነት አለው እንላለን ፡፡ አባላቶቹ የቻላቸውን ያህል አድርገዋል አሁን ከእኛ የሚጠበቀው ነገር ልፋታቸውን አውቀን እና ተረድተን በሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ከጎናቸው መቆምን ብቻ ነው ፤ እሳቱን ለማጥፋት ያደረግነውን ርብርብ መንገዱን ለመስራትም መድገም መቻል አለብን ፤ በጊዜው ዝቋ የነበራችሁ ሰዎች መንገዱ ምን ያህል እሳቱን ለማጥፋት አዳጋች እንደሆነብን የምታውቁ ይመስለናል ፤ ይህን ችግርም ለመቅረፍ በአሁኑ ሰዓት ከምዕመኑ በላይ ቅርብ ሰው አይኖርም የሚል እምነት አለን

በስራው ላይ የታዩ ድንቅ ተአምራት
·        ገዳሙ በር ፊት ለፊት ለመኪና ማዞሪያ መሬት ሲደለደል ዛፍ መጣል ነበረበት እናም በቦታው ላይ የነበሩትን ሁሉ ገለል አድርገው ስራቸውን ተያይዘውታል፡፡ ዛፉንም ትንሽ ከታገሉት በኋ ወደታች (የገዳሙን ዋና በር ፊት ለፊት ሲያዩ በስተግራ) ወደቀ ፤ ወዲያው ሰዎች ጮሁ ፈጥነው ዛፉን ሲመለከቱት እድሜ ጠገብ የሆኑ የአካባቢው እናት እጃቸውን አሾልከው የድረሱልኝ ምልክት ሲያሳዩ ተመለከቱ ፈጥነው ሲወጡ  በእጃቸው የያዙት ለጊዮርጊስ የተያዘ ጧፍ ከጃቸው ሳይወጣ እጃቸው ላይ ብቻ ትንሽ ተጭረው በለተ ቀኑ ሰማእቱ በተአምራቱ ከዛፉ ውስጥ አወጣቸው፡፡
·        ከአስተባባሪዎቹ አንዱ አቋራጭ መንገድ ቅየሳ ላይ ሆነው ከርቀት የመንገዱን አቅጣጫ ሊመራ የደረቀ ዛፍ ላይ ወጥቶ ነበር ፤የተቀሩት አባላት ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በረከት ለመቀበል የጽድቅ ስራቸውን ተያይዘውታል  እናም ቋጥኝ ድንጋይ ሲገጥማቸው ወደገደል መወርወሩን ተያይዘውታል ፤ በጣም ትልቅ ድንጋይ ወደ ከደል አንከባለሉ ፤ ነገር ግን ድንጋዩ ወደጎን መሄዱን ትቶ ቀጥታ አስተባባሪው ወዳለበት ዛፍ ገሰገሰ እናም ድንጋዩን በአይናቸው ሲከተሉት ማመን ያቃታቸውን ነገር መመልከት ያዙ ፤ ድንጋዩ ሲመጣበት ልጁ ባይኑ ቢመለከትም ፍጥነት ስላለው በፍርሃት ዛፉን አጥብቆ  መያዙን መርጧል ፤  ድንጋዩም በተአምር የዛፉን ወገብ በተወሰነ ብቻ ከፍሎ ይዞ ሄደ ፤ አስተባባሪው  በሰላም ከመጣበት አደጋ  ተረፈ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ስራው በጣም አድካሚ በመሆኑ  አስተባባሪ ከድካም ብዛት እረፍት ለማድረግ አፈር ላይ ጋደም ብሏል ፤ ጓደኞቹ የት ሄደ ብለው ሲፈልጉት ልጁን ጅብ ሊጎትተው ትንሽ ሜትር ርቀት ላይ ብቻ ቀርቶት ተመለከቱ ፤ ባደረጉት የማባረር ስራ ያልተሳካለት ጅብ እየደነፋ ወደ ኋ ሊመለስ ችሏል ፤ የጅብ እራት ከመሆን የተረፈው በዚህ አይነት አጋጣሚ ነበር ፡፡ ሌሎችም ብዙ ተአምራት የተደረጉ ቢሆንም ለሚያምን ይህ በቂ ነው፡፡

7 comments:

  1. kalehiywotin yasemalin egziabher simu yetemesegene yihunilin...hulum yaqimun yakil biyaderg melkam new

    ReplyDelete
  2. ኡኡፍፍ ደስ ይላል፣ እሳት ማጥፋት ላይ ብቻ ሳይሆን እሳቱ እንዳይከሰት መስራት (ከተከሰተም በቀላሉ ለመቆጣጠር ነገሮችን ማመቻቸት) በጣም ደስ ይላል፡፡ በበረከቱ እየተሳተፋችሁ እና ለመሳተፍ ላቀደችሁ ሁሉ፣ እግዚአብሄር በምድር ህይወታችሁን ያቃናላችሁ፣ ነፍሳችሁንም ከ አብርሀም ጎን ያስቀምጥልን፡፡ እንዲህ አይነት ጥሩ ነገር መስማት በጣም ያስደስታል፡፡ ደስታችን ምልዑ እንዲሆን እግዚአብሄር ይርዳን፡፡

    ReplyDelete
  3. የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ዋጋችሁን እጥፍ ድርብ አድርጎ ይክፈላችሁ ከማለት የዘለለ ምን ማለት እንችላለን፡፡ ነገር ግን እንደተባለው መቸረሻውን ሳናይ ጎርፍ እንዳየበላሸውና እንዳናዝን እሳቱን ለማጥፋት ያሳየንው አንድነትና ትብብር ሊደገም ይገባል፡፡ ይህንን ሥራ የጀመሩት የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ፋብሪካው ሊበረታቱ ይገባቸዋል፡፡ የእግዚአብሄር አገልጋዮች በሁሉም ቦታ ያሉ መሆናቸውን ተረድተንበታልና እናከብራቸዋለን እንወዳቸዋለን፡፡ እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመናቸውን ያብዛላቸው አሜን፡፡

    ReplyDelete
  4. Temesgen deg neger mesmat nafqogn neber. Egziabhere yistachihu.

    ReplyDelete
  5. Egziabher yistilin.

    ReplyDelete
  6. በኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስትያን የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና አካባቢዋ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ ምእመናኑን በማስተባበር ለዝቋላ አቦ ገዳም መርጃ ይሆን ዘንድ ከ24500 ድርሀም/ 112700ብር/በላይ በማሰባሰብ ወደ ገዳሙ ለመላክ ተዘጋጅተዋል።
    ለአባታችን እረዥም እድሜ ይስጥልን የአገልግሎት ዘመናቸውን ይባርክልን።

    ReplyDelete
  7. egiziabiher yemesigen teru sera new yeteseraw.lelalawime entebaberalen.

    ReplyDelete