Thursday, May 24, 2012

ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ባለ አሥር ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ


ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የተሰጠ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ ፤ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 164 በተደነገገው መሰረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የዘንድሮውን መደበኛ የርክበ ካህናት ስብሰባ ከግንቦት 1 2004 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሔድ ሰንብቷል፡፡ በዚሁ መሰረት የመክፈቻ ስርዓት ጸሎት ከተፈጸመ ከበዓሉ ዋዜማ ከሚያዚያ 30 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 15 2004 ዓ.ም ድረስ ለ16 ቀናት ያህል ባደረገው ጉባኤ ጠቀሜታ ባላቸው የአጀንዳ ነጥቦች ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡ ከተላለፉት ውሳኔዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. ባለፈው በጀት ዓመት የተከናወነ መንፈሳዊ እና ማህበራዊ ተግባር በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ አማካይነት ቀርቦ ምልዓተ ጉባኤው ያለውን ሁኔታ ከመረመረ በኋላ የተዘረጋው የልማት እቅድ ተፋጥኖ በተግባር እንዲረጋገጥ ለውጤት የበቃው ተጠናክሮ እንዲቀጥል መመሪያ ተሰቷል

2. አዲስ በወጣው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራዊ ኤጀንሲ አዋጅ ተመዝግበው የሚሰሩት የቤተክርስትያን የምግባረ ሰናይ ድርጅቶች

ሀ. የልማት ክርትያናዊ ተራድኦ ድርጅት

ለ. የህጻናትና የቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት የአዋጁ ድጋጌ በተግባር መተርጎም ይችሉ ዘንድ የኢፌድሪ የበጎ አድራጎት ድጅቶችና ማህበራ ኤጀንሲ ጽ/ቤት በቀረበው ጥያቄ መሰረት ድርጅቶቹን በቅርብ እየተቆጣጠረ የሚሰራ የቅዱስ ሲኖዶስና ከሊቃውንት ቤተክርስትያን መካከል በተመረጠ በድምሩ 20 አባለት የሚገኙበት ጠቅላላ ጉባኤ ተቋቁሞ ስራውን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን በማመቻቸት ላይ ይገኛል፡፡

3. ከቅርብ አመታት ወዲህ በሀገሪቱ መዲና በአዲስ አበባ የተጀመረው የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋት ጉባኤ ፤ በሁሉም አህጉረ ስብከት ተቋቁሞ ይሰራ ዘንድ ቀደም ሲል በተሰጠው መመሪያ መሰረት በአብዘኞቹ አኅጉረ ስብከት ተመሳሳይ ተቋማት ተከፍተው ስራቸውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ ፤ ከዚህ አንጻር አገልግሎቱ እጅግ በጣም የጎላ ሲሆን መንግስታችንም የሀይማኖት ተቋማት ግንባር ፈጥረው የራሳቸውን ችግር በራሳቸው እንዲፈቱ ለማስቻል የሰላም ተቋሙ እንዲቋቋም መፍቀዱ የሚያስመሰግን መሆኑን እያደነቅን ፤ ተቋሙ ያልተቋቋመባቸው አህጉረ ስብከት ካሉ አቋቁመው ለሀገር ሰላምና ለህዝብ አንድነት ጠንክረው እንዲሰሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

4. ማህበራትን በተመለከተ፡- የማህበራ ቁጥር መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተጠንቶ ይቀርብ ዘንድ ቀደም ሲል በተሰጠው መመሪያ መሰረት ሊቃውንቱን ባካተተ መልኩ በተቋቋመው አጥኒ ኮሚቴ የተጠናው ጽሁፍ ቀርቦ ታይቷል፡፡ ሆኖም ማህበራት በአሁኑ ጊዜ ለቤተክርስትያኒቱ እየሰጡ ያለውአገልግሎትና ብዛታቸው በቀላሉ የማይታይ መሆኑን ጉባኤው ተገንዝቧ፡፡ ይሁን እንጂ ማህበራቱ በህግና በስርዓት የሚመሩበት ደንብ ያልተሰጣቸው በመሆኑ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችም ሆነ ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች በቀላሉ የሚታዩ አይደለም፡፡ በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የጉዳዩን አሳሳቢነት በተገቢው አቅጣጫ ተመልክቶ ለወደፊቱ ራሱን የቻለና ማህበራን ሚያሰራ ህግ እዲዘጋጅ ብጹአን አባቶች ፤ ሊቃውንተ ቤተክርስትያንና የህግ ባለሙያዎች ያሉበት ደንብ አዘጋጅ ተሰይሟል
5. ማህበረ ቅዱሳንን በተመለከተ፡- ማህበሩ ቀደም ሲል በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀ ደንብ ተሰጥቶት ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጠ ቆየ እና አሁንም እየሰጠ ያለ መሆኑ ይታወቃል ፤ ይሁን እንጂ የተሰጠውን ደንብና የአሰራር መዋቅሩን ከወቅቱ ሁኔታ ጋር እንደገና መርምሮ ማሻሻል በማስፈለጉ ከብጹአን አባቶች ፤ ከሊቃውንተ ቤተክርስትያንና ከህግ አዋቂዎች በተወጣጣ ኮሚቴ ተሸሽሎ እንዲቀርብ ጉባኤው ወስኗል፡፡ ደንቡ ተሸሽሎ አስኪጸድቅ ማህበሩ ተጠሪነቱ ለብጹእ ጠቅላይ ስራ አስኪያጅ ሆኖ አመራር በመቀበል እየሰራ እንዲቆይ ጉባኤው መመሪያ ሰጥቷል፡፡
6. የአባይ ወንዝ ለሀገር ልማት ለማዋሉ የመታሰቡ ዜና ከተሰራጨበት ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስትያናችን በምታደርጋቸው ስብሰባዎች ሁሉ የህዳሴው ግድብ ጉዳይ አንዲ አጀንዳዋ እንዲሆን በማቀዷ የፕሮጀክቱ አጀማመርና አፈጻጸም ሂደት ሳይወሳ የታለፈበት ጊዜ የለም፡፡ አሁንም ለፕሮጀክቱ ውጥን ተግባር እገዛን ታደርግ ዘንድ ቀደም ሲል በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ክፍያውን የጀመሩ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ያልጀመሩ አህጉረ ስብከት ካሉም ግቤታቸውን እንዲወጡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስላልፋል፡፡

7. የአክሱም ቤ መዘክርን ይመለከታል
8. ሰላምን በተመለከተ
9. የሰላምና የአንድነት ጉባኤ አባላት ባደረጉት ጥረትና ትብብር መነሻነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስና በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ አባቶች መካከል የተጀመረው እርቀ ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተስማምቷል፡፡
10. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ስም የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟት ባላቸው እቅድ መሰረት ቀጥተኛ የሆነውን ትምህርት ሃይማኖትና ነባር ስርዓቷን በማዛባት የኑፋቄ ትምህርት ሲያስተላልፉ የተገኙት መናፍቃን ጉዳይ በልዩ አጥኒ ኮሚቴ ሲጠና ከቆየ በኋላ አድራጎታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሚፈታተን ሆኖ በመገኝቱ ከቤተክርስትያናችን እንዲለዩ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተወግዘዋል ፤ በቤተክርስትያኑ ላይ ላሳዩት ክብረ ነክ ጉዳይም በህግ እንድጠየቁ ተወስኗ፡፡ ህብረተሰቡ ይህን በመረዳት ብርቱ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እያሳሰብን አጥፊዎች በጥፋታቸው ተጸጽተው ወደ እናት ቤተክርስትያናቸው ከተመለሱ ግን ቤተክርሰትያኒቱ በሮቿን ከፍታ ትጠብቃቸዋለች፡፡

Read in pdf



No comments:

Post a Comment