የኦሮሚያ ቤተ ክህነት
አደራጅ ኮሚቴ ብሎ
ራሱን የሾመው አካል
በከፍተኛ የመተማመን ወይም
የመቅበዝበዝ ስሜት ውስጥ
ሆኖ እንደሆነ ግራ
በሚገባ መልኩ አስቸኳይ
የሲኖዶስ ስብሰባ መጠራቱ
ከተነገረበት ጊዜ ጀምሮ
እየፎከረ ነው፡፡ ቀሲስ
በላይ ከአሜሪካ “እስኪ
ውግዘቷን ይሞክሯትና እንታያያለን”
ሲል ኃይለ ሚካኤል
ደግሞ ከሀገር ቤት
በተደጋጋሚ የቀጥታ ሥርጭት
እየገባ ለሰኞ የተጠራውን
የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ
“እናንተ ፖለቲከኞች ለፖለቲካችሁ
ስትሉ ነው የጠራችሁት፣
ብታርፉ ይሻላል፣ ጉባኤው
የጉባኤ ከለባት (የውሾች
ጉባኤ) እንዲሆን አንፈልግም፣
ቄሮና ቀሪቲ ለሁሉም
ነገር ራሳችሁን አዘጋጁ” በማለት ከወዲሁ ጉባኤውን ዘልፎ፣ ነቅፎና አውግዞ ይባስም ብሎ ውሳኔውን በአመፃ ለመመለስ የራሱን ሠራዊት አሰልፎ እየጠበቀ ይገኛል፡፡
Wednesday, February 12, 2020
Tuesday, February 11, 2020
ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን ጥቃት ላይ መኾኗን ያውጅ !
ዲያቆን አባይነህ ካሴ

ቅዱስ ሲኖዶስን በተመለከተ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ የሚግባባበት አንድ ጉዳይ አለ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ይወሥናል አፈጻጸሙን ግን አይመረምርም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ እና መፍትሔው ምን እንደኾነ ብዙ ጊዜ ስንወተውት ቆይተናል፡፡ አሁንም የአስቸኳይ እና የመደበኛ ስብሰባ ሸብረብ እንጅ የወሠናቸው ጉዳዮች ከምን እንደደረሱ፣ ምን እንቅፋት እንደገጠማቸው፣ ምን ዓይነት ማረሚያ እንደሚሹ በጥሞና ለመመልከት ትዕግስቱ ሊኖረው ካልቻለ ከጉባኤው ማግሥት ታላላቆቹ አጀንዳዎቹ ሁሉ ውኃ ይበላቸዋል፡፡
ምሕረት የምሕረት ወንጌል ስባኪ እንጂ ፥የወንጀል ስባኪ አይደለም !!
(በዲ/ን ታደሰ ወርቁ)

ቅ/ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል።

Subscribe to:
Posts (Atom)