Tuesday, February 11, 2020

ቅ/ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል።


(አንድ አድርገን 02/6 2012 ዓ.ም)  :-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ለየካቲት 9 ቀን 2012 . አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ማድረጉን ቋሚ ሲኖዶስ አስታውቋል። አስቸኳይ ጉዳይ ካልገጠመው በስተቀር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ (ጥቅምት እና ግንቦት) የሚካሄድ እና በቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ኦርቶዶክሳውያን የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ በሚከተሉት አንኳር ጉዳዮች ላይ እንዲመክር እና ቁርጥ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ይጠብቃሉ።



1.     በጥቅምቱ ምልዐተ ጉባኤ ተመክሮ እና ተዘክሮ አልመለስ ባለው ራሱን "የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ" ብሎ በሰየመው ሕገወጥ ቡድን እና አፈንጋጭ "ካህናቱ" ላይ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ በአፋጣኝ እንዲወስድ!
2.     ኦፌኮን የመሠሉ አንዳንድ ዋልታ ረገጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአደባባይ ቤተክርስቲያኒቱ እና አማኞቿ ላይ የሚነዙት ሽብር ሕጋዊ ገደብ እንዲበጅለት፣ እስካሁንም ላደረሱት ጉዳት በሕግ እንዲጠየቁለት ግልጽ አቋም እንዲይዝ
3.     አንዳንዶ የመንግሥት ሠዎች መንግሥታዊ መዋቅርን እንደ ምሽግ በመጠቀም በአዲስ አበባ እና በክልሎች የቤተክርስቲያኒቱን ይዞታዎች መጋፋት፣ አብያተክርስቲያናትን ማፍረስ፣ ምእመናንን በመግደል እና በማሠር ግልጽ መድሎ እያደረጉ መሆኑን ማሳወቅ!

ይህ አካሄድ እየተባባሰ በመምጣቱ እስካሁን የደረሰው ጉዳት በገለልተኛ መርማሪ ቡድን እንዲጣራ እና እጃቸው ያለበት ባለሥልጣናት ተጠያቂ እንዲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ቁርጥ አቋም እንዲይዝ ምእመናን ይጠብቃሉ!

(Yohannes Mekonnen/Dn)

No comments:

Post a Comment