Tuesday, February 11, 2020

ምሕረት የምሕረት ወንጌል ስባኪ እንጂ ፥የወንጀል ስባኪ አይደለም !!


(በዲ/ን ታደሰ ወርቁ)
(አንድ አድርገን 02/6 2012 ዓ.ም):- ወንድማችን መምህር ምሕረተ አብ አሰፋ በእጁ የያዘው የፍቅር እና የስማዕትት ትእምርት የሆነውን ጧፍ እንጂ፥ጎመድና ሰይፍ አይደለም። ከአንደበቱ የሚወጣው ቃል እግዚአብሔር እንጂ ጥላቻና ልዮነት አይደልም። ዘመኑን ለቤተ ክርስቲያን ዘመነ ሰማዕታት ያድረጉባትን እንደ ጃዋር መሐመድ እና እንደ አህመዱን ጀበል ዐይነቱን የስይፍና የጎመድ፤ የሀገራዊ ልዮነትና ጥላቻ፤ የቤተ እምነቶች መቃቃሪያና መጠያያ ምንጮችና የአስተሳስብ አባቶችን የሚከባከብ ፖሊስ ፥መምህራችንን አይደለም የማዋከብ፥ ጠርቶ የማናገር የሞራል እና የሕግ መሠረት የለውም።እገሌ ያስተምር፤ እገሌ አያስተምር የማለት ሙሉ ሥልጣን የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን እንጁ፥የፖሊስ አይደለም


እነዚህ ስዎች የያያዙት ሀገራዊ ላምንና አንድነትን መጠበቅ ሳይሆን ማናጋት ነው። ምዕመኑን ነካክተው ነካክተው በእጁ የያዘውን የፍቅርና የሰማዕትነት ምልክት የሆነውን ጧፋን ፥ሀገር ወደሚያወድም እሳት እንዲለውጥ ግፊት የማድረግ የትንኮሳ ሥራ ነው። ኪዚያም መምህራችንን በማስር የማንቂያ መርሐ ግብሩን እንዲስትጓጎል በማድረግና ተጋድሏችንን ወደ" መምህራችን ይፈታነት" ለማስቅየር የተዘየደ የፖለቲካ ጫወታ መሆኑ ነው።

እንዲህ ዐይነቱ ፖሊሳዊ እብደት ለሀገራዊ ስላምና አንድነት ጠንቅ ነውና፥ መንግሥት የእርምት ርምጃ ሊወስድ ይግባል። ውዷ ቤተ ክርስቲያናችንም ከመምህር ምሕረተ አስፋ ጎን በመቆም ተቋማዊ ከለላነት ልትሰጠው ይገባል።ዛሬ በመምህራችን የተጀመረው ማዋከብ ፥ነገ ሊቃነ ጳጳሳትን ወደ ማዋከብ የማያድግበት ምክንያት የለምና፥ቅዱስ ሲኖዶስም አበክሮ ሊመክርበት ይገባል። ለእኔ ምሕረት የምሕረትን ወንጌልን ስበከ እንጁ፥ወንጀልን አልስበከም። እኔም ምሕረተ አብ ነኝ!!


No comments:

Post a Comment