Thursday, September 29, 2011

‹‹ ልጄ ቀስ በል ጵጵስናውን ትደርስበታለህ ኋላ ግን ሸክሙን አትችለውም›› አቡነ ቴዎፍሎስ ለአቡነ ጳውሎስ

 • አቡነ ቴዎፍሎስ በ1968 ዓ.ም ለአባ ገ/መድህን (የአሁኑ አቡነ ጳውሎስ) እንዲ ብለው ነበር …. አባ ገብረመድን (የአሁኑ አቡነ ጳውሎስ) በነገሮች በጣም ሲቸኩሉ ፤ ለመሾም በጣም ሲጣደፉ፤ ለጵጵስና እንዲያጯቸው እና በጊዜው የነበረው ሲኖዶስ እንዲያፀድቅላቸው ከልክ ያለፈ ምኞታቸውን የተመለከቱት አቡነ ቴዎፍሎስ ‹‹ ልጄ ቀስ በል ጵጵስናውን ትደርስበታለህ ኋላ ግን ሸክሙን አትችለውም›› ብለዋቸው ነበር፡፡.............ኢትዮጵያውያን አብዮትን የምናወቀው በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ሳይሆን በውስጡ አልፈን በቃጠሎው ተገርፈን ወላፈኑን ቀምሰን ነው፡፡ በዛን ወቅት የነበረው የሶሻሊስት ርዕዮት አለም አብዮታዊነትን እንደ ታላቅ ነገር ሲሰብክ የነበረ በመሆኑ ብዙ ወጣቶች አብዮተኛ ተብለው ሀገሪቱንም አብዮታዊት ኢትዮጵያ አስብለዋታል፡፡ በዚህች ተአምረኛ ሃገር አብዮታውያን ወንድሞቻችን ጸረ አብዮተኛ የተባሉ ወንድሞችቻቸውንና እህቶቻቸውን ቅርጥፍ አድርገው በልተዋል፡፡ በዚያ ክፍለ ዘመን አብዮት ልጆቿን ትበላለች በሚል ፈሊጥ ብዙዎች ወጣቶች ጸረ-አብዮት፤ ጸረ ህዝብ ተብለው አይሆኑ ሆነዋል..ጊዜው ጥቁር ጠባሳውን ጥሎ ያለፈው ሁሉም ላይ በመሆኑ የጊዜው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን 2ኛ ፓትርያልክ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ላይ የደረሰው በደል ግን ለየት ያደርገዋል....

በዚያ ወቅት ደርግ ጳጳስ እንዲይሾሙ ትእዛዝ አውጥቶ ነበር።አቡነ ቴዎፍሎስ የደርግን ትእዛዝ ሽረው ሦስት ጳጳሳትን ሾሙ።ደርግም ትእዛዜን አልሰማህም ብሎ ፓትሪያርኩንና ሦስቱን ተሿሚ ጳጳሳት እስር ቤት ጨመራቸው።በወቅቱ የተሾሙት ጳጳሳት አቡነ ባስልዮስ፤አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ጳውሎስ ነበሩ።ከጊዜ በኋላ ሦስቱ ጳጳሳት ከእስር ሲፈቱ ፓትሪያሪኩ ብቻ በዚያው ቀርተዋል።


ጥቂት ከመፅሐፉ የተወሰደ......
በእስር ቤት ደረሰባቸውን ፀዋትወ መከራ በዓይን ያዩ በታላቁ ቤተመንግስት አብረዋቸው ታስረው የቆዩ ፤ በአፄ ኃ/ስላሴ ዘመን በስልጣን ላይ የነበሩ ታላላቅ ሰዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ የአይን ምስክሮች መካከል እስካሁን ድረስ በህይወተ ስጋ ካሉት ከአቶ አብርሐም ወርቅነህ እና ከጀኔራል መኮንን ደነቀ በተገኝው የቃል መረጃ መሰረት ቅዱስነታቸው መጀመሪያ የታሰሩት ለብቻቸው በኢዮቤልዩ ቤተመንግስት ነበር፡፡ በዚህ ቦታ ጥቂት ቀናት ከቆዩ በኋላ ........

Wednesday, September 28, 2011

የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ አደጋ በቅኔም ሲጋለጥመጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ

 • “በቅዱስ ጳውሎስ ዘመን ስብከተ ወንጌል እንደበረታው ሁሉ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክናም ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቀ ትምህርት ተስፋፍቶ መሰጠት ይኖርበታል፤” /መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በዘመን መለወጫ - ቅዱስ ዮሐንስ የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር ላይ ቅኔያቸውን ሲያብራሩ ከተናገሩት/
 • “በቅኔው ካነሣችሁት አይቀር ስላሉት ችግሮች መናገር እፈልጋለሁ፤ የትኛው እግዚአብሔር ነው ያረጀው? የትኛዋ ቤተ ክርስቲያን ናት ያረጀችው? የሊቃውንቱ ዝምታ ምንድን ነው? አባቶችስ የማይገባ ትምህርት ሲሰጥ ዐውደ ምሕረታችሁን የማትጠብቁት ለምንድን ነው? ዝምድና፣ ጓደኝነት ወይስ ውለታ ይዟችኋል?. . . በ2004 ዓ.ም መሠራት የሚገባው ሥራ ይህችን ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ፣ በሚገባ ማስተዳደር ነው፤” (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቅኔውን መሠረት አድርገው ከተናገሩት)

ትንቢቱ ሲፈፀም


Monday, September 26, 2011

የግማደ መስቀሉ ታሪክዓለምንና በውስጡ የሚገኘውን ሁሉ ፍጡር ፈጥሮ የሚገዛውን አምላክ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ቤተ እሥራኤል በቀራንዮ ላይ በመስቀል ሰቀሉት ፡፡ መድኃኔዓለም በዕለተ ዓርብ ከቀኔ በዘጠኝ ሰዓት ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በገዛ ሥልጣኑ ከለየ በኋላ በኋላ ከመስቀሉ አውርደው ቀበሩት ፡፡በ፫ኛው ቀን ሲነሣ ተሰቅሎ የነበረው የእንጨት መስቀል ሌት ተቀን በሙሉ ሳያቋርጥ እንደፀሐይ ሲያበራ በተጨማሪም አጋንንት ሲያባርር ድውይ ሲፈውስ ሙት ሲያነሣ ቤተ እሥራኤል አይሁድ ቀንተው በዓዋጅ ትልቅ ጉድጓድ ቆፍረው በመቅበር የቤት ጥራጊና አመድ ጠቅላላ የቆሻሻ መከማቻ እንዲሆን ወሰኑ፡፡ ከዚያ ዘመን ጀመሮ እስከ ሦስት መቶ ዘመን ድረስ የተከማቸው ቆሻሻ እንደተራራ ሆነ፡፡

የድሬዳዋ ሀ/ስብከት በተሀድሶ መናፍቃን ዙሪያ ቁርጠኛ እርምጃ ለመውሰድ ተወያየ

 •  ተሀድሶ መናፍቃን በቤተክርስቲያን የሰገሰጓቸውን ከሀዲያንን ማሰልጠን መቀጠላቸው ተዘገበ፡፡
 • የድሬዳዋ ሀገረ ስብከትም እራሱን ይፈትሽ” የቅ/ገብርኤል አስተዳዳሪ
 • የተሀድሶነት ስልጠና በሐረር ከተማ በተለምዶ ቢራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ስውር ቦታ በዝግ ቤት ለ3 ቀን ስልጠና ሰጥተዋል፡፡በዚህ ስልጠና የደብር አለቆች፣ መሪጌቶች፣ ዲያቆናት እና የሰ/ት/ቤት ወጣቶች ተሳታፊ ነበሩ
 • ባለፈው ከሰለጠኑት 17 ሰልጣኞች ውስጥ 13ቱ የምእራብ ሀረርጌ የደብር አለቆች ቄሶች እና ዲያቆናት ናቸው
 • እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ ነገር ግን ……… ከሀዲው የመናፍቃን አሰልጣኝ ፅጌ ስጦታው

በምስራቅ ኢትዮጵያ እየተንሰራፋ ያለው የተሀድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በቤተክርስቲያን ውስጥ ተመሳስለው የተሰገሰጉ ‘ካህናት’፣ ‘ዲያቆናት’ እና መነኮሳትን በማሰልጠን ከጅጅጋ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ እና አሰበ ተፈሪ ሀገረ ስብከት ተመሳስለው በመግባት ቤተክርስቲያንን በሁለት ቢላዋ እያረዷት ያሉ ከሀዲያንን በተመለከተ ባለፈው ሳምንት የምስራቅ ሀረርጌ እና ሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያሬድ እና የሀገረ ስብከት መምሪያ ሀላፊዎች እየወሰዱት ያለውን ርምጃ ተከትሎ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከትም ጥብቅ ውሳኔ ለማሳለፍ ከደ/ምህረት ካቴድራል፣ ከሳባ ደ/ሀይል ቅ/ገብርኤል እና ከቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ፀሀፊ እና የአድባራት አለቆች በሀገረ ስብከት በ13/01/2004 ዓ.ም የተሰበሰቡ ሲሆን ስብሰባውን የመሩት የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ አባ አረጋዊ ነሞምሳ ጉዳዩን ማን? መቼ? ለምን? ብለው ከማጣራት ይልቅ ይህንን ግን ማነው የቀረፀው ?የሚለው ላይ ብቻ ማተኮራቸው ብዙዎችን አባቶች ቅር አሰኝቷል ፡፡  

Sunday, September 25, 2011

አባ ሰረቀ፤በመስቀል-ደመራ በዓል አከባበር ላይ በአደባባዩ እንዳይገኙ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

 • “እኔ ችግር [የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ] ካለብኝ ከመምሪያ ሓላፊነቴ መነሣት ብቻ ሳይሆን ከቤተ ክርስቲያንም ልወገድ ይገባኛል፤”/አባ ሰረቀ ለመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ አስተዳደር ጉባኤ፣ ለበዓል አከባበር ዐቢይ ኮሚቴ፣ ለሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ እና ለጸጥታ ኀይል የጋራ ስብሰባ ከተናገሩት/::
 • ውሳኔው  ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነንና ሕገ ወጦቹን እነ ጌታቸው ዶኒን፣ በጋሻው ደሳለኝን፣ አሰግድ ሣህሉን፣ ግርማንና የመሳሰሉትን እንደሚያካትት ተገልጧል፡ 
 • ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣‹ ‹‹ወጣቱ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና የሚያስጠብቅ ነውበአካል ወጣቱን አይቻለሁ፤ ጥሩ ዝግጅት ላይ ነው ያለው ››
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 14/2004 ዓ.ም፤ ሰፕቴምበር 25/2011)፦ በሐምሌ ወር 2003 ዓ.ም በመላው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አብያተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች፣ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ደሴ ከተማ የ12 አብያተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ የተቃውሞ መግለጫ የወጣባቸው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል መስከረም 16 ቀን 2004 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ በሚከናወነው የመስቀል-ደመራ በዓል አከባበር ላይ እንዳይገኙ ውሳኔ ተላለፈባቸው፤

የሀዋሳ ደ/ም/ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አዲስ ሰበካ ጉባኤ ተመረጠለት

 •   በምርጫው ሥነ ሥርዓት ከ1100 በላይ ምዕመናን ተገኝተዋል፡፡

 • እነ ያሬድ አደመ አመጽ ለማስነሳት ስላልቻሉ ከገዳሙ ሰ/ት/በት በሕገ ወጥ መንገድ የዘረፉትን ንዋያተ ማኅሌት ይዘው የግብር አጋሮቻቸው ወደ ሚገኙበት ማረሚያ ቤት አቅንተዋል፡፡
 •  የሰጣችሁንን አደራ ያለ ማንም ተጽእኖ እና ጣልቃ ገብነት በንጹሕ መንፈስ ማከናወናችንን እንገልጻለን ….. የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት
 • ተስፋዬ መቆያ በክብረ መንግስት ህገ ወጥ ጉባዔ እያካሄደ ነው፡፡

በተሃድሶ መናፍቃን አቀንቃኞች በተፈጠረ አመጽ ለበርካታ ወራት ያለ መደበኛ ሰበካ ጉባኤ የቆየው የሀዋሳ ደ/ም/ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በምዕመናን ከፍተኛ ተሳትፎ በዛሬው ዕለት አዲስ ሰበካ ጉባኤ ተመርጦለታል፡፡

Saturday, September 24, 2011

ከፈለጋችሁ ሬሳችንን አውጡ

 

 • አቶ በጋሻው ደሳለኝ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ስብከተ ወንጌል ሀላፊ ተደርጎ ተመደበ
 •  የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ማኅበረ መነኮሳት  ይህን ነገር እንደሰሙ ይህ ሰው እዚህ ተመድቦ አይሰራም በሚል ተቃዎሟ ቸውን አሰምተዋል
 • ’’በህብረት የሚያምፁት አንድ ላይ በመሰባሰባቸው ስለሆነ በየደብሩ አንበታትናቸው’’   የቤተክህነት ሰዎች ሴራ 
 • ስለ ቤተክርስያን አጥብቀው የሚሟገቱትን አባቶች ወደ ተለያየ ደብሮች ከቤተክህነት በወጣ ደብዳቤ የመደቧቸው ሲሆን የተመደቡት መነኮሳት ምደባውን አልተቀበሉትም፡፡ ከፈለጋችሁ ሬሳችንን አውጡ አንጂ ካደግንበትና ካገለገልንበት ከዚህ ቤተክርስትያን አንንቀሳቀስም በማለታቸው ፤ የተሰራውን ስራ እና የሚሰራውን እየተሰራ ያለውንም በመቃወማቸው የማስጠንቀቂ ደብዳቤ የተሰጣቸው ሲሆን ነገሩን ረገብ ለማድረግ ቤተ ክህነቱ በጉዳዩ ላይ እያሰበበት ይገኛል፡

  የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ማኅበረ መነኮሳት “የገዳሙን ት/ቤት እና ሁለገብ የአገልግሎት ሕንጻ ከገዳሙ አስተዳደር በመለየት ከወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ጋራ በዝብዘዋል” ያሏቸውን አስተዳዳሪውን መልአከ ሰላም ተክለ ማርያም ዘውዴን ከወራት በፊት ማባረራቸው ይታወሳል
  ጉዳዩ የደረሰበትን ደረጃ ይጠብቁን........

  እግዚሐብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅ 

  ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ “ሐውልቱ እስከ መቼ?” የሚል መጽሐፍ አሳተሙ


  • መጽሐፉ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ አራማጅ ነው በሚባል ሰው የተዘጋጀ እንደሆነ ተነግሯል፤
  • በመስቀል-ደመራ በዓል ዐውደ ትርኢት የሚያቀርቡ ወጣቶች የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊን ጨምሮ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ እና ሕገ ወጥ ሰባክያን በበዓሉ ላይ አንዳችም ተሳትፎ እንዳይኖራቸው አስጠንቅቀዋል፤
   (ደጀ ሰላም፤ መስከረም 12/2004 ዓ.ም፤ ሰፕቴምበር 23/2011)፦ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ አቡነ ጳውሎስን ሰርፕራይዝ አድርጌበታለሁ የሚሉትንና ከብር አራት መቶ ሺ በላይ ገንዘብ እንደወጣበት ተናገሩለት ሐውልተ ስምዕ በተመለከተ “ሐውልቱ እስከ መቼ?” የተሰኘ መጽሐፍ ማሳተማቸው ተሰማ፡፡ ወይዘሮዋ መጽሐፉን መስከረም 16 ቀን 2004 ዓ.ም ተከብሮ በሚውለው የመስቀል-ደመራ በዓል ላይ ለማሰራጨት እንደተዘጋጁ ተነግሯል፡፡

  ከ100 ያላነሱ ገጾች ያሉት ይኸው መጽሐፍ የተዘጋጀው፣ 

  Friday, September 23, 2011


  ለሃይማኖት ሰባኪያን ፈቃድ ሊሰጥ ነው!!!!


  • በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በኩል ፈቃድ የሚያገኙ ሰባኪያን በአብነት ትምህርት ቤት የተማሩ ወይም ከመንፈሳዊ ኮሌጆች በዲፕሎማ ወይም በዲግሪ የተመረቁ ብቻ ይሆናሉ፡፡
  • በተሰጠው ፈቃድ በአግባቡ የማያገለግል ሰባኪ ፈቃዱን እስከ መቀማት የሚደርስ እርምጃ ይወሰድበታል፡፡
  ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ.ም ታትሞ የወጣው ነጋድራስ ጋዜጣ ቅጽ 08 ቁጥር 297 የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የሠላም እና የምክክር ጉባኤ መስከረም 9 እና 10 በሒልተን ሆቴል ‹‹ፈቃድ በሌላቸው የሃይማኖት ሰባኪያን›› ላይ መምከሩን ዘግቧል፡፡

  Thursday, September 22, 2011

  አሁን እንኳን እንንቃ………


  ከቁጥር 2 ቪሲዲ ተቆርጦ የቀረበ  ..

  ይህን ቪሲዲ ገዝተው በአሁን ሰዓት በቤተክርስትያናችን ላይ መናፍቃንና የተሐድሶ አራማጆች እየሰሩ የሚገኙትን ስራ ይወቁ  ላላወቀ  ያሳውቁ ፤ ራስዎን ፤ ቤተሰብዎን  ቤተክርስትያንን ይጠብቁ....
  ሙሉ ቪሲዲውን በቅርብ አግኝታችሁ ማየት ለማትችሉ በቅርብ ቀን ሙሉውን ፖስት የምናደርግ መሆኑኑ ለመግለፅ እንወዳለን::


  በክርስቶስ ለሀዋርያነት ተመርጦ የነበረው ይሁዳ እንኩዋን ከፍሬው መች ተካፈለ የስጋ ጥቅሙን አስቀድሞ ጌታውን ሸጦ ጠፋ እንጂ የይቅርታ በሩን መመልከት አቅቶት እንደ ጠፋ ቀረ እንጂ ታድያ እነሱስ የተመረጡለትን ክብር ቢጥሉ ምን ያስደንቅ ? “አብዝቼ ብጠራቸው አጥብቀው ከፊቴ ራቁ “ ት.ሆሴ 11 / 2 እንዳለ ቅዱስ መፅሐፍ

  ከወራት በፊት ተሐድሶ የሚባል ነገር የለም ይህ የማህበረ ቅዱሳን የፈጠራ ወሬ ነው እያሉን የነበሩት የዋህ ምእመናንን ለማደናገር እና እውነቱ እንዲጠፋባቸው ለማድረግ እና ለማምታታት የተናገሩት ነገር እውነት እውነት ናትና እንዲህ በቪሲዲ መልክ ሊወጣ ችሏል :: አቶ ተስፋዬ መቆያ የተሐድሶ እና ምንፍቅና አራማጅ የእነ አቶ በጋሻው የያዙትን ጎራ የሚደግፍ በአሜሪካ እንዲህ ብሎ አስተምሮ ነበር.. 
  ያስተማረውን ለማንበብ http://andadirgen.blogspot.com/2011/08/blog-post_6935.html...


  እውን ‹‹ተሐድሶ›› የለምን?
  (በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ/):- ሰሞኑን በተደጋጋሚ ‹‹ተሐድሶ የሚባል ነገር የለም ማኅበረ ቅዱሳን የፈጠረው ወሬ ነው!›› የሚል ንግግር በመስማቴ ይህንን አጭር ማሳሰቢያ ለመጻፍ ተነሳሣው፡፡ በእርግጥ ንግግሩን ቀደም ሲልም ሰምቼው አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን መደጋገሙ ሲበዛ በተለይም ግምት የሰጠዋቸው ሰዎች ነገሩን ተቀብለዉት ስመለከት ለካ የሚናቅ ሐሰት የለም አሰኘኝ!   ሙሉውን ለማንበብ http://andadirgen.blogspot.com/2011/08/blog-post_1600.html  ከዚህው ጋር በተያያዘ
  ተስፋዬ መቆያ የተባለው የተሀዲሶ መናፍቃን አቀንቃኝ በአሜርካን ሀገር አልሳካለት ያለውን የተሀዲሶ ማስፋፋት ዘመቻ ይዞ ወደ ሀገር ቤት ብቅ በማለት በሐዋሳ የተከሰተውን አይነት ግጭት በክብረመንግስትም ለመድገም ከአቶ በጋሻው ደሳላኝና ከአቶ ትዠታው ሳሙኤል ጋር በመተባባር ከመስከረም 12-14 2004 ዓ/ም በክብረ መንግስት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሕጌ ወጥ ጉባኤ ለማድረግ በዝግጀት ላይ ነው፡፡
  ይህ ጉባኤ የቤተክርስቲያን አይደለም ተብሎ ከዚህ በፊት በሰኔ ወር 2003 ዓ/ም በሀገረስብከቱና በመንግስት አካላት መታገዱና አቶ በጋሻውም በወቅቱ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል፡፡

  ‹‹እግዚአብሔር ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን››
  አሜን

  የአቶ በጋሻው ደሳለኝ የብጥብጥ ሙሻአዙር


  • ‹‹ጳጳሱ ፈሪ ናቸው አስፈራሯቸው››…..አቶ በጋሻው ደሳለኝ
  • ‹‹ወንጌል እና ቅዳሴ አንድ ነው ››………ብጹዕ አቡነ ያሬድ
  • በብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ላይ ጫማዋን የወረወረች ቀንደኛ ሴትን ጨምሮ በርካታ የቀድሞ ተሐድሶዎች በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ላይ የተቃውሞ ድምጽ አሰምተዋል
  ‹‹አንደ  ልብሳቸው  ግብራቸው  ያላማረ››
    ‹‹እኛ ምርጦቹ የሪያል ማድሪድ ቡድን ነን›› 
  አቶ በጋሻው ደሳለኝ ከሮያል መፅሄት ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ 
  የምስራቅ ሐረርጌ እና የሱማሌ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንድሁም የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ያሬድ በሐረር እየተካሔደ ያለውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ በመገምገም ጠንከር ያለ የማስተካከያ ውሳኔ  በማስተላለፋቸው መስከረም 5 ቀን 2004 ዓ.ም ቁጥራቸው ከሃያ የማይበልጡ የቀድሞ የተሐድሶ አባላት(ዕጓለ ፀራዊ) ሊቀ ጳጳሱ ድረስ በማምራት ክርስቲያዊ ትውፊቱን ያልጠበቀ የቤተክርስቲያንን አስተዳደራዊ መዋቅር ያልጠበቀ የተቃዎሞ ድምጽ አሰምተዋል፡፡
  የተቃዉሞ ድመጹን እና የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስን ምላሽ እንደወረደ እንዲህ እናስነብባለን፡፡

  Tuesday, September 20, 2011

  አለመታደል


  ስለ ልጆቿ ችግር የሚያለቅስ አባት ያላት ቤተ ክርስቲያን የታደለች ናት። በፈንታው ደግሞ ስለ እርሷ ማልቀስ ሳይሆን የሚያስለቅሷት፣ ስለ እርሷ የሚያዝኑ ሳይሆን የሚያሳዝኗት፣ ልጆቿን በእንባቸውና በትምህርታቸው አጥር መከታ ሆነው ከመጠበቅ ይልቅ ከቅጽሯ የሚያባርሩ ጨካኞች ያሏት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ሊለቀስላት ይገባል።
  ስለ ልጆቻቸውና ስለ ቤተክርስትያን የሚያለቅሱ አባት

  tears of Pope Shenouda

   http://www.youtube.com/watch?v=ESG-KO4QX88&feature=share

  ቅዱስነታቸው ፖፕ ሽኖዳ 3ኛ 117ኛው የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው። እንደተለመደው ከምእመናን ለሚቀርብላቸው ጥያቄ የሚመልሱበት የተለያየ ዝግጅት አላቸው። ከዝግጅቶቻቸው መካከል በየሳምንቱ በካይሮ በመንበረ ማርቆስ የሚያደርጉት አንዱ ነው። እነዚህን የምእመናን ጥያቄዎች So Many Years With The Problems Of People” በሚል ርዕስ እየታተሙ ለንባብ በቅተዋል። ጥያቄዎቹ ዶግማን፣ ሥርዓትን፣ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርን የተመለከቱ ሊሆኑ ይችላሉ። መልሶቻቸው የማያወላዱ፣ በአጭር አባባል ብዙ መልስ የሚሰጡ ናቸው። አንድ ጥያቄ ግን በቃላት መልስ ከመስጠት ይልቅ በእንባና በዝምታ መመለስን መርጠዋል። ከንግግራቸው በአጭሩ እንመልከት።

  Monday, September 19, 2011

  “አቡነ ጳውሎስን እና አቡነ መርቆሬዎስን የማስታረቁ ጥረት ቀጥሏል”  (ነጋድራስ፤ ቅጽ 08 ቁጥር 296፤ ዓርብ፣መስከረም 05፤ 2004 ዓ.ም)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሥርዐተ ጵጵስና በምትመራበት ፍትሐ ነገሥት፣ በአንድ መንበርና ዘመን ሁለት ፓትርያሪክ መሾም እንደማይቻል መደንገጉን የቤተ ክርስቲያኗ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ ይህ ድንጋጌ በ1984 ዓ.ም ላይ አክባሪም አስከባሪም አልነበረውም፡፡ ስለዚህም በወቅቱ የቤተ ክርስቲያኗ አራተኛ ፓትርያሪክ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሕይወት እያሉ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ተመርጠው መንበረ ፓትርያሪኩን እንደተረከቡ ይታወሳል፡፡

  Saturday, September 17, 2011

  ምጽዋት - እዉነተኛዉ የተፈጥሮ ሚዛን  አንድ ገዳም ዉስጥ የሚኖሩ አንድ አባት አዉቃለሁ፡፡ እኝህ አባት ሁል ጊዜ የሚናገሩት በምሳሌና በተዘዋዋሪ ነዉ፡፡ በዚህ ምክንያት ለእርሳቸዉ እንግዳ የሆነ ሰዉ ነገራቸዉን ቶሎ ላይረዳዉ ይችላል፡፡ በአንድ ወቅት ከጓደኛየ ጋር ሆነን ስለ ምጽዋት ስናነጋግራቸዉ በአሁኑ ጊዜ ከጠቃሚነቱ ይልቅ ጎጂነቱ ያመዝናል የሚለዉ ሰዉ እንደሚበዛና በርግጥም ይህን ሊያስብሉ የሚችሉ ብዙ አጭበርባሪዎች መኖራቸዉን ነገርናቸዉ፡፡ እርሳቸዉም ዝም ብለዉ ካደመጡን በኋላ የሚከተለዉን ታሪክ ነገሩን፡፡ በንጉሡ ጊዜ ፈረንጆች መጥተዉ አንድ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ጥያቄዉም ጥቁር ነገር ለዓለማችን ጠቃሚ ስላልሆነ ከምድር ልናጠፋዉ እንፈልጋለን፤ የእርሰዎ ሃሳብ ምንድን ነዉ? የሚል ነበር፡፡ እርሳቸዉም ጎጂማ ከሆነ መጥፋት ይኖርበታል፤ ግን ጎጂነቱን አረጋግጣችኋል? ደግሞስ ምንም ሳታስቀሩ ሁሉንም ልታስወግዱ ቆርጣችሁ ተነስታችኋል ? ሲሉ ጠየቛቸዉ፡፡ እነርሱም አዎን ፤ ጥቁር ነገር ለሥልጣኔና ለመልካም ነገር እንደማይስማማ ደርሰንበታል፤ ካጠፋንማ የምናጠፋዉ ሁሉንም ጥቁር ነገር ነዉ አሏቸዉ፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሡም፡- ጥሩ የምትጀምሩትስ ከየት ነዉ፤ ከነጮች አገር ነዉ ወይስ ከጥቁሮች? ይላሉ፡፡ ፈረንጆቹም ሃሳባችንን እየተቀበሉት ነዉ ብለዉ እየተደሰቱ ፤ የምንጀምረዉማ በእኛ ሀገር ካለዉ ጥቁር ነገር ነዉ ሲሉ መለሱላቸዉ፡፡ እንደዚህ ከሆነና ምንም ምን የጥቁርን ትንሿንም ሳትንቁ በሀገራችሁ ካለዉ ማጥፋት የምትጀምሩ ከሆነ እስማማለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ዐይናችሁ ዉስጥ ያለችዉንም ጥቁር ነገር ንቃችሁ መተዉ የለባችሁም፡፡

  “አንተም ተው አንተም ተው” - አርዮስንና ቅዱስ ቄርሎስን?!


  • አርዮስ ተፀፅቻለሁ እያለ ይቅር ሲባል ወደ ቀደመ ምንፍቅናው እንደሚገባ ሁሉ ተሃድሶወችም በእምባ ሆነው ይቅርታ ይጠይቁና መልሰው ቅዱሱንና ማደሪያውን ያሳዝናሉ ፤
  •  የአርዮስ ትምህርት የረከሰና የተጠላ የማይጠቅምም እንደሆነ ሁሉ የተሃድሶወችም ትምህርት መልካምን ፍሬ የማያፈራ የማይጠቅም ዘር ነው፡፡
  •  የአርዮስ እውቀት ከዲያቢሎስ እንደሆነ ጥበቡም ለክርስቲያኖች የማይሆን እንደሆነ ሁሉ የተሃድሶወችም ጥበብ ለመንግስተ ሰማያት የማያበቃ ባዶ ጥበብ ከንቱ ጩኅት ነው፡፡ 
  • ስለዚህ ቅዱስ ቄርሎስና አርዮስ ህብረት የላቸውምና ይቅር ተባብላችሁ በአንድነት ስሩ አትበሉ ፡አይባልምና!! ወይንስ ቅዱስ ቄርሎስን አንተም ተው ስትሉ ቤተክርስቲያንህን ከመጠበቅ ቸል በል ማለታችሁ እንደሆነ ታስተውላላችሁ? የከበረ ማእድን የተከማቸበትን ቤት ለሌባ አሳልፋችሁ እየሰጣችሁ እንደሆነ አታውቁምን? 


  በስመ አብ ወወልድወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፡፡

  ፍቅርን አውቃለሁ በተግባርም እገልፃለሁ የሚል - - - ነገር ግን ፍቅሩ የይምሰል የዲያቢሎስ ያልሆነበት የመንፈስ ቅዱስን ፍቅር የተገነዘበ በማስተዋልም የከበረ በተዋህዶ እምነቱ የሚኮራ በእውነት ፊት ፡ በፍቅር ሽንጎ ፡ በማስተዋልም ጥበብ ዳኛ ይሁንና ይህንን ይዳኝ ፦ በሽንጎው ላይ ቅዱስ ቄርሎስና አርዮስ ቆመዋል፡፡ ስለጥንተ ነገራቸው፦

  የማይታዩ እጆች በቤተ-ክርስቲያን ላይ


  by ገብር ኄር   በሙላቱ ደቦጭ

  • አባ ሰረቀብርሃን ወልደሳሙኤል (እምነት ሳይለይ የሚያገለግለው ካህን!)
  • በጅብ ትከሻ የአህያ ሥጋ መጫን መሆኑን ሳያውቁት ከባድ ኃላፊነትን ሰጥተዋቸዋል
  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊት ታሪካዊትና አማናዊት ናት እየተባለ የሚነገረውን እውነት እየበለቱ ማሳየት ብቃቱ ባይኖረኝም እውነታው ግን ቅንጣት ታህል ሳልጠራጠረው የምቀበለው ነው፡፡ ዓለም አቀፋዊው ታሪክ እንደሚያስረዳን ይህቺ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሁለት አይነት ጠላቶች አሏት ቀለል ባለ አማረኛ ለማስቀመጥ የውጭና የውስጥ ልንላቸው እንችላለን በፋሺሽት ኢጣሊያን ዘመን የሀገሬ አርበኞች ተናገሩት የተባለ ነገር ትዝ አለኝ
  ጠላትማ ምንግዜም ጠላት ነው፣
  አስቀድሞ መምታት አሾክሿኪውን ነው፡፡
  የሚል በወቅቱ ለሀገራቸው አንድነት ለባንዲራቸው ክብር ለሃይማኖታቸው ጽናት እግራቸውን ለጠጠር፣ ደረታቸውን ለጦር፣ ግንባራቸውን ለሀሩር፣ በመስጠት በነፍሳቸው ጨክነው ከጠላት ጋር አንገት ላንገት ይተናነቁ ለነበሩት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ለነበሩት አርበኞች ትልቁ ፈተና የባንዳው /የጠላት ቅጥረኛው፣የከዳተኛው/ ጉዳይ ነበርና ይህንን አሉ፡፡ ለማለት የፈለኩት ለአንባቢዎቼ ግልጽ የሆነ ይመስለኛል ከውጭው ጠላት ይልቅ የሚበረታው የውስጥ ጠላት ጡጫ ነው፡፡

  Thursday, September 15, 2011

  አጥብቀን ልንታገለው የሚገባን እውነታ!

  • ስደተኛው ሲኖዶስ ብለው ሲነሱ፣ ተው አይሆንም ሲኖዶስ አይሰደድም ስንል፥ ዛሬ ደግሞ በአንድ መንበር ሥር በሚያገለግሉ ነገር ግን ግብራቸውን የለዩ ለከርሳቸው ያደሩ ከሃዲያን ተነስተውብናል

  ዛሬ ለሥርዓተ ቤተ ክርስትያን ግድ የሌላቸው ለግል ከርሳቸው እና ጥቅማቸው የሚሯሯጡ አባቶች ተብዬዎች፣ የጥንት አባቶቻችን የሰሩልንን ቀኖና ወደጎን በመተው ያለ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሥራዎችን እየሰሩ ያሉ ሰዎች እኛ ውስጥ ሆነው የኛ የሆነውን ለጠላት እየሰጡ ያሉበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

  ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወልዳ መካን፣ አሳድጋ ለመናፍቃን እረዳት የሆኑበት ከመቼውም ጊዜ በላይ ትልቅ ችግር ውስጥ ያለችበት ጊዜ አሁን ነው፣ ስለዚህ እያንዳንዱ የተዋሕዶ ልጆች በሙሉ በአርባና በሰማኒያ ቀን ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ የተወለድን ሁላችን በአንድነት ልንነቃ እና ልንጠብቅ የሚገባን ጊዜ አሁን ነው። ሰዎቹ በአሁን ሰዓት በትልቅ ቤተክርስቲያንን የማፍረስ ሥራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡ለምሳሌ በዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ "የቤተ ክርስቲያን የውጪ ግንኙነት" በሚል የተከፈተ ጽህፈት ቤት አለ፣ ይህ ጽህፈት ቤት በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ልዩ ፊርማ ተፈቅዶ የተከፈተ ጽህፈት ቤት ነው፣ ነገር ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚው ሲኖዶስ እውቅና የለውም ለዚህም ሥራ ሊሠሩ (ሊያስፈጽሙ) የተላኩት ሦስት ግለሰቦች በሃገሩ ነዋሪዎች ናቸው፣ ሕዝቡን ያውቁታል፣ ህጉን ኖረውበታል፣ በቀላሉ ሰዎች ሊቀበሏቸው ይችላሉ ተብለው የመጡ እና ሥራውን በመሥራት ላይ ያሉት ግለሰቦች የሚከተሉት ናቸው
  ፩ኛ/ አቡነ ፋኑኤል
  ፪ኛ/ አባ ሰረቀ ወልደ ሳሙኤል
  ፫ኛ/ ዲ/ን ኃይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን (ከድቁናው የተሻረ)

  Tuesday, September 13, 2011

  Wahabism in Ethiopia as "CULTURAL IMPERIALISM"


  http://wikileaks.org/cable/2009/07/09ADDISABABA1674.html
  CONFIDENTIAL SECTION 01 OF 03 ADDIS ABABA 001674 
   
  SIPDIS 
   
  E.O. 12958: DECL: 07/15/2019 
  TAGS: KPAO KISL KIRF SCUL PROP ET
  SUBJECT: WAHABISM IN ETHIOPIA AS "CULTURAL IMPERIALISM" 
   
  REF: 08 ADDIS ABABA 3230 
   
  Classified By: Ambassador Donald Yamamoto for reasons 1.4 (B) and (D). 
   
  SECOND OF THREE CABLES ON COUNTERING WAHABI INFLUENCE IN 
  ETHIOPIA 
   
  ------- 
  SUMMARY 
  ------- 
   
  1. (C) Arab Wahabi missionaries, mainly from Saudi Arabia, 
  continue to make inroads into the Ethiopian Muslim community, 
  but are meeting increasing resistance in doing so. Islam has 
  existed in Ethiopia since the time of the Prophet Muhammad 
  and the mainly Sufi Muslim community has enjoyed traditions, 
  customs, and cultural practices that have endured for 
  centuries. Yet this indigenous Muslim culture has come under 
  attack since 9/11 by Wahabi missionaries engaging in what 
  amounts to &cultural imperialism8 against Ethiopian Islam. 
  Prior to 9/11, there was little Wahabi proselytizing in 
  Ethiopia. As a result, Ethiopia's delicate Muslim/Christian 
  balance and historic attitudes between the faith communities 
  regarding tolerance and mutual respect are being challenged, 
  thereby undermining U.S. interests in the region. Sufi 
  Muslim leaders want support from the U.S. to counter this 
  pressure. END SUMMARY. 
   
  ----------------------------------- 
  WAHABIS CHALLENGE ETHIOPIAN MUSLIMS 
  ----------------------------------- 
   

  አቦይ ስብሀት


  ‹‹ጓደኛ ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ››

  የሰሞኑ የሕወሐት ሰዎች አጀንዳ “ማህበረ ቅዱሳን” ሆኗል፤ይህ በ1987 በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ላይ ያደረጉትንም ያስታውሰናል፤ሕወሐት የሥነ ምግባር እና የሞራል መሰረት የሆኑ ዕሴቶችን በማርከስ፣የነቀዘ ትውልድ ለማብቀል ቤተ ዕምነቶቻችንን የነውረኞች እና የሌቦች ዋሻ እንዲሆኑ የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት እና ድጋፍ ተጠናክሯል::

  በሃጂ መሃመድ አወል ረጃ እና በግራዝማች ሀዲስ መካከል የነበረውን አለመግባባት ተጠቅመው በታላቁ አንዋር መስጊድ ፍጅትን አነገሱ፤የእስልምና ሃይማኖት መሪዎችን ሰብስበው ከርቸሌ ወረወሩ፤እጅ አልሰጥም አሉ በሚል ሽፋን የታወቁ የእስልምና መሪንም አስወገዱ፤በዚህ መልክ የእስልምና ምክርቤቱን አዳክመው ምን እንደተከተለ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ይበልጥ ያውቀዋል፤እንኩዋን ለመሪነት በመስጊድ ደጃፍ ሊያልፉ የማይገባቸው የእስልምና ምክርቤቱን ተቆጣጥረው እስከቅርብ ግዜ ድረስ ቆይተዋል፤ ፤ዛሬ እኚህ ሰው በይፋ በሙስና ተወንጅለው በሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፍተኛ ትግል ስፍራቸውን ለቀዋል፡፡


  ከላይ ያለው ያለፈ ታሪክ ከ17 ዓመት ቆይታ በኋላ እኛ ላይ እንደማይደገም ምንም ማረጋገጫ የለንም ፡፡አሁን በቤታችች እየተከናወነ ያለው ይህን የመሰለው ስራ ነው፡፡ ይህን ያልኩት ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ ይህን የመሰለ ሸፍጥ የሰራ መንግስት ለእኛም ወደ ኋላ እንደማይል ለማሳሰብ ነው፡፡ አሁን ቤተክርስትያናችን ያለችበትን ክፍተት ተጠቅመው ሁሉም ጠላቶቸዋ ከውስጥም ከውጭም ያሉት በትብር እየሰሩባት ይገኛሉ፡፡

  Monday, September 12, 2011

  ከሐዋርያትም መጠራት የኢትዮጵያ መጠራት ይቀድማል፡፡

  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ውስጥ ከሃይማኖቷ አስተምህሮ እና ቀኖና ውጪ የሆኑ ድርጊቶች በከፍተኛ ደረጃ በመስፋፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ይህንን ድርጊት በሚመለከት መምህር ተስፋዬ ሸዋዬን እንደ አንድ የእምነቱ ተከታይ ግለሰብ ያላቸውን ሐይማኖታዊ አስተያየት ሰጥተውናል፡፡
  To read in Pdf .....click http://www.4shared.com/document/4L5K8CVd/memehir.html  ከተጠየቁት ጥቂት ጥያቄዎች

  • ብዙዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ እምነት ጥንታዊ እና ባህላዊ እና ልማዳዊ አስተሳሰብ ያጠቃታል ይላሉ ፡፡ ይህ አባባል በእርስዎ አመለካከት ምን ያህል እውተኛ ነው ? 
  •  በድርሳን በገድል በተዓምር ላይ የተገለፁ ታሪኮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በተለይም ከወንጌል ጋር ይጋጫሉ ? 
  • የተዋህዶ እምነት አስተምህሮ ከዘመን እና ከስልጣኔ ጋር አብሮ መጓዝ አቅቶታል የሚል አስተያየት ይሰነዘራል፡፡ በዚህ ላይ ምን ይላሉ? 
  • የተዋህዶ እምነት አስተምህሮ የተመሰረተው በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሳይሆን በአዋልድ መፃህፍት ላይ ነው የሚሉስ ምን መልስ ይኖሮታል ?  click read more...

  ቅዱስ ድሜጥሮስ እና የዘመን አቆጣጠር

  from  http://www.melakuezezew.info

  ድሜጥሮስ መስታወት ነው፡-በመስታወት ከዓይን ጉድፍ ከጥርስ እድፍ አይተው እንደሚያጸዱበት ሁሉ ባሕረ ሐሳብንም የተማረ ሰው ዓለም ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ እስከ ምጽአት ድረስ የሚሆነውን ቁጥር ያውቃልና፡፡ ባሕረ ሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ማለት ነው፡፡ አንድም ሐሳብ ባሕር ይለዋል ዘመን ያለው ቁጥር ሲል ነው፡፡
  ድሜጥሮስ መነጽር ነው፡- መነጽር የራቀውን አቅርቦ፣ የረቀቀውን አጉልቶ፣ የተበተነውን ሰብስቦ እንዲያሳይ እርሱም የተበተኑ አጽዋማትን በዓላትን አቅርቦ ያሳያልና፡፡
  ድሜጥሮስ ጎዳና ነው፡- በጎዳናው ተጉዘው ከቤት እንደሚደርሱ ሁሉ፣ ባሕረ ሓሳብም ወደ ኋላ ያለፉትን ወደፊትም የሚመጡትን አጽዋማት በዓላትን ለይቶ ያሳውቃልና፡፡

  Sunday, September 11, 2011

  አድናቂ እንጂ መካሪ ለሌላቸው የወንጌል መምህራን የተላከ መልዕክት  የሚከተለውን ጽሑፍ የዚህ ጡመራ መድረክ ተከታታይ ከሆኑ ግለሰብ የደረሰን ነው::  መልዕክቱም አድናቂ እንጂ መካሪ ለሌላቸው አንዳድ አስበውበትም ይሁን ሳያስቡበት በፖለቲካው ለተዘፈቁት የወንጌን መምህራንን ይመለከታል:: መልካም ንባብ:: 
  +++
  ለእኛ የማናውቀውን ንገሩን ለእናንተም የሚያምርባችሁን ልበሱ!
  በላፈው ዓመት ከእናንተ ብዙ ተምረናል። በሃይማኖት እና ማሕበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ብዙ ቁም ነገሮችን ቀስመናል። ቃለ ሕይወት ያሰማልን። ታዲያ ውጤቱን ሁላችንም በሕይወታችን የምናየው ቢሆንም፤ ዓመት መጨረሻ ላይ ስለትምህርት አሰጣጡ ሁኔታ ተማሪዎች በተራቸው አስተማሪዎቻቸውን የሚገመግሙበት አሰራር ደግሞ አለ። ይህ አሰራር ሀገራችን ውስጥ በመጠኑ ቢሰራበትም፤ በሰለጠነው ዓለም ግን በስፋት ይጠቀሙበታል። ዓላማውም ስህተቶችን አርሞ መጪውን የትምህርት ዘመን የተሻለ ውጤታማ ለማድረግ ብቻ ነው። በዚሁ መሠረት እኔም ከተማሪዎቹ አንዱ ስለነበርኩ ፤ ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀልኝ ፎርም ባይኖርም ራሴ ባመቸኝ መልኩ መስተካከል አለበት የምለውን  እነሆ!

  Friday, September 9, 2011

  አክራሪ ሙስሊሞች 3 ክርስትያኖችን በድንጋይ ገደሉ  ደሴ አሬራ እየተባለ በሚታወቅ አካባቢ በሚገኘው የደብረ ሣህል ቅዱስ ዐማኑኤል ፀበል ተፀብለው ወደ መኖሪያ ቤታቸው እየተመለሱ በነበሩ ወጣቶች ላይ፣  ጳጉሜን 3 ቀን 2003 ዓ.ም ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ በአካባቢው ያሉ አክራሪ ሙስሊሞች  አስበው እና አልመው ሲጠብቋቸው በነበሩ ክስርትያኖች ላይ የድንጋይ ናዳ በማውረድ ጥቃት አድርሰውባቸው ወዲያው አንድ ሰው የገደሉ ሲሆን ፤  ሌሎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ከገቡት ብዙ ክርስትያኖች ውስጥ አንዲት ሴት እና አንድ ወንድ በህክምና ላይ እያሉ የደረሰባቸው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ አካላቸውን በጥቃቱ የተጎዱ ክርስትያኖች በሆስፒታሉ ይገኛሉ፡፡የመጀመሪያው ሟች ከፍተኛ ጉዳት ልቡ ላይ ደርሶበት ነው፡፡


  በአካባቢው የነበሩ የአይን ምስክሮች ጠይቀን እንደተረዳነው ጉዳቱ የደረሰባቸው በጠመጠሙ አክራሪ ሙስሊሞች መሆኑን የተረዳን ሲሆን ደጀሰላም ላይ የተዘገበው ግን ‹‹አንዳንድ ምንጮች ለጥቃቱ በሰኔ ወር የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የእገዳ ውሳኔ ያስተላለፈባቸው “መምህር ግርማ” የተባሉትን አጥማቂ ተከታዮች›እንደሚጠረጠሩ ብለው የዘገቡት የተሳሳተ እና የተዛባ መረጃ ስለሆነ እንዲስተካከል ስንል እንጠይቃለን፡፡ ይህን መረጃ ቦታው ድረስ ሄደው ወይንም ጉዳቱ ደርሶባቸው በሆስፒታል ያሉትን ሰዎች አናግሮ እና አጣርቶ መዘገብ ያለበለዚያ ደግሞ ጉዳዩ እስኪጣራ እና ጉዳት ያደረሱት ሰዎች እስኪለዩ ድረስ በይሆናል የተሳሳተ መረጃ ለክርስትያኑ ማድረስ ተገቢ አለመሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

  ሀሰት አንናገር እውነትን አንደብቅም
  ‹‹እግዚሐብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ››

  ርእሰ ዓውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ


  እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ ዘመነ ማቴዎስም፣ ዘመነ ማርቆስም፣ ዘመነ ሉቃስም ሆነ ዘመነ ዮሐንስ በአራቱም ዘመናት አስቀድሞ ርእሰ ዓውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ ይዘከራል፡፡ ዮሐንስ የስሙ ትርጉም «ጸጋ እግዚአብሔር» ማለት ነው፡፡ ዘመናት ዘመናትን እየወለዱ፣ ሰዓታት ደቂቃን ቅጽበትን /ሰኮንድን/ ሳይቀር እየሰፈሩ/እየቆጠሩ/ ዕለታት ሳምንታትን፣ ሳምንታት ወራትን፣ ወራት ዓመታትን አሁን ላለንበት ዘመን ደርሰናል፡፡ ዓውደ ዓመት በግእዝ ሲሆን በአማርኛ የዘመን መለወጫ/ ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለም ይጠራል፡፡

  Thursday, September 8, 2011

  ድንቅ ተአምር

  ይህ የእመቤታችንን ድንቅ ተአምር የተነገረው  ነሐሴ 19/2003 በግቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የማታ ጉባኤ ሲሆን ነገሩም እንዲህ ነው::
  • “እማየ” ብሎ ጠራኝ እኔም “አቤት” አልኩት “ጆሮወቼ ሰሙልኝ” አለኝ፡፡ እኔም “ልብህ ቢሰማ ነውንጅ የሚሻለው” አልኩት፡
  ይህ የእመቤታችንን ድንቅ ተአምር የተነገረው ትናንት ነሃሴ 19/2003 በግቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የማታ ጉባኤ ሲሆን ነገሩም እንዲህ ነው ፦ ተአምሩን የመሰከሩት አንዲት እናት ሲሆኑ “የእመቤቴን ስም እየጠራሁ ያለአባት ያሳደግኩት ልጅ ነበርኝ ፡ እኔም ልጄም እመቤታችንን በጣም እንወድ ነበረ ፡ ያለአባት በእመቤቴ ስም ያሳደኩት ልጄ ተምሮልኝ ጥሩ ስራ ያዘልኝ ፡ በዚህ ደስ ብሎኝ ሳለ ልጄ በስራ ቦታ ካልሆኑ ልጆች ጋር ገጥሞ አዲስ ነገርን ተማረብኝ ፡ አንድ ቀን ማታ ሲመጣ “ እናቴ ሆይ ጌታን ተቀበይ” አለኝ ይህን ሲለኝ ደነገጥኩ “እመቤታችንስ” ስለው “ዙሪያ ጥምጥም መሄዱ ይበቃናል አንቺም እኔም ጌታን መቀበል አለብን” አለኝ ፡ እኔም ጧት ማታ አለቅስ ጀመር ፡ ለልጄም ይህ የነፍስ በሽታ ለስጋውም ተርፎ ሁለቱ ጆሮወቹ አልሰማም አሉት፡፡ በዚህም የተነሳ ጴንጤወች እንፀልይልህ ብለው በአዳራሻቸው ወሰዱት ፡ ጆሮወቼ ይድኑ ይሆን ብሎ ተስፋ ያደረገው ልጄም ይባስ ብሎ ሁለቱም አይኖቹ ጠፉ ፡ ከዚህ በኅላ እቤት ተኛ ፡ እኔም እያለቀስኩ እኖር ነበር፡፡ አስቡት ጆሮውንኳ ባይሰማ አይን ቢኖረው በምልክት እንግባባ ነበር ፡ ወይንም አይኑ ባይኖርና ጆሮው ቢሰማ በድምፅ እንግባባ ነበር አሁን ግን እጅግ ችግር ሆነብኝ፡፡ ከሁሉ የሚያስጨንቀኝ ግን እመቤቴን መክዳቱ ነበር፡፡ 

  ምን ዓይነት ለውጥ ለቤተ ክርስቲያን?   (ለግልጽ ውይይት የቀረበ)
  by Deje Selam on  September 8, 2011
  • ቤተ ክርስቲያንን ችግር በግልጽ አውጥቶ መነጋገር ገመና እንደመግለጥ የሚቆጠርበት ጊዜ አልፏል
  • አሁን የምንደብቀው፣ ብንደብቀውም የሚጠቅመን ገመና የለም
  • እጅ መጠቋቆሙ ለውጥ አያመጣም
  • ምእመናንን በስፋት ወደ አስተዳደር ማምጣት የዘላቂው መፍትሔ አካል ተደርጎ መታየት ይኖርበታል
  • በያዝነው መንገድ ከቀጠልን ግን የዛሬ አምስት ዓመት የምንነጋገርው ከአሁኑ በባሰ አዘቅት ውስጥ ሆነን እንደሚሆን ለመገመት ነቢይነት አይጠይቅም።
  • በትዕግስት አንብቡት፤ ሚዲያዎችን ጨምሮ ለአባቶችም ለምእመናንም በማድረስ ተባበሩን።
  (ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 3/211)፦ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጨርሶ መደበቅና ማስተባበል እንኳን ከማይቻልበት ደረጃ የደረሰው የቤተ ክርስቲያናችን ውስጣዊ ቀውስ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል። እንደ አንድ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታይ ነገሩን በተቻለን ቅርበት ስንከታተል ቆይተናል። በየሚዲያው የሚወጡትን ጽሑፎች፣ ዜናዎች እና ቃለ ምልልሶችንም ሳያመልጡን ለመረዳት ሞክሬያለሁ። ሆኖም በሚዲያ የሚቀርቡት ብዙዎቹ አስተያየቶች ችግሩን በተረዱት መጠን ወይም መልክ በማንጸባረቅ ላይ የተወሰኑ ናቸው። ችግርን በትክክል መረዳት የመፍትሔው ግማሽ እንደመሆኑ ውይይቱ የሚወደድ ነው። የመፍትሔ አቅጣጫ ለማመላከት የሞከሩ ፀሐፊዎችና ተናጋሪዎች ቢኖሩም ቅሉ ብዙውን ጊዜ ሐሳቦቹ ቅንጭብ በመሆናቸው አጠቃላይ ውጤታቸው በግልጽ የሚታይ አይደለም። ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱ የራሷን ችግር የምትመረምርበት ተቋማዊ ዝግጅት የሌላት ሆና ትታያለች። ምእመናንና ሌሎች ተቆርቋሪ ዜጎችም ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል አስተዋጽዖ የሚያደርጉበት ዕድል ዝግ ነው ማለት ይቻላል።

  የሐረሩ ስልጠናና ውጤቱ  • ገበየሁ ይስማው ሥልጠናው መካሄዱን አመነ የሠልጣኖች ምልመላ ሂደትን አብራርቷል
  • የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ለጉባኤ ከአዲስ አበባ ሳባኪ እንዳይጠራ ወሰነ
  • ማኅበረ ቅዱሳን በተሐድሶ ሰራዊትነት የሰለጠነ አባል የለኝም አለ
  • ከድሬዳዋ ለተሐድሶ ሰራዊትነት ሥልጠና ወደ ሐረር የተጓዙ በሀሳብ ባለመግባባት ለሦስት ተከፈሉ
   ገበየሁ ይስማው
   ገበየሁ ይስማው
  በቅርቡ በሐረር ከተማ በሉተራን 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተሐድሶ ሰራዊትነት ዙርያ የተሰጠው ሥልጠና ልዩ ልዩ ውጠየቶችን እያስከተለ እንደሆነ የምስራቅ ኢትዮጵያ የገብር ኄር መንጮች ገለጹ፡፡
  ሐረር
  የሐረር ከተማ እንዳንድ ምዕመናን ግብረ ተሐድሶን በተመለከተ ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው፡፡ እነዚህ ምዕመናን ‹‹በሌሎች አህጉረ ስብከቶች የታገዱ መምህራን ለምን ሐረር ላይ እንዲያስተምሩ ይፈቀድላቸዋል? በከተማው እየተፈጸመ ባለው ግብረ ተሐድሶ ላይ ሀገረ ስብከቱ አፋጣኝ እርምጃ ለምን አይወስድም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

  Wednesday, September 7, 2011

  መዝሙረ ዳዊት 1


  1    ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ 
       በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ 
       በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።
  2    ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ 
        ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።
  3    እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ 
       ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ 
        ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
  4   ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፥
       ነገር ግን ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ ናቸው።
  5   ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ፥ 
       ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም።
  6    እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ 
       የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።


  መዝሙረ ዳዊትን ከነትርጓሜው በሳምንት አንድ አንድ ምዕራፍ ማቅረብ መጀመራችንን ለመግለፅ እንወዳለን

  ‹‹እግዚሐብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ ››

  Tuesday, September 6, 2011

  የጌታችን ክህነትና የመልከ ፄዴቅ ክህነት  ቅዱስ ጳውሎስ ለምን ጠቀሰው? - - - ዕብ.3:1 “ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ” ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ በእብራውያን መልእክቱ ያተኮረው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ማስረዳት ነው፡፡ ይህንንም የሚያስረዳው ደግሞ በንፅፅር ነው፡፡ ከነቢያት ስለመብለጡ የእነሱን ንግግርና የእሱን ንግግር በማነፃፀር አስረዳ፡፡ ከዚያም በኅላ ደግሞ ከመላእክት መብለጡን አስረድቷል፡፡ አሁን ደግሞ ከካህናት መብለጡን ለማስረዳት ያመጣል፡፡ ከካህናት መብለጡንም ሲያስረዳ ዋናወቹ ምክንያቶች 1) በክህነቱ 2) በመስዋእቱ 3) መስዋእቱ በቀረበበት ድንኳን መሆኑን ያስረዳል፡፡ ስለክህነቱም በ ዕብ.5፡1-10 ፣ በዕብ. 6፡20 ፣ 7፡1-28 ፣ 8፡1-3 ባሉት አስረድቷል፡፡

  ክህነት ምንድን ነው? - - - አገልግሎት ሲሆን መሾምን መመረጥን ያመለክታል፡፡ በመፅሃፍ ቅዱስም ከአዳም ጀምሮ የተለያዩ ሰወች ለዚህ ክህነት በሰውም በእግዚአብሄርም ሲመረጡ ያሳየናል፡፡ 

  መልከ ፄዴቅ ማነው? - - ዕብ.7:3 “አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።” ይህ ሲባል መልከ ፄዴቅ ሰው አይደለም ማለት አይደለም ፡ ዘሩ ከካም ዘር ነበረና በሙሴ መፃህፍት አልተገለፀም ለማለት ነው፡፡ ይህ የተመረጠ ሰው አፅመ አዳምን እንዲጠብቅ የታዘዘ በብህትውና የሚኖር ነው፡፡ የመልከ ፄዴቅ ክህነትም ሙሴ አሮንን በሾመበት ሥርአት ቅብዕ አፍልቶ ፡ መስዋእተ እንስሳ ሰውቶ ፡ልዩ ልዩ ህብር ያላቸውን አልባሳት አልብሶ የሾመው ሰው የለም፡፡ይልቁንም እግዚአብሄር መረጠው ፡ በማይታወቅ ግብርም ሾመው እንጂ፡፡ አሮንና ልጆቹ በሙሴ እጅ ፡ ሙሴም በመልአኩ እጅ እንደተሾሙ (ሐዋ ፡ 6፡6) መልከፄዴቅ ግን ሹመቱ ከእግዚአብሄር ነውና ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ “ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።” ያለው ለዚህ ነው፡፡ “ለዘላለም” ማለቱም እስከ ህይወቱ ፍፃሜ ማለቱ ነው፡፡በዚህም ምክንያት ክህነቱ ከሌዋውያን ክህነት ፍፁም የተለየ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ እንደሌዋውያን ክህነትም የእንስሳት መስዋእት አይሰዋም መስዋእቱ ንፁህ ስንዴና ወይን ነውንጂ፡፡ በዚህም ተነስቶ ቅዱስ ጳውሎስ - - ዕብ.7:11 እንግዲህ ህዝቡ በሌዊ ክህነት የተመሠረተን ሕግ ተቀብለዋልና በዚያ ክህነት ፍጹምነት የተገኘ ቢሆን፥ እንደ አሮን ሹመት የማይቈጠር፥ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ግን የሆነ ሌላ ካህን ሊነሳ ወደፊት ስለ ምን ያስፈልጋል? ብሎ ይጠቅሰዋል፡፡

  ጳጉሜ


  • የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው
  • በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው

  ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ / Thirty months of sunshine / በመባ ትታወቃች ትለያለች፡፡ ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት / የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡

  Monday, September 5, 2011

  ይቅር በሉን

  ከሳምንት በፊት ‹‹ቤተክርስትያን ትዘጋ›› (http://andadirgen.blogspot.com/2011/08/blog-post_30.html) የሚል ሰላማዊ ሰልፍ August 30 2011 ሐረር መንገድ በቦርደዴ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ላይ አክራሪ የሚባሉ ሙስሊሞች ወጥተው ለአካባቢያቸው ወረዳ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው መጠየቃቸውን እና መንግስት በጊዜው የወሰደውን እርምጃ በመግለፅ መዘገባችን ይታወቃል፡:

  በጊዜው መንግስት ይህን ስራ የሰሩትን ሰዎች ገሚሶቹን በማፈስ ወደ እስር ቤት ያስገባቸው ሲሆን በአካባበቢው ላይ የሚገኙ የእስልምና አባቶች መፍትሄ  ለመሻት ይህን ጉዳይ በእርቅ ለመፍታት ከአካባቢው ክርስትያኖች ጋር በመነጋገር ይህን የሰሩት ሰዎች ይቅርታ እንዲሉ እና ክርስትያኖቹም ይቅር እንዲሏቸው ከአሁን በኋላ የዚህ አይነት ነገር በአካባቢያቸው እንደማይከሰት የተነጋገሩ ሲሆን የቤተክርስትያኒቱ አባቶችም ነገሩን በመመልከት ይቅር ብለዋቸው ችግሩን በመፍታት አካባቢው ላይ ሰላም ማውረድ ችለዋል፡፡ 

  ሐሰት አንናገርም፤ እውነትንም አንደብቅም 
  ‹‹እግዚሐብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ ››