Friday, September 2, 2011

‹‹ለቤተክርስትያን አገልጋዮች›› የተሐድሶ ሠራዊትነት ስልጠና ተሰጠ


በምስራቅ ኢትዮጵያ ከሚገኙ አራት ሀገረ ስብከቶች ለተውጣጡ ‹‹ለቤተክርስትያን አገልጋዮች›› የተሐድሶ ሠራዊትነት ስልጠና ተሰጠ



  • የሥልጠናው ዋና ርዕሰ ጉዳይ ኢየሱስን ማለመመድ የሚል ነበር
  • ስልተ በጋሻው በዝርዝር ቀርቦላቸው እንዲጠቀሙበት መመሪያ ተሰጥቷቸዋል
  • ፓስተር መስፍን ፤ገበየሁ ይስማውና  በጋሻው ደሳለኝ ከነሐሴ 13-15 ሐረር በቆየበት ጊዜ በሥልጠናው ዙርያ መምከራቸውን ለመረዳት ተችሏል
  • ለሥልጠናው ተሳታፊዎች ኢየሱስ አማላጅ ነው የሚል ማስታዎሻ እና መጸሐፍ ተሰቷቸዋል
  • ከሠልጣኞቹ መካከል ቀደም ሲል ማኅበረ ቅዱሳን በክረምት ተተኪ መምህራን ሥልጠና አሰልጠኗቸው ከነበሩት ሠልጣኞች አንድ ግለሰብ ተገኝቷል
ከድሬዳዋ ፤ ከሱማሌ ፤ ከምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ አህጉረ ስብከቶች የኦርቶዶክስ  አብያተ ክርስቲያናት ለተውጣጡ ‹‹የቤተክርስቲያን አገልጋዮች›› ግበረ ተሐድሶን በሚያስፋፉበት ስልት ዙርያ ሥልጠና መሰጠቱን  በሰነድ እና በድምጽ ወምስል የደረሰው መረጃ አመለከተ፡፡

‹‹ሃይማኖቶችን አንድ እናደርግ ሁላችንም በቀን አንዳንድ ሰው እንለውጥ›› በሚል መርህ የተጀመረው ሥልጠና በሐረር ከተማ ሉትራን 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከነሐሴ 23-30 ሊሰጥ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ትላንት ማምሻውን መጠናቀቁ ታውቋል፡፡ሥልጠናው ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽት 2፡30 እንደተሰጠ ለመረዳት ተችሏል፡፡የሰሌዳ ቁጥሩ ዕድ 00122 የሆነ ተሸከርካሪ ለሥልጠናው አስፈላጊ የሆኑ ሎጀስቲክስ ለማሟላት ሥራ ላይ ውሏል፡፡
የሥልጠናው ዋና አሰልጣኝ የቀድሞ የሐረር ቀበሌ 10 ሊቀ መንበር የአሁኑ ፓስተር መስፍን ነው፡፡ሌሎች ከአዲስ አበባ የተለያዩ የፕሮቴስታንት ድርጅቶች የመጡ በርካታ ፓስተሮች በአሰልጣኝነት የተሳተፉ ሲሆን ዋና አስታባባሪው ደግሞ ከአሰበ ተፈሪ ለዚሁ ሥራ ወደ ሐረር ያቀናው ገበየሁ ይስማው ነው፡፡ገበየሁ ይስማው በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ምንም የሥራ ኃላፊነት የሌለው ባለበት የሃይማኖት ችግር በተነሳ ውዝግብ በመቐሌው አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የተማረውን የዲግሪ መርሀ ግብር ማስረጃ ያለተሰጠው ወልደ ተሐድሶ ነው፡፡በዚሁ ምክንያት በምዕራብ ሐረርጌ የይብሮ ወረዳ ኮተራ ቅዱስ ገብረኤል ምዕመናን አታስተምረንም በማለት እነዳባረሩት ይታወቃል፡፡ፓስተር መስፍን እና ገበየሁ ይስማው በጋሻው ደሳለኝ ከነሐሴ 13-15 ሐረር በቆየበት ጊዜ በሥልጠናው ዙርያ መምከራቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡
የስብሰባው ተሳታፊዎችና አሰልጣኞች በከፊል

በሥልጠናው ዋና ትኩረት የተሰጠው ርዕሰ ጉዳይ ‹‹ኢየሱስን የማለማመድ ትምህርት›› ነው፡፡በዚህም ሠልጣኞቹ የበጋሻውን አሰረ ፍኖት እንዲከተሉ ተደጋግሞ ሲመከሩ ተስተውሏል፡፡ስልተ በጋሻው በዝርዝር ቀርቦላቸው እንዲጠቀሙበት መመሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
በሥልጠናው የተሳተፉት ግለሰቦች ከሐረር ከጅጅራ ከሰበ ተፈሪ እና ከድሬ ዳዋ ከተሞች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ ሲሆኑ ከነዚህ መካካል ማኅበረ ቅዱሳን በ2000 ዓ.ም ክረምት በጅማ ለግቢ ጉባዔያት ተተኪ መምህራን አዘጋጅቶት በነበረው ሥልጠና ተሳታፊ የነበረ አንድ ግለሰብ ይገኝበታል፡፡ በቅርቡ አባ ሠረቀ ብርሃን በመቐሌ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ አካሂደውት በነበረው ውይይት አንድ የኮሌጁ ደቀመዝሙር ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ካህናት ማሰልጠኛ ምንፍቅና አስተምሮኛል›› ብሎ መናገሩን ያስታወሱ ታዛቢዎች ማኅበሩ የሠልጣኞች ምልመላ ስርዓቱን መሰፈተሽ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡
አሰልጣኞች በከፊል
የሥልጠናውን ሙሉ ሂደት የሠልጣኞችን ዝርዝር የያዘ የሰነድ የፎግራፍ እና ቪዲዮ መረጃ ደርሶናል፡፡የተሐድሶን ሴራ በማጋለጥ የሚታወቀው ማኅበረ ቅዱሳንም መረጃው ተጠቃልሎ ደርሶታል፡፡የስልጠናው ተሳታፊዎች በቤተክርስቲያን አገልግሎት ከያዙት ቦታ እና ሊያደርሱት ከሚችሉት አደጋ አንጻር ማኅበሩ መረጃ አለኝ በሚል አጉል ብሒል እርምጃ ለሚወስዱ የቤተክርስቲያኒቱ አካል ፈጥኖ የማያደርስ ከሆነ ታሪክ የማይረሳው ስህተት እየፈጸመ እንደሆነ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት የሚጠቀምበት ከሆነ ይህንን መረጃ ያጠናቀሩ የቤተክረስትያን ልጆች እንደ ሀዋሳ ምዕመናን የድርሻቸውን ለመወጣት ቪሲዲዎችን በማዘጋጀት ላይ ናቸው፡፡እንደ አግባብነቱ መረጃዎችን ወደ ፊት የምንገልጥ መሆኑን እያስታወቅን ይህንን መረጃ በመሰብሰብ እና ለተገቢው አካል በማድረስ ለተጉት የቤተክርስቲያን ልጆች ያለንን አድናቆት ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

Source:-  
በማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com)
 From www.gebrher.com       
‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!!!! ›› 

4 comments:

  1. እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን:: አሜን አሜን
    አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን
    አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን
    አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን፡፡

    ReplyDelete
  2. I can't justify this kind of bickering in the church. This shouldn't happen in the non-religious world, let alone in this respected church.

    ReplyDelete
  3. ምንም እንኳን የምሰሩት ጥሩ ቢሆንም የወሰዳችሁበትን መግለጽ ግን ይገባል አስገዳጅ ምክንያት እስከለለ ድረስ ማቲዎስ አጥምዛ የገብርኄር ረፖርተር ስለሆነ መገረጽ ያለበት ገብርኄር ነው ስሙም እንዳለ ሆኖ በተረፈ በርቱ ጥሩ ይዛችኋል

    ReplyDelete
  4. አይናችሁ እያየ ቤተክርስቲያን ትታደሳለች፡፡ እግዚአብሔር ከተሀድሶዎች ጋር ነው፡፡ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ያድስልን፡ ጣኦታቶችዋን ያስወግድንል፡፡ አሜን አሜን አሜን፡፡

    ReplyDelete