- አቶ በጋሻው ደሳለኝ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ስብከተ ወንጌል ሀላፊ ተደርጎ ተመደበ
- የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ማኅበረ መነኮሳት ይህን ነገር እንደሰሙ ይህ ሰው እዚህ ተመድቦ አይሰራም በሚል ተቃዎሟ ቸውን አሰምተዋል
- ’’በህብረት የሚያምፁት አንድ ላይ በመሰባሰባቸው ስለሆነ በየደብሩ አንበታትናቸው’’ የቤተክህነት ሰዎች ሴራ
- ስለ ቤተክርስያን አጥብቀው የሚሟገቱትን አባቶች ወደ ተለያየ ደብሮች ከቤተክህነት በወጣ ደብዳቤ የመደቧቸው ሲሆን የተመደቡት መነኮሳት ምደባውን አልተቀበሉትም፡፡ ከፈለጋችሁ ሬሳችንን አውጡ አንጂ ካደግንበትና  ካገለገልንበት ከዚህ ቤተክርስትያን አንንቀሳቀስም በማለታቸው ፤ የተሰራውን ስራ እና የሚሰራውን እየተሰራ ያለውንም በመቃወማቸው የማስጠንቀቂ  ደብዳቤ የተሰጣቸው ሲሆን ነገሩን ረገብ ለማድረግ ቤተ ክህነቱ በጉዳዩ ላይ እያሰበበት ይገኛል፡ 
 
 የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ማኅበረ መነኮሳት “የገዳሙን ት/ቤት እና ሁለገብ የአገልግሎት ሕንጻ ከገዳሙ አስተዳደር በመለየት ከወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ጋራ በዝብዘዋል” ያሏቸውን አስተዳዳሪውን መልአከ ሰላም ተክለ ማርያም ዘውዴን ከወራት በፊት ማባረራቸው ይታወሳል
ጉዳዩ የደረሰበትን ደረጃ ይጠብቁን........
እግዚሐብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅ 
 
 
No comments:
Post a Comment