Monday, September 26, 2011

የድሬዳዋ ሀ/ስብከት በተሀድሶ መናፍቃን ዙሪያ ቁርጠኛ እርምጃ ለመውሰድ ተወያየ

  •  ተሀድሶ መናፍቃን በቤተክርስቲያን የሰገሰጓቸውን ከሀዲያንን ማሰልጠን መቀጠላቸው ተዘገበ፡፡
  • የድሬዳዋ ሀገረ ስብከትም እራሱን ይፈትሽ” የቅ/ገብርኤል አስተዳዳሪ
  • የተሀድሶነት ስልጠና በሐረር ከተማ በተለምዶ ቢራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ስውር ቦታ በዝግ ቤት ለ3 ቀን ስልጠና ሰጥተዋል፡፡በዚህ ስልጠና የደብር አለቆች፣ መሪጌቶች፣ ዲያቆናት እና የሰ/ት/ቤት ወጣቶች ተሳታፊ ነበሩ
  • ባለፈው ከሰለጠኑት 17 ሰልጣኞች ውስጥ 13ቱ የምእራብ ሀረርጌ የደብር አለቆች ቄሶች እና ዲያቆናት ናቸው
  • እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ ነገር ግን ……… ከሀዲው የመናፍቃን አሰልጣኝ ፅጌ ስጦታው

በምስራቅ ኢትዮጵያ እየተንሰራፋ ያለው የተሀድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በቤተክርስቲያን ውስጥ ተመሳስለው የተሰገሰጉ ‘ካህናት’፣ ‘ዲያቆናት’ እና መነኮሳትን በማሰልጠን ከጅጅጋ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ እና አሰበ ተፈሪ ሀገረ ስብከት ተመሳስለው በመግባት ቤተክርስቲያንን በሁለት ቢላዋ እያረዷት ያሉ ከሀዲያንን በተመለከተ ባለፈው ሳምንት የምስራቅ ሀረርጌ እና ሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያሬድ እና የሀገረ ስብከት መምሪያ ሀላፊዎች እየወሰዱት ያለውን ርምጃ ተከትሎ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከትም ጥብቅ ውሳኔ ለማሳለፍ ከደ/ምህረት ካቴድራል፣ ከሳባ ደ/ሀይል ቅ/ገብርኤል እና ከቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ፀሀፊ እና የአድባራት አለቆች በሀገረ ስብከት በ13/01/2004 ዓ.ም የተሰበሰቡ ሲሆን ስብሰባውን የመሩት የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ አባ አረጋዊ ነሞምሳ ጉዳዩን ማን? መቼ? ለምን? ብለው ከማጣራት ይልቅ ይህንን ግን ማነው የቀረፀው ?የሚለው ላይ ብቻ ማተኮራቸው ብዙዎችን አባቶች ቅር አሰኝቷል ፡፡  
በተሀድሶ እንቅስቃሴ ተሳታፊ የሆኑት ዲያቆናት የተገኙበት የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ችግሩ በእኛ አጥቢያ ብቻ ሳይሆን በማሰልጠን፣ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆኖ ሌሎች እንዲሄዱ የመግፋት ስራ የሚሰሩት፣ በተለያዩ አጥቢያዎች ብቻ ሳይሆን ሀገረስብከት ድረስ ግንኙነት እንዳላቸው መረጃዎች ስለሚጠቁሙ እኛ ኮሚቴ አቋቁመን የማጣራት ስራ እየሰራን እንደሆነ ሁሉ ሀገረ ስብከቱም እራሱን እንዲፈትሽ ሲሉ ቁርጠኛ የቤተክርስቲያን ልጅነታቸውን አስመስክረዋል፡፡ የሀገረ ስብከት የስብከት ወንጌል ሀላፊ የሆኑት ደግሞ ይህንን ሲያስረግጡ በአሁኑ ሰዓት በቤተክርስቲያን እና በተሀድሶ ወረራ ላይ ቄስ፣ ዲያቆን፣ መነኩሴ የሚባል ሳይሆን ሁላችንም በቁርጠኝነት ቤተክርስቲያንን ለመታደግ የምንተጋበት ስለሆነ ውሳኔዎቻችን ቁርጠኛ እና ጥንቃቄ የተሞላባቸው ሊሆኑ ይገባል አይጠቅምም ብለን የምናጣጥለው መረጃም መኖር የለበትም በማለት አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ ማን ቀረፀው የሚለውንም እኛ ማጣራት ያለብን እውነት ነው አይደለም የሚለውን ብቻ ነው በማለት የማያወላዳ አቋማቸውን ገልፀዋል ፡፡ የሰ/ት/ቤት ማደራጃ መምሪያውም ቢሆን መረጃ አላገኘንም አላየንም ላሉት አካላት መረጃው ወደ እናንተ አይመጣም እናንተ ወደ መረጃው መሄድና ሀላፊነታችሁን መወጣት እንጂ በማለት አሳስበዋል ፡፡ 

የተሀድሶ መናፍቃን ስውር እንቅስቃሴ የታየባቸው አጥቢያዎች በርካታ ቢሆኑም በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሰ/ት/ቤትን ተኩላዎችን አበጥሮ ስንዴውን ከእንክርዳድ ለመለየት ኮሚቴ ከማቋቋም ጀምሮ ቁርጠኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ቀዳሚ መሆኑን አረጋግጧል መረጃ አሰባሰቡም ከሌሎቹ የተሻለ ነበር። ይህም የመናፍቃን የውስጥ አርበኛ በመሆኑ ቤተክርስቲያንን እያጠፏት ያሉ 17 የተሐድሶ ሰራዊት በድብቅ በሐረር ከተማ በመናፍቃን ፓስተሮች ሲሰለጥኑ ከተያዙት መካከል ዲ.ን ይትባረክ እና ግብረ አበሮቹ ከመታወቁ እና ከማጋለጡ ጋር ጋር ተያይዞ ነው፡፡ በሌሎች አጥቢያዎች በተለያዩ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ላይ ያሉ ግን የተሐድሶን ክንፍ የሚያንቀሳቅሱ ተንኮለኞች መካከል አንዱ የሆነው ምዕመናን እና የሰ/ት/ቤት ወጣቶች ሲያገኟቸው በይፋ ይቅርታ እየጠየቁ ከልባቸው ከሆነ ቤተክርስቲያንን ይቅርታ ለመጠየቅ የተዘጋጁ ይመስላሉ፡፡ ሌሎቹ ግን አሁንም በተግባራቸው እንደገፉበት ይገኛሉ፡፡ አስቀድሞም ማለትም ከ1999 ዓ.ም የቁልቢ ስልጣና ጀምሮ የተሐድሶ አራማጅ በመሆኑ የሚጠረጠው እና የደብረ ምህረት ቅ/ሚካኤል ካቴድራል ሰባኪ ወንጌል የሆነው ዲ.ን ቤዛ እስከ አሁን ምንም አላለም እንዲያውም ለጊዜው ከቦታው ተሰውሯል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በሌሎች አጥቢያዎች ሰርገው የገቡ እና በስልጠናው የተያዙ ካህናት፣ መነኮሳት እና የሰ/ት/ቤት ወጣቶች እኛ ብቻ ሳንሆን በሂደቱ ውስጥ ግንባር ቀደምት ተዋናኝ የሆኑ ግለሰቦችን እንደሚያጋልጡ እሚሳቸው ካገኙ ለቤተክርስቲያን የቆሙ ሊቃውንት አባቶችንም ስም ለማጥፋት እንዳሰቡ ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ለማንኛውም ሀገረ ስብከቱ ብዙ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያሉበት በመሆኑ ጉዳይውን በእርጋታ በማየት አጥቢያዎችን በማገዝ የተጣራ መረጃ ተይዞ ውሳኔ መስጠት አለበት ውሳኔውም ማባረር ማስወጣት ሳይሆን ያመኑት በይፋ የበደሉትን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ እንደቤተርስቲያን ስርአትም ቀኖናን መስጠት ያላመኑትም በመረጃ ላይ በመነሳት ከቤተክርስቲያን ማሰናበት ይጠበቃል ፡፡


 የተሀድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ አሁንም ከ30 በላይ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናትን፣ መምህራንን፣ መነኮሳትን እና የሰ/ት/ቤት አባላትን በስውር ማሰልጠናቸውን ቀጥለው በሐረር ከተማ በተለምዶ ቢራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ስውር ቦታ በዝግ ለ3 ቀን ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ተዘገበ፡፡ ባለፈው ይሰጥ በነበረው ስልጠና ድብቅ ሴራቸው የተጋለጠባቸው መናፍቃን ሰልጣኞች በዝግ ቤት ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ስልጠና የደብር አለቆች፣ መሪጌቶች፣ ዲያቆናት እና የሰ/ት/ቤት ወጣቶች ተሳታፊ ነበሩ፡፡ በስልጠናው ላይ ፅጌ ስጦታው፣ ዶ/ር አባ ሀይለ ልዑል፣ ሰለሞን ዘሀገረ ግሸን እና ሌሎች ፓስተሮች በአሰልጣኝነት ተሳትፈዋል። 



     ከሀዲው የመናፍቃን አሰልጣኝ ፅጌ ስጦታው
ፅጌ ስጦታው ከትሪኒቲ(የመናፍቃን መፅሔት ) ጋር 
ቃለምልልሱ ‹‹እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ ነገር ግን ………እየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ነው፤ ፃድቃን ሰማዕታት ላይ ጥያቄ አለኝ፤ ስለ ፀበል ፤ መስቀል ፤ እምነት፤ ያልተመለሱልኝ ጥያቄዎች አሉ…ይላል. .......በማለት በደንብ አድርጎ ምንፍቅናውን የዘራበት መፅሔተ ነው እነ አቶ በጋሻው ደሳለኝ ፤ አቶ ትዝታው ፤ ያሬድ አደመ፤አሰግድ ሣህሉን የምንፍቅና ስራቸውን የሚሰሩት ከግብር ከሚመስላቸው ከእነደዚህ አይነቱ ሰው ጋር ነው.........

እዚህ ላይ ግን ሳናነሳ የማናልፈው የምእራብ ሀረርጌን ሀገረ ስብከት ነው ምክንያቱም ከሰለጠኑት 17 ሰልጣኞች ውስጥ 13ቱ የምእራብ ሀረርጌ የደብር አለቆች ቄሶች እና ዲያቆናት ሲሆኑ እስካሁን ምን አለማለቱ እንደውም ምልመላ እንዲሰሩ እድል መስጠቱ ምእመናንን አሳዝኖል እንደውም አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች እንዳሉት ከሆነ ሀላፊዎች ቢኖሩበት እንጂ… በማለት ተናገረዋል ይህ በእንዲህ እንዳለ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ለማጠናከር ያስችላል ተብሎ የታሰበ የስልጠና ፕሮግራም እንዳሳወቁ መረጃ ተገኘ፡፡ በቀጣይ የጥቅምት ወር ከሀረር መካነ ስላሴ ሰ/ት/ቤት፣ ሐረር ጤና ሳይንስ ግቢ ጉባኤ፣ ከድሬዳዋ ቅ/ገብርኤል ሰ/ት/ቤት፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ፣ ከሌሎችም አጥቢያዎች ለተውጣጡ አዳዲስ እና ነባር የተሐድሶ ሰራዊት አባላት ስልጠና ለመስጠት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተረጋግጦል፡፡ የአባላት ምልመላ ስራውም አሁን ሰልጥነው በመጡት እየተከናወነ መሆኑ ከታማኝ ምንጮች ለመረዳት ትችሏል፡፡


Posted  by ገብር ኄር
በሸዊት ገብረኪዳን shewitgbrkdn@gmail.com

‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን !!!››

1 comment: