Thursday, September 1, 2011

ሦስቱ መምህራን ፍርድ ቤት ቀረቡ


  • በጋሻው ደሳለኝ ስሜን በማጥፋት ከሰው ልቡና እንድወጣ አድርገውኛል በማለት አቤቱታ ያቀረበባቸው እነ መምህር ዘመንድኩን በቀለ ፍርድ ቤት ቀረቡ
  • የአቡነ ጳውሎስ ደብዳቤ ማስረጃ ሆኖ ቀርቧል
  • ለአቶ በጋሻው ‹‹አደባባይ ከመውጣት ተወግዶ ተቀምጦ እንዲማርና ለፈጸመው ስሕተቱ ንስሐ እንዲገባ መክረዋል››
  • እነ በጋሻው የተሐድሶ መናፍቅነት አቀንቃኝ በሆነው‹‹ አሸናፊ ቦሻ ›› ላይ ተስፋቸውን ጥለዋል
  • በጋሻውና ትዝታው ‹‹የተከሳሾቹ ጓደኞች በመኪና ሊገጩን ነበረ›› በማለት ጉዳዩን ለያዘው ዐቃቤ ሕግ መናገራቸው ተሰምቷል
  • / ዘመድኩን በቀለም በቅርቡ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄን አስመልክቶ በተለያዩ መጽሔቶች ላይ በሰጣቸው ቃለ ምልልሶቹ ነው የተከሰሰው(ይህን ቃለ ምልልስ አንድ አድርገን ላይ ከሳምንት በፊት ፖስት ተደርጓል)
የተከሰሱበት መፃህፍቶቻቸው
በሜቲ ኤጀታ (memettiej1@gmail.com)
ዲ.ን ደስታ ጌታሁን  የሰባኪው ሕጸጽ”  ፤ መ/ር ሣህሉ አድማሱ  በጋሻው ኦርቶዶክሳዊ ነውን?”  የተሰኙ መጻሕፍትን በመጻፋቸው እንዲሁም መ/ር ዘመድኩን በቀለ ከማራኪ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ስሜ ጠፋቷል በማለት በጋሻው ደሳለኝ ባቀረበው አቤቱታ መሠረት በተጣራው የምርመራ መዝገብ በስም ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱት ሦስቱ መምህራን ትላንት ነሐሴ 25 ቀን 2003 ዓ.ም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ወንጀል ችሎት ቀረቡ፡፡

ከተከሰሱት መምህራን መካከል የአንዱም የመኖሪያ አድራሻ በቦሌ ክፍለ ከተማ ያልሆነ ቢሆንም ከፍትሕ ሚኒስቴር የክርክር ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ጽ/ቤት በተለለፈ ትዕዛዝ መሠረት መዝገቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሊጣራ እንደቻለ እንደተነገራቸው ተከሳሾቹ ተናግረዋል፡፡
ሦስቱ መምህራን በተለያየ መዝገብ የተከሰሱ ሲሆን በዕለቱ ደኛው ክሱን ካነበበ በኋላ ‹‹ ጉዳዩ ስላልገባኝ ›› በማለት ዐቃቤ ሕጉ መብራሪያ እንዲሠጥ ጠይቀዋል፡፡
በጋሻው ፓትርያርኩ በቁጥር ል/ጽ/592/1639/03 በቀን 25/11/2003 ዓ.ም  ተሐድሶ ላይ የሚካሄደው እንቅስቃሴ ክትትል እንዲደረግበት በማለት የጻፉትን ደብዳቤ በማስረጃነት አቅርቧል፡፡የፓትርያርኩ ደብዳቤ ተሐድሶ የለም የሚል ይዘት የለውም፡፡ይህም ቅዱስነታቸው ከማኅበረ ቅድሳን ሥራ አመራርና አስፈጻሚ ጉባኤያት ተወካዮች ጋር ነሐሴ 15 ቀን 2003 ዓ.ም ስለ ማኅበሩ አገልግሎትና በተለይም የተሐድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴ  ውይይት ባደረጉበት ወቅት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግብረ ተሐድሶ በመረጃ ተደግፎ ከቀረበላቸው  በኋላ “ይህ ሁሉ የንብ ሠራዊት እያለ ወረራው ሲካሔድ የት ነበራችሁ?” ከማለታቸው ጋር የሚገናዝብ ይሆናል፡፡



ሦስቱም ተከሳሾች በበጋሻው ደሳለኝ የቀረበባቸውን ክስ እንደማይቃወሙት፣ ነገር ግን የስም ማጥፋት ድርጊት ፈጽመናል ብለው እንደማያማኑ ለችሎቱ ተናግረዋል፡፡ ከእነርሱም መካከል አንደኛ ተከሳሽ ዲያቆን ደስታ ጌታሁን ከከሳሽ ጋራ ያላቸው ልዩነት ሃይማኖታዊ በመሆኑ ክሱ በፍትሕ መንፈሳዊ መሠረት ይታይ ዘንድ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መንፈሳዊ /ቤት እንዲመራላቸው መጠየቃቸው ተገልጧል፡፡



ተከሳሾቹ የተከሰሱበት ጉዳይ በጽሑፍ እንዳልደረሳቸው ለችሎቱ በማስረዳታቸው ዐቃቤ ሕግ የክሳቸውን ጽሕፈት ለሁሉም ተከሳሾች እንዲሰጥ ታዝዟል፡፡ 


በመ//// የገዳማት መምሪያ ጸሐፊ የሆኑት ዲያቆን ደስታ ጌታሁን ‹‹የሰባኪው ሕጸጽ›› / ሣህሉ አሰግድ ‹‹በጋሻው ኦርቶዶክሳዊ ነውን?›› በሚሉ ርእሶች ባሳተሟቸው መጻሕፍት የበጋሻው ደሳለኝን ማንነትና በስሕተት የተሞሉ ስብከቶች ነቅሰዋል፤ አደባባይ ከመውጣት ተወግዶ ተቀምጦ እንዲማርና ለፈጸመው ስሕተቱ ንስሐ እንዲገባ መክረዋል ‹‹ራሱ ሕጋዊ ሳይሆን ስሜን የሚያጠፉትን በሕግ እጠይቃለሁ፤ ሓላፊነቱን የሚወስድ ሰው አጣሁ›› በማለት ለሚናገረውም ‹‹ፈረሱም ያው! ሜዳውም ያው›› ብለውታል - በመጽሐፎቻቸው፡፡ / ዘመድኩን በቀለም በቅርቡ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄን አስመልክቶ በተለያዩ መጽሔቶች ላይ በሰጣቸው ቃለ ምልልሶቹ ነው የተከሰሰው፡፡ የበጋሻው ክስ ጠቅላላ ይዘትም ‹‹ሕገ ወጥ ሰባኪ በመባሉ ከኅብረተሰቡ እና ከቤተሰቡ የመለየትና የመገለል በደል እንደተፈጸመበት›› የሚያመለክት ነው ተብሏል፡፡ 


/ቤቶች እስከ መጪው ዓመት ጥቅምት ወር ድረስ በሥራ ላይ የማይሆኑበት ሁኔታ በመኖሩ ተከሳሾቹን በእስር ለማሰንበት ቋምጠው በችሎቱ ቅጽር የተገኙ የሚመስሉት ከሳሽ እና ግብረ አበሮቹ (አሰግድ ሣህሉ፣ ትዝታው ሳሙኤል እና የጥቅም አጋራቸው ነው የሚባለው ኤፍሬም ኤርሚያስ) ተከሳሾች የዋስ መብታቸው ተጠብቆላቸው በመውጣቸው ከፍተኛ መከፋት አድሮባቸው ታይተዋል፡፡ በአንጻሩ እንደ ዐቃቤ ሕግ አነጋገር ተከሳሾች የተጠየቁትንጠበቅ ያለ ዋስትና›› ለማቅረብ በችሎቱ እና ከችሎቱ ውጭ በፀረ-ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ እንቅስቃሴው ዙሪያ ግንባር የፈጠሩ አካላት እና አባላት ከፍተኛ መረባረብ እና መደጋገፍ አሳይተዋል፡፡
የችሎት ውሎው ከተጠናቀቀ በኋላ እነ በጋሻው የተሐድሶ መናፍቅነት አቀንቃኝ ወደ ሆነው እና ባለው አናሳ የትምህርት ዝግጅት ከፍትሕ ሚኒስቴር ዐቃቤ ሕግነት ወደ ተቀነሰው  ‹‹ አሸናፊ ቦሻ ›› ቢሮ አምርተዋል፡፡ ‹‹ አሸናፊ ቦሻ ›› ወደ መደበኛ የሥራ ቦታው የሚመጡ ሴቶችን በመተናኮል የሚታወቅ ነው፡፡ በ2001 ዓ.ም የተዘዋዋሪ ሰባኪነት ፈቃድ ይሰጠኝ በማለት ለስብከተ ወንጌል መምሪያ ጥያቄ አቅርቦ ፈቃድ እንደተከለከለ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ እንዳች ነገር የመፈጸም ስልጣን እና አቅም ሳይኖረው እንደ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ለመታየት ያደረገው ጥረት በገብር ኄራውያን ትዝብት ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል፡፡ በዚሁ ወቅት በጋሻውና ትዝታው ‹‹የተከሳሾቹ ጓደኞች በመኪና ሊገጩን ነበረ›› በማለት ጉዳዩን ለያዘው ዐቃቤ ሕግ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከመጋረጃ በስተጀርባ ሁሉን የምታሠናዳው ‹‹ማትርያርክ›› እጅጋየሁ በየነ እነ ዲ/ን ደስታ ጌታሁንን ሥራ ገበታቸው ላይ አልተገኙም በማለት እና ሌሎች ሰበቦችን በመቃረም ጫና ለመፍጠር እና ከሥራ ለማሰናበት በጠቅላይ ቤተክህነት ግብ ሲሯሯጡ መዋላቸውን የቤተ ክህነት ምንጮች ገልጸዋል፡፡


በመጨረሻም ዳኛው ዐቃቤ ሕግ ክሱን ያስረዱልኛል የሚላቸውን ማስረጃዎች እንዲያቀርብ፣ ሦስቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው የብር 5000 ዋስ ጠርተው እንዲወጡና የሕግ ባለሙያ አማክረው ከጠበቃ ጋራ እንዲቀርቡ ለጳጉሜን ሦስት ቀን 2003 . ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡
Posted by:- ገብር ኄር and Dejeselam

No comments:

Post a Comment