Saturday, December 8, 2012

የምሥራቅ ጎጃም ምእመናን በብፁዕ አቡነ ማርቆስ ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ በደል ማዘናቸውንና መማረራቸውን ገለጹ



  •  ሊቀ ጳጳሱ ስድሰት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በ38 ሰዎች ላይ ሹም ሽርና እገዳ አካሄደዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት ከወንድም ልጅ ጀምሮ እስከ ወዳጅና የሀገር ሰው የሚዘልቅ የዝምድናና የጎጠኝነት ትስስር ያላቸው መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡
  •   ብፁዕነታቸው በትዕቢትና በንቀት በብዙ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ የተናገሯቸው ንግግሮች ምእመናንን እጅግ አሳዝኖአል።
  • መልክዓ መልክኡ ፤ማኅሌቱ፣ተዓምረ ማርያምም ቢሆንኮ ደብተራ የደረሰው ነው”  አቡነ ማርቆስ
  •  የሀገረ ስበከቱ ካህናትን ውኃ ግድግዳ ላይ መርጨት ብቻ የለመዱ ወንጌል ያልገባቸው ሲሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶችንና ማኅበረ ቅዱሳንን ደግሞ “ወንበዴዎች፣ሌባዎች፣አሸባሪዎች” ብለው መሳደባቸውን የደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡
  •  “እኛ የምንሰብከው ዛሬ ጠፍቶ የተገኘውን መስቀል ሳይሆን መስቀሉ ላይ የተሰቀለውን ክርስቶስን ነው” ,...... አቡነ ማርቆስ በዘንድሮ የመስቀል በዓል ላይ የተናገሩት።


ክፍል አንድ

(አንድ አድገን ኅዳር 29/2005 ዓ.ም ) ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በ1997 ዓ.ም ከ4 ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በቅዱስ ሲኖዶስ የጵጵስና ማዕረግ የተሰጣቸው አባት ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው ለ 17 ዓመታት ያህል በውጭ ሀገር የቆዩ ሲሆን ወደ ሀገር ቤት-ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ በመጀመሪያ ከ1997 ዓ.ም2001 ዓ.ም የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፤ ከ2001 ዓ.ም- 2003 ዓ.ም የአዊና መተክል ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው ከቆዩ በኋላ የጥቅምት 2004 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስን ስብሰባ ተከትሎ በተወሰነው ውሳኔ መሰረት ተወልደው ባደጉበት፣ በተማሩበትና በቅኔ መምህርነት ባስተማሩበት የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው በማገልገል ይገኛሉ፡፡


ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሊቀጳጳስ ሲሆኑ ወደ ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት እንደመጡ ሕዝበ ክርስቲያኑ በመልካም አቀባበል የተቀበላቸው ሲሆን በተለይም ከወጣቱ የቤተክርስቲያኒቱ ክፍል ጋር ውጭ ሀገር ለብዙ ዓመታት መቆየታቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት የሰመረ አገልግሎት ይኖራቸዋል የሚል ግምት የነበረ ሲሆን ብፁዕነታቸውም ይህን ግምት  እውን የሚያደርጉ ብዙ እቅዶችና ሃሳቦች እንዳሏቸው በብዙ መድረኮች ቢሰነዝሩም ገና ሦስት ወራት ሳይቆዩ ብዙ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችንና ትውፊቶችን በቸልተኝነትና በድፍረት ማቃለል መጀመራቸውና በሀገረ ስብከቱ ላይ ቃለ አዋዲውንና ተዋረዱን ያልጠበቁ ፍትሐዊ ያልሆኑ መጠነ ሰፊ ሹም ሽሮችንና እገዳ ማካሄድ  መጀመራቸው ጉዟቸውን ከጅምሩ እንከን እንዲገጥመው አድርጎባቸዋል፡፡

በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት እና በደብረማርቆስ ወረዳ ቤተክህነት ብቻ (በሀገረ ስብከቱ ያሉ 18 ወረዳ ቤተ ክህነቶችን ሳይጨምር) በ34 ሰዎች ላይ ሹም ሽርና እገዳ ያካሄዱ ሲሆን የብዙዎቹ በሥጋ ዝምድና፤ በቀድሞ ወዳጅነት፣ በጎጥና በአድር ባይነት የተደረገ ሲሆን የብዙዎቹ ሹም ሽርና እገዳም ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ በእርሳቸው ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሠረተ መሆኑን የደብረ ማርቆስ ምእመናን ያቀረቡባቸው የሰነድ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡ በዚህ አካሄዳቸው የተነሳም ለአንድ መንፈሳዊ አባት ሊሰጡ ቀርቶ ሊታሰቡ በፍጹም የማይገባቸውን በጽሑፍ ለመጻፍም የሚከብዱ የአፍሪካና ሌሎች ሀገሮች አምባገነን መሪዎች ስሞች እየተሰጧቸው መሆኑን የደረሰን መረጃ ይገልጻል፡፡ 

ብፁዕነታቸው በምእመኑ ዘንድ በጥብቅ የሚከበሩትንና ያልተለመዱትን የእምነቱም መጠበቂያ የሆኑትን ሃይማኖታዊ ጉዳዮችና ትውፊቶች በቸልተኝነት በድፍረት በተግባርና በንግግር መተላላፋቸው መፈጸማቸው ምእመናንን በእጅጉ ማሳዘናቸውን በተደጋጋሚ ለብጹዕነታቸው በምሬት መግለጣቸው ምንጮቻችን ገልጠዋል፡፡ ካህናት በንስሐ ልጆቻቸው ቤት በመሄድ የሚረጩትን ጠበል “ውኃ ” ካሉ በኋላ “ውኃ ግድግዳ ላይ ከመርጨት በቀር ወንጌል የማያውቁ” ብለው ካህናትን ሲሰድቧቸው ካህናቱም “ብዙ እናውቃለን ብንናገር ግን እናልቃለን” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ሊቀ ጳጳሱ በቤተክርስቲያኒቱ /ቅዱስ ሲኖዶስ/ እውቅናና ሕግ ወጥቶላቸው የተቋቋሙትን ሰ/ት/ቤቶችን በንግስ በዓል ላይ ሌባዎች አሸባሪዎች” በማለት የሰ/ት/ቤት መለያ-ዩኒፎርም የለበሱትን በምእምኑ ፊት ሲያሸማቅቁ በሀገረ ስብከቱ ያሉ ሁሉንም ወረዳ ቤተ ክህነቶችን  ሰብስበው ማኅበረ ቅዱሳንን ወንበዴዎች በማለት መሳደባቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

በተጨማሪም እርሳቸው ወደ ሀገረ ስብከቱ ከመጡ ከአንድ ወር በኋላ ጀምሮ “እኔ ልማታዊ ነኝ ጊዜውን በአግባቡ መጠቀም አለብን” በሚል ተገቢ ባልሆነ ምክንያት የሃይማኖተ አበው መጽሐፍ እንዳይነበብ መከልከሉ፤ መቅድመ ተዓምረ ማርያምም መቅረቱና ካላንደር ነው ማለታቸው፤ የቅዳሴው ጸሎት እንደተፈጸመ የእርሳቸው የቅዳሴ ጠበሉን በጆግ በጅምላ ምእመናንን መርጨት መደጋገም፤ የታቦተሕጉን መንበር በመግለጥና መጋረጃውን በመክፈት ቤተመቅደሱን ቀና ብሎ ለማየት በሚሰቀጥጥ ሁኔታ እንዲቀደስ ማስገደድ፤ በልዩ ልዩ የወረዳ አድባራትና ገዳማት ላይ “መልክዓ መልክኡ ፤ማኅሌቱ፣ተዓምረ ማርያምም ቢሆንኮ ደብተራ የደረሰው ነው” እያሉ በምእመኑ ዘንድ በጥብቅ የሚከበሩትን ሃይማኖታዊ ጉዳዮችና የሃይማኖቱ በጎ ትውፊቶችና እሴቶችን ማቃለላቸውና እንዲተው ማስገደዳቸው በምእመኑ ዘንድ ከፍተኛ ሀዘንና ቁጣን ቀስቅሷል፤ ጉዳዩም ስህተት ሳይሆን መሠረታዊ የማንሸራተት ስትራቴጂ መሆኑን በተደጋጋሚ እየተገለጸ ይገኛል፡፡ 

 ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ለቅዱሳን ያላቸውን አመለካከት “ቅዱሳንን የቀደሰ ክርስቶስ ነው ስለሆነም ወንጌል ክርስቶስ ነው እንጂ መነኩሴ አይደለም፤ አቡሀይ እሙሀይ አትበሉ ክርስቶስን ስበኩ” በማለት በግልጽ በሕዝብ መሀል ተናግረዋል፡፡ በ2004 ዓ.ም ጾመ እግዚእ/ዐብይ ጾም/ ወቅት በደብረ ማርቆስ ጽርሐ ጽዮን አብማ ማርያም ቤተክርስቲያን በተደረገ ጉባኤ ላይ ከበሮ እያስመቱ ያስጨበጨቡ ሲሆን፤ በተደጋጋሚ ለቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ያላቸው ዝቅተኛ ግምት እህቶቻችንና እናቶቻችን በወር አበባ ወቅት እንዲገቡ መፍቀዳቸውና ማስገደዳቸው፤ ጸሎተ ቅዳሴውን አቋርጦ መውጣት እንጂ መግባት እንደሚቻል በተደጋጋሚ መናገራቸው የብፁዕነታቸው አካሄድ አባታዊ ምክርና ማስተካከያ ሳይሆን መሠረታዊ የሃይማኖት ችግር መሆኑን ምእመናን እንደተረዱ ገልጸዋል፡፡

ፁዕነታቸው በዞኑ ዋና  ከተማ  ደብረማርቆስ ከሚገኙ 9 አድባራትና ገዳማት በስድስት ወራት የ8ቱን አስተዳዳሪዎች ለውጠዋቸዋል፡፡ከእነዚህም ውስጥ የ4ቱን ለ3ኛ ጊዜ ቀያይረዋቸዋል፡፡ የአንዱ ቤተክርስቲያንም ቢሆኑ ሊቀ ጳጳሱ ሲጠሯቸው አቤት ሲልኳቸው ወዴት የሚሉ አድር ባይ በመሆናቸው ብቻ በኃላፊነታወ መሰንበታቸው ይነገራል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ ምእመናንም ከፁዕነታቸው ጋር ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የመንግሥት አካላትንም በመጨመር የሞከሩ ቢሆንም “እናንተ አታውቁኝ እኔ አላውቃችሁ” ቢሉም “አባታችን እርስዎ ባያውቁንም እኛ እናውቅዎታለን ያወያዩን”  ብለው ከከተማው “ከእናንተ ጋር እነጋገር ዘንድ አባትነቴም አይፈቅድልኝ ከፈለጋችሁ ጥያቄያችሁን ለሰበካ ጉባኤያችሁ አቅርቡ እንጂ ከማንም ውሪ-(ጉብል፣አላዋቂ ልጅ እንደማለት) ጋር ምን በወጣኝ፣ ማንም  ጳጳስ የማያደርገውን ያቀረብኳችሁም ስለገባኝ እንጂ የእኔ ድርሻ አይደለም” በማለት በአባትነታቸውና በቤተክርስቲያን እጂጉን አዝነው መመለሳቸውን የደረሰን መረጃ ይገልጻል፡፡

የዞኑ የመንግስት ከፍተኛ የአስተዳደር አካላትም ችግሩን ለመፍታት ከመጓጓት የተነሳ ከሚገባው በላይ በመንቀሳቀስ “ብፁዕነትዎ የልጆችዎን ጥያቄና አስተያየት ይስሟቸው” በማለት ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከነጋዴ ባለሀብቶችና ከሰ/ት/ቤቶች የተወከሉትን  እስከ ማወያየት የደረሰ ብርቱ ጥረት ቢያደርጉም እንዳልተሳካ የደረሰን መረጃ ያብራራል፡፡ 

የሀገረ ስብከቱ ምእመናንንም  ቅዱስ ሲኖዶስ አስፈላጊውን መፍትሔ እንዲፈልግላቸው የቤተክርስቲያኒቱን አማኞችም በጸሎት እንዲያስቧቸው ጠይቀዋል፡፡

በቀጣይ በተለይ ብጹዕነታቸው በግብረ ሲሞን ስላከማቹት ሀብትና ስለፈጸሙት አስተዳደራዊ በደል እንዲሁም በሃይማኖታቸው ርቱዓን የሆኑ ምእመናን የያዙባቸውን የድምጽ ወምስልና የሰነድ ማሰረጃዎች የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን!!!



ለጽሁፎቻችን ሁሉ የድምጽ ፤ የምስል ፤ የሰነድ ማስረጃዎች በእጃችን ይገኛሉ



ሌሎች መረጃዎችን ይጠብቁን..
 
 
ቸር ወሬ ያሰማን!
የቅዱሳን አምላክ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን


16 comments:

  1. Ye'Aba Paulos fire yihew engidih qen eyetebeqe yitayal. Eski Amlak yitareqen.

    ReplyDelete
  2. ayee Abune markos eko lik abat nachew yetim hedachehu betkesu manim ayesmachehum enanete Abatochen asado lematifat minew ende saol honachehuu ahun lemin mk tesedebin gudachen lemin weta belachehu meemenan yaletenagerutin mitaweru weregnoch hula

    ReplyDelete
  3. I hope z holy Synod will remove him soon.

    ReplyDelete
  4. እነ በላይ ዘለቀን የመሳሰሉ ጀግኖች የነበሩባት ጎጃም ለእንደነዚህ ዓይነት በጥቁር ቀሚስ ለተሸፈኑ ወንበዴወች መሸነፏ አንገትን ያስደፋል. ምነው አንድ ወንድ ጠፋ! ያን የውንብድና ካባውን አስወልቆ የሚያንበረክክ አንድ ምእመን እንዴት ይታጣል!? እረ አንድ ሰው!

    ReplyDelete
  5. ANDAIRGEN,IS IT TRUE? IF IT IS TRUE GOD HAS PLANNED
    TO SHOW US A MIRACLE.WE SHOULD NOT WORRY ABOUT ALL
    THESE MESSES.DEVIL CAN DO MANY EVILS IN THIS
    COUNTRY. WE WILL SEE A LOT .BUT WE SHOULD BE ALERT
    AND KEEP ON OUR EYES ON OUR CHURCH.MANY INDIVIDUALS
    ARE DOING THEIR BEST TO WEAKEN US BEING JIHUDA INSIDE AND PHARISES OUTSIDE.TIME HEALS. GOD BLESS
    US ALL.MAY GOD HELP US ALL TO CLEAN OUR HEARTS.

    ReplyDelete
  6. Ebakachu and adirgen yihnin guday chel yemibal silalihone lemimeleketew kifil maletim betecristiyanachin higina denb alat lemimeleketew kifil asasibulin egni abat wede alasfelagi neger eyegebu newina and libalu yigebal tamire mariyaminina lelochun metsiaft bemenebebachew tetekimenal enji altegodanim. abetu yekidusan amlak betecristiyanachinin kewisitina kewich telat ante tebikilin. CHER WERE YASEMAN ENATINA LIJU BETECRISTIYANACHININ YITEBIKULIN.

    ReplyDelete
  7. ABBA MARKOES YE YENTA TAYE TEMARIE YENYENTA HIENOK LIJ YEGEDAME ....AYY KIBAATT

    ReplyDelete
  8. ENIE WIST AWAKIE NEGN KIBATUIN ABIZITEWAL ABATACHIN

    ReplyDelete
  9. endi aynetun new atbeken lenekawem yemegeban begeltse mena
    ger ena selehaymanotachen memesker yemegeban

    ReplyDelete
  10. በመጀመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ "የተመረጡትን እንኳን እስኪያስቱ ድረስ......" ማቴ 24᎙24 ይላልና የሁላችንንም ጅማሬያችንን ሳይሆን ፍጻሜያችንን ያሳምርልን የተጠሩት ብዙዎች "የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው" እንደተባለ በቤቱ ፀንተን እንድንኖር አምላካችን ይርዳን በጣም ልንጠነቀቅ የሚገባን ዘመን ላይ ነው ያለነው በእውነት እኛ እድለኞች ነን የተዋህዶ ልጆች በመሆናችን ክርስትና ብዙ ተከፍሎባታልና የተማርነውን ልንመሰክር ያስፈልጋል በዚያም አካባቢ ያላቹም አባቶችና ምዕመናን በግልጽ ልክ እንዳልሆኑ ልትነግሯቸው ይገባል። እዚህ ጋር አንድ ነገር አስታወስኩ ታላቁ አባታችን ተፍጻሚተ ስማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ አርዮስ የክህደት ትምህርትን እያስተማረ መሆኑን ሲሰማ አስጠርቶ እንዲህ ብሎት ነበር "እንዲህ ያለ ትምህርት ከኔ አልተማርከው አስበኧው እንደሆነ አትናገረው ተናግረኧው እንደሆነ አትድገመው" ብሎት ነበር እኛም ከሀይማኖት ትምህርት ውጪ የክህደት ትምህርትን የሚያስተምሩትን ቢቻል ማስተካከል ባይቻል ግን ሌሎችንም ይዘው እስከመጥፋት ይደርሳሉና እናስብበት እላለው። እሳቸውንም ይዟቸው ሊጠፋ ካለ የዲያቢሎስ ወጥመድ መድኃኔአለም ይታደጋቸው ለተናገሩትም ነገር ይቅር ይበላቸው።"ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።"

    ReplyDelete
  11. በመጀመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ "የተመረጡትን እንኳን እስኪያስቱ ድረስ......" ማቴ 24᎙24 ይላልና የሁላችንንም ጅማሬያችንን ሳይሆን ፍጻሜያችንን ያሳምርልን የተጠሩት ብዙዎች "የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው" እንደተባለ በቤቱ ፀንተን እንድንኖር አምላካችን ይርዳን በጣም ልንጠነቀቅ የሚገባን ዘመን ላይ ነው ያለነው በእውነት እኛ እድለኞች ነን የተዋህዶ ልጆች በመሆናችን ክርስትና ብዙ ተከፍሎባታልና የተማርነውን ልንመሰክር ያስፈልጋል በዚያም አካባቢ ያላቹም አባቶችና ምዕመናን በግልጽ ልክ እንዳልሆኑ ልትነግሯቸው ይገባል። እዚህ ጋር አንድ ነገር አስታወስኩ ታላቁ አባታችን ተፍጻሚተ ስማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ አርዮስ የክህደት ትምህርትን እያስተማረ መሆኑን ሲሰማ አስጠርቶ እንዲህ ብሎት ነበር "እንዲህ ያለ ትምህርት ከኔ አልተማርከው አስበኧው እንደሆነ አትናገረው ተናግረኧው እንደሆነ አትድገመው" ብሎት ነበር እኛም ከሀይማኖት ትምህርት ውጪ የክህደት ትምህርትን የሚያስተምሩትን ቢቻል ማስተካከል ባይቻል ግን ሌሎችንም ይዘው እስከመጥፋት ይደርሳሉና እናስብበት እላለው። እሳቸውንም ይዟቸው ሊጠፋ ካለ የዲያቢሎስ ወጥመድ መድኃኔአለም ይታደጋቸው ለተናገሩትም ነገር ይቅር ይበላቸው።"ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።"

    ReplyDelete
  12. በመጀመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ "የተመረጡትን እንኳን እስኪያስቱ ድረስ......" ማቴ 24᎙24 ይላልና የሁላችንንም ጅማሬያችንን ሳይሆን ፍጻሜያችንን ያሳምርልን የተጠሩት ብዙዎች "የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው" እንደተባለ በቤቱ ፀንተን እንድንኖር አምላካችን ይርዳን በጣም ልንጠነቀቅ የሚገባን ዘመን ላይ ነው ያለነው በእውነት እኛ እድለኞች ነን የተዋህዶ ልጆች በመሆናችን ክርስትና ብዙ ተከፍሎባታልና የተማርነውን ልንመሰክር ያስፈልጋል በዚያም አካባቢ ያላቹም አባቶችና ምዕመናን በግልጽ ልክ እንዳልሆኑ ልትነግሯቸው ይገባል። እዚህ ጋር አንድ ነገር አስታወስኩ ታላቁ አባታችን ተፍጻሚተ ስማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ አርዮስ የክህደት ትምህርትን እያስተማረ መሆኑን ሲሰማ አስጠርቶ እንዲህ ብሎት ነበር "እንዲህ ያለ ትምህርት ከኔ አልተማርከው አስበኧው እንደሆነ አትናገረው ተናግረኧው እንደሆነ አትድገመው" ብሎት ነበር እኛም ከሀይማኖት ትምህርት ውጪ የክህደት ትምህርትን የሚያስተምሩትን ቢቻል ማስተካከል ባይቻል ግን ሌሎችንም ይዘው እስከመጥፋት ይደርሳሉና እናስብበት እላለው። እሳቸውንም ይዟቸው ሊጠፋ ካለ የዲያቢሎስ ወጥመድ መድኃኔአለም ይታደጋቸው ለተናገሩትም ነገር ይቅር ይበላቸው።"ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።"

    ReplyDelete
  13. I am sure. You will never post it. But let me ask you these: Have you ever asked abune Markos about it? Do you have enough knowledge about the teaching of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church? Could you please tell us the mistake that Abune Markos has done? Do you think that he is anti- orthodox Tewahdo? I am sorry to say this. You know nothing about the teaching of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church. Believe it or not, His grace Abune Markos is one of our beloved fathers; he is a true preacher of the gospel. We all preachers of the Church agree with his teaching. So, please stop acting like this.

    ReplyDelete
  14. There is bishop so knowlegable so spirtual a true shepherd as Abune Markos you guys are wrong. Because i've been his graces student for four years and i know enough to witness he is a holy and man of God!

    ReplyDelete
  15. The Archbishop talks sense with regard to the basis of some of our practices: they are not biblical. But his alleged nepotism and insulting other members of the church is reprehensible. Legesse.

    ReplyDelete