Thursday, March 8, 2012

የቦረና ጉጂና ሊበን ዞኖች ሃገረ ስብከት የፍርድ ቤት ውሎ

  • (አሁን የደረሰን ዜና)ታስረው ከነበሩት ክርስቲያኖች መካከል ፖሊስ 33ቱ ላይ ክስ መስርቶ የሰው ማስረጃ ለሶስት ቀናት ሲያሰማ ከዋለ በኋላ ዛሬ(29/06/2004) እኩለ ቀን ላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔዎችን ሰጥቷል፡፡ በዚሁ መሰረት ክስ ከተመሰረተባቸው ውስጥ 24ቱ  ተከላከሉ የተባሉ ሲሆን 9ኙ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ተለቀዋል፡፡ የቀሩት 16 ሰዎቸ በምን ሁኔታ ሊለቀቁ እንደቻሉ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም፡፡
  • ምናልባት የተወሰኑት ለሌላ ተግባር ሆን ተብሎ እኒዲቀላቀሉ ተደርገው ስራቸውን በማጠናቀቃቸው በውስጥ መስመር የተለቀቁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ምንጮች ከስፍራው ጠቁመዋል፡፡ 
  • ተከላከሉ የተባሉት 23ቱ ለመጋቢት 19 2004ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞላቸዋል፡፡
  •  በተያያዘ ዜና በቦታው የነበሩ አንድ የፖሊስ መኮንንና የአሰተዳደር ባለስልጣን ለክርስቲኖቹ ጥብቅና የቆሙት ባለሙያ ከየት እንደ መጡና ማን እንደላካቸው እንዲጠና ሲወያዩ መደመጣቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ይህ ክትትል ወዴት ሊያመራ እንደሚችል ወደፊት የምናየው ይሆናል፡፡ ጌታ እግዚአብሔር የዚያ ሰው ይበለን፡፡

(አንድ አድርገን የካቲት 29 ፤ 2004ዓ.ም )፡- የቦረና ጉጂና ሊበን ዞኖች ሃገረ ስብከት የክብረመንግስት ከተማ  በተነሳው ብጥብጥ በጊዜው አርባ ያህል ክርስትያኖች መታሰራቸውን መዘገባችን ይታወቃል ፤ ፖሊስም ንጹሀን ታሳሪዎችን ፍርድ ቤት ማቅረቡንና ፍርድ ቤቱን የ11 ቀን የማጣሪያ ጊዜ ጠይቆ ወደ እስር ቤት መመለሳቸውን ጠቁመናል ፤ የማበረ ቅዱሳን አባል ናችሁ የሚል ታግ የተለጠፈባቸው ሆን ተብሎ የተሰራ ሴራ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ ፖሊሶችም ህዝብ የጣለባቸውን አደራ ወደ ኋላ በመተው ግልፅ አድልዎ እየፈጸሙ መሆኑን ለማወቅ ችለናል:: ከዚህ ጋር በተያያዘ የክልሉ የመንግስት ባለስልጣናት ይህን ጉዳይ ማን ለአንድ አድርገን ወሬ እንዳቀበለ አውጫጭኝ ሲያካሂዱ ከርመዋል፡፡


አቡነ ፊሊጶስ አዲስ የቤተክርስቲያን መዋቅር ሰርተዋል ‹‹የሃገረ ስብከቱ ቆሞስ” የሚባል አስተዳደራዊ መዋቅር በመፍጠር አንድ አባ  ሃይለጊዮርጊስ የሚባሉ ቆሞስ (ሰውዬው ግን ኤጲስ ቆጶስ ነኝ ይላሉ) የሚባሉ አንድ አይና ሰው መድበው ላኩ፡፡ ለሃገረ ስብከቱ ጳጳስ ይመደብልን ብሎ ህዝቡ በመጠየቁ፡፡ ህዝቡም ግለሰቡን ተቀብሎ እንዲሀ የሚባል መዋቅር ከየት መጣ ብሎ ጠየቀ ፤  ከብዙ ውይይት በሁዋላም  ‹‹እኔም ተሳስቻለሁ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሄጄ ሪፖርት አደርጋለሁ›› ካሉ በኋላ ክብረመንግስት ሄደው ከተሾመ ሃይለማርያም ጋር ነገሮችን በማጦዝ ግፍ ለመስራትን ነገረሮቸችነን ሸረቡ ፤ በተወሰነ መልኩም ተሳካላቸው፡፡

እንግዲህ በእመቤታችን በዓለ ንግስ ላይ የተፈጠረውን አሳዛኝ ድራማ  ከኋላ  ሆነው የመሩት እኚህ ግለሰብ ናቸው፡፡ የክስ ሂደቱ ከትናንት በስቲያ 27/06/2004 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ምስክር የመስማቱ ሂደት ዛሬ ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎ ውሉዋል፡፡ የክስ ጭብጡ ‹‹የሰዎችን የእምነት ነጻነት መጋፋትና ተደራጅተው ንግስ እነዳይከናወን ማድረግ›› እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ ፖሊስ 16 ምስክሮች ያስመዘገበ ሲሆን እስከ ትናንትና ድረስ ሰባት ሰዎች መስክረዋል፡፡ በምስክር ማሰማት ሂደት ላይ የሀሰት መስካሪዎች ዳኛው የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎች በወረቀት በመፃፍ ሲቀባበሉ ፖሊስ ሁኔታውን እያየ ዝም ማለቱ በጣም አሳዛኝ ድርጊት ሆኖ አልፏል ፤ ይህ የፍትህ ሂደቱ በአግባቡ እዳይከናወን ፤ ንፁሀን ሰዎች ያለ ስራቸው ወንጀለኛ ለማድረግ የተሸረበ ሴራም ጭምር ነው ፤ በትላንትናው እለት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ ምስክሮች ሲሰሙ አምሽተዋል ፤ የተቀሩት 7 ምስክሮች በጣቢያ አድረው ዛሬ የመመስከር ሂደቱ ተጀምሯል ፤ምስክሮቹ በአብዛኛው “በህግ አምላክ አሉ፤ ኡኡ ብለው ጮሁ” ብለው መመስከራቸው የተሰማ ሲሆን ፤ ሰው በፖሊስ ሲደበደብ እልል እንዲል ተጠብቆ ከሆነ …….. ፡፡

መስካሪዎቹ ከዚህ ቀደም ከተሃድሶ አቀንቃኞች ጋር በጥምረትና በግልጽ ሲሰሩ ቆየተው ዛሬ ተከሳሽ ሆነው ከቀረቡት ክርስቲያኖች ጋር ከፍተኛ ጠብ የነበራቸው ሲሆን እስከ ሃይል ጥቃት ድረስ ደርሰው ክስ ላይ የነበሩ ግለሰቦችና ደብዳቢ ፖሊሶች መሆናቸው ታውቋል ፤ ህጉ ፖሊስ በእሰረኞች ላይ ምንም አይነት ጥቃት እንዲያደርስ አይፈቅድለትም ፤ የፖሊስ ስራ ጸጥታ ማስከበር ፤ የህዝብን ሰላም መጠበቅ ሲሆን የቦረና ጉጂና ሊበን ዞኖች ሃገረ ስብከት የክብረመንግስት ከተማ  ግን ይህን ለመመልከት አልቻልንም፡፡ ህዝቡ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ጥያቄ እንዲያነሳ ህዝብን ከመንግስት ለማጋጨት የአካባቢው ባለስልጣናት ቀን ከሌት እየሰሩ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፡፡ ከከተማው ፖሊስ የተገኘው ሚስጥራዊ መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ አጠቃላይ የታሰሩት ሰዎቸ ብዛት 48 የደረስ ሲሆን ፖሊስ 6ቱን  ለጊዜው ለቅቄአቸዋለሁ ብሏል ፤  27ቱ ላይ ደግሞ ማስረጃ ሰብስቤ ጨርሻለሁ ብሎ ሪፖርት አድርጓል፡፡

እጅግ የሚያሳዝነው ነገር የደብሩ አስተዳዳሪ ይህን ችግር ለመፍጠር የተዘጋጁ ሰዎች መኖራቸውን (እነ ቆሞሱ) ጠቅሰው እኚህ ግለሰብ እንዳይመቱባቸው እንዲደረግ ለከተማው ፖሊስ እና ለቀበሌው የጸጥታ አካል በቅድሚያ አሳውቀው ሳለ ታቦቱን ሊያከብሩ የተዘጋጁት ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም ምእመናን ታፍሰውና ታስረው እያለ ንግስ ከለከላችሁ ብሎ መክሰስ ስላቅ ያስመስለዋል፡፡


እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው ፤ ቤተክርስትያንንም እስከ ደም ጠብታ ድረስ ያልባሌ ሰዎች መፈንጫ እንዳትሆን ዘወትር እሰራለን ፤ ቤተክርስትያ የማትወክላቸው ሰዎችን በአውደ ምህረቱ እንዲቆሙ አንፈቅድላቸውም ፤ ቤተክህነቱ ከላይ መመሪያ ቢያወርድም ከታች ያለው ምዕመን ለመመሪያዎቹ ተፈፃሚነት ሁሉም የበኩሉን የመወጣት አላፊነት አለበት ፤ መንግስት ባለበት ሀገር ፤ በተፃፈ ህግ በምትተዳዳር ሀገር ህጉን ያለአግባብ የሚተረጉሙ ፤ ለህዝብ ሳይሆን በጥቅም ለተቆራኝ ግለሰብ ቅድሚያ የሚሰጡ ሰዎችን እንቃወማለን ፤ 



8 comments:

  1. cher ware yaseman egziabher talaqi negern yadergal

    ReplyDelete
  2. Uhhhh...semonun be Borena Yalu keresitiyanoch yesost ken mihjila bgudayu lay yizew endekoyu yesemahugn sihon..egziabher enkuan tselotachihun semachihu belulign..beabatoch fanta lijoch teweledulish...ililililil....

    ReplyDelete
  3. ይህንን ጉዳይ እንደተለመደው ለሚመለከተው አካል ለማመልከት ወደ አዲስ አበባ ያቀናው ከ6 ወረዳዎች የተውጣጣው ቡድን ማመልከቻውን ለተለያዩ የመንግስት አካላትና የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር (ለጠቅላይ ቤተክህነት) ካስገቡ በሁዋላ ተመልሰዋል፡፡ አመልካቾቹ ካመለከቱባቸው ቢሮዎች መካከል በኦሮሚያ እና በፌደራል ቢሮዎች የይማኖት ጉዳዮች ሰክሬታሪያት፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፡ አቡነ ፊሊጶስ የጠቅላይ ቤተክነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም አቡነ ህዝቅዔል በጠቅላይ ቤተክነት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ ናቸው፡፡
    ከሁሉም የሚያሳዝነው ነገር ከበታቻቸው ተኮልኩለው ያሉት በሙሉ የሚያውቁትን 46 ሰዎች ጉዳይ አቡነ ፊሊጶስ ምንም አለማወቃቸው እና ከአመልካቹ ቡድን መስማታቸው ነው;;;;;;;;
    ማን ያውቃል አቡነ ፊሊጶስም ከተኙበት ነቅተው፡ ማመልከቻው ከደረሳቸው ውስጥም ለእግዚአብሄርና ለእውነት ያደረ ይኖርና የጉጂ ቦረና ብቻ ሳይሆን በየሀገረ ስብከቱ ያለው የተሀድሶአውያን ሴራ መስመር የሚይዝበት ጊዜ ...
    አዶላዎች የከፈላችሁት መስዋዕትነት ዋጋ አለው
    አምላከ ቅዱሳን ኢትዮጵያንና ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅ

    ReplyDelete
  4. It is shameful act to ban Christians from attending church services. Those that put their hands should pay the price.

    ReplyDelete
  5. አምኃኢየሱስMarch 9, 2012 at 12:59 AM

    ለታሰሩት ወገኖቻችን እግዚአብሔር አምላክ መጽናናትን ይስጥልን፤ለህዝብ ሳይሆን በጥቅም ለተቆራኝ ግለሰብ ቅድሚያ የሚሰጡ ሰዎችን እንቃወማለን

    ReplyDelete
  6. christianity is like this it is not some thing easy ok brothers you will win finaly this what it is

    ReplyDelete