መጽሀፉን በፒዲፌ ያንብቡ
(አንድ አድርገን የካቲት 26 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ለዛሬው ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ እንድዳፈር ያበረታታኝ ‹‹እውነትና ንጋት›› የተባለው የካርዲናል አባ ሰረቀ መፅሀፍ ነው ፡፡ ይህ መፅሀፍ ባልጎለመሰው እውቀቴና በተራው እኔነቴ ልደፍረው ያላሻሁትንና ለእናንተ አእምሮ በመጨነቅ ልገልጸው ያልፈለኩትን ጉዳይ አድበስብሶና ለሌላ አላማ አድርጎ ወደ ህዝቡ አድርሶታል፡፡ ድፍረቱ ላይ ግልፅነትን አክላችሁ ሌሎች ተደብቀው የቆዩና ተሰውረው ያሉ የመንፈሳዊ መሪዎቻችንን ሃይማኖታዊ ጉዳዮች (የመንፈሳዊ መሪዎቻችንን እንጂ የቤተክርስትያናችንን አላልኩም ፤ ቅድስት ቤተክርስትያን ምንም አይነትት የተደበቀ የሃይማኖት ጉዳይ የላትም ) የሚሳዩ መጻህፍት ታስነብቡኝ ዘንድ ፍላጎቴና ምኞቴ ነው፡፡
ፍላጎቴና ምኞቴ የሃይማኖት መሪዎቻችንን ሰብዓዊ ማንነት እና ግለሰባዊ ህይወታቸውን መግለፅና ማወቅ አይደለም ፤ እሱ የኔ ወይም የናንተ ጉዳይ አይደለም ፤ ባውቅም ምንም አይጠቅመኝም፤ የእኔ ፤ የእናንተ እና የእነርሱ የጋራ ጉዳይ የሆነው ሐይማኖት ነው ፡፡ ከሃይማኖት ደብቀው እና ሳይገልፁት የቆዩትን ወይም አባት ሆነው እየመሩት ካሉት እምነት አንፃር እርስ በእርስ የሚጋጭ አስተምህሮና እሳቤ ሌሎችንም ነገሮች ማወቅ ነው የኔ ፍላጎት ፡፡ ለምን ስለ ድብቁ ሃይማኖታዊ እሳቤያቸው ማወቅ አሰፈለገክ ? ትሉኝ ይሆናል፡፡ መልሴ ለጠቅላላ እውቀት የሚል አይደለም ፤ መልሴ ስለ ሃይማኖቴ ይገደኛል ፤ ይመለከተኛል የሚል ነው ፤ በእምነቴ ዙሪያ የሚነሱ ይህን የመሰሉ ጉዳዮችም ሳይሆኑ ትናንሾቹንም ቢሆኑ ማለፍ ስለማልችልም ጭምር ነው፡፡
በእርግጥም ስለ እምነቴ እጨነቃለሁ ስለ ቤተክርስትያኔ አስባሁ፡፡ እምነቴ ውስጥ እኔ ፤ ቤተክርስትያኔ ውስጥ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ እና ደጋግ ሕዝቦቿ አሉ ፤ እናም ይገደኛል ፤ አውቀህስ ምን ታደርጋለህ ? ልትሉኝ ትችላላችሁ ፤ እኔ ደግሞ እቃወማለሁ እላችኋለሁ ፤ ልክ እንዳልሆኑ እየተናገርኩ እቃወማለሁ ፤ የተሳሳተውን ነገር በመግለፅ እቃወማለሁ ፤ የቤተክርስትያናችን አስተምህሮ አይደለም እያልኩ እቃወማለሁ ፤ እምነቴን በህይወቴ እየመሰከርኩ እቃወማለሁ ፤ ስለ እውነት አጥብቄ እየጮህኩ እቃወማለሁ ፣ ……. ጩህት የት ሊደርስ ? ብትሉኝ መቼም ወደ ጎን ስለማልጮህ ወደ ላይ እንደመጮሄ ጩህቴ ከሚደርስበት ይደርሳል ፡፡ አዎን በእነዚህ ነገሮች እቃወማለሁ ተቃውሞዩ ምን ለመፍጠር ወይም ምን ለማምጣት እንደሆነ ለእናንተ መንገር አይጠበቅብኝም ፡፡ ታውቁታላችሁና
‹‹እመቤታችን የአዳም የውርስ ሀጥያት(ጥንተ አብሶ) ነበረባት›› እና ‹‹ እመቤታችን ጥንተ አብሶ የአዳም የውርስ ሀጥያት የለባትም›› ሰሞኑን ቤተክህነት አካባቢ መነጋገሪያ የሆነ ርዕስ ነው ፡፡ ርዕስነቱ ‹‹አለባት›› ፤ ‹‹የሌባትም›› በሚል ሳይሆን የቤተክርስትያኒቱ ፓትርያርክ (ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ) እመቤታችን የአዳም የውርስ ሀጥያት ነበረባት ማለታቸውን የሚገልጥ መጽሀፍ (የሚገልፅ ከምለው የሚጠቁም ብለው ይሻላል) ምክንያቱም መፅሀፉ ‹‹እውነትና ንጋት ›› ላይ የአቡነ ጳውስ መፅሀፍም ይህን ሀሳብ ይደግፋል ብሎ ያቀረበው ፅሁፍ አሻሚ ስለነበረ ነው ፤
(According to the eastern Orthodox church the blessed virgin is truly human , sharing the original sin which is part and parcel of humanity, and its in her it infirmity which ultimately expresses itself in natural death) ገፅ 61
(እንደ ምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አስተምህሮ ቅድስት ድንግል ማርያም ሰው እንደመሆኗ በሰው ዘር ላይ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ራሱንም በተፈትሯዊ ሞት የሚገልጸውን ጥንተ አብሶ ትጋራለች፡፡) ይህ የሚወራው ስለ ምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ስለሆነ አቡነ ጳውሎስ ሀሳቡን ይደግፉታ አያስብልም ፤ ነገር ግን አቡነ ጳወሎስ ሊደግፉት ይችላሉ የሚል ጥቆማ ሰጥቶን ያልፋል ምክንያቱም ‹‹የእውነትና ንጋት›› መጽሀፍ ጸሀፊም ሆኑ አብሯቸው ያሉ ሰዎች ከመሬት ተነስተው አቡነ ጳውሎስ ይህን ሀሳብ ይደግፉታል አይሉም፡፡ ( በቤተክርስትያኒቱ አባት ተጽፎ በጠቅላይ ቤተክርስትያን አዳራሽ ውስጥ መመረቁ አንዱ ነው)፡፡
ሰለምን እያወራሁ እንዳለ ተረድታችሁኛል ፤ ስማንስ እየጻፍኩ እንደሆነ ፤ ያቺ ገና ከማህፀን ሳትወጣ ጀምሮ ስሟን የሰማነው ፤ አነዚያ ቅዱሳን አባቶቻችን ስሟን ሲያወድሱ ውለው ቢያድሩ የማይጠግቧትን ፤ ለውሻ ራርታ በወርቅ ጫማዋ ውሃ ያጠጣችውን ፤ የሰማይና የምድር ጌታን ዘጠኝ ወር በማህጸኗ የተሸከመችውን ፤ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ነው የማወራው ፡፡ አሷ ከሴቶች የተለየች ከፍጥረት ሁሉ የተለየች መሆኗ ተረስቶ ፤ እሷም እንደ እኔ እና እንደ እናንተ የአዳም የውርስ ሀጥያት ተካፋይ ናት ተባልን ፤ ይህን ማን እንዳለሁ እነግራችዋለሁ፡፡ የዛሬ 24 ዓመት በፊት አሜሪካ ፕሪስተን ዩኒቨርሲቲ የያኔው የ52 ዓመት የዶክትሬት ተማሪ የአሁኑ የ76 ዓመት ፓትርያርክ ፤ የያኔው ተማሪ የአሁኑ ዶ/ር ፤ የያኔው ስደተኛ የአሁኑ ፓትርያርክ ፤ ብጽዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ናቸው ይህን በመጽፋቸው ያሰፈሩት፡፡ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ በፍልስፍና ዶክትሬታቸውን ያገኙት ወይም ለዶክትሬታቸው ማሟያ የሆነው (Dissertation) የጻፉት ይህን በማለት ነው ፡፡ ይህን ሲሉም የግል አመለካከታቸው ወይም የእሳቸው ብቻ እሳቤ እንደሆነ አይደለም የገለፁት ፤ እናንተ እና እኔ ብሎም እነዚያ በህይወት ያለፉት ደጋግ ቅዱሳን አባቶቻችን የሚያምኑት እውነትና እምነት ብለው ነው የተናገሩት ፡፡ “The author shows that Ethiopia Orthodox Trilogy sees the blessed virgin Mary, Mother of God on the one hand as honored by God above all other creatures is being chosen as the mother of God , the word incarnate, but on the other hand as a human being, born under the shadow of original sin “ (page Viii)
አጥኝው ማሳየት የፈለጉት ‹‹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ብፅእት ድንግል ማርያምን የአምላክ እናት አድርጋ ብትመለከትም በሌላ አገላለጽ አካላዊ ቃል በስጋ ለመውለድ የአምላክ እናት በመሆን ምርጫ ውስጥ ከፍጥረታት ሁሉ በላይ የተከበረች ብትሆንም ፤ ነገር ግን በሌላኛየሰው ዘር በጥንተ አብሶ (የአዳም የውርስ ሀጥያት) ጥላ ስር የተወለደች መሆኗን የኢትዮጵያው ገፅታ እንደማንኛውም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የስነ መለኮት አስተምህሮ ይገልፃል…››
ይህን ጽሁፍ የምታገኙት በጥናቱ አስተዋፅኦ (ABSTRACT) ላይ ነው:: የጥናታቸው ርዕስ “ Filsata : the Feast of the Assumption of the virgin Mary and the Mariological Tradition of the Ethiopia Orthodox Tewahedo Church” ይሰኛል ፡፡ “Princeton Theological Seminary” ጎግል ላይ ገብታችሁ “Order NO 8818495” እና “Yohannes Paulos” የሚለውን ስትጽፉ ጎግል ጎልጉሎ ያወጣላችኋል፡፡ ይህ አስተምህሮ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ይወክላልን? ቤተክርስትያናችን እንዲህስ ብላ አስተምራ ታውቃለችን? የቤተክርስትያኒቱ የእምነትና የሥርዓት መፅሀፍ ሆኖ በ1988 ዓ.ም በ22 ሊቃውንት ተጠንቶ በዘመነ አቡነ ጳውሎስ ጊዜ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እምነትና ስርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኑነት›› በሚል ርዕስ በአማርኛና በእንግሊዘኛ የታተመው መፅሀፍ ይህ ከላየ የተመለከታችሁት የአቡነ ጳውሎስን ፅሁፍ እንዲህ በማለት ይቃወማል፡፡
‹‹አምላክን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደችው የእመቤታችን የድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኃጥያት(ጥንተ አብሶ) ያላገኛት መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በአምላክ ህሊና ታስባ ትኖር የነበረች…››(ገጽ 49)
ሁለት ተቃራኒ የሆኑ ሀሳቦችን በአንድ ሰው በዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ሲዘነዘሩ አይተናል ፤ በመጀመሪያው ላይ ራሳቸው ቃል በቃል ‹‹ በጥንተ አብሶ (በውርስ ሀጥያት) ጥላ ስር ነበረች›› ብለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ ሳይሆን ‹‹ነው›› በማለት ዶክትሬታቸውን አግኝተውበታል ፡፡ ( ልብ ይበሉ የዶክትሬት ማግኛ ፅሁፋቸውን የተሰራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በማታምነውን ፤ እኛም በማናምነው ጉዳይ ነው ፡፡ የሚገርመው ደግሞ ይህን የገለጹት ለህዝብም በይፋ ያሳወቁት ካርዲናል አባ ሰረቀ መሆናቸው ነው፡፡ የቤተክርስትያን አባቶች ቅዱስ ሲኖዶስ ስራቸውን ሚዛን ላይ አስቀምጦ ከሀላፊነታቸው በጥቅምት ወር ያነሳቸው ፤ የአቡነ ጳውሎስ የቅርብ ወዳጅ በሆኑት ካርዲናል አባ ሰረቀ ነካክተው የተደበቀውን ነገር አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ጉዳዩ ጸሀይ እንዲሞቅ በአደባባይ አውጥተውታል ፡፡ ማንም ሰው በመንፈሳዊም ሆነ በአለማዊ ትምህርት ላይ የፈለገውን ሀሳብ አንስቶ ማራመድ ይችላል መብቱም ነው ፤ ሀሳቡን እንደፈለገው የማንሸራሸር መብት አለው፤ እግዚአብሔርም የለም ብሎ ማመን የእሱ ብቻ መብት ነው ፡፡ ነገር ግን አንድን እምነት ወክሎ የራሱን ሀሳብ የእምነቱ አድርጎ መናገርም ሆነ ማቅረብ ግን አይችልም፡፡
‹‹እውነትና ንጋት›› የተሰኝው መጽሀፍ ለህዝብ እስከሚደርስ አቡነ ጳውሎስ ያን የጥንቱን የአሜሪካውን ትምህርት ቤት እሳቤያቸውን በትምህርት ቆይታቸው ወይም ዶክትሬታቸውን እስኪይዙ ድረስ ብቻ አብሯቸው የቆየ ነው የመሰለኝ ፡፡ ምክንያቱን በዘመነ ፓትርያርክነታቸውም በእሳቸው መልካም ፍቃድ ይህን የተማሪ ቤት ቆይታቸው ወቅት ያንፀባረቁትን መጽሀፍ በማፃፋቸው ነው፡፡ ከ24 ዓመት በፊት ያሉትን ነገር ትተውታል ወይም በነገሩ ላይ የበሰለ እውቀት ሳይኖራቸው የፃፉት ነው ብዬ አስብ ነበር ፡፡ አሁንም ሊሆን ይችላል ፡፡ ግን የአባ ሰረቀ መጽሀፍት በቤተክህነት አዳራሽ ተመርቆ ለህዝብ መቅረቡን አቡነ ጳውሎስ በነገሩ ላይ ዝም ማለታቸው ዳግም አስገርሞናል፡፡
እርግጥ ነው ዶ/ር አቡነ ጳውሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አምስተኛ ፓትርያርክ ናቸው፡፡ ቢሆንም እሳቸውም ሰው ናቸው ፤ አባትም ናቸው ፤ ስለሆኑም እኔ ሀጥያተኛ እና መሀይም ልጃቸው ነገሩ ቢያጠራጥረኝ ጉዳዩ ጥያቄ ቢፈጥርብኝ አይፈረድብኝም፡፡ ያነሳሁት ጉዳይ ቤታችንን ስለሚያምሱ አውርቶ አዳሪዎች እና ሴት ወይዛዝርቶች አይደለም፡፡ ለሰው ልጅ ድህነት ምክንያት የሆነችው ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ቀኑን ሙሉ ስሟን ሲጠራ ቢውል የማይረካን የእመቤት ማርያምን ጉዳይ ነው ያነሳሁት፡፡ ስለዚህ አትዘኑብኝ እሷ ከደሜ እና ከደማችሁ ተዋህዳለች ፤ እንግዲህ እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ይህን ብያለሁ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ‹‹የመመረቂያ ፅሁፍዎን›› ወይም ‹‹የቤተክርስትያኒቱን አስተምህሮ›› ከሁለት አንዱን ይምረጡ ብያለሁኝ፡፡ አበቃሁ
ተስፋዬ አዳነ
የእኛ ሀሳብ
ሰው በሃምሳዎቹ እድሜ ላይ እያለ እንዲህ አይነት እሳቤ ይኖረዋ ብሎ ማሰብ ለእኛ ጭንቅላት በጣም ይከብደዋል ፤ የሀገሬ ሰው ‹‹እድሜ ራሱ ትምህርት ነው›› የሚል አባባል አለው ፤ የሰው ልጅ ትምህርት ቤት ገብቶ ከሚያገኝው እውቀት በላቀ ሁኔታ እድሜ ያስተምረዋል ፤ ቀን አልፎ ቀን ሲመጣ እሳቤያችን አመለካከታችን እየሰፋ ይሄዳል ፤ እይታችንም ከራስ በዘለለ መልኩ ለወገን ለሀገር ቤተክርስትያን መሰረት ያደረገ ይሆናል ፤ ይህ ማለት ግን ለሁሉም አይደለም ፤ አቡነ ጳውሎስ ከ24 ዓመት በፊት ይህን ማለታቸው የፃፉት ፅኁፍ ማረጋገጫ ነው( ከላይ በፒዲፌ አማካኝነት አቅርበነዋል)፡፡ አሁንሰ ያላቸውን እሳቤ በምን እናውቃለን ? (የሰማይ አምላክ ይወቀው እኛ ለእሱ ትተናል)፡፡ ለቤተክርስትያኗ የበላይኛው ክፍል የተመረጡ አባት እንዴት በእውቀት ማነስ ይህን ፃፉ ልንል እንችላለን ? ይህን ብንል የዋህነታችን ባህር ሆኖ ያሰጥመናል ፤ ይህ የቤተክርስትያናችን አስተምህሮ እኮ የ20 ዓመት እድሜ ያለው አይደለም ፤ እሳቸው ወደ ፓትርያርክነት ከመጡ በኋላም የተቀየረ ሆኖ አይደለም ፤ 2000 ዓመትን ያስቆጠረ ስረ መሰረቱ ከሐዋርያት የመጣ ፤ በመጽሀፍ ቅዱስ የተደገፈ አስተምህሮ ነው ፡፡ ከወራት በፊት ካርዲናል አባ ሰረቀ ይህን የመሰለ የኑፋቄ አስተምህሮ የሚከተሉ ሰው መሆናቸውን በብፁእአን ሊቃነ ጳጳሳት በሲኖዶ ጉባኤ ተረጋግጧል ፤ በጉባኤው ላይም ብዙዎች አባቶችን አስደንግጧል ፤ ከዚህ በፊት ያስተማሩት እና የጻፏቸው መጽሀፍቶች እውነታውን ያረጋጡልናል ፤ ይህ የእሳቸው እሳቤም ሆነ አስተምህሮ እኛ ላይ ይህ ነው የሚባል ችግር ሊያመጣብን ይችል ይሆን ? ብለን አንሰጋም ፤(ሰውን ለራሱ አመለካከት አሳልፎ መስጠት ነው) የካርዲናሉ ሲገርመን የአቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ከመሆናቸው በፊት የዚህ እሳቤ አራማጅ መሆናቸውን ስናውቅ በጣም አዝነናል ፡፡ አርስዎ ምን ይላሉ ?
Well written, I believe that Abune Paulos has to correct his belief and make a public confession and come to the truth. And if possible I will be happy to see Aba Sereke doing the same.
ReplyDeleteGod you know what is right, please reveal all to us. Amen.
Dear Tesfaye and Andadrgen
ReplyDeleteIt is big time written documents good on u guys, Thank u very much I was looking this kind of document. May GOD bless u all.
Abune Paulos has got hidden secret to divide and destroy Ethiopian Orthodox Tewahedo church that what he is doing to all against true Tewahedo Abatoch. we are hearing at daily basis this day,but he can not do that GOD will Judge.
This topic and idea also shared by Abune Melketsadik, secretary of the church who residing(living) in America calling themselves Synod in exile. He left the country because the SYNOD ( by the way SYNOD can't be and never be in exile can only be one SYNOD that is in Ethiopia,) asked Like seltanat Habtemariam to come and explain about his way of teaching and book about KIDEST DENGILE MARIAM he has got(Eses) the same idea with Abune Paulos, the SYNOD gave him time to come and clean but instead he left the country.
Now he is trying to confuse innocent people that he left the country because "KENONA FERESE" that all white lie, he was there when Abune Paulos was taking this position he is the one who supported it and knelled down and kissed the knee of Abune Paulos says "Yedelwo" now he seems against Abune paulos but they are the same.
Abune Melkasadik has done his master in Greek Theology college he shared and support Greek orthodox not Ethiopian Orthodx.
Abune Gorgoriwos 'Kaleh'Ye Shewa lekepapas yeneberut' the one who died in 1983, who has done his master in Teology once told Abune Melkesadik he can't be 'Abune" while Abune Gorigoryos is alive, it is true that what happened, Abune Giorgorios died in 1983, Likee seltanat Habtemarim Got his "ABUNE Mekasadik name" since then.
Why Abune Giorgorios said that i think you all now understand after 20 years time.
" EGZIABHERE TEWAHEDON" Yetebekilin
where can we get his disertation. please help us to get it. why do not u scann it and made it puplick
ReplyDeleteuse the following link to get his dissertation
Deletemedhanialemeotcks.org/wordpress/wp-content/uploads/.../Filsata.pdf
አምላክ፡ልቦና፡ይስጣቸው፡፡የሳቸውን፡ነገር፡አለቃ፡አያሌው፡ጨርሰውታል፡እኛ፡አልሰማ፡ብለን፡ነው፡እንጂ፡፡የአቡነ፡ጳውሎስን፡
ReplyDeleteካቶሊክነት፡እንደተናገሩ፡ኖረው፡ነው፡የሞቱት፡፡ነፍሳቸውን፡ይማርልን፡፡አሁን፡ሊቃውንቱ፡በጠፉበት፡ወይም፡ያሉትም፡ለሆዳቸው፡በተገዙበት፡ወይም፡በፍርሀት፡በማይናገሩበት፡ዘመን፡ቤተ፡ክርስትያናችን፡የመናፍቃን፡መፈንጫ፡ሆናለች፡፡
አምላካችን፡ይታረቀን!!!
የእመቤታችን፡ጥበቃ፡አይለየን!
አምላክ፡ልቦና፡ይስጣቸው፡፡የሳቸውን፡ነገር፡አለቃ፡አያሌው፡ጨርሰውታል፡እኛ፡አልሰማ፡ብለን፡ነው፡እንጂ፡፡የአቡነ፡ጳውሎስን፡
ReplyDeleteካቶሊክነት፡እንደተናገሩ፡ኖረው፡ነው፡የሞቱት፡፡ነፍሳቸውን፡ይማርልን፡፡አሁን፡ሊቃውንቱ፡በጠፉበት፡ወይም፡ያሉትም፡ለሆዳቸው፡በተገዙበት፡ወይም፡በፍርሀት፡በማይናገሩበት፡ዘመን፡ቤተ፡ክርስትያናችን፡የመናፍቃን፡መፈንጫ፡ሆናለች፡፡
አምላካችን፡ይታረቀን!!!
የእመቤታችን፡ጥበቃ፡አይለየን!
Amlak b/crstiyanin yitebkiln amen.
ReplyDeleteየኔ ጥያቄ በአሁነ ሰዓት ይህንን ሀይማኖታዊ ርዕሰ ጉዳይ ማንሳቱ ለምን አስፍለገ?
ReplyDeleteወደምንስ ለማመራት ታስቦ ነው?
Mefenkile Patriarch
DeleteDear Fikremariam,
ReplyDeleteIf you said "የሞት ፍርድን ያስከተለው የአዳም ስህተት ስለሆነ ፣ ከአዳም የውርስ ኃጢአት የለባትም ካልን ሞት የተባለው ስለምን አገኛት ?" what would you say about the scarification & death of Jesus Christ?
What would you say about the scarification & death of Jesus Christ?
ReplyDeleteይህንን ጥያቄ ያቀረብክልኝ አንባቢ ሆይ ፣
1. የእኔ ጽሁፍ ጽንሰ ሃሳብ በእኔ አእምሮ ጥበብ የተፈጠረ አይደለም ፡፡ ትምህርቱ ጥያቄውና የተጠቀሰው ምክንያት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እምነት መሥራቾችና ተከታዮች ከሆኑ ወገኖች ነው ፡፡ እኔ በንባብ ያገኘሁትን መልስ ለማግኘትና ቃላችን አንድ እንዲሆን ፣ ትክክለኛውን የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮን ለማወቅ በጥያቄ መልክ አቅርቤዋለሁ ፡፡ ስሜን ፍቅረ ማርያም እያልኩ ከእመቤታችን ጋር የተቀያየምኩና ያኮረፍኩ እንዳይመስልዎ ፡፡
2. በተረፈ ኢየሱስ የሞተው በተፈጥሮ ሞት ሳይሆን ፣ ህግን ፈጽሞ እኛን ለማዳን ስለፈቀደ ብቻ ነው ፡፡ ስለዚህም አምላካችን በሥጋው ሞተልን እንላለን ፡፡ ነፍስና ሥጋውን የለያት ተነጥቆ ሳይሆን በገዛ ፈቃዱ ነው ይላልና መጽሐፍ ፡፡ በፈቃድ የተፈጸመና በአስገዳጅ የሆነ ነገር ልዩነት ያለው ስለመሰለኝ አነሳሁት ፡፡
3. አሁንም አንባቢዎች እንዲገነዘቡ የምፈልገው የኢኦተቤ ሊቃውንትና ምእመን ስለምን ምክንያት ተብሎ ሁለት አቋምና ቋንቋ እንናገራለን ፡፡ ይኸ ተራ ነገር አይደለም ፤ ከላይ በጽሁፌ እንደገለጽኩት የሃይማኖታችን መሠረት ስለሆነ የአስተምህሮው ባለቤቶች መግለጫቸውን ያሰሙን የሚል አቤቱታ አሁንም አቀርባለሁ ፡፡ ከሌሎች እህት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያኖች የእኛ ቤተ ክርስቲያን ስለ ምን ምክንያት ትለያለች በማለት ጥያቄ ማቅረብ መልስ የሚሰጥ አካል ከተገኘ አግባብ መሰለኝ ፡፡ ይኸን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናትን አቋም የሚገልጸውን ለማግኘት ካስፈለገ የደብረ ሣሕል መድኃኔዓለም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካንሣስ ፊት ገጽ ላይ ይገኛልና በ http://medhanialemeotcks.org አድራሻ ይመልከቱት ፡፡
በተረፈ ከሰዎች የሚገኘው መልስ የሚለያየን እንጅ አንድ የሚያደርገን ስላልሆነ እግዚአብሔር እራሱ መልሱን ይስጠን ፡፡
@ Fikremariam
ReplyDeleteJusus Christ ye Adam hatiat wurs hatiat alebet bileh taminaleh?
ende betekrstianachin astemihiro Emebetachinin ke Enatua mahitsen gemiro menfeskidus ke adam yewurs hatiat tebekat. yihm bizu yeabatochachinin metshaf bitaneb tiredawaleh. lebelete merega " NETCH ENQUE BE ADAM GELA " yemilewn ye MEMIHIR HABTEMARIAM TEDLA book anibibew. bizu merega tagegnaleh.
ke diro gemiro ene ATHNATIOUS ZE ESKNDRIA, KERLOS... YEMIAMNUT YIHEN NEW.
BEAHUNU SEAT POPE SHINOUDA ENA ESKNDRIA WUST YETEWESENE MEMTATAT ALE. YIHEM TEWOFLOS BEMIBAL YEGIBTS POPE GIZE MENAFKAN WODE COPT POPE GEBTEW SILENEBERE (ENDE AHUNU YE EGNA BETEKRSTYAN MALET NEW)YASTEMARUT TIMIHIRT ZAREM BE COPT CHURCH YIHE HASAB AKERAKARI ENDEHONE NEW.
EGNA GIN ABATOCHACHIN YASTEMARUNIN MAWOK ENA MEKETEL YINORIBNAL.
ስለዕውቀትዎ አምላክ! ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እመቤታችንን “ኃይል አርያማዊት ናት፡፡ ወይም የተፈጠረችው ከሰው ካልሆነ ዘር ነው፡፡” የሚል ትምህርት የላትም፡፡ እንዲህ የሚል አላት ካሉም ተሳስተዋል፡፡
ReplyDeleteነገር ግን “ከመ ሰዶም እም መሰልነ ወከመ ገሞራ እምኮነ እመእግዚአብሔር ኪያኪ ለእመ ኢያትረፈ ለነ፡፡” (የእግዚአብሔር እናት አንቺን ባያስቀርልን ኖሮ ሰዶምን በመሰልን ገሞራንም በሆንን ነበር፡፡) ብሎ ነቢዩ ኢሳይያስን ጠቅሶ የማኅሌተ ጽጌ ደራሲ እንደተቀኘው፣ ወይም ቅዱስ ያሬድ “ማርያምሰ ተኀቱ ውስተ ከርሱ ለአዳም” (ማርያም በአዳም ሆድ ውስጥ ታበራ ነበር፡፡) እንዳለው፣ ወይም ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት በውዳሴ ማርያም ትርጓሜያቸው “መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እም ከርሰ እማ” (መንፈስ ቅዱስ ከእናቷ ሆድ ጀምሮ ጠበቃት፡፡) እንዳሉት የእመቤታችን ቅድስት፣ ንጽሕት፣ ድንግል ማርያም ከአዳማዊ ኃጢኣት ነጻ ናት፡፡ እግዚአብሔር ባወቀ ጠብቋታል ብላ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ታስተምራለች፡፡ ነቢዩ ዳዊት “መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን” እንዳለ፡፡ የእመቤታችን ጽንሰቷ ልዩ ነው፤ ማለትም አዳማዊ ኃጢኣት (Original Sin) ያላረፈባት ጽንሰትን ገንዘብ አድርጋለች ማለት ነው እንጂ ከመላእክት ትወለዳለች ማለት አይደለም፡፡ እርሷን ሰው ካልሆኑ ፍጥረታት እንደተወለደች ካመንንማ መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰው ያልሆነ አምላክ ነው ልንል ነው (ሎቱ ስብሐት! ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንደጻፈልን ቃል ሥጋ ሆኗል፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስም እንደመሰከረው ሰውን አምላክ ያደርገው ዘንድ አምላክ ሰው ሆኗል፡፡) በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ማንም ይሁን ማን የአሕዛብ ብርሃን የሆነችውን ተቋም ዘወርቅ እመቤታችንን አዳማዊ ኃጢኣት አለባት የሚል የተወገዘ ነው!
ለነገሩ የክርክሩ መነሻ “አዳማዊ ኃጢኣት ምንድነው?” የሚለውን መረዳቱ ላይ ነው፡፡ አዳማዊ ኃጢኣት ምንድነው? አዳማዊ ኃጢኣት ሥነ ሕይወታዊ (ባዮሎጂካል) የሆነ ቫይረስ ወይም ባክቴሪያ ወይም ድኩም መል (deficient gene) ነው? መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከአዳማዊ ኃጢኣት ነጻ አውጥቶናል ማለትስ ምን ማለት ነው? ጌታችን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ከራሱ ጋር ማስታረቁን ካመንን እና በጥምቀት ነጻ እንደምንወጣ ካመንን ዛሬ ለምን እሞታለን? ወይም ሰዎች ለምን ይሞታሉ? ሴቶችስ ለምን በምጥ ይሰቃያሉ? ሞት ከአዳማዊ ኃጢኣት ውጤቶች አንዱ ነው ወይስ የአዳማዊ ኃጢኣት መገለጫ? እስከአሁን ድረስ ይህን ጥያቄ ቁርጥ ባለና ሁሉን ሊያስማማ በሚችል መልኩ መመለስ የቻለ የነገረ መለኮት ሊቅ የለም (እኔ እስከማውቀው ድረስ ሁሌም ለክርክር ክፍት የሆነ ነጥብ ነው፡፡ አንዱ ስንፍና ነው ይላል፤ ሌላኛው ፍትወት ነው ይላል፤ ሌላኛው አልረካ ባይነት ነው ይላል፡፡ ሌላኛው ጠማማነት ነው ይላል፡፡)፡፡ ራሱ እግዚአብሔር ካልገለጠልን በስተቀር ልንረዳው የሚያስቸግር ምሥጢር ነው፡፡
ለማንኛውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመጣ የሚጠይቀን ምን ያህል በነገረ መለኮት ተራቀቃችሁ? ሳይሆን ምን ያህል እኔን በታናናሾች ወንድሞቻችሁ ችግር ውስጥ አስተናገዳችሁኝ? የሚል ስለሆነ የእመቤታችንን ረድኤት ተደግፈን ለበጎ ሥራ እንትጋ፡፡ ያለ አዳም ኃጢኣት የተጸነስሽ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ! ለምኝልን ለኛ ደጅ ለምንጠናሽ፡፡ አሜን!
ZEMENU KERBAL NESEHA GIGU ,
ReplyDeleteጥያቄዬን የመለሳችሁልኝንና ለመመለስ የሞከራችሁልኝ በሙሉ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ፡፡
ReplyDeleteየኔ ዕውቀቴ በድኀረ ገጽ ከሚተላለፈው ቅንጭብጫቢ ጽሁፍ ንባብ የተገኘ ነው እንጅ ከራሴ የፈለቀ አይደለም ፡፡ ስለዚህ ዛሬም ትንሽ ዕውቀት የጨመርኩ መስሎኛል ፡፡
- ወንድሜ ሃብተ ማርያም ለጠየከኝ ጥያቄ በሉቃስ ወንጌል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በውል ስለተገለጸ የውርስ ኃጢአት አላገኘውም ፡፡ በተረፈ የጠቆምከኝን መጽሐፍ አፈላልጌ ለማንበብ እንደምሞክር ቃል እገባለሁ ፡፡ ስለ ጥቆማህ አመሰግናለሁ፡፡
- ለአባቴ አባ ሣህለ ሚካኤል ስለሰጡኝ ጥልቅ ትምህርት የከበረ ምስጋና አቀርባለሁ ፡፡ ያነበብኩት ጽሁፍ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን ሌሎች ወገኖች እንዲህ ይሏታል ለማለት ነው እንጅ ፣ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የድንግል ማርያም አፈጣጠር ከሰው የተለይ ወይም እንደ መልአክ የሆነ እንደማትል አውቃለሁ ፡፡ ሌሎች የጥንተ ተአብሶ ጽንሰ ሃሳቧን የማይቀበሉ ግን ድንግል ማርያምን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን ያልሆነ አፈጣጠር አላት ትላለች በማለት ይወቅሳሉ ፡፡ ሃሳቤን በደንብ መግለጽ ስላልቻልኩ ነውና ስህተቴን ወደፊት ለማረም እተጋለሁ ፡፡ አንዳንዴም ይኸ የስማ በለው ነገር የሚፈጥረው ችግር ነውና ፣ አስቆጥቼ ከሆነ ልጅዎ ስለምሆን ይቅርታ ፡፡
መልዕክቶውን እንደተቀበልኩ ለማረጋገጥ በእርሶው ቃል እኔም እዘጋዋለሁ ፡፡ "ያለ አዳም ኃጢኣት የተጸነስሽ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ! ለምኝልን ለኛ ደጅ ለምንጠናሽ፡፡ አሜን"
መምህሮቼን ቃለ ህይወት ያሰማልኝ ፡፡
በአባ ሣህለ ሚካኤል በመደምደሚያው አካባቢ የተደረደሩልን ጥያቄዎች ፣ እንደ እኔ ላሉ ደካማዎች የክርስትና እምነታችንን የሚፈታተኑ ሆኖ ስለተሰማኝ ፣ በመሃይም አእምሮየ ስለ ክርስትና እምነታችን የተገነዘብኩትን ወደ እርሳቸው ወይም ለህዝብ ብታቀርቡት በማለት ጫጫርኩ ፡፡
ReplyDeleteየአዳም ኃጢአት ምንድነው ?
- አዳምን የፈጠረው አምላካችን የሰጠውን ትእዛዝ በሴት ምክንያት መተላለፉ ነው ፡፡ ማለትም ፈጣሪአችን አትብላ ያለውን ፍሬ በመብላቱ ፤ አታድርግ ያለውን በማድረጉ እንደ አዳም ኃጢአት ሆኖ ተቆጠረ፡፡
አዳማዊ ኃጢአት ሥነ ሕይወታዊ /ባዮሎጂካል/ ወይም ቫይረስ ነውን ?
- የአዳምና የሴት ቀደም አፈጣጠራቸው ለመሞት አልነበረም ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አትብላ ያልኩህን ከበላህ ሞትን ትሞታለህ በማለት ህግን አስቀድሞ ሰጥቶት ስለነበረ ፣ ትእዛዝን አፍርሶ በተገኘበት ሰዓት ወደ መጣህበት አፈር ትመለሳለህ ተባለ ፤ ለሴትም ደግሞ በአዳም አካልነቷ ከሚደርሳት የፍርድ ውሳኔ በተጨማሪ በምትወልድበት ወቅት ምጥ እንደሚጠነክርባት ተነገራት ፡፡ ይህም ፍርድ በቀጣይ ትውልድ ላይ ሁሉ ተፈጻሚ ሆነ ፡፡ እንደምረዳው አዳማዊ ኃጢአት ሥነ ህይወታዊ ወይም ቫይረስ ስለሆነ ሳይሆን ፣ የአዳም ቀጣይ ትውልድ በሙሉ የተገኘው ወደ አፈር እንዲመለስ ከተወሰነበት ከአዳም ሥጋ በመሆኑ ነው ፡፡ አዳም ትውልድ የሚተካበት ፣ ያልተረገመ ሌላ አካል ቢኖረው ኑሮ ፣ የፍርዱ ውጤት እስከ እኛ አይደርስም ነበር ፡፡ ስለዚህ ከተረገመው የአዳም አካል በመገኘታችን እንሞታለን ፡፡
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከአዳማዊ ኃጢአት ነጻ አውጥቶናል ማለትስ ምን ማለት ነው ?
- ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ ፣ የአዳምን ሞት ሞቶ እኛን ነጻ አውጥቶናል የምንለው ነፍሳት በሙሉ በሲዖል ታስረው ፣ ሥጋም በስብሶና ወደ አፈርነት ተቀይሮ ለዘለዓለም እንዳይቀር በማድረጉ ነው ፡፡ የሱን ትንሳዔ ሰንደቅ አድርገን በእምነትና በምግባር ከሞትን ፣ በልዩ አካል /መንፈሳዊ አካል/ እንደ እሱው በመነሳት ፣ ታቅዶልን ለነበረው ዘለዓለማዊ ህይወት እንበቃለን ማለት ነው ፡፡ ኢየሱስ ስለእኛ ኃጢአት መስዋዕት ባይሆን ኖሮ የአዳም ዘር በሙሉ ለዘለዓለም ትንሣዔን ሳያገኝ ተረስቶ ፣ አፈር ውስጥ በስብሶ ይቀር ነበር ፡፡
ጌታችን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ከራሱ ጋር ማስታረቁን ካመንን እና በጥምቀት ነጻ እንደምንወጣ ካመንን ዛሬ ለምን እንሞታለን?
- ከላይ እንደገለጽኩት ጌታችን የሞተው የተሰጠው ፍርድ ዘለዓለማዊ እንዳይሆንብንና ፣ በትንሣዔም እንድንነሳ ለማስቻል ነው ፡፡ እግዚአብሔር ሰው አይደለምና ፣ ቃሉን አይቀያይርም ተብሏል ፡፡ ፍርድ ፈርዷል ፣ ፍርዱ ተፈጻሚ እየሆነ እስከ ዓለም ፍጻሜ ይቀጥላል ፡፡ ነገር ግን የዓለም መድኀን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በድንግልና ተወልዶ ፣ በመስቀል ላይ ታግሶና ሞቶ በመነሳት ለእኛም ትንሣዔን አወጀልን እላለሁ ፡፡ አምነን የምንሞተው ጊዜያዊ ሞትን እንጅ ዘለዓለማዊ ሞትን ስላልሆነ ከራሱ ጋር ፣ ከአብና መንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀን እንላለን ፡፡
ሴቶችስ ለምን በምጥ ይሰቃያሉ?
- ከላይ እንደገለጽኩት የእግዚአብሔር ቃል ተለዋዋጭ ባለመሆኑ ምክንያት ነው ፡፡
ሞት ከአዳማዊ ኃጢኣት ውጤቶች አንዱ ነው ወይስ የአዳማዊ ኃጢኣት መገለጫ?
- የአዳም ትእዛዝን ያለማክበር /ለአምላኩ ተገዢነትን ያለመቀበል/ ስህተት ያስከተለው የፍርድ ውጤት ነው ፡፡ ሞትን ስናስብ የአዳምን መሳሳት ፣ የአምላክን ትእዛዝ አለመከበሩን እናስታውሳለን ፡፡
እኔ ይህን መልስ ለመስጠት የሞከርኩት በሃይማኖት ሊቅነት ተሰምቶኝ ሳይሆን ፣ የጥያቄዎቹ በእንደዚሁ መቀመጥ መደምደሚያቸው ወደ ክህደት ሊያደርሱን ስለሚችሉ ነው ፡፡ አንድም የክርስትና ሃይማኖት የሚገልጸው የሃሰት ትምህርት ነው ፤ አለበለዚያም እንደ አይሁድ እውነተኛው ኢየሱስ ክርስቶስ ገና አልተወለደም ብለን ወደ አይሁድ እምነት መሸጋገር ሊያስፈልገን ነው ፡፡ በአካል ወይም በደብዳቤ የምታገኟቸው ቢሆን እኔ የገረዳደፍኩትንና ያጐዳደፍኩትን አርመው መልሱን እሳቸው ለልጆቻቸው ቢያቀርቡልን እመርጣለሁ ፡፡ የኔ ትርፍ የክርስትና እምነታችን እውነተኛ ሃይማኖት መሆኑን ማስረዳት ብቻ ነው ፡፡
አመሰግናለሁ ፡፡
Have you presented this to the likawente of the Ethiopian orthodox Church, it would be much better to do that then to spread this shamful thing on the internet.
ReplyDeleteIt will just make the menafikans look down on our church.
MAZENAGIA NEW ZEMEDOCHE. it has something in it, we Got all this from our past we shall focus on Waldba and unit like Muslims do this days. Who knows may be this is the new fighting strategy to divide our Poeple. Just like they stan against our History we heard all this days.
ReplyDeleteStay Focus. May God be with US.
i would suggest more explanation on original sin, just on the research questions raised by aba sahle michael and fikremariam. i read the book 'nech enku be adam gela'. it is much powerful book but still it left me with the questions without answers. such as
ReplyDelete- why we die now?
- why women see periodic flow of blood and pain during giving birth?
- what is the main points explained by death of jesus?
etc.
i really love to have more answers.
1. ዘመኑ በየግላችን ራሳችንን እንድናድን የተጠራንበት ወቅት ይመስለኛል ፡፡ ዛሬ በቂ ዕውቀት ያለው ፣ ተምሮ የሚያስተምረን ፣ ለምናቀርበው ጥያቄ ሁሉ አጥጋቢ ምላሽ የሚሰጠን ፣ ቅን ፣ ፈቃደኛ ምድራዊ አባትና ጠባቂ እረኛ የለንም ፡፡ በአጠቃላዩ በእውነት ፣ እውነትን ከመመመስከር ይልቅ ክብርና ጥቅማቸውን ፣ ዝናቸውን ጭምር ያስተውላሉ ፡፡
Delete2. አንዳንዱ በሙያውና ከዛም ውጭ /የሃይማኖት ሊቁም ይሆን ሌላው ማለት/ የሚሯሯጠውና ስለ ሃይማኖት የሚጽፈው ፣ ትንሽ ለአፉ የማር ወለላን ለማግኘት ነው እንጅ ፣ ስለነፍስና ስለ ቅድስና ማስተማሪያ እንዲሆን አስቦ አይደለም ፡፡ ስለዚህም ሃይማኖትን በተመለከተ የምናነበውን መጽሐፍት ፡
a. በማን ተጻፈ ? - የግለሰቡን ስለ ሃይማኖት ያለውን አቋሙን በተመለከተ
b. ስለምን ዓላማና ግብ ተጻፈ ? ለንግድ ፣ ሃይማኖትን ለማስተማር ወይስ ለመተቸት ፣ ለማጠንከር ወይስ ለመበታተን
c. የጸሃፊውስ እምነትና ሃይማኖትስ ምንድር ነው ? የሚሉትን ጥያቄዎች በአግባቡ ለመመለስ አጠቃላይ ቅኝት ማድረግ ያስፈልገናል ፡፡ ሁሉን ማንበብና መፈተሽ መልካም ነው ፤ ነገር ግን የተጻፈውን ሁሉ ተቀብሎ ተግባራዊ መመሪያ ለማድረግ መሞከር ትልቅ ድክመት ነው ፡፡ የምናነበው ቢያንስ እምነታችንን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚገፋልን መሆን አለበት እንጅ ፣ ከምናውቀውና ከተቀበልነው የሚያጐድል ፣ ወይም ወደ ኋላ የሚጐትተን ሊሆን አይገባም ፡፡ ስናነብ እምነታችንን ለማጠንከር ማሰብ አለብን እንጅ በውስጣችን ጥርጣሬን የሚተክል ፣ አለማመንን የሚያነግሡ ችግሮችን እየፈለግን ትኩረት መስጠት ደግ አይደለም፡፡ ከእንደዚህ ዓይነቱ የመመርመር ዓላማ ውጭ የተጓዙ ወገኖች በመጽሐፍ ቅዱስም ውስጥ ለአእምሮአቸው የሚስማማ ጉዳይን አግኝተው አንድም ሃይማኖትን ክደዋል ወይም ከትክክለኛው እምነት አፈንግጠዋል ፡፡ የሰዎቹ የትምህርት ደረጃም ቢሆን በእኛ ላይ ተጽእኖ ማድረግ የለበትም ፡፡ ሉተርን ብትወስደው ደካማ የሃይማኖት ሊቅ አልነበረም ፣ ሩሴልም ቢሆን መሃይም አይደለም ፡፡ ነገር ግን ትምህርታቸው እኛ ከምንቀበለው በብዙ የተለየና የራቀ ነው ፡፡ አንድ ሰው አንድን መጽሐፍ ሲጽፍ ሁልጊዜም ለሆነ ዓለማ ማስፈጸሚያ ነውና የምናነበውን ጠንቅቀን እንመርምር ፡፡
ስለ እራሴም ፡- ኢየሱስ ፣ ጠፍቶ የተገኘ ልጅ በማለት ያስተማረው በፈጣሪነቱ እኔ ታይቼው ይመስለኛል ፡፡ በዓለማዊው ነገር አቅሜ የሚፈቅደውን ተጉዤ ፣ ብዙውን ቃኝቼ የተመለስኩ ነኝ ፤ አምላክ ከሚለው ትንሽ ቃል የሌለበት የሩጫና የውድድሩ ዓለም ፡ ጠቢቡ እንዳለው ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ መሆኑን በመገንዝብ ፣ በመጨረሻ ዘመን ላይ ሃየማኖትን ለማሰብ የተነሳሁ ተራ ምእመን ነኝ ፡፡ ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች እኔም ቤት አሉ ፡፡ እነዛን ሁሉ ወደ ውጭ አውጥቼ ብዘራቸው መርዝ የመርጨት ያህል ይሆናል፡፡ ወዳጄንም የምመክረህ እንዲህ የሆድ ቁርጠት የሚፈጥሩትን ነገሮች በሆድ መያዝ እንድትለማመድ ነው፡፡ ሰው የለንማ ፤ ሰው እስከሚገኝ ከመያዝ ሌላ ታድያ ምን ይደረጋል?
ጊዜ ካለህ http://en.wikipedia.org ሰርች ኢንጅን ላይ Original sin, Mariology, Immaculate conception, Mary … ብለህ ብታስገባ ፣ ስለሁሉም ብዙ የሚነበብ የተለያየ ኢንፎርሜሽን ታገኛለህ ፡፡ የእምነት መሠረት ግን ከዛ ውስጥ አይወጣም ፡፡ የተደበላለቀ መጠጥ አንድ ሰው ቢጠጣ እንደሚገጥመው ትርፉ ሥካር ብቻ ነውና በጥንቃቄ ተመልከተው ፡፡
ይቀጥላል
አባ ሣህለ ሚካኤል /አንተም ተከትለህ ያስተጋባሃቸውን/ ለምን ጉዳይ እነዚህን ጥያቄዎች ለእኛ ምንም ለማናውቀው ምእመን እንደ ደነቀሩብን የሚከተለውን በማንበብ ምናልባት ተልዕኮ ካለው ለመረዳት ሞክር፡፡
Delete“Roman Catholics believe in the Immaculate Conception of Mary, as proclaimed Ex Cathedra by Pope Pius IX in 1854, namely that she was filled with grace from the very moment of her conception in her mother's womb and preserved from the stain of original sin. The Latin Rite of the Roman Catholic Church has a liturgical feast by that name, kept on 8 December. The Eastern Orthodox reject the Immaculate Conception principally because their understanding of ancestral sin (the Greek term corresponding to the Latin "original sin") differs from that of the Roman Catholic Church, but also on the basis that without original sin.” ---- http://en.wikipedia.org/wiki/Mary_(mother_of_Jesus)
በተቻለኝ ከዚህ በቀደመው ጽሁፌ በተዛማጅ ለጠየቅካቸው መልስ ለመስጠት በማለት ተደናብሬአለሁ ፡፡ ከዚያ የተሻለ አመለካከት የለኝም ፡፡ ገፍተህ ከመጣህ ግን ፣ መልሴ አትጠራጠር ፤ እመን ብቻ ትድናለህ የሚል ነው፡፡ ከዚህ ከላይ ከተገለጸው ጽሁፍ ስነሳ የአዳም በደልን ምንነት ማወቅ ለእኛ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመን የቤት ሥራ ሊሆን አይገባም ፡፡ አዳም አምላክን ማሳዘኑን ፣ በእባብ ምክንያት ከአምላክ ፈቃድና ዕቅድ መኰብለሉን ቤተ ክርስቲያናችን አስተምራናለች ፡፡ ይኸ አለመታዘዝ ያመጣውንም ፍርድ ለመታደግ አምላክ በአዘኔታው ሰው ሆኖ አዳነንም ብለን እናምናለን ፡፡ ሌሎች በራሳቸው ቤት የተነሳባቸውን ጥያቄ ወደእኛም ቤተ ክርስቲያን ለማስተላለፍ የፈለጉት ቡድንና ወገን ለማበጀት ይመስለኛልና ይበቃኛል ፡፡
ስለ ድንግል ማርያም መፈጠር ክብረ ነገሥት በገጽ 71– ምዕራፍ 68 ፡ 1-33 የማቴዎስ ወንጌል የሚጠቅሰውን የትውልድ ሃረግ የመሰለ ነገር ይገልጻል ፤ ቆራርጨ ለዓይነት የወሰድኩት ማስታወሻ ይህን ይላል፡፡
“አዳኙ ከዚህ እንደሚመጣና ከአባቶቻችሁ ከአንተና ከዘርህም ጋር እንደሚያድንህ ምልክት ይሆንልሃል ፡፡ በመምጣቱም ከሄዋን በፊት መድኃኒታችሁ እንደ ባህር እንቁ ከአዳም ሆድ ውስጥ ተፈጠረች ፡፡ ሄዋንንም ከአዳም ከጎኑ አጥንት በፈጠራት ጊዜ ወደ ቃየንና ወደ አቤል አልወጣችም ፡፡ ከአዳም ሆድ ወጥታ ወደ ሶስተኛው ወደ ሴት ሆድ ገባች እንጂ ፡፡ ከእሱም ይህች እንቁ በኩር ወደ ሆኑት ስትሄድ እስከ አብርሃም ደረሰች ፡፡ ከአብርሃም ወደ ንፁህ ይስሃቅ ገባች እንጂ ወደ በኩሩ ወደ እስማኤል አልወጣችም ፡፡ ከይስሃቅም ወደ ያእቆብ ገባች ፤ ከያዕቆብም ወደ የዋሁ ይሁዳ ፣ ወደ ትእግሥተኛው ፋሬስ ፣ ከዛም እስከ እሴይ ድረስ በየበኩሩ ተላለፈች ፡፡ ቀጥሎም ወደ ዳዊት ከዛም ወደ ሮብአም ሄደች ፡፡ እነሱ በክህደታቸውና በክፋታቸው ይሰቅሉታልና ፤ ባይሰቀል ኑሮ መድሃኒታችሁ ባልሆነ ነበር ፡፡ ያለ ኃጢአቱ ይሰቀላል ፤ ያለጥፋትም ይነሳልና ፡፡ ...”
“በዚህችው እንቁ የነፁ ይሆናሉና ፡፡ እሷ የተቀደሰችና የነፃች ናትና በእሷ ትቀደሳላችሁ ፡፡ ትነፃላችሁም ፡፡ ዓለሙን ሁሉ ስለ እሷና ስለ ፅዮን ፈጥሯታልና ፡፡ ፅዮን ግን በበኩርህ ነበረች ፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝቦችም እስከ ዘላለም መድኃኒታቸው ትሆናለች ፡፡”
“ዘመኑም በደረሰ ጊዜ ይህችው እንቁ ከዘርህ ትወለዳለች ፡፡ ከፀሃይ ሰባት እጅ የነፃች ናትና ፡፡ አዳኙም ከመንበረ መለኮቱ ይመጣል ፡፡ በላዮም ላይ ያድራል ፡፡ ስጋዋንም ይለብሳል /ይዋሃዳል/”
ክብረ ነገሥት ገጽ 77 -- 71፡3
“ከማርያም ፣ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ፣ ከአምላክ የተገኘ አምላክ ፣ የእግዚአብሔር ቃል ይሄውም ከአብ የመጣው ወልድ ተወለደ ፡፡ ፍጥረቱንም ከሲኦልና ከሰይጣን እጅ ከሞትም አዳነን ፡፡ ያመነውንም ሁላችንንም ወደ አባቱ ሳበን ፡፡ ወራሾቹ እንሆን ዘንድ ወደ ሰማያዊው ዙፋን ሳበን ፡፡ እሱ ሰውን ወዳጅ ነውና ፡፡ ለእሱም ለዘላለሙ ምስጋና ይገባል ፡፡”
ወስብሐቱ ለእግዚአብሔር
kibir lesimua hulem yihun amlakin nedinigilina welida yealemin atiyat yatefach emebizzuhan tewahido orthodoxn titebiq amen!!!
ReplyDeleteI appreciate your concern and effort. I found what is written on page Viii and said that Mary...born under the shadow of origional sin..''.But I couldnot find what you have cited on page 61.Any ways what the Pop did is this is insulting the holy spirit.So better for him to confess.
ReplyDeletei would suggest the organiser of this blog presenting details of this issue from church scholars. we all are dying of hanger from words of GOD. please, please would you put one separate topic to entertain questions like this.
ReplyDeletethanks,
“አዳኙ ከዚህ እንደሚመጣና ከአባቶቻችሁ ከአንተና ከዘርህም ጋር እንደሚያድንህ ምልክት ይሆንልሃል ፡፡ በመምጣቱም ከሄዋን በፊት መድኃኒታችሁ እንደ ባህር እንቁ ከአዳም ሆድ ውስጥ ተፈጠረች ፡፡ ሄዋንንም ከአዳም ከጎኑ አጥንት በፈጠራት ጊዜ ወደ ቃየንና ወደ አቤል አልወጣችም ፡፡ ከአዳም ሆድ ወጥታ ወደ ሶስተኛው ወደ ሴት ሆድ ገባች እንጂ ፡፡ ከእሱም ይህች እንቁ በኩር ወደ ሆኑት ስትሄድ እስከ አብርሃም ደረሰች ፡፡ ከአብርሃም ወደ ንፁህ ይስሃቅ ገባች እንጂ ወደ በኩሩ ወደ እስማኤል አልወጣችም ፡፡ ከይስሃቅም ወደ ያእቆብ ገባች ፤ ከያዕቆብም ወደ የዋሁ ይሁዳ ፣ ወደ ትእግሥተኛው ፋሬስ ፣ ከዛም እስከ እሴይ ድረስ በየበኩሩ ተላለፈች ፡፡ ቀጥሎም ወደ ዳዊት ከዛም ወደ ሮብአም ሄደች ፡፡ እነሱ በክህደታቸውና በክፋታቸው ይሰቅሉታልና ፤ ባይሰቀል ኑሮ መድሃኒታችሁ ባልሆነ ነበር ፡፡ ያለ ኃጢአቱ ይሰቀላል ፤ ያለጥፋትም ይነሳልና ፡፡ ...”
ReplyDelete“በዚህችው እንቁ የነፁ ይሆናሉና ፡፡ እሷ የተቀደሰችና የነፃች ናትና በእሷ ትቀደሳላችሁ ፡፡ ትነፃላችሁም ፡፡ ዓለሙን ሁሉ ስለ እሷና ስለ ፅዮን ፈጥሯታልና ፡፡ ፅዮን ግን በበኩርህ ነበረች ፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝቦችም እስከ ዘላለም መድኃኒታቸው ትሆናለች ፡፡”
“ዘመኑም በደረሰ ጊዜ ይህችው እንቁ ከዘርህ ትወለዳለች ፡፡ ከፀሃይ ሰባት እጅ የነፃች ናትና ፡፡ አዳኙም ከመንበረ መለኮቱ ይመጣል ፡፡ በላዮም ላይ ያድራል ፡፡ ስጋዋንም ይለብሳል /ይዋሃዳል/”
መምህሮቼን ቃለ ህይወት ያሰማልኝ ፡፡
አቡነ ጳውሎስ ካቶሊክ ተከታይ መሆናችዉን ይሰማዉት የዛሬ 20 አመት ነዉ፡፡ እናንትስ???
ReplyDeleteIf you read the points that Abune Paulos wrote in his thesis, it does not make him a catholic.
DeleteYes, you are right. He was repeatedly accused by our father"Aleka Ayalew" because he(the so called pop) wrote such rubbish things. Let us give time to God for such 'Tekula' to be the end of his crone.
ReplyDeleteBefore judging others you should try to know what others teach. The teachings of the Catholic Church should be learned from what the Catholics have written rather than what others said about the Catholic Church. Before judging whether Aba Paulos is a Cathoic or not you should understand what the Catholic Church teaches. Please, act like Christians. Read with an open mind what the Catholic Church says through her Books of Catechism. Then you will be able to say what you have to say in a very logical manner.
DeleteIf you want to solve the problem in EOTC the major problem is lack of knowledge among its clergy and laity. You guys have closed the door for knowledge over yourselves. You only want to hear what you would like to hear. Stereo types and prejudices will never let you to grow up; instead it pushes you down the cliff of ignorance.
To me, talking about St. Mary being born without original sin is not as important as it sound. Because history teaches us that both in orthodox and catholic church believers were divided just because of this topic. Even Ethiopian orthodox priest's have two different ideas. When some of them said she (St. Mary) born with original sin and the Holy Spirit sanctify her and others do not agree with that.
ReplyDeleteTwo point I want to make is that:
1. The question is not about when she became holly. It is if she is holly or not? I believe whether she is holly (free from sin (original or other)) before she was born or not is not the point. The point is she was holly when she born Jesus Christ and she is holly right now.
2. The other question, if you people said that St. Mary did not pass through the original sin, then why did Jesus came to this world? The bible tell us that all generation of Adam were under the sin (whether original or personal). If St. Mary did not pass through the original sin, then why she did not crossified and saved.
Anyways, I do not encourage to confuses yourself. I hope you will agree with my first point and live by it. Having faith in the name of Jesus Christ and applying his love in our day to day life will only makes us to be saved not arguing about the original sin.
Oh God please keep me from a person who lives with out any religious knowledge (like this blogger)
DeleteIf the Holy Virgin is free from Original Sin why did she die
ReplyDeleteሰው በስጋ ይሞታልበነፍስ ግን ህያው ነው::
Deleteለምን እየሱስ ክርስቶስ ሞተ????
ሰው በስጋ ይሞታልበነፍስ ግን ህያው ነው::
Deleteለምን እየሱስ ክርስቶስ ሞተ????
እግዚኣብሄር መልስ ይስጠን እንጂ ሰውማ የየራሱ ልተነትን እየ መኮረ ነው
ReplyDelete