Tuesday, March 20, 2012

ዝቋላ በሰላም አድሯል




(አንድ አድረገን መጋቢት 12 2004ዓ.ም)፡- ዝቋላ በሰላም አድሯል ሁኔታዎችም እየረገቡ ናቸው ፤ በተከታታይ 4 ቀናት ውስጥ 500 ሄክታር ቦታ እሳቱ ማጥቃቱን ለማወቅ ችለናል ፤ ጠቅላላ ጠፍቷል ብለን የምንቀመጥበት ጊዜ አይመስለንም ፤ አንጻራዊ ለውጥ ቢኖረውም እሳቱ ዳግም እንደማይነሳ ማረጋገጫ ማግኝት ግን አይቻልም ፤ በጣም በርካታ ሰው ወደ ቦታው በትላንትናው እለት እንደጎረፈ ፤ ከሰው ብዛትም የተነሳ ግጭቶች እንደተነሱ ለማወቅ ችለናል ፤ በአሁኑ ሰዓት  ነገሮች እየተረጋጉ ነው፡፡

በተያያዘ ዜና በትላንትናው የኢቲቪ የዜና ዘገባ የዋልድባን ጉዳይ አንስቶ የውሸት ዜና አቅርቧል ፤ ከቤተክህት በኩል ተወክለው የሄዱት ሰው አፋቸውን ሞልተው ስኳር ልማቱ ከገዳሙ ጋር ምንም የሚያያይዘው ነገር እደሌለ ተናግረዋል ፤ ተሰበሰቡ የተባሉት ሰዎች የገዥው ፓርቲ ደጋፊዎች እና ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ጥቂት መነኮሳት ብቻ ነበሩ ፤ ይህ ጸረ ሰላም አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች አሉባልታ ነው ብለዋል ፤ ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫቸውን አንብበዋል፡፡

1 comment:

  1. እኔ ግን የእሳቱን ባህሪይ እና አነሳስ አይቻለሁና አንድ ሳምንት ሳይሆነው ስሜታዊ ሆነው በስልክ ተነግሮን በተዘገበ ወሬ አላምንም፡፡ እሳቱን ሰኞ እለት 11፡00 አካባቢ በቁጥጥር ስር ካዋልነው በኋላ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ የተነሳበትን ሃይልና አቅጣጫ ላይ እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል ሲባል በቀላሉ ይከብዳል፡፡ ጥበቃ ሲያደርጉ የነበሩ ወጣቶች ያደረባቸው ብርድና ርሀብ አድክሟቸው ለእረፍት እንደሄዱ ከ5 ኪሎ ሜትር ርቀት አካባቢ ያለውን ደን በልቶ የተከለለውን የደን ክፍተት አልፎ እንዳይደርስበት ከተከለለው ደን 30 ሜትር ያህል ደን እንዳቃጠለ ላየ እሳቱ በቁጥጥር ስር ውላል አይልም፡፡ ስለዚህ በዚሀ ተዘናግተን ርስታችንን እንዳናጣ እፈራለሁ፡፡

    ReplyDelete