Wednesday, March 14, 2012

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ


 ከአሐቲ ተዋሕዶ የተወሰደ
አጽራረ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለማዳከም በተጠና እቅድ ይንቀሳቀሳሉ:: ከእቅዶቻቸውም መካከል ለቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርት እና የጸሎት ማዕከል በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ታላላቅ ገዳማትን የሚጠፉበት ሁኔታ ማመቻቸት ነው:: ከእነዚህ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያኒቷ የአስተምህሮ ማዕከላት መካከል አንዱ ገዳመ ዋልድባ ነው:: እነዚህን የትምህርት ማዕከላት ገዳማት ለማጥፋት በተለያየ ግዜ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ሞክረው ነበረ:: ነገረ ግን በቀደሙት አባቶቻችን ፍጹም ተጋድሎ ለዚህኛው ትውልድ አስተላልፈው አልፈዋል:: 

ከጥንታውያን ታላላቅ ገዳምት ውስጥ የምትመደበው የዋልድባ ገዳም ህልውና አስጊ ደረጃ ላይ መሆኑን የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል:: አሁን በእኛ ዘመን መንግስ ልማት ተገን በድረግ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን እቅድ እውን እያደረገላቸው ይገኛል:: ዋልድባ ለብዙ ዘመናት በአባቶቻችን ተጋድሎ ተከብሮ እኛ በአደራ እንደተረከብነው ሁሉ ለሚቀጥለው ትውልድ እስከነ ሙሉ ይዘቱ በአደራ የማስተላለፍ ግዴታ አለብን::

 ስለገዳማችንና ስለ እነዚህ አባቶች ግድ ሊለን ይገባል

ገዳሞቻችን የማፍረስ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን እቅድ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በታላላቅ ገዳማት አካባቢ የሚደረጉ ተግባራት ገዳማቱን ያማከለ ጥናት ሳይጠና መከናወን የለበትም:: መንግስት የገዳማቱ አስተዳደር ሳያማክል ያጠናው ጥናት ተገቢ አይደለም:: በገዳማቱ አካባቢ የሚደረጉ ልማቶች ለገዳማቱ ህልውና አስጊ እንዳይሆን መንግስት መከላከል አለበት::

አሁን በዋልድባ ገዳም እየተደረገ ያለው የልማት እንቅስቃሴ ለገዳሙ ህልውና አስጊ መሆኑን የገዳማቱ አባቶች የአቤቱታ ጥሪ ማስተላለፋቸው በመገናኛ ብዙኃን ተገልጾልናል:: መንግስት የአባቶች አቤቱታ ችላ በማለት እንቅስቃሴውን ቀጥሎበታል::

ይህንን የገዳማቱ አባቶች አቤቱታ የሰሙ ቅናተ ቤተ ክርስቲያን ያደረባቸው/የበላቸው ወንድሞች የአቤቱታ ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ የዓለማችን ከተሞች ለማድረግ እቅድ ይዘዋል:: የመጀመርያው ሰላማዊ ሰልፍ የአሜሪካ መንግስት መቀመጫ በሆነችው በዋሽንግተን ዲሲ ማርች 26፣2012 ወይም መጋቢት 17፣2004 ከጠዋቱ 3 ሰዓት፤  ይደረጋል::  ሰልፉ ላይ ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን አማኝ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ልዩነት ሳይገታቸው በአንድነት ድምጻቸውን እንዲያሰሙ አዘጋጆቹ የአደራ ጥሪ አስተላልፈዋል::

የታላላቅ ገዳማት ህልውና መጠበቅ ለቤተ ክርስቲያናችን ህልውና መጠበቅ ስለሆነ በተለያየ ዘርፍ የተከፋፈሉት የቤተ ክርስቲያኒቷ ልጆች በዚህ እንዲተባበሩ አሐቲ ተዋሕዶና አንድ አድርገን ጥሪያቸውን ያስተላልፋሉ:: 

እግዚአብሔር አሐቲ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን!!!
መጽሐፈ አስቴር 4.. .. . . . .ያንብቡት
1 መርዶክዮስም የተደረገውን ሁሉ ባወቀ ጊዜ ልብሱን ቀደደ፥ ማቅም ለበሰ አመድም ነሰነሰ፥ ወደ ከተማይቱም መካከል ወጣ፥ ታላቅም የመረረ ጩኸት ጮኸ።
2 ማቅም ለብሶ በንጉሥ በር መግባት አይገባም ነበርና እስከ ንጉሡ በር አቅራቢያ መጣ።
3 የንጉሡም ትእዛዝና አዋጅ በደረሰበት አገር ሁሉ በአይሁድ ላይ ታላቅ ኀዘንና ጾም ልቅሶና ዋይታም ሆነ ብዙዎችም ማቅና አመድ አነጠፉ።
4 የአስቴርም ደንገጥሮችዋና ጃንደረቦችዋ መጥተው ነገሩአት፥ ንግሥቲቱም እጅግ አዘነች ማቁንም ለውጦ ልብስ ይለብስ ዘንድ ለመርዶክዮስ ሰደደችለት እርሱ ግን አልተቀበለም።
5 አስቴርም ያገለግላት ዘንድ ንጉሡ ያቆመውን አክራትዮስን ጠራች እርሱም ከጃንደረቦች አንዱ ነበረ፥ እርስዋም ይህ ነገር ምንና ምን እንደ ሆነ ያስታውቃት ዘንድ ወደ መርዶክዮስ እንዲሄድ አዘዘችው።
6 አክራትዮስም በንጉሥ በር ፊት ወደ ነበረችው ወደ ከተማይቱ አደባባይ ወደ መርዶክዮስ ወጣ።
7 መርዶክዮስም የተደረገውን ሁሉ፥ አይሁድንም ለማጥፋት ሐማ በንጉሡ ግምጃ ቤት ይመዝን ዘንድ የተናገረውን የብሩን ቍጥር ነገረው።
8 ለአስቴርም እንዲያሳያት ለመጥፋታቸው በሱሳ የተነገረውን የአዋጁን ጽሕፈት ቅጅ ሰጠው ወደ ንጉሡም ገብታ ስለ ሕዝብዋ ትለምነውና ትማልደው ዘንድ እንዲነግራትና እንዲያዝዛት ነገረው።
9 አክራትዮስም መጥቶ የመርዶክዮስን ቃል ለአስቴር ነገራት።
10 አስቴርም አክራትዮስን ተናገረችው፥ ለመርዶክዮስም እንዲህ የሚል መልእክት ሰጠችው።
11 የንጉሡ ባሪያዎችና በአገሮችም የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን ሳይጠራ ወደ ንጉሡ ወደ ውስጠኛው ወለል የሚገባ ሁሉ፥ በሕይወት ይኖር ዘንድ ንጉሡ የወርቁን ዘንግ ካልዘረጋለት በቀር፥ እርሱ ይሞት ዘንድ ሕግ እንዳለ ያውቃሉ እኔ ግን ወደ ንጉሡ ለመግባት ይህን ሠላሳውን ቀን አልተጠራሁም።
12 አክራትዮስም የአስቴርን ቃል ለመርዶክዮስ ነገረው።
13 መርዶክዮስም አክራትዮስን፦ ሂድና ለአስቴር እንዲህ በላት አለው። አንቺ። በንጉሥ ቤት ስለ ሆንሁ ከአይሁድ ሁሉ ይልቅ እድናለሁ ብለሽ በልብሽ አታስቢ።
14 በዚህ ጊዜ ቸል ብትዪ ዕረፍትና መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?
15 አስቴርም እንዲህ ብሎ ለመርዶክዮስ እንዲመልስ አዘዘችው።
16 ሄደህ በሱሳ ያሉትን አይሁድ ሁሉ ሰብስብ፥ ለእኔም ጹሙ ሦስት ቀን ሌሊቱንና ቀኑን አትብሉም፥ አትጠጡም እኔና ደንገጥሮቼ ደግሞ እንዲሁ እንጾማለን ምንም እንኳ ያለ ሕግ ቢሆን ወደ ንጉሡ እገባለሁ ብጠፋም እጠፋለሁ።
17 መርዶክዮስም ሄዶ አስቴር እንዳዘዘችው ሁሉ አደረገ።

10 comments:

  1. Kidanemariam Ze Did LibanMarch 14, 2012 at 3:45 AM

    Min Waga alew begna hager lay selamawi self yemdireg mebtum wenewum yelenim

    ReplyDelete
  2. mengest yalfal yewdkal sewem yemotal bet kiresityan EN gedamat LezeLaLem yenoralu.... Egezyabher Ethiopian yebark.... HAYEL YEGEZYABHER NEWEEE.....!!!

    ReplyDelete
  3. እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ያስፈጽመን፡ ያባቶቻችን አምላክ ተዋህዶን ይጠብቅ ፡ወላዲተ አምላክ በምልጀዋ አትለየን፡ አሜን፡፡

    ReplyDelete
  4. Amlak Kidusan gedamachenen Yitebkelen!!!

    ReplyDelete
  5. ትላንት የነበረች ዛሬም ያለች ወደፊትም የምትኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
    እግዚአብሔር ይጠብቅሽ፡፡

    ReplyDelete
  6. egzeabher bat krstyanen ytabek

    ReplyDelete
  7. abetu agerachinin tebk

    ReplyDelete
  8. iske meche ,manew haymanotachinin yemiastebikew,amlak hoy yikir belen

    ReplyDelete
  9. Lemin endezih aynet poster sytachihu lay post adirgachihu ethiopia wust yalutin christianoch selamawi self atiterum. I will be the first to come.

    ReplyDelete