Monday, March 12, 2012

ነፍሴን በሐዊረ ሕይወት ደስ አሰኝኋት


(አንድ አድርገን መጋቢት 3 2004ዓ.ም)፡-ቀኑ መግቢት 2 2004 ዓ.ም ዕለተ እሁድ ሲሆን ማህበረ ቅዱሳን ሐዊረ ህይወት በሚል ስያሜ ለሶስተኛ ጊዜ ጉዞ የሚያደርግበት ቀን ነው ፤ እኔም ቲኬቱን 105 ብር ገዝቼ የህይወት ጉዞውን ለመሄድ ጓጉቻለሁ ፤ በጠዋት ከቤቴ ብወጣም ቲኬቱ ላይ ባለው ሰዓት 12፡30 ቅድስት ማርያም 5 ኪሎ መድረስ አልቻልኩኝም ፤ ቦታው ላይ 30 ደቂቃ አርፍጄ ስደርስ ብዙ መኪኖች ምእመኑን ጭነው መንቀሳቀስ ጀምረዋል ፤ ጓደኞቻቸውን የሚጠብቁ ጥቂት ምዕመኖች ደግሞ የጠዋቱን ቅዳሴ እያስቀደሱ ይሁን ሰው እየጠበቁ በማይታወቅ መልኩ ቤተክርስትያን በር ላይ ተኮልኩለዋል ፤ የማህበሩ የጉዞ ኮሚቴ አባላት ለጉዞው መሳካት ምእመኑን እየለመኑ ነበር ወደ አውቶቡስ ውስት ሲያስገቡ የነበሩት ፤ ያው የኛ ነገር ቀጠሮ ላይ ችግር ስላለብን ምንም አይደለም ብዬ አልፌዋለለሁ ፤ እኔም የምጠብቀውን ሰው ካገኝሁ በኋላ ለመሳፈር አይኔን ወደ ኋላ መስመር አውቶቡሶች በተሰለፉበት በኩል ብልከው መጨረሻውን ማየት አልቻልኩም ፤ ከፊት ለፊቴ ያለው አውቶቡ 26 ቁጥር መንቀሳቀስ ጀምሯል ፤ ምን ያህል ሰው እና ምን ያህል አውቶቡስ እንደተዘጋጀ ለማወቅ ለጊዜው አልቻልኩም ፤ በጣም በጠዋት ማህበሩ ከሚያሰራው ህንጻ ስር ከአስር የማያንሱ ላፕቶፖች ሰልፍ ወጥተዋል  እነዚህ ደግሞ በጠዋት ምን ሊሰሩ ነው የወጡት ? ብዬ ራሴን ጠየኩኝ ፤ ለካ የጉዞውን ሂደት በድህረ-ገፅ ፤ በፓልቶክ ፤ በፌስቡ እና ዘመኑ በፈቀደው የቴክኖሎጂ አይነት ለማስተላለፍ ስራቸውን ጨርሰው ለጉዞ የተዘጋጁ መሆኑን አወኩኝ ፡፡ እንዴት ደስ ያሰኛል መጽሀፉስ ጊዜውን ዋጁ አይደል የሚለው ፤ ይህንስ ፎቶ ማንሳት አለብኝ ብዬ ከእጄ በማትጠፋው ካሜራዬ ውስጥ ለናንተው ለማሳየት ከተትኳቸው ፤ እኔ እነሱን ፈዝዤ ሳይ አውቶቡሶቹ እየሞሉ መሄዳቸውን አላቋረጡም ፤ እኛስ በየትኛው አውቶቡስ ነው የምንሄደው ብለን ወደ ኋላ ቢያንስ 20 አውቶቦሶችን እየቆጠርን ሄድን መጨረሻውን ግን ልናገኝው አልቻልንም ፤ ከ20 አውቶቡሶች በምዕመን የተሞላ ለአምልኮተ እግዚአብሔር የሚሄድ ሰው በኋላ 21ኛ አውቶቡስ ቁጥር 68ተኛ አውቶቡስ ተራችን ሆኖ ገባን፡፡ አውቶቡሶቹ ተራቸውን የተበቁ አይደሉም ፤ እኔ በህይወቴ ብዙ አጭርም ረዥም ጉዞ ሄጃለሁኝ ነገር ግን 5000 ሺህ በላይ ምዕመን ከ100 በላይ አውቶቡሶች የሄዱበት ጉዞ ግን ሲያጋጥመኝ ይህ የመጀመሪዬ ነው፡፡


አውቶቡሳችን እስኪንቀሳቀስ ድረስ ሀሳቤ ይህን ሁሉ ሰው እንዴት ሊያስተዳግዱት ነው?  ምን ላይስ ይቀመጣል?  ለምሳ ዝግጅት ላይ እንከን እንዳፈጠር ሰዎች እንዳያማርሩ በመስጋት እኔ ያዘጋጀሁት ይመስል ሀሳብ ገብቶኛል፡፡ የአውቶቡሳችን አስተናባሪ ሁሉን ሰው መዝግቦ ቲኬት መያዙን ካረጋገጠ በኋላ ‹‹አባታችን ሆይ›› የሚለውን ታላቅ ጸሎት አድርገን ጉዞ በኬ ደብረ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ፤ ከአዲስ አበባ ተነስተን 60 ኪሎ ሜትር ያህል የምትርቀውን የበኬ ወረዳ ለመድረስ ከ100 በላይ ትልልቅ አውቶቡሶች ተከታትለው ሲሄዱ ለተመለከታቸው ለትልቅ የቤተክርስያን ጉባኤ እንደሚሄዱ ለማወቅ ጊዜ አይወስድበትም ፤ በዕለተ ሰንበት በእግዚአብሔር ቤት ቁጭ ብሎ ለመማር ይህን ጉዞ መታደምም እድለኝነት ነው ፤ ከ5ኪሎ በተነሳት ከ1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኋላ    በኬ ደብረ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ደርሰናል ፤ ቀድመውን የተነሱት አውቶቡሶች ምዕመኑን አውርደው በመስመር ተደርድረው ላያቸው የሚገርሙም ጭምር ናቸው ፤ ወደ ውስጥ ስንዘልቅ በር ላይ ቲኬት እያዩ የሚስገቡ አስተናባሪዎች ጉባኤው ላይ ያልተመዘገቡ ሰዎች ገብተው ችግር እንዳይፈጠር በጥንቃቅ ሁሏንም ልቅም አድርገው እያዩ ሲያስገቡ ነበር ፡፡ ግቢ ውስጥ የተጣለው በጣም ትላልቅ ከ12 በላይ የሆነ ነጭ ሸራ በዓይን የግቢውን ግማሹን ክፍል ሸፍኖት ይታያል ፤ ሁሉም ሴቶቹ ወንዶቹም ነጭ በነጭ ክርስትያናዊ አለባበስ ለብሰው ሲመለከቱ ልብዎት በሀሴት ይሞላል ፡፡ ከግቢው በስተግራ በኩል በርካታ የአብነት ተማሪዎች ከአስተማሪዎቻቸው ጋር ሆነ ይማራሉ ፤ በጉባኤ ላይ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው የቤተክርስትያናችን ሊቃውንት ፤ ከሁለት ዓመት በፊት ክርስትና የተነሱ የከረዩ ማህበረሰብ ባላባቶች ፤ ምዕመናን ቦታ ቦታቸውን ይዘው የፕሮግራሙን መጀመር በጉግት ይጠባበቃ፤ እኔ ግን ለብሎጌ የሚሆን ፎቶ ለማንሳት ጊቢውን ስዞር ቦታ ሞልቶ ኖሮ ወደ ተጣሉት ሸራዎች ስገባ ወንበሩ ከአፍ እስከ ገደቡ ሞልቶ ኖሮ አይደለም ባዶ ወንበር ድንጋይ መጣያ ክፍት ቦታ አይታይም፤ በራሴ ስህተት መሬት ለመቀመጥ ተገደድኩኝ ፤ የምትወጣውን ፀሀይ ግን ልቋቋማት እንደማልችል አስቀድሜ አውቄዋለሁኝ ፤የወጣችው ፀሀይ ከዛፍ ላይ ይመስል አናት ሰንጥቃ የምትገባ ነበረች፡፡

የመርሀ ግብሩ የመጀመሪያ ክፍል ትምህርተ ወንጌል በዲያቆን ብርሀኑ አድማስ አማካኝነት ‹‹የዮሴፍ ደሞዝ›› የሚል አርዕስት በጣም መሳጭና ከ5000 ምዕመን በላይ ጸጥ ያሰኝ ትምህርት የታሪኩን ፍሰት ጠብቆ ዮሴፍ ወንድሞቹ ከሸጡት ጀምሮ እስከ ኤጲፋራ ቤት ድረስ ያለውን ታሪክ በአጭሩ ገላጭ እና ጆሮን በሚይዝ መልኩ የዮሴፍን ታማኝነት ፤ ታዛዥነት እና ፍቅሩን ፤ ከዮሴፍ እረፍት በኋላ 615,000 ሺህ የሚሆኑ ወገኖቹ እስራኤላውያን ለ215 ዓመት ያህል በግብጽ ውስጥ በሱ በረከት መኖራቸውን አስተማረን ፡፡ ቀጥሎም ስውን ቀና ብላ ማየት የማትችለውና አይናፋሯ ዘማሪት ማርታ ሁለት ዝማሬዎችን አቀረበች ፤  ስለ በኬ ደብረ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ታሪክ እና በደብሩ ስለተሰሩ ስራዎች አሁን ሀላፊነታቸውን የማላስታውሳቸው አባት በጣም ገላጭና ዝርዝር በሚባል መልኩ አቀረቡ ፤ በዚህ መሀል ብጹእ አቡነ እንድርያስ እና ብጹ አቡነ ቆዎስጦስ በመምጣታቸው ምዕመኑ ለአባቶች የሚገባውን ክብር በመስጠት ቆሞ ተቀመጡ እስኪባል ድረስ በመጠበቅ ተቀበላቸው ፤ ከምሳ በፊት ባለው የመጨረሻው መርሀ ግብር አቡነ እንድርያስ ረዘም ያለ ትምህርት አስተምረው የከሰዓት በፊት ዝግጅቱ በምሳ ተዘጋ፡፡

ምሳ ሰዓት ላይ በመጀመሪያ አባቶች ወደ ተዘጋጀላቸው ማረፊያ ሄደው ምግቡን እንዲባርኩ ሲሄዱ አቡነ ቆዎስጦስ በሁኔታው በመገረም ደስ ተሰኝተው ‹‹እግዚአብሔር ይባርካችሁ›› ‹‹ጸጋውን ያብዛላችሁ›› ‹‹እግዚአብሔር ይባርካችሁ›› ‹‹ጸጋውን ያብዛላችሁ›› በማለት ባለቋረጥ ሲባርኩ ፊታቸው ላይም የሚያስደስት ነገር ይነበብባቸው ነበር ፤ ብጹአን አባቶች ደስ የሚሰኙበት ስራ መስራት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኝት ነው ፤ እኔ በዚህ መሀከል በአባታችን በአቡነ ቆዎጦስ   እንደ መባረክ ደስ የሚያሰኝ ፊታቸውን ፎቶ ለማንሳት ስቦዝን ነበር ፤ ሳባረክ ቀረሁ እንጂ (ቦታው ላይም ደርሶ መመለስ በእግዚአብሔር መባረክ ነው፡) ፤ እኔ በበኩሌ ለአቡነ ቆዎስጦስ ባለፈው 2003 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ምርጫ ጊዜ ቅዱስ ሲኖዶስ አቡኑን ሲመርጣቸው ‹‹ እኔ ከአሁን በኋላ ገዳም ገብቼ ለሀገሬ እና ለቤተክርስትያን መጸለይ ነው የምፈልገው እንጂ ይህን አይነት ሹመት አልፈልግም›› ካሉ በኋላ ለሳቸው የተለየ ቦታ ነው ያለኝ ፤ ለካ በዚህም ዘመን እንዲህ የሚሉ አባቶች አሉ? ለካ በእኛ ዘመን ስለኛ ግድ የሚላቸው እረኝነታቸውን ለመወጣት የሚተጉ አባቶች አሉ?  ለካ በእኛ ዘመን ሹመቱ ይቅርብኝ ገዳም መግባት ነው የምንፈልገው የሚሉ አባቶች ከመካከላችን አሉ ፤ ሁሉ የማይገባውን ወንበር ለመቆናጠጥ ሲጥር ‹‹ዓለም ለምኔ›› በቃኝ የሚሉ አባቶች አሉን ፤ እግዚአብሔር ይመስገን ማለት እንጂ ሌላ ምን ይባላል ፤ እርስዎን የመሰለውን አባቶች ያቆይልን ፤

ምሳ ሰዓት ደርሷል ፤ በጣም ብዙ ጠረጴሳዎች ለምሳ በሶስት ዓይነት ወጥ ዳቦ እና፤ በአቢሲኒያ የተፈጥሮ ውሀ ተጨናንቀዋል ፡፡ ለዚህ ጉባኤ መሳካት 2000 በላይ የሆኑ ባለ 500 ሚሊ ሊትር የሆኑ ውዎችን አቢሲኒያ ውሀ በነፃ እንደሰጣቸው ወደ መጨረሻ በቀረበው ሪፖርት ማወቅ ችያለሁ፡፡ በጠጨማሪም የተጣለው ድንኳን አንዲት ክርስትያን ‹‹እቃዬ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ ይባረክልኝ ብለው ›› በግማሽ ዋጋ ቀንሰው ነበር እቃውን ያከራዩት ፤ ሌላም ሌላም….

ከምሳ በኋላ
ምሳ ከተበላ በኋላ የነበረው ፕሮግራም ሊቃውት አባቶች የልጆችን ጥያቄ የሚመልሱበት መርሀ ግብር ነበር ፤ ሊቀ ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ ዳኜ ፤ መጋቢ አዲስ እሸቱ አለማየሁ እና መጋቢ ሚስጥር ፍሬው በኢሜል አድራሻ  እና በአካል የተሰበሰቡ በርካታ ጥያቄዎችን ለመመለስ ቦታቸውን ይዘዋል ፤ መርሀ ግብሩን ሲመራ የነበረው አገልጋይ ከእንደዚህ አይነት አባቶች ለጥያቄዎቻን መልስ ማግኝት ማለት ከምንጩ ውሀ ቀድቶ እንደ  መጠጣት መሆኑን አበክሮ ተናገረ ፤ አዎን እውነት ነው በአሁኑ ሰዓት ብዙ ምዕመን በውስጡ የሚመላለሱ በርካታ ጥያቄዎች አሏቸው ነገር ግን ትክክለኛውን የቤተክርስትያን አስተምህሮ መሰረት በማድረግ የሚመልሱ አባቶችን ማግኝት ከባድ ነገር ነው ፤ አሁን ግን ጥያቄዎችን ከሊቃውንት አንደበት ምን መልስ ሊሰጥባቸው እንደሚችል ለመስማት እኔ በበኩሌ ጓጉቻለሁ፡፡ ከጥያቄዎቹ ጥቂቶቹ
1.      ስለ ነገረ ስጋዌ
2.     አንድ ሰው አስራ ማውጣት ያለበት ከGross ነው ከnet ?(ተቆራርጦ ከደረሰው ላይ ነው የሚል መልስ ተሰቷል) ፤ አንድ ምዕመን አጥቢያ ቤተክርስትያን ተው ወይስ ደስ ያለው ቦታ አስራቱን ማውጣት ይችላል ወይ?
3.     ሁለት እጮኛሞች እሱ ድንግል ቢሆን እሷ ደግሞ ባትሆን ለሁለቱም ተክሊል ማድረግ ይቻላል ወይ ? ወይንም እሱ ድንግል ባይሆን እሷ ደግሞ ብትሆን ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ( መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ‹‹መኪና እና ቤት ነው የጋራ ንብረት እንጂ ድንግልና አይደለም›› ፤ ይህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠር ለአንዱ ይደረጋል ለአንዱ አይደረግም የሚል መልስ ሰጥተዋል)
4.     አንዲት ልጅ ለአቅመ ሄዋን ሳትደርስ በቤተሰብ ገፋፊነት በህጻንነቷ ብትዳር ፤ ራሷ መወሰን በምትችልበት እድሜ ላይ ብትደርስ በተክሊል ማግባት ትችላለች ወይ ?  ( መጋቢ ሀዲስ ሲመልሱ ‹‹ ጥይት ቢያምባርቅም ፤ ታስቦ ቢተኮስም ገደለ ገደለ ነው የሚባለው›› እንዲ የሚባል ነገር በስርዓተ ቤተክርስትን ውስጥ የለም ብለዋል፤ ዋናው ነገር ህጉ ተጥሷል ብለዋል)
5.     ንስሀ አባት መርጦ መያዝ ይቻላል ወይ ? ፤ ንስሀ አባት በምን ሁኔታ መቀይር ይቻላል?  ፤ እና በርካታ አሁን የማላስታውሳቸው ጉዳዮች ተነስተው መልስ ተሰቶባቸዋል፡፡
6.    ከባለትዳሮችም ጥቂት መሰረታዊ ጥቄዎች ተነስተው መልስ ተሰቷቸዋል
ከመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ምክሮች በጥቂቱ
ሃይማኖታችሁ ምንድነው? ስትባሉ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እንጂ ኦርቶዶክስ ብቻ አትበሉ፡፡ ብዙ ኦርቶዶክሶች አሉና፡፡ ለምሳሌ አበበና አበበ ስማቸው ቢመሳሰልም አንዱ ሐኪም አንዱ በሽተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ‹‹ሳትሮጡ የሚያጨበጭብላችሁ ካለ እርሱ እያፌዘባችሁ ነው፤ ሳትሆኑ ናችሁ የሚላችሁም››
ከዚህ በፊት ደጋግሜ ነግሬአችኋለሁ፤ አሁንም ደግሜ እነግራችኋለሁ፡፡ በመንግሥተ ሰማያት ማቻቻል የለም፡፡ ወደዚያ የምንገባው በአሚነ ሥላሴና በምግባር ስንገኝ ብቻ ነው ጊዜ የሆነ ነገር እንድታሟሉ ጊዜ አይሰጣችሁም የሥጋን በሽታ በላስቲክ ተከላከልነው፤ የነፍስንስ? ቃየን በድንጋይ የጀመረው ጦርነት ዛሬ ኒውክሊየር ላይ ደርሷል ከምርጫ በኋላ ቅስቀሳ የለም፤ ከተጋቡ በኋላም መጠናናት የለም፡፡
እኛን ለቀቅ ክርስቶስን ጠበቅ
ሊቃውንት አያሳጣን!!!!!!

በስተመጨረሻም በተደረገው ጉባኤ ላይ ለቤተክርስትያኗ 116ሺህ በላይ መሰብሰብ ተችሏል:: አቡነ ቆዎስጦስ ጉባኤውን ሲዘጉ ‹‹ በጣም ደስ ብሎኛል ይህን በማየቴ ፤ ይህን ያህል ምዕመን የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰማ እንዲህ ተሰብስቦ ማየት ደስ ያሰኛል ፤ እናንተ ከውስጥ ጠላት ጋር በብርታት እየተዋጋችሁ ይህን ማዘጋጀታችሁ ያስመሰግናችኋል ፤ ምግባችንን በልተው እኛው ቤት ተምረው ከተነሱብ ጠላቶች ጋር በመታገል ይህን ነገር ማድረጋችሁ ያስመሰግናችኋል ፤ የውጭ ጠላት ጋር መታገል ከባድ አይደለም ፤ ከወዳጅ ጠላት ያድናችሁ ፤ ይህች ቤተክርስያን በደሙ የዋጃት ስለሆነች ጠባቂዋ እሱ ነው ፤ እነዚህ የውስጥ ጠላቶች እንደ እግዚአብሔር ቸርነት ይከስማሉ እመኑኝ ፤ እኔ ከዚህ በኋ አልሰጋም ፤ ልጆች በአባቶች እግር ተተክተዋል ፤ አንዳንዴ ሳስበው ይህች ቤተክርስትያን የወደፊት እድሏ ምንድነው ብዬ እጨነቅ እጠበብ ነበር ፤ አሁን ግን አልሰጋም ፤ ተስፋዬም በእናንተ ስራ ለምልሟል ብለዋል››፡፡  ከዚህ ሰዓቱ ሲደርስ ጉባኤውን በጸሎት ዘግተው የጉባኤው ማጠናቀቂያ ሊሆን ችሏል፡፡

እኛ ደስ ብሎናል ፤ በርቱ ለበጎ ተግባራችሁ ከጎናችሁ ነን ፤ እንዲህም ተደርጎ ቤተክርስያን መርዳት ይቻላል ፤ በጣም ደስ ብሎናል ፤ አንዳች ነገር ሳይጎልብን እደ እርሱ ፍቃድ በሰላም ወደ ቤታችን ልንመለስ ችለናል፡፡ ምንም የማይወጣለት ጉባኤ መሆኑን አፋችን ሞልተን መናገር እንችላለን ፤ ሚያዚያ 27 ቀን በመላው ኢትዮጵያ ያሉ 120 ሺህ ምዕመናን ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው የማህበረ ቅዱሳንን 20ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሚደረገው የእግር ጉዞ መልዕክት ተላልፏል፡፡ እኛም የዚያ ሰው ካለን ብለን ቲኬቱን ገዝተናል ፤ እርስዎም የዚህ ጉዞ አካል በመሆን ቤተክርትያንን ፤ ገዳማትን እና አድባራትን፤ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን እንዲረዱ አንድ አድርገን መልዕክቷን ታስተላልፋለች ፡፡

ሌላ ደስ ያሰኝን ዜና
የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ 500 የከረዩ ማህበረሰቦች መጠመቃቸውን የምናስታውሰው ነው ፤ ከእነዚህ በተጨማሪ መጋቢት 16 ቀን 700 ተጨማሪ የማህበረሰቡ አካላት ቤተክርስያናቸው በምትመረቅበት ቀን ይጠመቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህን ጉባኤ መሳተፍ ለምትፈልጉ ሰዎች በቦታው ተገኝታችሁ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን ፤ በትላንቱ ጉባኤ ከከረዩ ማህበረሰብ ሁለት የጎሳ መሪያቸው በቋንቋቸው ከሚያስተምሯቸው አባት ጋር ሆነው በመድረክ ወጥተው ከምዕመኑ ጋር ተዋውቀዋል፡፡ ‹‹ገና እንበዛለን›› የሚያስብል ስራም በሀገሪቷ በተለያዩ ቦታዎች ላይ እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡ እውነት ነው እንበዛለን፡፡

ብራቮ ማህበረ ቅዱሳን ብለናል….. ለበጎ ስራችሁ ተባባሪ ‹‹አንድ አድርገን ብሎግ››



17 comments:

  1. አንድ አድርገን ብሎጎች በጣም ጥሩ ዘገባ ነው፡፡ግን አባቶቻችን በጉባኤው ለተነሱት ጥያቄዎች የተሰጡትን መልሶች አንደ በአንድ አፈላልጋችሁ በየጥያቄዎቹ በሰፊው ዘግቡልን፡፡አደራ አደራ አደራ፡፡፡፡፡፡

    ReplyDelete
  2. እግዚአብሔር ይስጥልን! በጥሩ ሁኔታ ገልጸኸዋል፡፡

    ReplyDelete
  3. ሃይማኖታችሁ ምንድነው? ስትባሉ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እንጂ ኦርቶዶክስ ብቻ አትበሉ፡፡ ብዙ ኦርቶዶክሶች አሉና፡፡ ለምሳሌ አበበና አበበ ስማቸው ቢመሳሰልም አንዱ ሐኪም አንዱ በሽተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ‹‹ሳትሮጡ የሚያጨበጭብላችሁ ካለ እርሱ እያፌዘባችሁ ነው፤ ሳትሆኑ ናችሁ የሚላችሁም…››

    ReplyDelete
  4. ወ/ጊዎርጊስMarch 12, 2012 at 7:02 AM

    በቦታው መገኘተ ላልቻሉ ምዕምናን በጣም ጠቃሚና ቁጭትን የሚፈጥር ጽሑፈ ነው፡፡ ይህን ጽሑፍ ያነበቡ ሁሉ በሚያዝያ 27 ጉዞ ለመሳተፍ ከፍተኛ ጉጉት እነደሚኖራቸው ተስፋ አለኝ፡፡

    እግዚያብሔር ያበርታህ

    ReplyDelete
  5. Kidanemariam Ze Negelle BoranaMarch 12, 2012 at 7:13 AM

    እናንተ ከውስጥ ጠላት ጋር በብርታት እየተዋጋችሁ ይህን ማዘጋጀታችሁ ያስመሰግናችኋል ፤ ምግባችንን በልተው እኛው ቤት ተምረው ከተነሱብ ጠላቶች ጋር በመታገል ይህን ነገር ማድረጋችሁ ያስመሰግናችኋል ፤ የውጭ ጠላት ጋር መታገል ከባድ አይደለም ፤ ከወዳጅ ጠላት ያድናችሁ ፤ ይህች ቤተክርስያን በደሙ የዋጃት ስለሆነች ጠባቂዋ እሱ ነው ፤ እነዚህ የውስጥ ጠላቶች እንደ እግዚአብሔር ቸርነት ይከስማሉ እመኑኝ ፤

    ReplyDelete
  6. አንድ አድርገኖች በርቱ @Bernabs በጣም ጥሩ፡፡ እስቲ እንደ Bernabs የነበራችሁ እንዲህ ጣል ጣል እያደረጋችሁ አሳውቁን፡፡

    ReplyDelete
  7. አንድ አድርገኖች
    Thank you so much for making us travel with ማህበረ ቅዱሳን ሐዊረ ህይወት through your wonderful article.

    God Bless you!

    ReplyDelete
  8. Wawu!!!! It is good to hear such kind of positive news at this bad time.

    Nabute

    ReplyDelete
  9. ቃለ ህይወት ያሰማልን

    ReplyDelete
  10. Egziabhere yakiberelen!it is interesting and inspirational report.

    ReplyDelete
  11. pls post your article with pdf format so that we could read it from any computer.

    Thank you

    ReplyDelete
  12. ሰጠችኝማረያምMarch 13, 2012 at 3:06 PM

    በጣም ጥሩ ዘገባ ነው እግዚአብሄር መጨረሻውን ያሳምርልን

    ReplyDelete
  13. በባሕር ዳር ማእከል ማህበረ ቅዱሳን ሐዊረ ህይወት ወደ ታሪከዊዋ ደብረ መዊዕ ማርያም ገደም በመጋቢት 16 – 2004 ዓ.ም እንደተዘጋጀስ የውቃሉ?
    መነሸ፤- መጋቢት 16 ከጠዋቱ 11፡30 ሰዓት፣ ከፈ/ገ/ቅ/ጊዮርጊስ ገደም
    መመለሻ፡- መጋቢት 16 ከቀኑ 10፡30

    ReplyDelete
  14. I am very pleased with MK in Ethiopia. I'm really happy to see this. God bless you with all things you do. I do all my best to help MK from foreign country. As the same time, MK in Ethiopia, please plan the same type of trip to the villages that churches are burnt. These villages need a lot of help. So, by doing such thing the peoples up there feel they have help with them.
    Please do asap...

    Selame EgziAbher Ayleyen,
    ... tadami

    ReplyDelete