Saturday, March 17, 2012

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 3ኛ አረፉ





በጣም አሳዛኝ ዜና!!
አንድ አድርገን መጋቢት 7 ፤ 2004ዓ.ም)4 ዐሠርት ዓመታት የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ሁላችንንም በትጋትና በጽንዕት ያገለገሉት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ 88 ዓመታቸው እንዳረፉ ቢቢሲ ዘገበ፡፡ ቅዱስነታቸው 5ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ የቲዎሎጂ ሴሚናሪ ዲን የሆኑ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ሲሆኑ በአገልግሎት ዘመናቸው 3 የአሜሪካን እንዲሁም 1 የጀርመን ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ተቀብለዋል፡፡ቅዱስነታቸው ሕይወታቸው የትምሕርምት፣ የጸሎትና የአገልግሎት እንደነበር የሕይወት ታሪካቸውን የሚዘግቡ ድርሳናት የሚገልጹ ሲሆን ባለፉት 20 ዓመታት የዓለምን ሕዝብ ያስተማሩባቸው ከ100 በላይ መጻሕፍትን ደራሲና የቤተ ክርስቲያኗ ኦፊሴላዊ መጽሔት ኤል-ኬራዛ ዋና አዘጋጅ ነበሩ፡፡

በግብፅ ርዕሰ ብሔር አንዋር ሳዳት ጊዜ አክራሪ ሙስሊሞች በክርስቲያኖች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት መጨመርና መፋፋም ያሳሰባቸው ቅዱስነታቸው በመንግሥቱ ላይ ባነሱት ተቃውሞ፣ 40 ወራት ከመንጋዎቻቸው ተለይተው ወደ ቅዱስ ቢሶይ ገዳም ተግዘው የአባቶቻቸውን በረከት ተካፍለው እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በኋለኛው መሪ ሆስኒ ሙባረክ ዘመን ወደ መንበራቸው ተመለሰው እስከ ዛሬ ድረስ ጠቦቶችን ሲጠብቁ፣ ግልገሎችና በጎችን ሲያሰማሩ ቆይተው ዐርፈዋል፡፡ ለእርሳቸው ወደ ክርስቶስ መሄድ የሚናፍቁት ቢሆንም ለእኛ በሕይወተ ሥጋ ላለን ግን አጽናኝን አባት ማጣት ነው፡፡


ወዮ… ወዮ
ፊል 1፣21 “… ልሂድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፤ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፡፡ ”
    • ወዮ… ወዮ የ21ኛው መ/ክ/ዘ ታላቁን አባት ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ 3ኛ አረፉ፡፡
    • ወዮ…ወዮ የተሰጣቸው መክሊት እጥፍ አድርገው ያተረፉ፤ በጎቻቸውን በፍቅር፣በትህትና እና በትጋት ያገለገሉ መልካሙ እረኛ ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ አረፉ፡፡
    • ወዮ….ወዮ የመናፍቃንን አንገት ያስደፉ፣ የዓለማችን ፈላስፋዎች በቃለ እግዚአብሔር አፍ ያስያዙ፣በትምህርታቸው የብዙ ሰዎች ነፍሳትን ያለመለሙ፣ቅዱሳን ሐዋርያትን የመሰሉ ታላቁ አባት ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ አረፉ፡፡
    • ወዮ…ወዮ ከመቶ በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን የጻፉ፣ በዓለም ዙሪያ በርካታአብያተክርስቲያናትን ያሳነጹ፣በመቶዎች የሚቆጠሩ ዲያቆናት፣ቀሳውስትንና ኤጲስ ቆጶሳትን የሾሙ ታላቁ አባት ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ አረፉ፡፡
    • ወዮ…ወዮ በካህናት ፣ በምእመናንና በኢአማንያን ዘንድ ከልብ የሚወደዱ፤ ንጹሁ፣ድንግል፣ካህን፣ባህታዊ፣ትህርምተኛ፣ወንጌላዊ፣ደራሲ፣ተርጓሚና ገጣሚ የሆኑት ታላቁ አባት ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ አረፉ፡፡
    • ትልቅ አባት በእውነት አጣን ፣ ሥራቸው ግን ለዘላለም ይኖራል ፣ በገነትም በሰላም ከቅዱሳኑ ጋር ያኑራቸው። የአገልግሎት ጊዚያቸውን በመልካም እረኝነት አሳልፈዋል:: መክሊታቸውንም አትርፈውበታል:: ሞት ለማንም አይቀርምና እርሳቸውም አርፈዋል:: እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይቀበላቸው ፤ ከቅዱሳን ጋርም ያኑርልን::
    • አቤቱ የቅዱሳን አምላክ ሆይ፣ በነቢዩ ኤልያስ የነበረውን ቅዱስ መንፈስ እጥፍ አድርገህ በነቢዩ ኤልሳ ላይ እንዳወረድክ፣ እንዲሁም በአባታችን በብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ የነበረውን ቅዱስ መንፈስ በቅዱስ ማርቆስ መንበር ላይ ለሚተካ አባት እጥፍ አድርገህ ታወርድለት ዘንድ ፍቃድህ ይሁን፤ አሜን፡፡
    • ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ መልካሙን ገድል ተጋድለዋል፣ ሩጫዎቶን ጨርሰዋል፣ ሃይማኖቶን ጠብቀው አስጠብቀዋል፣ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶሎታል፣ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያን ቀን ለእርሶ ያስረክባል፡፡
    • ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ ሆይ ለዚህ ታላቅ ክብር ያደረሶት ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፣ በዚያን ጊዜ ቅዱስነትዎ እኛም ከእርሶ ጋር በክብር ትንሳኤ እንድንገልጥ በጸሎቶ ያስቡን፡፡

በጣም አዝነናል በዚህ ጊዜ አቡነ ሺኖዳን በማጣታችን ፤ ይህ የኮፕቶች ሀዘን ብቻ አይደለም ፤ የእኛም የእህት አብያተክርስያናት ጭምር ነው ፤ በጣም በጣም አዝነናል ፤
አምላክ ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን 

ታላቁን አባታችንን ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳንን ማጣት ምን ያህል ይከብዳል!!!....
አምላክ ሆይ እኛን ባሪያዎችህን እባክህ ያለ እረኛ አታስቀረን ፡፡




የአቡነ ሺኖዳ ሞት ለእኔ ‹‹ትልቅ ዋርካ የወደቀ ያህል ነው የተሰማኝ›› 
ለእምነታቸዉና ለሐይማኖታቸዉ የኖሩ ሰዉ መሆናቸዉን ያወቁ እዉነተኛ አባት ፤  አስተማሪ መካሪ ታላቅ የሀይማኖት ሰው ማጣት በጣም ከባድ ነውየቅዱስነታቸው በረከት አይለየን፤ ይደርብን፤ ለግብጽ ቤተ ክርስቲያንም የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳን ዐይነት አባት ይተካላቸው፤ ይስጣቸው። አሜን 

ቀና ወደ ሰማይ!!!
ይቺን ቤተክርስቲያን አምላኬ ጠብቃት 
ፍሬን የሚያፈራ ተተኪ ተካላት
እኔ ጨርሻለው ልምጣ ወደ ቤቴ
ሰላምህ ይብዛልኝ ውሰዳት ህይወቴ

አራት ሰው ሞተ 
አራት ሰው ሞተ ደረሰ እና ጥሪ
ደራሲ፣ ሰባኪ፣ ጳጳስ እና መሪ
እንግዲህ መቃብር ደኅና አርገህ እፈስ
መጽሐፍ ተሸክሞ መጣልህ ጳጳስ
በግብጽ በካይሮ ጩኸት በረከተ
የዓለሙን አናውቅም አንድ የእግዜር ሰው ሞተ
ሞተዋል እንዳይሉ ጽፈው አገኟቸው
አልሞቱም እንዳይሉ ተኝተው አዩዋቸው
ምናሉ ቅብጦቹ ሰው ሲጠይቃቸው
ለወሬ አልተመቸም በችግር ላይ ናቸው 
(ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)



በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስትያናችን ላይ እየደረሰ ያለውን ነገር ሳስተውል ፤ የአቡነ ሺኖዳን ሞት ስመለከት ፤ ውስጤ በጣም ፈራ 

24 comments:

  1. Egziabher ye abatachenen nebse yemarelen betekerestiyan telek abat new yatachew.

    ReplyDelete
  2. oh no no no noooooooo nooooooo please wushet new belugne pleaseeee wushet yihun! abatey lemin? lemin?? be akal alawqwotm gin metshaftwon degagmey anbibealew hiwot honewgnal hulem eyedegagemku anebachewalew fetsimo yemiyaregagu yemiyatenekru nachew , fiqerwon abatnetwon lemayet ejig silemnafeq ctv coptic channel etebqwotalew getsiwo yimarkal,yaregagalm,ababa lemin lemin tilewn hadu? gena eko yasfelgunal, eeeee enbayen maqom alchalkum yemenfes abateyn ataw....amlake hoy ebakhn nefsachewn be qegnih anur..bereketachewn asadrben!! baba behiwot salew fetsimo fetsimo alresawotm,be akal bayawqugnim bemenfes yeeledugne lijwo negne tselotwo yitebqegne,bereketwo yiderbegne erswos yegenet mushira newot uuuuhhhhhhh hazenen min biye labkaw yihon amlake.................

    ReplyDelete
  3. ende abat yemitebekbachewin sertew yalefu bemehonachew le'ersachew kedikam maref new. anuanuarachewinima endet endet endeneber enawkewalen michot, dilot sayfeligu lemiemenan ewnetegna eregna neberu yesachewin metsehafit yalanebebe sew yelem biye asibalehu endih new krstian kerasu alfo lelelaw yemiyabera.
    የቅዱስነታቸው በረከት ይደርብን

    ReplyDelete
  4. በጣምና በጣም አሳዛኝ መርዶ ነው!!!! አምላካችን ሆይ ያለ እረኛ አትተወን!

    ReplyDelete
  5. በጣም አዝነናል። አባታችንን የሚተካ አባት ያድለን።

    ReplyDelete
  6. የአባታችን ነፍስ በገነት ያኑርልን፤ ነፍስ ይማር፡፡

    ReplyDelete
  7. Nefisachewun yimarlin!

    ReplyDelete
  8. የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን። ሥራ 21፤14

    የዘመናችን ጳውሎስና አትናቴዎስ ከኛ መለየት የማያሳዝነው እውነተኛ ክርስቲያን ያለ አይመስለኝም፡፡
    ሥራዎቻቸው ግን እንደ ሌሎቹ ቅዱሳን ሥራዎች ህያዋን ሆነው ሰዎችን ወደ ህይወት መንገድ ሲመሩ ይኖራሉ፡፡

    አቤቱ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ በርቀት ያጽናኑንና ያበረቱን አባታችንን እንዲያርፉ ፈቃድህ ከሆነ ፤
    የሳቸው እግር የሚከተሉትን አብዝተህ ትሰጠን ዘንድ ቅዱስ ፈቃድህ ይሁን፡፡


    አሜን
    ገብረሚካኤል ዘ እንዳሚቺአል

    ReplyDelete
  9. help help help
    Ziquala monastrey forest is under fire
    the fire is hard to control b/c of wind with monks alone.
    for more information call 0115545452 or 0920675349

    ReplyDelete
  10. Berketachew Yederben, Melekam Ergana

    ReplyDelete
  11. nafes yemar nafesachwen begnat yanurelne

    ReplyDelete
  12. nefisachewun be gent yanerln

    ReplyDelete
  13. ersachewen teto yegnawen lemen aywesedelenem?

    ReplyDelete
  14. ye abbatechin nefse Egziabiher amlakachin begenet yanurilin !! bereketachew be igna be lijochu yidaribin!!amen

    ReplyDelete
  15. Egziabiher Nefsachwen Begenet Yanurilin.....Telek Abate Bematatachen Ejege betam Aznenale...

    K

    ReplyDelete
  16. Egziabiher Nefsachewen Begenet yanurilin....Legna le Orthodoxawian talake astaraki astemari meri abate atetenale. Bezi fetagne gize esachewen yemiakele talake talake abate matate ejege betam yasazenale....Bereketachew be egnal laye yiderriben ...Amen!!!

    ReplyDelete
  17. እንደእርስዎ ያለ አባት
    በሚያስፈልግ ሰአት
    ሁሉ አላምር በሎዎት
    ሄዱ ወይ ወደሞት
    እንግዲህ ምን ይባላል በቀኙ ያኑርዎት

    ReplyDelete
  18. EGZIO SELAME HABA LAGERKE LETSDKENI BET KIRSTIYAN:
    AGRER TSERHA TAHIT EGERIHA EQEB HIZBA WE HAYMANOTA LE HAGERITNE ETHIOPIA:
    orthodoxawiyan ebakacehun ke enkilfashehu niku!!!!!!!! are be emeberhan yesew yaleh!!!! gedamatochahen siqatelu zime blo be esatu yemimoke tiwled

    ReplyDelete
  19. ‹‹…ዝም ብለን የእግዚአብሔርን ማዳን እንጠብቃለን… ፡፡››
    እንደእርስዎ ያለ አባት
    በሚያስፈልግ ሰአት
    ሁሉ አላምር በሎዎት
    ሄዱ ወይ ወደሞት
    እንግዲህ ምን ይባላል በቀኙ ያኑርዎት
    በጣም አዝነናል። አባታችንን የሚተካ አባት ያድለን።

    ReplyDelete
  20. Tadiya min enilalen?.....yefeterkawun yematitewu nigus liul Egziabiher hoy le kristiyanoch abat siten!....gin lemin?....Yelelawu sayihon Ye Ethiopianis ferawu...bicha Egziabiher yawukal!!!!!tselotachewu,bereketachewu ayileyan!

    ReplyDelete
  21. atefra lekereseteyanoch abat feter malet new

    ReplyDelete
  22. YE ABTACHIN BITSU WEKIDUS ABUNE SHINODA MOT BATAM YASAZNAL. EGZIABHER NEFSACHOWN BEGENET YASARF ! AMEN !!!

    ReplyDelete
  23. BEREKETACHEW AYLEYEN

    ReplyDelete
  24. ንጋት /ወለተ ጊyorgis/
    የብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ ሞት አሳዛኝ ነው ::በመጻሕፍቶቻቸው የክርስትናን ብርሀን በውስጤ ያበሩ እረኛ አባት ነበሩ:: እርሳቸውስ ወደ ፊትም የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶላቸዋል:: እኛ ስለ ወደ ፊት እናልቅስ እርሳቸውን የሚተካ እረኛ አባት እግዚአብሔር እንዲሰጠን::
    በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስትያናችን ላይ እየደረሰ ያለውን ነገር ሳስበውና ፤ የአቡነ ሺኖዳን ሞት ስመለከት ፤ ውስጤ በጣም ፈራ ፈራ ፈራ ፈራ ...::
    እንደእርስዎ ያለ አባት
    በሚያስፈልግ ሰአት
    ሁሉ አላምር በሎዎት
    ሄዱ ወይ ወደሞት
    እንግዲህ ምን ይባላል በቀኙ ያኑርዎ




    የቅዱስነታቸው በረከት ይደርብን

    ReplyDelete