- የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአስመላሽ ኮሚቴ ውስጥ አልተካተተችም ፤
- ሐውልቱ እንዴት ወደ ቦታው እንደሚመለስ ቤተክርስቲያኒቱ የምታውቀው ነገር የለም፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት ይህ ሐውልት ከቦታው ሲነሳ ቤተክርስቲያን ፤ ሕዝብ እና የሚመለከታቸው አካላት
ያልመከሩበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሚነሳበት ወቅትም በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገፆች ፤ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ሬድዮን
ጣቢያዎች ወሬው በመመላለሱ ምክንያት በስተመጨረሻም መንግሥት በሚመለከተው አካል አማካኝነት መልስ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ በወቅቱም
እንዴት እንደሚነሳ እና መቼ እንደሚነሳ ለሕዝቡ ግልጽ ያለመደረጉ ይታወቃል፡፡ መጀመሪያ ሐውልቱ ከቦታው ሲነሳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጉዳዩ ላይ ምንም የምታውቀው
ነገር እንደሌለ ከሚመለከተው አካልም ምንም አይነት ደብዳቤ ያልደረሳት ሲሆን አሁንም ከመጀመሪያው ስህተት ባለመማር መንግሥት ቤተ
ክርስቲያኒቱ የሐውልቱን ወደ ቦታው የመመለስ ሂደት ላይ ታሳታፊ ያላደረጋት መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡
No comments:
Post a Comment