Sunday, December 21, 2014

ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ አገዱ

 • / ሲኖዶሱ በአድባራት ሓላፊዎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ  ሕገ መንግሥቱን የሚፃረር ነውፓትርያርኩ

(አዲስ አድማስ ታህሳስ 11 2007 ዓ.ም):-  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ‹‹የቤተ ክርስቲያን አባቶችና ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና በሰጠችው ማኅበር ላይ ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል›› ባላቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት አስተዳዳሪዎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ አፈጻጸም ‹‹ሕገ መንግሥቱንና ሰብአዊ መብትን የሚፃረር ነው›› በሚል ፓትርያርኩ ማገዳቸው ተገለጸ፡፡ ፓትርያርኩ ባለፈው ኅዳር 30 ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ /ቤት በጻፉት ደብዳቤ ‹‹አፈጻጸሙ እንዲቆይ›› በማለት ያገዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት በተካሔዱ ጉባኤዎች÷ ‹‹ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል፤ ይህም አነጋገር ጉባኤውን ቅር አሰኝቷል፤›› ያላቸው የአድባራት አስተዳዳሪዎች፤ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው በአንድ ድምፅ ተስማምቶ ያሳለፈው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡


በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ በመንበረ ፓትርያርክና በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሾች በተካሔዱት ስብሰባዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን መልካም አስተዳደርና ወቅታዊ ችግሮች የተመለከቱ የጉባኤተኞች አስተያየቶችና ሐሳቦች መቅረባቸውን በደብዳቤያቸው ያስታወሱት ፓትርያርኩ፤ ተሰብሳቢዎቹ ሐሳባቸውንና አስተያየታቸውን በግልጽ መናገራቸውና አሉ የተባሉ ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ መጠየቃቸው ‹‹በዓለም አቀፍ ደረጃም ኾነ በሀገራችን ለሕዝብ የተፈቀደ ዴሞክራሲያዊ መብት መኾኑ አያጠያይቅም›› ብለዋል፡፡ ሐሳባቸውንና አስተያየታቸውን በግልጽ ያቀረቡ ሰዎችን መገሠጽና መውቀስም ሕገ መንግሥቱን እንደሚፃረር ጠቁመዋል፡፡

ጉባኤዎቹ በቤተ ክርስቲያን ጠሪነት የተካሔዱ እንደነበሩና ተሰብሳቢዎቹም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት፣ አገልጋዮችና ሠራተኞች መኾናቸውን ፓትርያርኩ ጠቅሰው÷ የጎደለው እንዲሟላ የጠመመው እንዲቃና ያላቸውን አስተያየት በማቅረባቸው ተግሣጽና ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈው ውሳኔ ‹‹የስብሰባ ነፃነትንና መብትን ነፍጎ ሐቁ እንዳይነገር›› የሚከለክልና ውጤቱም ‹‹ጊዜ ያለፈበትን አፈና በማንገሥ ችግሮች ተባብሰው እንዲቀጥሉ የሚያደርግ ነው›› ብለዋል፡፡በውይይቱ ወቅት ‹‹የዳኅፀ ልሳን ወለምታ›› አጋጥሞም ከኾነ በወቅቱ ማብራሪያና ማስተካከያ ይሰጥበታል እንጂ እንደ ከባድ ጥፋት ተቆጥሮ ሰዎች ሊገሠጹበትና ሊወቀሱበት አይገባም፤ ሕግም አይፈቅድም፡፡ሲሉ ገልጸዋል - በደብዳቤያቸው፡፡ 

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ‹‹ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል›› ያላቸው አንዳንድ የአድባራት አስተዳዳሪዎች በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ቀርበው ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው ያሳለፈው ውሳኔ ‹‹ሕግንና ሰብአዊ መብትን የሚፃረር›› ብቻ ሳይኾን ‹‹ትልቁን ጉባኤ በታሪክና በሕግ ዐዋቂዎች ዘንድ ግምት ውስጥ የሚጥለው እንዳይኾን አቡነ ማትያስ አስጠንቅቀው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ጉዳዩን እንደገና በጥልቀትና ከሕግ አንጻር ፈትሾ እንዲያጤነው በማለት አፈጻጸሙ እንዲቆይ አስታውቀዋል፡፡

በሕገ ቤተክርስትያን /ሲኖዶሱ በሙሉ ድምፅ ተስማምቶ ያሳለፈውን ውሳኔ ፓትርያርኩ የማገድ ሥልጣን እንደሌላቸው ያመለክታል፡፡ ሕገ መንግሥቱ ከተጠቀሰበት አግባብ አኳያም፣ቤተ ክርስቲያናችን በቂ ሕግጋት አሏት፤ እነዚህ ሕግጋት ማዕከሉ ተጠብቆ ሊሠራባቸው ይገባል፤ሲልም /ሲኖዶሱ አሳስቧል፡፡

ባለፈው መስከረም መጨረሻየቤተ ክርስቲንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልጸግበሚል መርሕ በተካሔደው ስብሰባ አንዳንድ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፤ ‹‹ፈጣሪ የለም ይላል፤ አሸባሪና አክራሪ ነው፤›› በማለት ቤተ ክርስቲያኗ ዕውቅና የሰጠችውን ማኅበረ ቅዱሳንን ከዓለም አቀፍ ጽንፈኞች ጋራ እያመሳሰሉ መወንጀላቸው ተገቢ እንዳልኾነና የማኅበሩ አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ እንደኾነ ቅዱስ ሲኖዶሱ አረጋግጧል፡፡ 


‹‹ቆራጣ ደብዳቤ ይበቃዋል፤ ከመንግሥት ጋራ በመተባበር እስከ ጫፍ አድርሱልን፤ በቶሎ ቁረጡት›› እያሉ መጠየቅ፤ ሊቃነ ጳጳሳቱንምከፈለጉ ቆባቸውን አስቀምጠው ወደዚያው ይግቡእያሉ መዝለፋቸውስ በምን መመዘኛ ነው ዴሞክራሲያዊና ሕገ መንግሥታዊ የሚኾነው በማለት የሚገልጹ የስብሰባው ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ ፓትርያርኩ የውሳኔውን አፈጻጸም ማገዳቸው፣ አድሏዊ እንደሚያደርጋቸውና በካህናቱና በምእመናኑ ዘንድ መንፈሳዊ አባትነታቸውንና ታማኝነታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባው እንደሚኾን ጠቁመዋል፡፡

7 comments:

 1. keduse abatachen ye Egzabher heg new ye mengest heg yemiakbrute ymyasfesmute

  ReplyDelete
 2. +++
  ሁሌም ሳስበው የሚገርመኝ፥ የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እጅግ ዘመናዊና በርካታ ወጪ የወጣበት የራሱ ድረ-ገጽ ሲኖረው፣ እንዲሁም በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሥር ያለ አንድ መምሪያ /የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ/ የራሱ የሆነ ድረ-ገጽ ሲኖረው፤ የቤተክርስቲያኒቱ ዋና መሥሪያ ቤትና
  ዋናው የሥራ አስፈጻሚ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የራሱ የሆነ ድረ-ገጽ እንዲሁም በሥሩ ላሉ ሁሉም መምሪያዎች የድረ-ገጽ አገልግሎት መጠቀም ያልተቻለበት ምክንያት ሳስበው በጣም ይገርመኛል። ምክንያቱም ቤተክርስቲያኒቱ ለዚህ የሚሆን ሀብት ሳታጣ፣ በሙያው በቂ ልምድ ያላቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ሳይጠፉ ምን አዚም ቢደረግብን ነው እላለሁ? ወይንስ የተቀነባበረ ሴራ?
  እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን።

  ReplyDelete
 3. Alemetadel sintichigir asalufehu ezih sidersu ye egziabiherin bet liyarekisut ere ayizengut min silu endenoru ande gjze new yeminorut esum yetemase gudiguad pls abatschin woyanen sayihon egiziabiherin yifru
  Egiziabher ethiopuan yibark

  ReplyDelete
 4. Kedusenetu yalefew yebekanale tekekeleja ereja yasefelegenale besemayebaitem yemiyaseteyekuten bemederem yemiyasemesegenuten sera yeseru aleyam yeweneberu balebait beguthun yeteyekutale

  ReplyDelete
 5. He is a father for all of us, not only for MK. So,even if i admit power of Holy Synodus, i prefer his holiness approach, that reflect idea of justice. MK is doing immense and silly lobby on individual Bishops, which is tuned in herd mentality.no way! MK should be under strict rule and regulation,unless....

  ReplyDelete
 6. kedus abatachen ebakewen Lekdest bietkersetianachen wedfit eta fenta yasbu?

  ReplyDelete
 7. እየታገልን ያለው የእግዚአብሔርን ሐሳብ ለማገልገል ነው ወይስ የሰዎችን ቅዱስ ጴጥሮስ ራሱን ጠንካራ አስተዋይ ደቀመዝሙር አድርጎ ቆጥሮ ሌሎች ወንድሞቹን በማሳነስ ሌሎች ቢክዱት እንኩዋን እሱ እስከሞት ድረስ እንደሚታመን ለጌታችን እርግጠኛ ሆኖ ስሜቱን እምነት አስመስሎ ተናግሮ ነበር፡፡
  ግን ጌታችን ራስን ማሳነስን እንጂ ሌሎችን ማሳነስን አይፈቅድምና እራሱ የክህደት ፈተና ውስጥ ወደቀ፡፡ ያልታሰበው ወንጌላዊ ዮሐንስ ግን ታምኖ ተገኘ፡፡ ብዙዎቻችን እውቀት ብለን የምንጠራው ነገር በ ጌታችን ፈቃድ የተፈተነ ሳይሆን ራስን በማክበር ላይ የተደገፈ በመሆኑ ውሳኔአችን ሁሉ የእግዚአብሔርን በጎች የሚሰበስብ ሳይሆን የሚበትን መሆኑ ያሳዝናል፡፡
  ትልቅነት ወይም ታላቅነት ወይም ታላቅ ኃላፊነት ራስን ዝቅ ማድረግና ሌሎችን ማስበለጥ መሆኑን ከጌታችን አገልግሎት የምናውቅ ቢሆንም ምላሳችን እንጂ ልባችን አልተሰበረም፡፡ አሁንም ያወቅናቸው የሚመስሉንን የጌታችንን የእውነትና የሕይወት መንፈሳዊ ቃላት ከመጥቀስ አልፈን በተግባር ካልነካናቸው የናቅናቸው ፊተኞች ናቂዎቹም ኋለኞች በመሆን ቦታ የመቀያሩ ነገር አስቀድሞ የተነገረ ነው፡፡
  ድፍረታችንና ትዕቢታችን በመንፈስ ማደጋችንንና ለጌታ መታዘዛችንን ሳይሆንን የሚገልጡት ሥጋዊ ድንዳኔአችንን ነው፡፡ እግዚአብሔር በእምነት በማደጋችን እንጂ በሥጋ በመራቀቃችን የሚደሰት አይደለም፡፡
  ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፡፡ ሥጋ ምንም አይጠቅምም እንዲል፡፡ የቀደሙት መንፈሳውያን የኖሩበት የጽድቅ ጥበብ ምነው ተሰወረብን እነሱ እያወቁ(እውቀት እያላቸው) ሌሎችን ለማክበርና ወደ በጎ ለመምራትና ላለማሰናከል ራሳቸውን እንደአላዋቂ ዝቅ ሲያደርጉ፤ እኛ ደግሞ ሳናውቅ አዋቂ ሆንንና ወንድሞቻችንን ተቺዎችና በተገላቢጦሽ የሌሎችን ኃጢአት ተራኪዎች ሆንን፡፡ ጽድቁ ሞኝነት ብልግናው እውቀት ሆኖብን ቦታውን አቀያየርነው፡፡ እግዚአብሔር ይጎብኘን!!!

  ReplyDelete