(አንድ አድርገን ግንቦት 29 2009 ዓ.ም)፡- ባሳለፍነው አስር ዓመት ውስጥ በተሐድሶ እንቅስቃሴ ስማቸው አዘውትሮ
ከሚነሳው አንዱ አቶ አሰግድ ሳህሉ ባሳለፍነው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ስራው ተመዝኖ ቀሎ ስለተገኝ ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ለይቶታል
፤ ይህን ሰው ለማውገዝ 20 ዓመታት ያስቆጠረ ቢሆንም በስተመጨረሻ መወገዙ ምዕመኑን ከመሰል ተኩላዎች እንዲጠበቅ ማስገንዘቡ እንደ
ጥሩ ጎን ይወሰዳል ፤ አሁንም ቢሆን በርካታ ‹ዘማሪያን› ፤ ‹ሰባኪያን› እና መሰሎቻቸው በዚህ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ የማጠልሸት
እና አዲስ አስተምህሮ የመትከል ሥራ ላይ የተሰማሩ እንዳሉ ይታወቃል ፤ ከዓመታት በፊት አቶ በጋሻው ደሳለኝ ፤ አቶ አሰግድ ሳህሉ
፤ ወ/ሮ ዘርፌ ከበደ ፤ ያለ አግባብ በብልጠት የቅስና ማረግ የወሰደው አቶ ትዝታው ሳሙኤል እና መሰሎቻቸው በEBS ቴሌቪዥን ላይ
የአንድ ሰዓት አየር ሰዓት በመግዛት ሲንቀሳቀሱ እንደነበር እና ከጊዜ በኋላ የቴሌቪዥን ጣቢያው ላይ በተነሳበት ጥያቄ መሰረት ሁሉንም
በቤተክርስቲያኒቱ እውቅና የሌላቸውን መርሀ ግብሮችን መዝጋቱ ይታወቃል፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላ በገንዘብ አቅማቸው እየተመናመነ እና
መድረክ እያጡ የመጡት ተሀድሶያውያኑ አሁን goFundMe በሚባል
የማሕበራዊ ድረ ገጽ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘዴ ላይ የልመና ስራቸው በይፋ ጀምረዋል ፤ ይህ አሁን ላይ ወርደው የተገኙበትን ደረጃ
የሚያሳይ ሆኖ ተገኝቷል ፤ በዚህ ገጽ ላይ የሚሰበሰበው ገንዘብ ተቋሙ እስከ 20 በመቶ የሚሆነውን ወስዶ የተቀረውን ለባለቤቱ እንደሚያስረክብ
ይታወቃል ፤ ሆኖም ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ አንድም ሰው ምንም ገንዘብ ያላበረከተ መሆኑን ከገጹ የሚገኝ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወ/ሮ ዘርፌ እና መሰሎቿ ‹በዝማሬያችን ምድርን ከፍ ሰማይን ዝቅ› እናደርጋለን ብለው እንዳልተመጻደቁ ዛሬ ላይ ምዕመኑ በእነርሱ ላይ በደረሰበት
የመረዳት ደረጃ አንቅሮ ሊተፋቸው የቀረው ጥቂት ጊዜ መሆኑን የሚያመላክ ነው፡፡
አንድ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይነቱ ላይ ጥያቄ የሚነሳበት ሰው የቤተክርስቲያኒቱን ስም ጠርቶ መለመን የለበትም
፤ ይህ ምዕመኑን የሚያወናብድ ተግባር ስለሆነ የሚመለከተው አካል አጽንኦ ሰጥቶ ሊመለከተው ይገባል ፤ የቤተክርስቲያንን ስም ጠርቶ
ጉባኤ ለማዘጋጀት ፤ ልማት ለማከናወን ፤ ቤተክርስቲያን ለመስራት እና መሰል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ድርጊት ለመፈጸም የቤተክርስቲያኒቱ
ፍቃድ ሊተየቅ ይገባል ፤ ቀድሞ ካለፍቃድ የተዘጋው የቴሌቪዥን መርሀ ግብር የተዘጋበት ምክንያት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ፍቃድ
ስላልሰጠች ነው ፤ ይህን የመሰለ ልመና ራሳቸው ችለው መለመን ሲገባቸው ስሟን እየጠሩ መለመን ግን አግባብ አይደለም፡፡
አሁንም ቢሆን ከአውደ ምህረት እንዲርቁ ፤ ስራቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ተገልጦ
ፍቃደኛ ከሆኑ ጥፋታቸው አምነው እንዲመለሱ ፤ ያለበለዚ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ እንዲለያቸው ለተሄደበት መንገድ ሁላ በግለሰብ ደረጃ
መረጃ በየጊዜው ለሚመለከተው አካል ስታደርሱ የነበራችሁ ምዕመናን ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡ የዚያን ሁሉ ዓመታት ዘርፈ ብዙ ተጋድሎ
ማድረጋችሁ ዛሬ ላይ እነዚህ ሰዎች በግልጽ የልመና አደባባይ ላይ እንዲወጡ አድርጓቸዋል፡፡ ዛሬ ላይ ወ/ሮ ዘርፌ በዓለም ላይ ሁሉ
በልመና ያገኝችው ገንዘብ ቀድሞ አንድ አውደ ምህረት ላይ ተጋብዛ ከምታገኝው በታች ሆኖ ይታያል ፤ ምዕመኑ አሁንም ራሱን ፤ ቤተሰቡን
፤ አጥቢያውን እና አንዲት ቤተክርስቲያንን ከእነዚህ በልቶ ካጅ ፤ ጡት ነካሽ ከሆኑ የዘመኑ ብር አምላኪዎች እንዲጠብቅ መልዕክታችን
የጸና ነው፡፡
ልመናው ይህን ይመስላል
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ዘማሪት ዘርፌ ከበደ በቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን ሁሉ የምትወደድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ናት። በተለይ መንፈስ ቅዱስ በሚለው አልቨምዋ ብዙዎች ያውቁአታል። ጥልቅ ትርጉም ባላቸውና የሰውን ልብ እየነኩ ወደ እግዚአብሔር በሚያስጠጉ ዝማሬዎችዋ ብዙ ምእመናን ታንጸዋል ተገልግለዋል። ዘማሪት ዘርፌ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ ሁሉ በሚኖሩ አብያተ ክርስቲያናት እየተጋበዘች በውጭው ዓለም ያለውንም ህዝባችንን እያገለገለች የምትገኝ ትጉ አገልጋይ ናት።
ዝማሬዎችዋን በሲዲ ከለቀቀች ወደ አራት ዓመት አካባቢ መሆኑን ስንረዳ ለምን ይህን ያህል ጊዜ ሌላ የዝማሬ ሲዲ ሳትለቅ እንደዘገየች ጠየቅናት። መልስዋም የሲዲ ህትመት ሥራ ዋጋው እየጨመረ ከመሄዱና ለቀረጻና ለህትመት ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቅ መሆኑን ነገረችን። ፥ በመሆኑም አለች ዘማሪት ዘርፌ በመሆኑም እግዚአብሔር ፈቅዶ ሲዲ ማሳተም እስከምችል ድረስ በተቻለኝ መጠን በዓለም ዙሪያ ሁሉ በአካል እየዞርኩ የምወደውን የእግዚአብሔርን ህዝብ እያገለገልኩ ነው አለችን። ሻማ ለራሱ እየቀለጠ ለሌሎቹ እንደሚያበራ ብዙ የቤተ ክርስቲያናችን አገልጋዮችም ለኛ እያበሩ ለራሳቸው ግን በብዙ ውጣ ውረድ እንደሚያልፉ ለሁላችንም ግልጽ ነው።
እኛም ይህንን ከሰማን በኋላ እንደ ጠራ ውሀ ኩልል እያሉ በመንፈሳዊ ጥም ያሉትን ብዙ ምእመናን ልብ የሚያረሰርሱትን ዝማሬዎችዋን በጊዜው ለህዝብ ጆሮ እንዳታደርስ ያገዳት የህትመት ወጪ መናር ከሆነ በዝማሬዎችዋ የተገለገልንና እየታንጽን ያለን እኛ ለምን ከጎንዋ ቆመን የድርሻችንን አንወጣም? ብለን አሰብንና ይህንን አካውንት ከፈትን። በመሆኑም በዝማሬዎችዋ የታነጻችሁ ምእመናን ሁሉ በቅርቡ ልትለቀው ያለውን ሲዲ ህትመት ለመደገፍ በሚቻላችሁ መጠን ከጎንዋ እንድትቆሙ በአክብሮት እንጋብዛችኋለን።
እስከ ዛሬ ዝማሬዎችዋን እየሰማን ለተጠቀምንበት አገልግሎትዋ ያለንን አክብሮትና ፍቅር ይህን አጋጣሚ በመጠቀም እንግለጽላት። አባቶቻችን ሲናገሩ «ሐምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ለሐምሳ ሰው ግን ጌጥ ነው» እንደሚሉት ሁላችን ከእህታችን ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ጎን ብንቆምና ድርሻችንን ብንወጣ በቅርቡ አዳዲስ ዝማሬዎችዋን እንሰማለን ብዙዎችም ይጠቀማሉ። ከዘማሪት ዘርፌ ጎን ስለቆማችሁና በሁሉም ስለምትደግፋዋት እርስዋን ወክለን እግዚአብሔር ይስጥልን እንላለን።
listen (Yene Nardos)
https://www.facebook.com/ZemedkunBekeleB/videos/443223042709260/

Siyalk Ayamr
ReplyDeleteበጣም ይገርማል ሰው ሲዋረድ እነዲህ ነው እንግዲህ ዘርፌ መንፈሳዊ ህይወት ሳይኖርሽ ዘማሪ ነኝ ማለት በጣም ይደብራል ባልተማረ አንደበት ና ጭንቃላት የማይገናኝ ግጥም ሊቃውንት ያላዩትና ያልመረጡት ግጥም መስማት አስጠልቶናል ንሥሀ ገብታ ብትመለስና ብትማር ይሻላታል ፡፡ ዘርፌ የዋህ መዕመን ምንም የማታውቅ ጨዋ ነች ግን ባለማወቋ በተሀድሶ ተመጨለፈች ምስኪን አሁንማ መንገድ ቁጭ ብላ መለመን ቀራት አሁን ከሁሉም በፊት ወደ ቤቷ ትመለስ ንገሯት
Deleteegziabher yihunat sewun mitsiwat kemelemen ke fetari mihiretin bitlilemin yishalatal. lenisiha yabkash
ReplyDeleteምን አድርጋ ይቅር ይበልህ
Deleteሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀ
ReplyDeleteLenisha hiwet yabkash
ReplyDeleteKiristos leniseha Mot yabkash...
ReplyDelete
ReplyDeleteየማቴዎስ ወንጌል 5:1012
ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።
ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።
ዘርፌ እንደሰው እህታችን ናት የተሰደደችው ግን ስለሰማያዊ ክብር ሳይሆን ስለ ብር ነው የክብር እና የብር ልዩነት ከጠፋችሁ እንግዲህ ምን እንላለን?ጥቅስን ያለቦታው አትጥቀሱ ቢያንስ ከአባታችሁ ተማሩ እርሱ አምላካችንን በገዳመ ቆሮንጦስ ሲፈትነው በጥበብ ነበር ወቅታዊ ፈተናን በማቅረብ ምንም እንኳ አባታችን የአባታችሁን ጥበብ በጥበቡ ረትቶ ድል ቢነሳውም ታድያ የርሱ የክፉው ልጆች ሆናችሁ ሳለ ያለቦታው ጥቅስ መጥቀሳችሁ ምነው? አባታችሁ የታላላቅ ፈተናዎች ባለቤት ሁኖ ሳለ ምነው እማይረባ ፈተና ትፈትኑናላችሁ?ኤዲያ!!!
ReplyDelete