Friday, November 9, 2012

በፓትርያርክ ምርጫ ላይ መንግስት ተጽህኖ ለማሳደር የራሱን ቡድን መሰረተ


(አንድ አድርገን ጥቅምት 30 2005 ዓ.ም )፡- የቀድሞ ፓትርያርክ ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ ብዙዎችን እያነጋገሩ ካሉት ነገሮች ውስጥ ስለ ቀጣይ ፓትርያርክ ምርጫ  እና እርቀ ሰላም ይገኙበታል ፤ ከሁለት ሳምንት በፊት በፌደራል ጉዳዮች አማካኝነት የራሱን ተጽህኖ ማሳረፍ የሚልች 7 ሰዎችን የያዘ ቡድን በሚስጥር መመስረቱ ጉዳዩን በቅርበት ከሚያውቁ ሰዎች  ተሰምቷል ፤ ይህ ቡድን የሚመራው በዶ/ር ሽፈራውና በምክትላቸው በአቶ ሙሉጌታ አማካኝነት ነው ፤ ባሳለፍነው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ይህ ነው የሚባል ጫና ያላደረበት ጉባኤ ቢካሄድም ወደፊት የምርጫ ሕጉ ተዘጋጅቶ ካበቃ በኋላ ሁሉም ነገሮች በሕግና በሕግ ብቻ እንዳይከናወኑ መንግስት እጁን በዚህ ቡድን አማካኝነት እንደሚያስገባ እና እንደማያስገባ ቀኑ ሲደርስ የሚታይ ነገር ይሆናል፡፡በሕገ-መንግሥቱ ላይ “ሃይማኖት በመንግሥት ጣልቃ አይገባም ፤ መንግሥትም በሃይማኖት ላይ ጣልቃ አይገባል” የሚል አንቀጽ ቢኖርም በተዘዋዋሪ መንገድ የመንግሥት እጅ ከሃይማኖቶች ላይ ጣልቃ እየገባ ይገኛል፡፡ 
በአሁኑ ሰዓት ይህን ስውር እጅ ማክሸፍ ይቻል ዘንድ መፍትሄው ያለው ብጹአን አባቶቻችን ጋር ነው ፤ በጊዜው በውስጥም ይሁን በውጪ የሚካሄዱ ሕገ ወጥ የሆኑ ድርጊቶችን በመቃወም የተሰጣቸውን እና የተሸከሙትን ከባድ ኃላፊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ኃላፊነታቸውን መወጣት መቻል አለባቸው፡፡ ይህ ምርጫ አልጋ በአልጋ ይሆናል ተብሎ ባይጠበቅም የሚመጡትን ጫናዎች በመቋቋም ስለ ህዝበ ክርስትያን እና ስለ ቤተክርስትያን ብለው ሁሉንም ነገር በአግባቡ ያከናውኑ ዘንድ ምዕመኑ ከፍተኛ ተስፋ ጥሎባቸዋል፡፡ 
ስለ ቀጣዩ እርቀ ሰላም እየተሄደበት ያለው መንገድ መልካም ቢሆንም ለዓመታት የአዲስ አበባው እና የአሜሪካው ሲኖዶስ በመባል ሲጠሩ የነበሩትን አንድ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ጊዜ ይመጣል ብሎ ማሰብ ይከብዳል ፤ አንድ የምንሆንበት ጊዜ አሁን ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ፤ ነገር ግን ከውስጥም ከውጭም ያሉ አባቶች ያለፈውን ሳይሆን የወደፊቱን በማሰብ ሆደ ሰፊ በመሆን ቤተክርስቲያኒቱ አንድ የምትሆንበትን መንገድ ቢጠርጉ መልካም ነው ፤ ከታሪክ ተወቃሽነትም ለመዳን ይችሉ ዘንድ ምርጫው በእጃቸው ይገኛል ፤ አሸናፊም ተሸናፊም ሳይኖር ይቅር ለእግዚአብሔር ቢባባሉ ቤተክርስትያኒቱን ወደ ቀደምት ስሟ እንደሚመልሷት ተስፋ አለን፡፡
በሌላ ዜና ወ/ሮ እጅጋየሁ የምታንቀሳቅሰው ቡድን በሊቀ ሊቃውንት እዝራ የሚመራው ቡድን የራሱን ተጽህኖ ለማሳደርና ከመንግስት ጋር አብሮ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ፤  ሊቀ ሊቃውንት እዝራ በቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስትያን ላይ ዘረፋ በማካሄድ ታስረው እንደወጡ ይታወቃል ፤ በሌላ በኩልም በአዲሱ ሚካኤል ቤተክርስትያን ላይ ባደረጉት የገንዘብ ምዝበራ ጉዳዩ ምዕመኑ አቤት ለማለት 10 ትላልቅ  መኪናዎችን በመመሙላት ቤተክህነት ድረስ መምጣታቸው ይታወቃል፡፡ 
ጊዜው ሲደርስ ሁሉን ነገር በግልጽ እናየዋለን
እግዚአብሔር ለአባቶቻችን ብርታትና ጥንካሬን ይስጥልን

7 comments:

  1. let's pray for our Ethiopian orthodox church to get a solution from God about the situation we have in beetween us and also to see our church as one we have to forgive each other this is the KEY !!! THANK GOD FOR EVERYTHING!!!

    ReplyDelete
  2. Hulum abat ayidelem, meche naw ye E/her tegetsats labatoch' yemiasfeligew?

    ReplyDelete
  3. like likawent ezra sibal talaqun abat endalhone bigelets tiru new. anbabi limtata selemichel yeseme mokshe hono new. Ezih lay yetegeletsut lezemenat betekrstiyanen sibezebzu ena siyasbezebzu yenoru nachew.

    ReplyDelete
  4. ለመሆኑ ይህን አይነት እድልና መመርያ የሰጣት ምንነው በውነት አባቶችም ይህችን ምንነቷ ያልታወቀ በሕገ ቤተክርስቲያን ገብታ ለመበጥበጥ ያስቻላት ያባቶች ደካማነት እንጂ ምንም አይነት ስልጣን ይሁን አግባብ የሌላት በመሆንዋ በምርኩዝ አርገው ማባረር እንጂ በቤተክርስቲያን ገብታ ማርከስ በጣም ድፍርትትና ሃይማኖታችንን ማራከስ በመሆኑ እጅጋየሁ ምክር ከሰማሽ መልካም ካልሆነ አምላካችን በንጽሕና የመሰረታትን በተመቅደስድ በማጉደፍሽ ጽላቱ አደጋ እንዳያመጣብሽ እግርሽን ስብሰብ አርገሽ ክዛች ደጃፍ እንድትወግጂ ምክር ይሁንሽ አልያ ሰበሉን እንዳትቀምሺ

    ReplyDelete
  5. hi ande adegen why not write about his holiness aba merkorious ?

    ReplyDelete
  6. ye mengsit behymanotoch talqa gebinet ayqomim::alamawu ke eminet yeraqe tiwuld memesret ena mezref silehone bemuslimu emnet gebto mejlis bekebele endasmerete hulu ahunim bihon esu yemifelgewn papas kemasmeret wede huwala aylim .muslimu hule arb eyeteqaweme wedefit yiketlal enantes? ye eminet nesanet mekeber malet hulentenawi selam ena mechachal malet new silezih yitasebibet .ande kehone wediya kemenferaget be eminetachin talqa atgba bilo bedifret menager yegid yihonal

    ReplyDelete
  7. In the Woyane-controlled Synod, seventeen of the 48 Abuna are from Tigray. What kind of representation is this?

    ReplyDelete