Wednesday, October 31, 2012

አባ ናትናኤል ዳግም በፖሊስ ተይዘው ዘብጥያ ወረዱ

(አንድ አድርገን ጥቅምት 21 2005 ዓ.ም)፤- አባ ናትናኤል ትላንት ማክሰኞ ጥቅምት 20 ቀን 2005 . በድጋሚ ታስረው ከአዲስ አበባ ወደ አዋሳ ተወስደዋል፡፡ ግለሰቡ ባለፈው ከመኖሪያ ቤታቸው አዋሳ ድረስ ታስረው ከተወሰዱና በዋስ ከተፈቱ በኋላ ጥቅምት 11 ቀን እሁድ በአየር ጤና ኪዳነ ምህረት / አውደ ምህረት ላይ ሰዎች በክፋት ወንጅለውኝ ነበር፣ የህግ አካላት ግን አባታችን ይቅርታ ብለው አሰናብተውኝ መጥቻለሁ፡፡ እነኝህ የሚሳሳቱ ሰዎችን እግዚአብሔር ይቅር እንዲላቸው ምዕመናን ጸልዩላቸው ብለው ነበር፡፡ በዕለቱም ሲወጡና ሲገቡ ልዩ ጥበቃ እንዲያደርጉላቸውና በየምክንያቱ ህገወጥ እገዳ በሚያደርጉባቸው ምዕመናን ላይ መሳሪያ ይዘው እንዲያስፈራሩ ከቀጠሯቸው 5 ዘበኞች አንዱ፣ ከጽጌ ማዕድ ትርፍራፊ ለመቃረም ከተሰበሰቡ ነዳያን መካከል አንድ ምስኪን በዱላ አንገቱን መትቶ ገሏል፡፡ ሁኔታው እንደተፈጠረ አባ ናትናዔል ግቢውን ትተው ቢሸሹም ጥበቃውና አንድ ካህን፣ እንዲሁም የሟች አስክሬን በፖሊሶች ተወስዷል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ለክሊኒክ መገንቢያ በሊዝ የተገኘን የደብሩን ይዞታ ለቱርኮች ያለሰበካ ጉባዔው ዕውቅና (ራይ ውሉ ምን እንደሚል እስካሁን ማወቅ አልተቻለም፡) በማከራየትና የተሳሳተ መረጃ አውደ ምህረት ላይ በማቅረብ ምዕመኑን ለመከፋፈል ሲሞክሩ ቆይተዋል፡፡ የቦታው ጉዳይ ምዕመኑን ቦታውን ወደሚያሳጣ ውዝግብ ወይም በመቶ ሺዎች ብር የካሳ ክፍያ እንዳያሰጠይቀው የህግ ባለሙያዎች በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡ ከዚህም አልፈው በቤ/ክኗ ስም የአዲስ አበባ መታወቂያ እንዲሰጣቸው የወረዳውን አስተዳደር መጠየቃቸው ምዕመኑን ግራ አጋብቷል፡፡

የደብሩ ምዕመንም ሁሉ ነገር ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት ምእመናንንና ወጣቶችን ሳይከፋፍል፣ የደብሩን ሰላም ሳያደፈርስ፣ ስብከተ ወንጌልን ሳያዳክም የደብራችንን ንብረት ከብክነት ጠብቆ፣ መልካም አስተዳደር አስፍኖ፣ በመንፈሳዊ ሕይወት አርአያ ሆኖን የደብራችንን ልማት የሚያፋጥን አስተዳዳሪ እንዲመደብልን እኛ የአየር ጤና // ኪዳነ ምህረት / ምዕመናን ቅዱስ ሲኖዶስን እንለምናለን!” የሚል መሸኛ ያለው ፊርማ በማሰባሰብ አቃቢ መንበሩንና የቋሚ ሲኖዶስ አባላትን በመለመን ላይ ከርመዋል፡፡
በዚሁ በመበሳጨት ጥቅምት 18 እሁድ በዚሁ ዓውደ ምህረት ላይ ስለ ግድያና የካህን እስር፣ ከወረዳው መሬት አስተዳደር ጋር በተከራየው ቦታ ምክንያት ስለፈጠሩት ፍጥጫ ትንፍሽ ሳይሉ በሃሰት እየተገፉ መሆኑን አብራርተው ከሳሾቻቸውንሆዳሞች” እያሉ ተሳድበዋል፡፡ ከግብር ጓደኛቸው ንቡረእድ ኤልያስ ሐምሌ 11 ቀን 2004 አስጽፈው ያመጡትን ደብዳቤም በማንበብ ሰበካ ጉባዔውን፣ ህንጻ አሰሪ ኮሚቴውንና ሰንበት /ቤቱንበዚህ መሰረት ካልሄዳችሁ ከባለፈው በከፋ እንበጣበጣለንሲሉ ዝተዋል፡፡ አዋሳ በነበረው ረብሻ ቀንደኛ አስተባባሪናያለነውጥ ለውጥ የለምማለታቸው ይታወሳል፡፡ በዕለቱ 130 በፈጀ ዘለፋዊ ትምህርታቸው ግራ የተጋባው ምዕመን እያዘነ ነበር የተበተነው፡፡

ይኽውለቀጣይ እሁድ ሰበካ ጉባዔ አስመርጣለሁ (ነባሩ ሰበካ ጉባዔ ሪፖርት ገና አላቀረበም) የሚቃወሙኝን ልክ አስገባለውያሉት አባ ናትናኤል በአዋሳ ከተማ ከፍተኛ /ቤት አቃቤ ህግ እጃቸውን ተይዘው አዋሳ ዘብጥያ ወርደዋል፡፡ አዋሳ ፖሊስ ጣቢያ ሲደርሱምአቃቤ ህጉ መንገድ ላይ ሰው ገጭቶ ነው የመጣው” የሚል ክስ ካልመሰረትኩ ብለው መሳቂያ ሆነዋል፡፡

በመነኩሴ ቀሚስ ውስጥ የተደበቀውበነፍስ ግድያ ሙከራ፣ በገንዘብ ዝርፊያና በንብረት ብክነትየተከሰሰው አባ ናትናዔል ነገ ሐሙስ ለፍርድ ይቀርባል፡፡ እዛው የሚቆይ ከሆነ የአየር ጤና ምዕመንም ከኪዳነምህረት ታቦት ፍትህ እንዳገኘን እንቆጥራለን ብለዋል፡፡
 
ግብር አበሮቻቸው በብሎጋቸው  እንዲህ ብለው ጽፈውላቸዋል
“አባ ናትናኤል፣ ቤተክርስቲያን በልማት ራሷን እንድትችል ካላቸው ፅኑ ፍላጎት የተነሳ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል ት/ቤት ያሳነፁ፣ ለቤተክርስቲያኗ ገቢ ማስገኛ ካቻማሊ አውቶቡስ አስገዝተው ዋናውን መልሶ ትርፍ ማስገኘት እንዲጀምር ያስደረጉ፣ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ አስቆፍረው ብሎኬት ማምረቻ ያቋቋሙ፣ ለወንጌል ማስፋፊያ ሞንታርቦ ድምጽ ማጉያዎችን ያስገዙ፣ መሠረቱ የተጣለውን የቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ሕንፃ ወደ ፍጻሜ ያደረሱ፣ በሕፃን ዐዋቂውና በሁሉም ምዕመናን ዘንድ ፍቅር የሆኑ የወንጌል ማስተማር ሀብተ ፀጋ የታደላቸው፣ የዜማ ችሎታ ያላቸው፣ በሁለ-ነገራቸው ተወዳጅና አርአያ የሆኑ፣ ከሕዝብና ከቤተክርስቲያን ገንዘብ ሊዘርፉ ቀርቶ በተቃራኒው የግል ወርሃዊ ደመወዛቸውን ለቤተክርስቲያንና ለወንጌል ማስፋፋት የሚሰው፣ በሥርዓተ ምንኩስና የታቀቡ ድንቅ አባት ናቸው፡፡ ምዕመናንም እርሳቸውን ከመውደዳቸውና ከማፍቀራቸው የተነሳ “አባ ናቲ” እያሉ ነው የሚያቆላምጧቸው፡፡” ይህን አንብበን ስንጨርስ ሌላ አባ ናትናኤል የሚባሉ አባት ፍለጋ ያዝን……..
 

3 comments:

 1. Afrodayt /KARLSRUHEOctober 31, 2012 at 11:57 AM

  ለመሆኑ ቤተክርስቲያን ስው የላትም እንዴ ? የሌባና የወንበዴ ዋሻ የምትሆነው እስከመቼ ነው ሲኖደሱ የቤተክርስቲያኖን ጠባቂ ሲሆን ከለምድ ከለበሱ ተኩላ ማለኮሳት ሕዝበ ክርስቲኑን ቤተክርስቲያንን የሚተብቀው መቼነው በጎቹ ተበትነው የተኩላ በጫወቻ ከሆኑ በኃላ ነው እስከ መቼ እያዮ እንዳላዮ ሰምተው እንዳልሰሙ መሆን አያዋጣም የእግዚአብሔር ፍርድ ቅርብ ነው በቃል ኬዳን የተቀበላችሁበት ስልጣነ ክሕነት ፍርድ ይስጣል እግዚአብሔር ለተበተኑት በጎች ጠባቂ ያዘጋጃል የቅዱሳን አባት የፈሰሰውን እንባ ያብሳል ላዘኑት መጽናናትን ያመጥል ቢተክርስቲያን እጆቻን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።

  ReplyDelete
 2. Abetu eskemeche fetsemh tetewenalh? eskemeches fithen kegna teseweralh? Yebetkirstiyan amilak yetadegen .wedajoche tselot tselot tselot .Ye Jerusalem gedamatem yehew yewenbede washa huno yechawetubetal ye Ante yalehh yeminlew atenal ke Lik eske dekin hulu ande aynet.

  ReplyDelete
 3. ያሳዝናል እሳቸዉም እናንተም እሳቸዉስ እንደናንተ አባባል ከሆነ ተፈትነዉ ከወደቁት አንዱ ሆነዋል የሞተላቸዉ አምላክ የድንግል ማርያም ልጅ ለንስሃ ያብቃቸዉ የናንተ ግን የክርስትያን ልብ የሌላችሁ ጨካኝ "ዘብጥያ ወረዱ" አባባላችሁ ከጣላቸዉ ሰይጣን ጋር አብሮ ደሰ ያላችሁ ነዉ የሚመስለዉ ሰየጣን ከዚሌላ ምን ይላል ከጣላቸዉ ሰይጣን በምን ተለያችሁ

  ReplyDelete