Wednesday, October 17, 2012

ቂል የያዘው ሰይፍ
(ፕሮፌሰር መስፍን ጥቅምት 2005 ዓ.ም):-  በቅርቡ አቶ ስብሐት በአደረገው ቃለ መጠይቅ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የተሾመው ወያኔ ዱሮም አስቦበት ወንበሩን ከአማርኛ ተናጋሪዎችና ከኦርቶዶክስ አማኞች ለማጽዳት በተዘጋጀበት እቅድ ነበር ብሎአል፤ ልብ ላለው አነጋገሩ በሁለት በኩል ስለት ያለው ቂል የያዘው ሰይፍ ነው፤ ከፊት ለፊት የተሰነዘረው አማርኛ ተናጋሪውንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አማኙን ለመምተር ነው፤ ቂል የሚያደርገው አማራ የሚባል ጎሣ ቢኖርም የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በአማርኛ ተናጋሪዎች ታጥሮ ትግሬንና ኦሮሞን፣ ወላይታንና ጉራጌን፣ ሌሎችንም የማይነካ መስሎት ከባድ ስሕትት ላይ መውደቁ ነው፤ ከሁሉም በላይ እሱን የሚያህል ሰው የተክለ ሃይማኖትን ታሪክ አለማወቁ ያሳዝናል፡፡

አማራንና የኦርቶዶክስ ተከታዮችን መትሮ ሲመለስ ደግሞ ሰይፉ የሚቀላው ወላይታንና ጴንጤነትን፣ ምናልባትም እስልምናን ይሆናል፤ አቶ ስብሐት በፊት ለፊት የተናገረው ገና የዛሬ ሀያ አንድ ዓመት ‹‹እንዳያንሰራራ አድርገን አከርካሪቱን እንሰብረዋለን›› ተብሎ ያለቀለትን አማራ ዛሬ ወንበር ማጣቱን ለማብሰር አልነበረም፤ ይህ በጣም ግልጽና ከማንም ያልተሰወረው እውነት ነበር፤ ስውር ዓላማም አለው፤ ያንን ብዙ ሰው አይገነዘበውም ይሆናል፤ በአቶ ስብሐት አነጋገር ውስጥ ዋናውና ተንኮልን ያዘለው ዓላማ ወንበሩን የያዘው ዋናው የወላይታ ጴንጤ ሲሆን ምክትሉ ደግሞ እስላም መሆናቸውን ለመናገር ያለው ፍላጎት ላይ ነው፤ ከአቶ ስብሐት ነጋ በቀር የአዲሶቹን ሹሞች ዘርና ሃይማኖት ከጉዳይ ያስገባ ያለ አይመስለኝም፤ አቶ ስብሐት በፊት-ለፊት ዓላማው ተስፈንጣሪ ተራማጅ ሲመስል በስውሩ የተንኮል ዓላማው ግን ኋላ-ቀር ወግ-አጥባቂ ይሆናል፤ በዘርና በሃይማኖት ላይ ሲያተኩር ዋናውን ቁም-ነገር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ምክትሉ ሰዎች፣ ከዚያም ቀጥሎ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ፈጽሞ ዘንግቶታል፤ ለእኛ ትልቁ ነገር ይህ ነው፤ በሁለታችን መሀከል ያለው ልዩነት ስብሐት ኢትዮጵያውያንን የሚያዛምዳቸውን ሁሉ አያይም፤ እኔ ደግሞ ኢትዮጵያውያንን የሚለያያቸውን ሁሉ አላይም፡፡


መጥፎ ልማድ 

(አንድ አድርገን ጥቅምት 7 2005 ዓ.ም)፡- የዛሬ ዓመት ግድም ቅዱስ ሲኖዶስ መርጦ ያስቀመጣቸውን ብጹአን አባቶቻችንን አቶ ስብሐት ተነስቶ የስድብ ውርድብኝ ሲያወርድባቸው ቤተክርስትያኒቱንም ሆነ አባቶችን ወክሎ መናገር የደፈሩ አባቶችን አልተመለከትንም ፤ “ቤተክርስትያኒቱ በጳጳሳቱ አማካኝነት ገደል አፋፍ ላይ ናት” ፤ ጳጳሳት እንዲህ ናቸው…” በማለት አቦይ ስብሐት ሲናገር መልስ የሰጠ አካል አልነበረም ፤  ሰውየው ሳይናገር ሳይሆን ተናግሮ እንደሚያስብ የሚያውቁት ይናገራሉ ፤ ይህ የመሰለው ያለአግባብ ዘለፋ በምዕመኑ ዘንድ የሚያሳድረውን የውስጥ መሰበር ማንም አልተመለከተውም ፤ አፉን ለከፈተ ሁላ ቅዱስ ሲኖዶስም ሆነ ብጹአን አባቶች መልስ ይስጡ እያልን ሳይሆን ከአንድ ትልቅ የሚባልና የመንግስትን ቁልፍ ቦታ የያዘ ሰው ያለ አግባብ ንግግር በቤተክርስቲያን እና በአባቶች ላይ ሲናገር ግን ዝም ተብሎ መመልከት ያለበት አይመስለንም ፤ የተሰደቡት አባቶች ብቻ ሳይሆኑ በሚሊየን የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች ጭምር መሆናቸው መዘንጋት የለበትም ፤ ዝምታችንን ጥቅሙንና ጉዳቱን በአግባቡ ያወቅነው አይመስለንም ፤ “ዝም አይነቅዝ” የሚለው የሀገራችን ብሂል የሚባልበት ቦታ እንዳለ ሁላ ዝምታም የሚነቅዝበት ውሎ አድሮም ችግር የሚያመጣበት ሁኔታም እንዳለ መዘንጋት መቻል የለብንም ፤ 


በየጊዜው ከመንግስትም ይሁን ከተለያዩ አካላት የሚነሱትን ዘለፋዎች እና ስም ማጥፋቶች በጊዜው መልስ መስጠት ካልቻልን ውሎ አድሮ የምንሰጠው ምላሽ ውሃ ያዘለ ላይሆን ይችላል የሚል እምነትም ስላለን ጭምር ነው ፤ እስከ አሁን ድረስ ቤተክርስቲያኒቱ ስትሰደብ ዝም ፤ ጳጳሳቱ ሲሰደቡ ዝም ፤ ማህበራት ስማቸው  ሲጠፋ ዝም ፤ ምዕመኑም ስም እየተሰጠው ሲንገላታ ዝም ካልን ነገ ህዝቡ ላይ የሚያመጣው Psychological impact ሊናጤነው ይገባል ፤ ሰው ዝም ሲል ሁለት አይነት ምልከታ አለው አንድም “ጉዳዩ አያገባኝም ፤ ጉዳዬም ጉዳዬ አይደለም” በማለት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ውስጡ እየተቃጠለና በነገሩ እየተንቦገቦገ አቅም ስለሌለው ብቻ ዝም ማለቱ ነው ፤ ብዙዎች በየትኛው ውስጥ እንዳሉ ማወቅ አዳጋች አይሆንም፡፡ 


10 comments:

 1. ሙሀመድ ነኝ(የብሎጉ ደንበኛ)
  ወገኖች ይህን መንግስት በቆይታ ስትርረዱት ያኔ ምንም አይነት እምነት እንደሌለው እና እምነቱም ስልጣን እና ንዋይ ብቻ እንደሆነ ትርረዳላችሁ!ባለፈው ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ካልጠፋ ስኳር ፋብሪካ ዋልድባ ለምን ሄደ?የሚል ነገር አንስተን ከአንድ ጓደኛየ ጋር ስንወያይ
  የክርስቲያኖችም ቢሆን የሃገር ታሪክ እና ቅርስ ይመለከተናል እና ለምን ዝም እንላለን ተባባል።ያኔ ነው እነሱ የ እኛን መብት መጣስ እንዴት በዝምታ ያውታል?ብሄራዊ ስሜት ካላቸው ለምን በሃይማኖታችን ጣልቃ ተገብቶ መንግስት ሃገር ሲረብሽ ነገ ሲኖዶስ ቀበሌ ላለመመረጡ ምን ማስረጃ አለ?በማለት ሞገተኝ።ስልጣን ከአማራ እና ከ ኦርቶዶክስ ለመንጠቅ አስበን አድረግነው የሚባለውን ለሁለተኛ ጊዜ መስማቴ፡ነው የኔ እይታ ከ እናንተ የተለየ ሊሆን ይችላል።ይህ መንግስት እነዚህን ሃይማኖቶች የሚዘልፍበት ምክንያት ምንድድን ነው?ለምን ፕሮቴስታንት አልተባለም?ለምን ካቶሊክ አልተባለም?ይህ አባባል አሁን በጥሬው ያልተዋጠለት ቋንጣውን ይቆረጥመዋል።መንግስት ህዝበ ክርስቲያኑን በሙስሊሙ ላይ ለማነሳሳት ያደረገው ሙከራ ሲከሽፍ በተናጠል የመኮርኮም እቅድ አውጥቶ ማህበረቅዱሳን እና ወሃብይ ብሎ ሁለት ጎራ ፈረጀን።እናንተ ያኔ ወሃብይ አለ ግን ማህበረቅዱሳን ለምን ተጠቀሰ ስትሉ ተቃወማችሁ።አሁን ኦርቶዶክስ ተብሎ በገሃድ ሲወራ ስልጣን ለሙስሊም ስለተሰጠ ያን ለመግለጽ ነው ካላችሁ ተሳስታችኋል።ምክትሉ የተሾመበት የራሱ የወያኔ ድብቅ አላማ አለው እንጅ ከ እስልምና ተከታይነት ጋር ግንኙነት የለው።ጊዜ መስታወት አይደል?ሃይለማርያም ለኦርቶዶክስ እና ለሙስሊሙ ያለውን ጥላቻ የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።በ እርግጥ የሙስሊምሙን እያየነው ነው።ታዲያ የ እኛ መብት እና እምነት ሲጥታስ ለምን ከጎናችን አትቆሙም?የ እናንተ በአደባባይ እስኪጣስ ድረስ ከሆነ ወያኔ ዕምነት የለውም፡፤ኪሱ ከደለበ እኛን አባልቶ ወደ ውጭ ይኮበልላል።የቱባ ባለስልጣን ልጆችም ውጭ ናቸው።ምስኪኑ ኢትዮጵያዊ ቢባላ ለነሱ ምናቸውም አይደለም እና ይህን መንግስት ከድንበሩ ብናስቆመው ይምመረጣል።ሃይማኖታችንን ለቀቅ እንዲያደርግልን።እኛማ ትግሉን ጀግኖች ጀምረውታል።እስር ቤትም ገብተዋል እነሱ ቢሰው እንኳ ትግሉን ጀግኖች ይጨርሱታል።የ እኛ ትግል ከጨቋኞች ጋር ብቻ ነው።ቢሆንስ አፍ አውጥቶ ስልጣን ከአማራ እና ከኦርቶዶክስ ነጠቅን ይባላል?አያያዙን አይቶ ጭብጦውን ቀማው ይላሉ እንዲህ ነው።ስለዚህ ይህን መንግስት በጋራ እንታገለው እና በመከባበር እንንኑር።ያስኬዳል?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yes! I support yur idea. Let us join our hands together (Muslim and Christian) and wipe woyane out of the picture!!

   Delete
  2. Yes!! I support your idea. Let us join our hands together and wipe woyane out of the picture. It is possible!!

   Delete
 2. First and foremost than you for you information.We know these people very well.
  As the saying goes,SEBHAT NEVER DO THAT.BECAUSE THE FAMILY HE HAD
  BROUGHT UP HAD NEVER SHARPEN HIS TONGUE AND GULLIBLE HEART.HIS HATRED IS BASED ON THE
  FRUITLESS AND INFERTILE PHLOSOPHY < A MULE NEVER GIVE BIRTH THEREFOR IT DISLIKES
  THOSE WHICH GIVE BIRTH.>BROTHERS,BE PATIENT AND PERFORM WHAT GOD COMMANDS YOU TO DO.LOOKING AT EARTHLY CREATURES WE MAY LOSE HEAVENLY PLACE.HE CANNOT LEARN.
  AS WE

  ReplyDelete
 3. Muhamd

  Bedenb yashedal!!!! This people are waiting ther days. Any one who raise his hand on God, he will be uprooted. See soon what happen in between this thieves.

  ReplyDelete
 4. ENANTE SEWOCH MIN SEWEN TAGACHALACHEHUU ENDEE LEMEHONU EGZIABHER YIHEN ASTEMAREN ENDEE? LETENAGERE HULU MELS MESTET YELEBINIM EGZIABHER ERSU HAYEL ALEW GIZEM ALEW ERE POLETIKA AYETEKIMENEM TSELOT ENA TSOM YESHALAL LEMIND NEW EGNA ORTODOXAWEYANOCH ENDEZHI NEGEREGNOCH YEHONEW?EGNA EYETENAGERN NEW EGZIABEHER MELS YAKOMEW 21 Amet TASHEN GENA DEGEMO SENT ENTASH YIHON??? AYEEE MEKERACHENNN

  ReplyDelete
 5. Can you please drop a reference to this so that it is credible? Thank you

  ReplyDelete
 6. It is a surprise to hear such a silly words, wishes and imaginations, Sbhat is a hero of heroes, this is totally black painting (defamation) no matter from which side it comes, as we are diversified, the most confusing and toxic rumors came from the religious perspective, but this doesn`t bring any change and is considered as thrash message.
  Long live ETH with its Heroes!!

  ReplyDelete
 7. Devil usually assign sinister individuals among innocents to stir up the life
  of God's children.Nowadays,we are being tormented by inhumane militias of devil.We should say"I can do through Him who strengthens me."Time heals
  everything.God has time to perform His duties.Regarding the old guy,he is a half-baked person who does not act his age.He is one of"waterless springs".2peter17.

  ReplyDelete
 8. አማራ የኢትዮጵያዊነት ፍቅር አንቆት ነው ላለፉት ሃያ ሁለት አመታት የሚያርና የሚከስለው።
  አማራ ኢትዮጵያ ባይል ኖሮ እንደ ወያኔ ስራ ቢሆን ግን ዛሬ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አትኖርም ነበር።
  አማራ ቢደራጅና በአንድነት የመገንጠል አላማ ቢኖረው ንጹህና ከዘረኞች ነጻ የሆነች ኢትዮጵያን መመስረት እንደሚችል አትጠራጠሩ።

  ReplyDelete