Thursday, October 25, 2012

በርሀ ላይ ላሉት አብያተክርስቲያናት የተደረገ እርዳታ
 (አንድ አድርገን ጥቅምት 14 ፤ 2005 ዓ.ም)፡-ጊዜው ከሁለት ዓመት በፊት ነው ፤ ቦታው ሀረር ድሬዳዋ መንገድ አዋሽ አለፍ ብለው አውላላ በረሀ ላይ የሚገኙ አብተክርስቲያናት ናቸው ፤ ከነርሱም ውስጥ ኮራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ፤ ቦርደዴ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን፤ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እና በቅርብ የተሰራችው ኪዳነ ምህረት ቤተክርስትያና ናቸው ፡፡ ሁሉም አንድ የሚያደርጋቸው በርሀ ላይ መገኝታቸውና በጣም ጥቂት የሚባሉ ምዕመናን በመኖራው ነው ፤ በአራቱም ቦታ የሚገኙ ምዕመናን ቢደመሩ ሶስት መቶ አይሞሉም ፤ ሁሉም ለቤተክርስትያናቸው ያላቸው ቅንአትም አንድ ያደርጋቸዋል ፤  በወቅቱ ከአራቱ ሁለቱን ቤተክርስትያኖች የማየት እድል ገጥሞን ነበር ፤ በዚያን ጊዜ የነበሩ ካህን እንደገለጹልን ከሆነ ቅዳሴ ለመቀደስ ጧፍ አጥተው በኩራዝ ወንጌልን ያነበቡበት ጊዜ መኖሩን አጫውተውናል ፤ እነዚህ ቤተክርስትያናት ንዋየ ቅዱሳት የሚያገኙት በምዕመኑ ከእጅ ወደ አፍ ከሆነ ኑሮ በሚዋጣ ጥቂት ገንዘብ አማካኝነት ነው፡፡ በየጊዜውም አሰበ ተፈሪ አካባቢ የሚገኙ ወጣቶች ብር በመሰብሰብ ለቅዳሴ የሚያስፈልጋቸውን ነገር አቅም በፈቀደ መጠን እንደሚያመጡላቸው ነግረውናል ፡፡ 

አንድ ወቅት በእለተ ቅዳሜ በቤተክርስትያኑ ውስጥ ጧፍ አጥተው በምንድነው በእለተ ሰንበት ቅዳሴ የምናደርሰው ? በምንስ ነው ወንጌልን እና ድርሳናትን የምናነበው ? እያሉ ተጨንቀው ነበር ፤ ከዚያን በሚቀጥለው እሁድ ቀን እርሱ ያውቃል በማለት ባለችው ጧፍ ቅዳስ ገቡ ፤ ይህ እንዲህ እያለ አንድ ወጣት ቅዳሴ ገብተው ትንሽ እንደቆዩ ሲፈጥን ወደ ቤተመቅደስ ገባ ፤ በእጁም በርካታ ጧፍ ይዞ ነበር ፤ ይህ ወጣት ይዞት በመጣው ጧፍ አማካኝነት ቅዳሴው ሳይስተጓጎል በሰላም መጠናቀቅ ቻለ ፤ ይህ ወጣት በዚያች ለሊት በህልሙ ያየውን እንደተናገረው ጧፍ ተቸግረው እንደተመለከ እና ይህ መልዕክት ያለ አንዳች ምክንያት ለእኔ ሊታየኝ አልቻለም በማለት በለሊት ተነስቶ ከአቅራቢያው ደብር በመሄድ ጧፍ በመግዛት በህዝብ ትራንስፖርት ሲጣደፍ እንደመጣ ከቅዳሴ በኋላ ተናግሯል ፤ እግዚአብሔር ለቤቱ ያስባል ማለት እንዲህ ነው ፤ ቤቱ የሚያስፈልገውን ነገር ብናሟላ የምንጠቀመው እኛው ነን ፤ ማድረግ እየቻልን ሳናደርግ ብንቀር የሚቀርብን እኛው ነን ፤

ቦርደዴ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ከሚገኙ ከ30 የማይዘሉ ክርስትያኖች የአህዛብ ፈተናን ተቋቁመው ሲኖሩ የንዋየ ቅዱሳት ነገር ደግሞ የሁል ጊዜ ችግራቸው መሆኑን በጊዜው ባየነው እና በተመለከትነው ነገር መረዳት ችለናል፡፡ ቤተክርስትያኑ ግድግዳው የተቀደደ ነው ፤ ፀሀይና ንፋስ ሰተት ብለው እንደሚገቡም ተመልክተናል ፤ ቤተክርስትያኑ ውስጥ ገብተው ወደ ጣራው አይኖትን ቢልኩት በርካታ ቀዳዳዎችን ያስተውላሉ የሰማይ ከዋክብትም ጣሪያው ላይ የወረዱ ይመስሎታል ፤ ቤተክርስትያኑ ያረፈበት ጥቁር አፈር ላይ ስለሆነ በጥቂት ጊዜ ውስጥ እንደሚፈርስ ያስተውላሉ ፤ በአሁኑ ሰዓት ለትውልድ የሚተላለፍ ቤተ ህንጻ ለመገንባት ዲዛይኑ በአንድ ወንድም በነጻ ተሰርቶ አልቋል ፤ “እኛ እንጀምረው እግዚአብሔር በፈቀደ ሰዓት ይጨርሰው” በማለት ትልቅ ቤተክርስትያን ለመስራት እነዚሁ 30 የማይሞሉ ክርስቲያኖች ወገባቸውን ታጥቀው ተነስተዋል ፤ የግንባታ ወጪም 2 ሚሊየን ብር ይደርሳል ተብሎ ይገመታል፤ ወደፊት ስለ አዲሱ ህንጻ ቤተክርስትያን ለመርዳት የሚፈልጉ ሰዎች ዲዛይኑን የሚያስፈልገውን ብረት ፤ አሸዋ፤ ጠጠር ሲሚንቶ እና መሰል የህንጻ መሳሪያዎችን በዝርዝር እናቀርባለን፡፡

ይህ ቤተክርስትያን አካባቢ ያሉ አህዛቦች የዛሬ አመት የእመቤታችን ጾም ወቅት ላይ “ቤተክርስትያኑ ይዘጋልን” በማለት ለወረዳው ሃላፊ ጥያቄ አቅርበው ነበር ፤በቦታው ላይ ያለው ፈተና ከዚህም የሚበልጥ ነው ፤ በቦታው ላይ በሄድንበት ወቅት የቤተክርስትያኒቱ አስተዳዳሪ አባት ስለ ቤተክርስትያኑ እና ስላለባቸው ፈተና በድምጽ ማጉያ ትንሽ ከነገሩን በኋላ አካባቢው ላይ ያለ ሰው እንዳይሰማ በማለት እደረሱባቸው ያለውን ችግር ማይኩን ወደ ታች በማድረግ እና በአነስተኛ ድምጽ አይናቸው እምባ ሞልቶት ሲናገሩ ለተመለከታቸው በበረሀ ላይ የሚገኙት አብያተክርስትያናት ምን ያህል ተነግሮ የማያልቅ ችግር እንዳለባቸው ይገነዘባል ፤ እሳቸው ሲናገሩ እኛ የበርሀው ሙቀት በጀርባችን ላባችን ይንቆረቆር ነበር ፤ ማይኩን ወረድ አድርገው የተናገሩበት ምክንያት እንዴት እንዲህ ትላላችሁ በማለት ሌላ ችግር እንዳይፈጥሩባቸው መሆኑ ገብቶናል ፤ ቤተክርስትያኑ ዙሪያውን አጥሩ የተከበበው በአህዛቦች ነው ፤ እኛ ለሰዓታት መቆየት ያልቻልንበት ቦታ እነርሱ ግን ኑሯቸውንም አገልግሎታቸውንም በበርሃ ላይ ያደረጉትን አባት ስናስብ እጅጉን ገረመን፤  ፡፡

ከቦርደዴ ጥቂት ኪሎሜትር አለፍ እንዳሉ ኮራ ቅዱስ ገብርኤልን ያገኙታል ፤ እርሱም ከቦርደዴው ቤተክርስትያን በጊዜው በባሰ ሁኔታ ይገኝ ነበር ፤ ቦርደዴ ሁለት ቄሶች እና አንድ ዲያቆን በቋሚነት ሲያገለግሉ ፤ ኮራ ገብርኤል ግን እስከ አሁን ድረስ የአገልጋይ ችግር እንዳለበት ነው ፤ ማህበረሰቡም በዚህ ምክንያት ዘወትር ሰንበትን ብቻ እንኳን ቅዳሴ ማስቀደስ አልቻለም ፤ የአገልጋይ እጦት የመታው ቤተክርስትያን ቢኖር የኮራው ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ነው፡፡ እኛም ያየነውን ነገር ብንጽፍና ሺዎች ቢያነቡት እንኳን አንድ ወይም ሁለት ሰው እግዚአብሔር ያነሳሳው ሰው ጥቂትም ብትሆን ሊረዳቸው ይችላል ብለን በማሰብ በቦታው ያየነውንና የተመለከትነውን ነገር በጽሁፍ አማካኝነት ሰዎች ዘንድ እንዲደርስ በጊዜው አድርገናል ፤ ጽሁፋችንን በብሎጋችን ላይ ያነበቡ ሰዎች ቦታው ድረስ በመሄድ ለቦታው ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያስብል መልኩ የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በአል በሚከበርበት ወቅት ለኮራ ገብርኤል 23 ሺህ ብር መሰብሰብ ችለዋል ፤ መግቢያ በሩ በጭራሮ የነበረው ቤተክርስትያን አሁን አሰበ ተፈሪ አካባቢ በሚገኙ ወጣቶች አማካኝነት ጥሩ በር ተገጥሞለታል ፤ የቤተመቅደሱን ወለል ፤ ኮርኒስ እና ግድግዳ በጥሩ ሁኔታ ሰዎች ተነሳስተው ማስተካከል ችለዋል ፤ አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ትልቅ የሚባል አዳራሽም እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ ይህ ሁሉ ነገር ይበል የሚያስብል ቢሆንም የአገልጋዩ እጥረት ግን አሁንም ችግር ሆኖ ይገኛል፡፡ 


ለቤተክርስትያኑ የተገዛበት ደረሰኝ…(የተላከው ብር ምን ቦታ እንደዋለ ስካን አድርገን ከቀናት በኋላ ፖስት እናደርጋለን)
ከወራት በፊት አንዲት እህት ከአረብ ሀገር በላከችው ብር አማካኝነት በአካባቢው ለሚገኙ ቤተክርስትያኖች ንዋየ ቅዱሳት በመግዛት  መላክ ችለን ነበር ፤ አሁን ደግሞ አንድ ወንድም በላከልን 2900  ብር አማካኝነት ጧፍ እጣን እና ሞጣህት በመግዛት ወደ ቦታው ለመላክ ተዘጋጅተናል ፤ ይህን ለመጻፍ የወደድነው ይህን አንብበው ጥቂት ሰዎች እጃቸውን ሊዘረጉ ይችላሉ ብለን በማሰብ ነው ፤ እኛ እንደተመለከትነው ለቦታው አንዲት ጧፍ ዋጋ አላት ፤ እኛ  በስታዲየም ፤ በሰዎች ቀብር ላይ ፤ በተለያዬ ጉባኤያትና በተለያዩ ቦታዎች  ብርሀን ሳያጥረን በሺህ የሚቆጠሩ ጧፎችን ለስነ-ስርአት ድምቀት ሲባል እናነዳለን ፤ እዚህ ቦታ ግን አንዷ ጧፍ ዋጋዋ ብዙ ነው ፤ ይህን ብር ለላክልን ወንድማችን እግዚአብሔር ይስጥልን እያልን መርዳት የምትፈልጉ ሰዎች 0913-833532 (አባ ፍጹም ) በመጠቀም የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያንን አስተዳዳሪ ማግኝት እንደምትችሉ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ከሁለት ወር በኋላ የሚከበረውን የቅዱስ ገብርኤልን ዓመታዊ በአል ላይ ወደ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ለምትሄዱ ሰዎች አዋሽን አለፍ እንዳላችሁ ቦርደዴ አካባቢ ስትደርሱ ጧፍ ፤ እጣን እና መሰል የቤተክርስትያን መገልገያዎችን የሚቀበሉ የአቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ዲያቆናትና ቀሳውስት  ስለምታገኙ በእርሱ አማካኝነት መርዳት እንደምትችሉ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡    
ማን ያውቃል የጧፍ ፤ የእጣንና  ችግራቸውን የሚቀርፍ ሰው አለሁ ሊላቸው ይችላል፡፡


ይህን ጽሁፍ ጽፈን እንደጨረስን ለእነዚህ ቤተክርስትያን የሚሆን ሌላ ተጨማሪ 1923 ብር አግኝተናል.. .. ለሰጣችሁ እግዚአብሔር ይስጥልን ብለናል ፤ ምን ነገር ላይ እንደዋለ ከቀናት በኋላ ሙሉ መረጃው እንለጥፋለን4 comments:

 1. Mechem Melkam Neger mesimat bicha Waga yelewim Mesirat yasifelgenal Behagerachin Berkata Habitam Adibaratna Gedamati Endalu Hulu Mekedesha Techegirew yemitayu degimo Berkata Nachew Genzeb Lemelak Eidichin Ketsitega Addirashachihun Mezigubulig Beteley Ahun lezegebachihut Malete new behagerechin yalutin berkata gedamatina Adibarat lemerdat beyegizew emokiralehu Ahunim Kechaliku Kerase kalifekede kebego adirag emokiralehu Tebareku

  ReplyDelete
 2. Endet meredat enechilalen - please more info.

  ReplyDelete
 3. Dear brothers and sisters
  I read the whole content that you wrote last time and I called with the phone number that you mentioned above. I asked the Priest which bank account does I will send the money then he replied with traditional way of our home. Then after, I am not happy to give in that way. The other thing it is not easy for me to send items way at last I gave up. But still the money is available.I advice you instead of showing receipt and phone number to us, it is better to open bank account with the name of all the church together and post on Andadirgen. The remain auditing is the task of BETEKINETI and the church.In this way it is extremely easy for all the believers to use the account from all over the world to send money. I appreciate your commitment, I hope God will help you! What TEWAHIDO needs a person like you! Instead of always talking to problem let start to put our share. I wish to see the account soon! God bless us!

  ReplyDelete
 4. The Angry EthiopianOctober 26, 2012 at 7:22 PM

  I support your cause 100%. So, should we just contact Aba Fetsum or is there another platform that one could use to send money ?

  ReplyDelete