
ቅዱስ ሲኖዶሱ 20 ያህል
የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳላፈ ሲሆን፥ በተለይ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ቅኝት አድርጎ ቤተክርስቲያኒቱ የበኩሏን ድጋፍ ለማድረግ አብይ ኮሚቴ አቋቁማለች። ከዚህ ውጪ ስርአተ ቤተክርስቲያንን ከማስጠበቅ ባለፈ ሃገራዊ ልማቶች ላይ ተሳትፏዋን ይብልጥ ለማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ ውሳኔዎችም ተላልፈዋል ነው
ያሉት።
የመልካም አስተዳደር ዕጦትንና የሙስና መስፋፋትን አስመልክቶ ቤተክርስቲያን
በተገኘው አጋጣሚ አጥብቃ እንድታስተምር ሲኖዶስ ወስኗል። ቤተክርሰቲያኗ
የራሷን ሃይማኖታዊ ትምህርት እና ሌሎች መልእክቶች ተደራሽ በሆነ መንገድ ለማስተማር የሚያስችል ፕሮጀክትም መንደፏን በመግለጫው ላይ ተመልክቷል።
ሲኖዶሱ ከ159 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር
በላይ ዓመታዊ በጀት አጽድቋል።
No comments:
Post a Comment