Wednesday, November 4, 2015

መምህር ግርማ ማናቸው? በቀድሞው ዳኛ ዘውዱ ታደሰ "

  •  መምህር ግርማ እውነት አጥማቂ ነውን ?
  • የመጀመርያ ሚስቱ በአሁን ሰአት ተለያይተው ሰው ቤት እንጀራ በመጋገር ነው የምትተዳደረው

(አንድ አድርገን ጥቅምት 23 2008 ዓ.ም)፡- እኔ መምህር የሚባለውን ሰው አቶ ነው የምለው ግርማን የማውቀው የቀድሞ ጦር ሰራዊት መቶ አለቃ ሆኖ በጡረተኝነት በመቂ ከተማ ነዋሪ እያለ ትዳርም የነበረውና 2 ልጆች እንዳሉትም አውቃለው።  አቶ ግርማን የት እና እንዴት አወኩት? እኔ የምስራቅ ሸዋ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኜ 1996 መቂ እኖር ነበር ፤ ከዛም ጋር ተያይዞ በቤተክርስቲያና ቅርብ ስለነበርኩ ከምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አብነ ጎርጎሪዬስ ጋር የቀረበ ግንኘነት ስለ ነበረኝ ፡፡ የዝዋይን ሀመረ ኖህ መንፈሳዊ ኮሎጅ ሰበካ ጉባኤ ሆኜ 3 አመት መርቻለው በዚህ ጊዜ አቶ ግርማ የዘበኝነት (የጥበቃ ስራ ) ማስታወቂያ ስናወጣ ወታደር ስለሆነ ተፈትኖ አልፎ በእኔ ፊርማና ማህተም ቀጥሬዋለው፡፡
ይህ ግለሰብ እንደማንኛውም ተራ አማኝ ነው፡፡ እኔ ሳውቀው የክህነት ትምህርት ፈፅሞ የለውም፡፡ በጥበቃ ከሰራ በኋላ ቋሚ አድርጉኝ ደሞዝም ጨምሩልኝ ብሎ በደብዳቤ ወረቀት ለኔ ቢሮም በአካልም አናግሮኝ ታገስ አባታችን ይምጡና እንነግራቸዋለን ብዬው የተከበሩ ብፁዕ አባታችንም አባ ጎርጎሪዬስ ‹‹የልጆች አባት ነው ቋሚ አድርጉት ደሞዝ ግን አሁን አይጨመርልህም›› ብለው መልስ ሰጡ ከጥቂት ወራት በኋላ አቶ ግርማ ስራውን ተወው ፡፡ ስራውን በመተው ሱዳን እንደሄደ ለስራ ከባለቤቱ አፍ ሰምቻለው 3 አመት በኋላ ወደ ኢትዮጰያ በመምጣት አባ ግርማ .መባሉን ሰማው ፡፡ ጠቃላይ ይህ ሰው በሱዳን እፅ ወይም መተት እንደሚሰራ ግልፅ እና የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ስለሚታወቅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አንድም ቦታ ላይ ሰርቶም አያውቅም፡፡ አሁን በመላው ኢትዮጵያ እንደተከለከለ አውቃለው፡፡ ይህ ሰው የሚሰራው ስራ ተራ የማታለል እና የውንብድና ስራ ነው አሁን አዲስ አበባ ሌላ ወጣት ሚስትም አግብቶ እንደሚኖር አውቃለው ፤ የመጀመርያ ሚስቱ በአሁን ሰአት ተለያይተው ሰው ቤት እንጀራ በመጋገር ነው የምትተዳደረው ይህንን ማወቅ የፈለገ በአካልም በስልክም ላገናኘው እችላለው ከአስመሳዮች እንጠቀቀ፡፡


መምህር ግርማ አታላይ ነው።"

15 comments:

  1. gena bizu yimetal lenegeru masreja anisham masrejachin enkirdadun kezeru yemileyut enat bekrstian erasua nat

    ReplyDelete
  2. ምእመናን አትደናገጡ አነ ጳውሎስ ሲያስተምሩ ሲያጠምቁ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አልሆነላቸውም ከእኛ የሚጠበቀው ለአባታችን መጸለይ ነው;;በሁሉም ነገር አጋእይዝተ ስላሴ ከእርሳቸው ጋር ይሁኑ!!!

    ReplyDelete
  3. egzaw mharen eyesses crestos!! bent Mary me mharen crestose !!men gowed new ymsamaw sntw saw tatalwe endhe staff ydana meslowt bseta sgaza sytan schawetebat menaw eskahune zm tabale sytanan tafert! ysaznal egezabher hulacnn lnesh mot ybkan endtfan anker aman!!

    ReplyDelete
  4. yemataqutin neger batzebariqu desyilal. lehulum geta le Abatachin yiqumilachew. Yesew were ena haxiyatu ende milasu yirezimal. Get yiqir yibelachihu

    ReplyDelete
  5. አታላይ ብሎ ለመናገር እኮ መረጃ ያስፈልጋል፡፡ ሰውን እኮ ተነስቶ በግምትና ሊሆን ይችላል የሚባሉትን ቃላቶች ተጠቅሞ አታላይ ማለት እንደህግ ያስቀጣል፤ እንደክርስትና ኃጢያት ነው፡፡ የተናገርኩት እውነት ነው ለማለት የተጠቀምካቸው ቃላቶች ማለቴ በስልክ ላገናኛችሁ ምናምን ማለትህ አንተ እራሱ ችግር እንዳለብህ ነው የሚያሳብቅብህ ለምን ካዲያ ስልክ ቁጥርህን አላስቀመጥክም?????? መቼም ክርስትናው ቢገባህ ይህንን አትናገርም፡፡ አትፍረድ ይፈረድብሀል ማቴ 7፣1፡፡ ቢጣራ አንተ ስንቱን አግብተህ ፈተሀል፡፡ እራስህን መርምር፡፡ ስንቱ በአይንህ አስበህ አመንዝርሀል ለምን የወንድምህን ጉድፍ ትመለከታለህ? እግዚአብሔር ስንቱን ኃጢያታችንን ተሸክሞ እሱ ያልከበደው አንተ ምን ቤት ነህ???? ለምን በገባንና ባወቅነው መጠን አንሄድም???? ሱዳን የሄደ ሁሉ መተተኛ ነውን??????????????? እንግዲህ ብዙ ሰው ሱዳን የሄደ አውቃለሁ፤ ለስራ፣ ለብዙ ነገር ይኬዳልና ይህም አያሳምንም፡፡ ሚስት አግብቶ ፈቷል ለሚባለው ሚስት አግብቶ መፍታት በእሷቸው ነው እንዴ የተጀመረው???? ስንቱ የቤተክርስቲያን ካህን አገልጋይ ያውም በቅዱስ ቁርባን አግብተው እንደገና ፈትተው ሌላ ያገቡ ብዙ እኔ በግሌ የማውቀውን ከአንድም 3 ሰው አውቃለሁኝ፡፡ ቤተክርስቲያን ግን ውስጥ ድረስ ገብተው የሚያገለግሉ፡፡ኧረ ቤተክርስቲያናችን ስንቱን ነው የተሸከመችው????????? እኔ ግን ማግባታቸው አይደለም የገረመኝ፡፡ ማጥመቃቸው ትንሽ ቢገርመኝም ግን የቤተክርስቲያኒቷ ከዚህ በላይ ብዙ ወንጀል የሰሩ አባቶችን ስለተሸከመች ይህም አያስደንቅም፡፡ ገበናንን ወደ አደባባይ ከማውጣት በቀር ትርጉም የለውም፡፡ መፍትሄው ጸልዩ በእንተ ቤተክርስቲያን አሀቲ ቅድስት ጉባኤ፡፡ ስለሀጢያታችን እንጸልይ፤ ይህ ሁሉ የሆነው ኃጢያታችን ስለበዛ ነውና ስለራሳችን እንጸልይ፡፡ ፍቅር ይኑረን፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ፍቅር ከቤተክርስቲያን እስከምእመን ስለጠፋ ነው፡፡

    ReplyDelete
  6. ወታደር ነበሩ ምናምን የሚለው ለክርስቲያን ምእመን አይባልም፡፡ ክርስትና መቼ ሆነና ከስጋዊ ማንነት ጋር!!! ሰው ፊትን ያያል እግዚአብሔር ልብን ያያል!!!!!!!!!!! ትልቁ ነገር ከውስጥህ ማንነት ጋር ነው ምስጢሩ!!!!!!!!!! ይህንን ስል አሁንም እሷቸው ንጹህ ናቸው እያልኩኝ አይደለም፡፡ አናውቅም፡፡ እያላችሁ ያለውን ነገር አያሳምንም፡፡ አንድን ሰው አታላይ ለማለት የሚያስደፍር አይደለም፡፡ ተጨባጭ ነገር ሳንይዝ ኃጢያት በነገሰችበት አለም፣ ሀሰት ተቀባይነት ባገኘበት አለም ውስጥ ሆነን ይህንን ማለት አይገባም፡፡ ፍርዱን ለምን ዝም ብለን አንመለከትም?????????????? እኛው ከሳሽ፣ እኛው ተከሳሽ፣ እኛው ፈራጅ!!! እግዚአብሔር የቱ ጋር ገብቶ ይስራ??? እንደዚህ ዓይነቱን ክስ የተማርነው ከየት ይሁን????? ይህ የሚያሳየው ተኩላው ምን ያህል ውስጣችን ገብቶ እየሰራ እንደሆነ ነው የሚያሳየው!!! ባህሪያችን ሁሉ፣ ንግግራችን ሁሉ ከተኩላው የወረስነው እኮ ነው???? እስኪ የምንናገረውን እንመርምር???? ከማን እንደወረስነው ያሳብቅብናል???? መናፍቃንን እንመልከት በቃ ይህ አነጋገር መገለጫቸውን መለያቸው ነው፡፡ እኛም እንደዚህ እኮ ነው እየሆንን ያለነው???? ከክርስቶስ ይህንን ነው እንዴ የተማርነው????? እንደዚህ ወገባችንን ታጥቀን የምንከራከርላቸው ቅዱሳን አባቶቻችንን እስኪ እንመልከታቸው ገድሎቻቸው ገደል ለምን ይሆንብናል???? ዕብ 13፣7 እስኪ እናንብብ፡፡ ማስተዋል ይስጠን፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. አይናቸው የበራውንስ ምን እንበላቸው? እያጭበረበሩ ነው እንጂ አይናቸው አልበራም? ቆመው የሄዱትም እያጭበረበሩ ነው እንጂ ሸባነታቸው አልተፈወሰም? የቆረቡትም እያጭበረበሩ ነው እንጂ ቅዱስ ቁርባን አልተቀበሉም? ወጣቱንስ - እያጭበረበረ ነው እንጂ ጫትና ሲጃራውን አልተወም? ጠንቋዩንስ - እያጭበረበረ ነው እንጂ ንስሐ አልገባም? …እያጭበረበሩ ነው እንጂ ሕይወታቸው አልተቀየረም??? አልገባኝም! ዘበኛም ወታደርም ሆነው ከነበረ ምንድነው ኃጥያቱ? ማለት ጌታችን "ያቺን ውርንጭላ ፈታችሁ አምጡልኝ" ማለቱ ምንም አላስተማረዎትም ማለት ነው ክቡር "Ex-ዳኛ"? እግዚአብሔር እኮ እንደእርስዎ "ዳኛ" ከነበሩት ይልቅ በተናቁት ላይ ክብሩን መግለጽ ይወዳል! ሰው ሱዳን ሄዶ ከነበረ በቃ ዕጽ ለመጠቀሙ ለእርስዎ 'ማስረጃ' (admissible evidence in court of law) ነውን? እውነት ዳኛ ከነበሩ ይህንን ጭንቅላት ይዘው ነበር ሲፈርዱ የኖሩት? ፈራሁ!

      Delete
  7. ዘውዱ ታደሰ ስልክህን ገልጸህ ጻፍልን፤ እወነት አንተ ጋር ናት ማለት ግን አይደለም፤ መቼስ ዳኛ ነበርኩ ካልከን አሁን አንተ ያልከንን በሙሉ እንደወረደ እንደማንቀበለው በሚገባ ትረዳዋለህ። ስልክህን እንጠብቃለን።

    ReplyDelete
  8. You are liers, no one believes you! We need to be strong enough to believe in the work of God. The more you strugle & serve God the more the hurdles will be. So, let us pray for kes Girma. The one who believes in him will always be the winner.

    ReplyDelete
  9. አይናቸው የበራውንስ ምን እንበላቸው? እያጭበረበሩ ነው እንጂ አይናቸው አልበራም? ቆመው የሄዱትም እያጭበረበሩ ነው እንጂ ሸባነታቸው አልተፈወሰም? የቆረቡትም እያጭበረበሩ ነው እንጂ ቅዱስ ቁርባን አልተቀበሉም? ወጣቱንስ - እያጭበረበረ ነው እንጂ ጫትና ሲጃራውን አልተወም? ጠንቋዩንስ - እያጭበረበረ ነው እንጂ ንስሐ አልገባም? …እያጭበረበሩ ነው እንጂ ሕይወታቸው አልተቀየረም??? አልገባኝም! ዘበኛም ወታደርም ሆነው ከነበረ ምንድነው ኃጥያቱ? ማለት ጌታችን "ያቺን ውርንጭላ ፈታችሁ አምጡልኝ" ማለቱ ምንም አላስተማረዎትም ማለት ነው ክቡር "Ex-ዳኛ"? እግዚአብሔር እኮ እንደእርስዎ "ዳኛ" ከነበሩት ይልቅ በተናቁት ላይ ክብሩን መግለጽ ይወዳል! ሰው ሱዳን ሄዶ ከነበረ በቃ ዕጽ ለመጠቀሙ ለእርስዎ 'ማስረጃ' (admissible evidence in court of law) ነውን? እውነት ዳኛ ከነበሩ ይህንን ጭንቅላት ይዘው ነበር ሲፈርዱ የኖሩት? ፈራሁ!

    ReplyDelete
  10. tadai eskahun yetnebu? zare new ende menager ? aba girma 20 amet belay honachew eko. ene adinakiachew aydelehum gin andande be agatmiwoch bicha baninager melkam new. ewunet be agatami aydelem yemitnegerew!! Amlak hulachininim yirdan!!

    ReplyDelete
  11. enkanim wetader honu.....wetader ye_egzabher kal or egzabher besu lay te_amir ayseram yale manew .....weys egzabher be_akalu mayet felek....doma neger nek yetameme sifewes be_aynea bebretu ...yetawere siyay eyayehu.......yefelege masreja bitakerbim ...Ke_aynea yemaminew manim yelem....

    ReplyDelete
  12. Antes maneh? ye lelawun indih yale yelelewun yemitizekezikew. yih new andi madireg?E/r yasibih.

    ReplyDelete
  13. SEW SEWN AYFERDM MANEW KEHATIYAT NETSA BEZICH MDR HULACHNM HATIATEGNOCH NEN SLEZIH KERASH AYN YALEWUN GND SATAWETA YELELAWN TAYALEH EGZABHER AMLAK HULACHNM YRDAN.

    ReplyDelete
  14. አባታችንኮ ከቤተመንግስት ተወለድኩ፣ ጳጳስ ነበርኩ አላሉም የነበበሩበትን ሁሉ ነግረውናል ይታወቃል ምን አዲስ ነገር አለው ታዲያ ጸጋ በሹመት ነው; የጌታ ስጦታ ነው ከሰማይ!!!!! የሚገርመው እነዚህ ሱዳን ያሉ ታምር የሚያስተምሩ ሱዳኖች እንዴት ጎበዞች ናቸው የእግዚያቤሄርን ጥበብ የሚያሸንፍ የጥንቆላ ጥበብ ማስተማራቸው እንዴት እነሱ በአለም ላይ ታዋቂ ሳይሆኑ ቀሩ የሚገርመኝ ቅናታችን ጭንቅላታችን ሲያስተን ሳይታወቀን ለአስማትና ለመተት የእግዚያበሄርን ሀይል ማሳነሳችን ይገርመኛል ለዚያውም ከኦርቶድክስ ተዋህዶ አማኞች መናፍቁስ ተበለጥኩ ብሎ ነው አንተ ግን ምን እየሆንክ ነው ዳኛ ምናምን ነበርኩ ቀፎራስ አንተ የፍርድ ሸንጎ ዳኛ ነህ እድሜህም ለዚያ አይደርስም ምክንያቱም ንግግርህ የበሰለ አይደለም አልተሳካልህም እንደገና ሌላ ወሬ ቀምም!!! እግዚያበሄር አባታችንን በጤና ጠብቅልን!!!!

    ReplyDelete