Saturday, June 14, 2014

‹‹አንድ ሚሊዮን ወጣትም ቢሆን የፈለገበት ይድረስ ፤ ምንጣፍ አነጠፈም አላነጠፈም የፈለገበት ይድረስ›› የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ


  •  " ገመድ የምትበላ ብትሄድ ጠፍር የምትበላ ትመጣለችሀገርኛ ብሂል

(ፋክት ቅዳሜ ግንቦት 7 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ወጣቶች ማኅበራት ሕብረት ፍቃድ መሰረዙ ተሰማ፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ግንቦት 8 ቀን 2006 ዓ.ም ለሕብረቱ በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸው ፤ ሕብረቱ ከሕገ-ቤተክርስቲያን እና ከቃለ አዋዲው ሕግጋት ፍቃድ መሰረዙን ገልጿል፡፡

86 ማኅበራትን ያቀፈው እና ከ200ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ወጣቶችን እንደያዘ የሚነገረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  መንፈሳዊ ወጣቶች ማኅበር ሰብሳቢ ወ/ሪት ፌቨን ዘሪሁን ለዝግጅት ክፍላችን ‹‹የማኅበራቱ ሕብረት ፍቃድ እንዲያገኝ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲሰጥ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጠየቅነው መሰረት  ያገኝነው ፍቃድ ፤ ቋሚ ሲኖዶስ ሀገረ ስብከቱን ፍቃዱን እንዲሰርዝ ሲያዝ ፤ ሕብረቱ ስለጉዳዩ ሳያውቅና ሳይጠየቅ ፤ ሕብረቱም ለምን እንደታገደ ሳናውቅ ነው ደብዳቤ የደረሰን›› ስትል ጉዳዩን ገልጻለች፡፡

ሀገረ ስብከቱ ፍቃዱን የሰረዘው ሕብረቱ ‹‹ከሕገ ቤተ ክርስቲያን እና ከቃለ ዓዋዲው ሕግጋት ውጪ›› እንደሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ በማዘዙ እንደሆነ ገልጿል፡፡ ‹‹ቃለ ዓዋዲው መሻሻል ይችላል›› የምትለው ሰብሳቢዋ በብጹዕ አቡነ ጳውሎስ ጊዜ ቃለ ዓዋዲው ይሻሻላል ተብሎ እንደነበር ገልጻለች፡፡ሕብረቱ  ፍቃዱ እንዲመለስለትና እያከናወነ ያለውን መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲቀጥል በተደጋጋሚ ፓትርያርኩን ለማግኝትና ጉዳያችን እንዲታይ ለማድረግ ያደረግነው ጥረት ሊሳካ አልቻለም ብላለች፡፡

በተደጋጋሚ ጊዜ ተመላልሰን  ያገኝናቸው የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማትያስም ‹‹አንድ ሚሊየን ወጣትም ቢሆን የፈለገበት ይድረስ ፤ ምንጣፍ አነጠፈም አላነጠፈም የፈለገበት ይድረስ›› ብለውናል የምትለው ወ/ሪት ፌቨን ‹‹በየአካባቢው የተደራጁ ማኅበራት እውቅና ካላገኙ ለቤተክርስቲያኒቱ ጉዳት ›› እንደሆኑ ገልጻ ‹‹ቤተ ክርስቲያን መጥቶ እውቅና ያላገኝው ወጣትን ለመቆጣጠር እና ለመምራት አዳጋች ይሆናል›› ስትል የሁኔታውን አሳሳቢነት ትገልጻለች፡፡

ከ6ተኛው ፓትርያርክ ጋር መጪ  ዘመናችንን ለመተንበይ ነብይ መሆንን አይጠይቅም ፤ የሀገሬ ሰው “ገመድ የምትበላ ብትሄድ ጠፍር የምትበላ ትመጣለች” ይላል፡፡

6 comments:

  1. “ገመድ የምትበላ ብትሄድ ጠፍር የምትበላ ትመጣለች” ጌታ የሰቀሉ አሁዶች በናተ መበለጣቸውን ቢሰሙ ምን ይሉ የሆን????

    ReplyDelete
  2. betam yasazianal........lemanignawum lebetekirstiyan ......ageligilot enitiga.

    ReplyDelete
  3. ከ6ተኛው ፓትርያርክ ጋር መጪ ዘመናችንን ለመተንበይ ነብይ መሆንን አይጠይቅም ፤ የሀገሬ ሰው “ገመድ የምትበላ ብትሄድ ጠፍር የምትበላ ትመጣለች” ይላል፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. Esachewim egnam altadelnim. Yetadelut (legizewim bihon) telatochachin nachew!!!! Maren Maren Maren !!!!!!

      Delete
  4. ይህን ባዩ ራሱ የፈለገበት መድረስ ይችላል ቤተ ክርስቲያን የሁሉ ናት ለነሱ ብቻ ማን ሰጣቸው

    ReplyDelete