Wednesday, June 4, 2014

መንግሥት በዋልድባ ገዳም በመሥራት ላይ ያለውን የሥኳር ፕሮጀክት 12 በመቶ ማጠናቀቁን ገለጸ


(አንድ አድርገን ግንቦት 28 2006 ዓ.ም)፡- ከወር በፊት መንግሥት በዋልድባ ገዳም በመሰራት ላይ ላለው የሥኳር ፕሮጀክር  ቻይና መንግሥት ሥራውን ማጠናቀቂያ የገንዘብ ብድር ማግኝቱ ይታወቃል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ የኢቲቪ የምሽት ዜና ላይ የሥኳር ፕሮጀክቱ 12 ከመቶኛ መጠናቀቁን ተገልጿል፡፡ ከወር በፊት ቦታው ላይ በአካል ደርሰው ከመጡ ምዕመናኖች እንደተረዳነው ከሆነ በገዳሙ የሚገኙ መናንያን ጋር በመቅረብ መረጃ ማግኝት አስቸጋሪ ቢሆንም መነኮሳቱ የዘወትር የሥራ መርሃ ግብር በተጨማሪ  በጾምና በጸሎት መጠመዳቸውን ገዳሙ ድረስ ደርሰው ከመጡ ሰዎች ለመረዳት ችለናል፡፡ በቦታው ከሄዱ ሰዎች አንዱ አንድን አባት ስለ ሁኔታው ለመጠየቅ ሞክሮ ‹‹ጸልዩ›› ተብለናል ስለዚህ ‹‹ሁሉንም ነገር በሂደት የምናየው ነገር ይሆናል እኛ እየጸለይን ነው፡፡›› በማለት መልስ ሰጥተውታል፡፡


ይህ ጉዳይ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከማለፋቸው በፊት በመጨረሻው የሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ምልአተ ጉባኤው ያልመከረባቸውንና ውሳኔ ያላሳለፈባቸውን አንገብጋቢ አጀንዳዎች አቋም እንደተያዘባቸው አስመስሎ በማቅረብ በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሳቢያ በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ የተነሣውን ስጋት ምልአተ ጉባኤው በአጀንዳ ይዞ መነጋገር ሲገባው  ሳይነጋገርበት መለፉ የሚታወቅ ነገር ነው፡፡ ይኹንና በጊዜው ተረቅቆ በቀረበው መግለጫ ላይ ፕሮጀክቱን የሚቃወሙት የፖለቲካ ዓላማ ያላቸው ኀይሎች እንደኾኑና ቤተ ክርስቲያን ግን ልማቱን እንደምትደግፍ የሚናገር አንቀጽ እንደነበረው ይታወሳል፡፡

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከማረፋቸው በፊት የመንግሥታቸውን የ9 ወር ሪፖርት በሚያቀርቡበት በመጨረሻ የፓርላማ ቆይታቸው በዋልድባ ገዳም በሚሠራው የሥኳር ፕሮጀክት በሚመለከት  ከተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ወደ መንግሥት ተጠሪ ቢሮ ወ/ሮ ሮማን ገ/ሥላሴ(ሚኒስትር ፤  የመንግሥት ዋና ተጠሪ) የተላከ ቢሆንም በእርሳቸው በኩል ለክቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢደርስም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚያዚያ 9 ቀን 2005 ዓ.ም በመጨረሻ የፓርላማ ቆይታቸው መልስ ይሰጡበታል ተብሎ የተጠበቀው ጉዳይ መልስ ሳይሰጡበት አልፈዋል፡፡

በህይወት የተለዩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ እና  5ተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጉዳዩ ላይ በወቅቱ በሚዲያ ላይ የተናገሩት ነገር አልነበረም፡፡ አሁንም ቢሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝም ይሁኑ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በጉዳዩ ላይ የተናገሩት ነገር የለም፡፡


3 comments:

  1. የሁለቱንም መጨረሻ ወደፊት እግዚአብሔር ያሳየናል፡፡ እነሱ ዝም ቢሉም እግዚአብሔር ግን ይናገራል፤ ይፈርዳልም፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. Ewnetegha ferage eyesuse kirstise. Medaferachewene yemelkete. Firdune yesete

      Delete
  2. እግዚአብሔር ቀን አለው ። ልብ ያለው ልብ ይበል ።

    ReplyDelete