Monday, June 2, 2014

የጎመጀው ፤ የደነዘዘው እና የደነቆረው ሕዝብ……

ኃይለጊዮርጊስ ማሞ
(የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል መምህር)

(አንድ አድርገን ግንቦት 25 2006 ዓ.ም)፡- ሰሞኑን የከተማችን ወሬ ሆኖ የከረመው አንድ አስገራሚ(እንደዚህ ጸሐፊ እምነት አሳፋሪ) ክስተት ነበር፡፡ ክስተቱ አንድ ዜግነቱ የማላዊ የሆነ “ነብይ” ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ ጋር በተያያዘ በሚሊኒየምና እንዲሁም በነጋታው ‹‹መድህን ዲኮር›› በተባለ አዳራሽ የታየ “ሕዝባዊ ውርደት” ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ አይነት ክስተቶችን ልብ ብሎ ለተመለከተ ሃገሪቱ ጠባቂ የሌላትና ማንም እንደፈለገ እየገባና እየወጣ የሚፈነጭባት ‹‹መሰማሪያ›› ትመስለዋች፡፡ በተለይም ደግሞ የሕዝብ ድህነት ፤ መጎምዥት ፤ መንፋሰዊ ክስረትና ውድቀትን ተገን አድርጎ በየስፍራው የሚነሳው “ሃገር በቀል ቦጥቧጭ” አልበቃ ብሎ ‹‹አለም አቀፉን›› ደግሞ እየጋበዙ  በማምጣት እንዲህ ሕዝብን መጫወቻ ማድረግን ስንሰማ ከዚህ በላይ ሕዝብ የራሱን ክብር ከጭቃ የሚጥልበት ትንሽነት ከወዴት ሊመጣ ይችላል? በማለት ለመጠየቅ እንገደዳለን፡፡

በአንድ ወቅት ‹‹ፓስተርና ፖስተር›› ሲባልበት የነበረው ከተማ ዛሬ “ወደ ነቢያት ጉባኤ” ተቀይሮ ሁሉ በየፊናው  የነብይነት ካባን በየአደባባዩ እየተጎናጸፈ የሕዝቡን መጎምዥትና  ጭንቀት ተገን አድርጎ መቆምን አስተማማኝ የትርፍ መስክ ሲያደርገው “ኧረ ሃይ ባይ የለም ወይ?” የሚያስብል ሆኗል፡፡ እርግጥ ነው ትውልድና ዘመን ብዙ ዓይት መልክ ያለው ክስረት  ውስጥ ለመግባቱ በድፍረት ብቻ ሳይሆን በተሰበረ ልብ እንናገራለን፡፡ ዛሬ የመንፈሳዊነት አገልግሎት በኢትዮጵያ ከሰማዩ ይልቅ የምድራዊውን ሕይወት ጥያቄ ምላሽ በመስጠት የተያዘ የትርፍ መስክ ያደረገውም ይኽው ክስረታችን ነው፡፡ ደርግ የሃይማኖት ነጻነትን ነፍጎ ሕዝቡን ኮሚኒስት (ኢ-አማኒ) ለማድረግ ሲታትር በዚያ ዘመመንና ትውልድ በመንፈሳዊነት ጸንተው ዋጋ የከፈሉ በርካቶች ነበሩ፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ መጣና “የሃይማኖት ነጻነት”  በማለት ሲያውጅ “ዋጋ የተከፈለበት” መንፈሳዊነት “ዋጋ የሚያስከፍሉበት” ሆኖ ቀረ፡፡ በመሆኑም ለዚህ አይነቱ በሀገር ላይ ለመጣ መንፈሣዊ ብቻ ሳይሆን  የማንነት ውድቀት ተጠያቂው ማነው? ወዴትስ እየሄድን ይሆን ?


ከዓመት በፊት በ “ቢቢሲ” የቴሌቪዥን ጣበያ የተሰራጨ አንድ አስገራሚ ሪፖርት አስታውሳለሁ፡፡ ሪፖርቱ በአውሮፓ ሀገር አንዳንድ ሀገራት ውስጥ  የሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት በሰባኪ እጥረት መቸገራቸውንና ምዕመናንም እንዲሁ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ በማቆማቸው  ባዷቸውን እንደቀሩ የሚያሳይ ነበር፡፡ ታዲያ በዚሁ ሰባኪ መጥፋት ምክንያት እነዚሁ ባዷቸውን የቀሩ ምዕመናን ከመካከላቸው እየተመራረጡ መጽሐፍ ቅዱስ በመስበክ ሰንበትን እንሚያሳልፉም ጋዜጠኛው አክሎ አቀረበልን፡፡ በዚህ ሪፖርት ላይ አስገራሚው ክስተት የሰባኪ መጥፋት ወይም የምዕመናን ቁጥር መመናመን ብቻ አልነበረም ፤ ነገር ግን ቀሩትም ምዕመናንም ቢሆኑ በዕድሜ እጅግ የሸመገሉ የመሆናቸው ነገር ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ መንፈሳዊ ክስረት በዚች ሀገር ወደፊት አለመድረሱን እርግጠኛ ሆኖ ማስተማመኛ መያዝ አይቻልም፡፡ ይልቁንም ዛሬ የተያዘው መንፈሳዊ መሳይ ‹‹ሸቀጣ›› ነገ ሕዝቡ እጁን ለዘመናት ከዘረጋበት አምላክ ወደ ራሱ መሻትና ፍላጎት በመቀሰር የእርስ በእርስ መተሳሰቡና መከባበሩ እንደ ጉም እንዳያበነው ስጋት ገብቶናል፡፡ መጽሐፉ ‹‹ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች››ይላል የሰሞኑን ውጥንቅጥ ከዳር ቆሞ ለታዘበ ደግሞ እጆቹን ወደ አምላኩ ሳይሆን ወደ ገንዘብ የዘረጋው ትውልድን መመልከት ፤ ከስጠኝና ባርከኝ ጋር የተቆራኝ ‹‹የመጎምዥት ልክፍት›› በትውልዱ ላይ ማየት በጣም ያሳዝናል፡፡ 

ሰውየው ዜግነቱ ማላዊ ሲሆን መጠሪያው ደግሞ ነቢይ “ሼፐርድ ቡሽሪ” ይባላል፡፡ God Channel የተባለውና የተለያዩ ፕሮግራሞች የሚተላለፍበት  የእሱ የቴሌቪዥን ፕሮግራም Prophetic Channel በሚል መጠሪያ ይተላለፋል፡፡ ‹‹ነብዩ›› በዙሪያው የሚሰበሰቡትን ሰዎች ያለፈ የሕይወት ታሪክ ፤ በመስሪያ ቤታቸው ወይም በመኖሪያ ቤታቸው የሚገኙ ወይም የሚያጋጥሟቸውን የግል ጉዳዮችና ሚስጢሮች ፤ በተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸውን በኢሜል የተላላኳቸው መልዕክቶች ፤ የፍቅረኞቻቸውን ስምና አድራሻ ፤ ..ወዘተ እየተናገረ መደነቅ መገረምን እንዲሁም ድንጋጤን  የሚፈጥር “መገለጥ” የሚከናወንበት ፕሮግራሞችን ያስተላልፋል፡፡ በዙሪያው የተሰበሰቡ ሰዎች የግል ሚስጢራቸው የተነገራቸው  ተከታዮች  ደግሞ ስለ ወደፊቱ የሚነገራቸውን  ያለአንዳች  መጠራጠር ቢቀበሉ የሚደንቅ አይሆንም፡፡

እዚህ ላይ ከእንደዚ አይነቶቹ የ‹‹ነቢይ›› ቡሽሪ የመገለጥ ቀናት በአንዱ ምሽት ለአንዲት ሴት ሲነግራት የሰማሁትን ከቶ ልረሳው አልቻልኩም፡፡ አስቀድሜ ለማስፈር እንደሞከርኩት ይኽ ‹‹ነብይ›› የሰዎችን የግል ጉዳይ አደባባይ ማውጣት የሚታወቅበት ጥበቡ ነው፡፡ አንዲህ አይነቱን የጠንቋይ አይነት ማስተማመኛ በቅድሚያ ጉባኤውን ካስያዘ በኋላ ወደ ቀጣዩ ‹‹ትንቢቱ›› ይዘልቃል እንጂ ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ሰፍረው እንደምናገኛቸውና የአምላካቸውን ድምጽ ሰምተው ይህንኑ መልሰው እንደሚያስተጋቡት ነቢያት አይነት የትንቢት ወግ አናይበትም፡፡ ታዲያ በዚህ ምሽት “ነብዩ” ቡሽሪ በአዳራሽ ውስጥ እየተንጎማለለ እንደተለመደው የአንዱን የፍቅረኛውን ስም ፤ የሌላኛውን የመኖሪያ አድራሻ  ፤ እንዲሁም የሌላኛውን የተወለደበትን ቀንና ወር እየተናገረ ጉባኤውን ‹‹በመደነቅና በአድናቆት›› ሲያጅበው ቆይቶ አንዲት ከፊት ለፊቱ የቆመችን ሴት ወደ እርሱ እንድትመጣ ይጠራታል፡፡

ሴቷ ፍርሃት ይሁን አክብሮት በውል ባለየለት ስሜት እየተንቀጠቀጠች ከፊቱ ትቆታማለች፡፡ ለጥቂት ሰከንዶች አትኩሮ ካየ በኋላ  “ኤድዋርድ የሚባል ከአንቺ እድሜ የሚያንስ ጓደኛ አለሽ” አላት፡፡
ሴትየዋም በድንጋጤ መጮህ ትጀምራለች፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹ነብዩ›› እንደተለመደው መተንበይ እችላለሁ ! (Can I prophesai !) በማለት ሲጮህ ከኋላ በጩኽት ዘወትር የሚያጅበው ደግሞ ተንብይ ! ተንብይ! አለው፡፡
በዚህ ጊዜ ታዲያ የሴትዮዋን ያህል ድንጋጤም ባይሆን መገረም የፈጠረብኝ ነገር ‹‹ነቢዩ›› ሲናገር የሰማሁት፡፡
“…ነገር ግን ደግሞ አንዲ ኢትዮጵዊ ከፍተኛ የፖለቲካ ባለስልጣን በከባድ ሚስጢር ፍቅረኛሽ አድርገሽ ይዘሻል!” አላት
ሴትየዋ በድንጋጤ ፈዝዛ ተረታችና እያለቀሰች “እውነት ነው!” አለችው፡፡
“መተንበይ እችላለሁ! ….. “ተንብይ ! ተንብይ!” በዚህ ፕሮግራም ላይ ‹‹ነብዩ››  ቡሽሪ ስለ ኢትዮጵያዊው ባለስልጣን ማንነት የተናገረው ተጨማሪ ጉዳይ አልነበረም፡፡ ስለ ሴትየዋ የወደፊት እጣ ክፍል ሲተነብይም አልሰማሁም፡፡  ይልቁንም ከፊቱ ቆመው በተመሳሳይ መንገድ የግል ጉዳያቸውና ምስጢራቸው ሲነገራቸው ለመስማት ወደጓጉት አመራ፡፡ ‹‹ነብዩ›› ቡሽሪ የዚያን ቀን የባለስልጣኑን ስም ተናሮ ቢሆን ኖሮ  ምናልባት ወደ ኢትዮጵያ መግቢያ ቪዛ ባለገኝም ነበር ስል አሰብሁ፡፡

እንግዲህ ይህ ሰውዬ በመንፈሳዊ ቻናል እንዲህ የግለሰቦችን ምስጥር ሲገልጥ የሚያውቁት ብቻ ሳይሆኑ ዝናው ተጨማምሮ የተነገራቸው ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ የመምጣቱ ዜና በየመንገዱ ላይ ከተሰቀለው ማስታወቂያ ሲመለከቱ መጓጓታቸውና መጠበቃቸው ብዙም የሚያስደንቅ ላይሆን ይችላል፡፡ በሥፍራው ታድመው ከነበሩ ሰዎች እንደሰማሁት ሰውየው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሰባኪ ሆኖ ሳለ ከብዙ አይነት እምነት  የተውጣጣ የሕዝብ ትርምስ የመታየቱ ምስጢር ግን ሁሉንም የሚያገናኝ የአንድ የጋራ አላማ የያዘ አጀንዳ በ”ነብዩ” እና በጋባዦች ዘንድ መታየቱ ነበር፡፡ ይህ አላማ ደግሞ “ገንዘብ” ነው፡፡ ሰውየው “ነብይ” የነብይነት ዘመኑ ትርጉም ደግሞ ሰዎችን ባለጸጋ ማድረግ ፡፡ እናም ሕዝቡ የቱንም ያህል ውርደት ቢገጥመው ችሎ ‹ነብዩ› እጁን እንዲጭንበትና እንዲባርከው በሌሊት እንቅልፉን በመሰዋት ከአዳራሹ ደጃፍ ተኮልኩሉ ወደ ውስጥ ለመዝለቅ ተጋድሎውን ጀመረ ፡፡ “የጎመዥ ፤  ደነዘዘ  ሕዝብ”…

ብር ፤ ወርቅ ፤ዳይመንድ
አንድ ቀን ወደ ሀብት ማማ ላይ ለመፈናጠጥ እና ህይወቱ በቅጽበት እንዲቀየርለት የጎመዥው እና የደነዘዘው ሕዝብ ‹‹ነብይ› ተብዬውን ከማላዊ የመጣውን ሰው በጉጉት ሲጠብቅ ነበር፡፡ ይህን የጎመዥ ህዝብ የተመለከቱና ‹‹ነብዩ››ን ወደዚች ሀገር ‹‹እንግዳ ተቀባይ›› እያሉ ‹‹እዳ ተቀባይ›› ወደ መሆን ወዳደረሷት ሀገር የጋበዙትም ሆኑ የተቀበሉት አስተናጋጆች ይህን የትርፍ አጋጣሚ በቀላሉ ሊያልፉት አልፈለጉም በዘመኑ ቋንቋ ቢዝነስ ሆነላቸው፡፡ ኢየሱስ በምኩራብ “ገንዘብ ለዋጮችን”ን እና “ርግብ ሻጮችን” በተመለከተ ጊዜ ይካሄድ የነበረውን ዓይነት ትዕይንት የሚያስታውስ ድራማም በቦታው ተተካ፡፡ ስፍራው በደቂቃዎች ውስጥ ባዛር መሰለ፡፡
  ‹‹ጸሎቱን የምትፈልጉ በስክሪኑ ላይ በምትመለከቱት አድራሻ ገንዘብ ላኩ” ፤ “ለብልጽግና የሚሆን ዘይት የምትፈልጉ ብልቃጦቹ በአድራሻዎቻችሁ እንዲደርሳችሁ በቅድሚያ ገንዘብ በመላክ መግዛት ትችላላችሁ›› ‹‹መሻታችሁ ትዳር ፤ ጤንነት ፤ የአሜሪካ ቪዛ .. ወዘተ ከሆነም የተጸለየበት ውሃ አለ ፤ ከፍላችሁ በአድራሻችሁ ይደርሳችኋል ›› እያለ እና እያስባለ ሲያስተዋውቅና ሲቸበችብ ከርሞ ‹‹ነብይ›› ተብየው ሰው እንደ ቀድሞዎቹ የጥፋት ሃይሎች(ቦንኬ…..) በወሩ ወደ ኢትዮጵያ መጣ፡፡

ቡሽሪ በኢትዮጵያ ከደረሰ በኋላ የሕዝቡን መጎምዥት ያስተዋሉት የሀገር ውስጥ ሸሪኮችና የእሱ አጃቢዎች ስፍራውን ባዛር ለማስመሰል ቅጽበት አልፈጀባቸውም፡፡ የተለያየ ሰው ሞልቶ ተትረፍርፏል፡፡  የፈጣሪን ሃሳብ ለምድሪቱና ለሕዝቡ ይዞ እንደመጣ የተነገረለት ‹‹ነብይ›› አጃቢዎቹ ውሃ ፤ ዘይት ፤ ሳሙና ስቲከር ፤ እራፊ ጨርቅ ፤ የእጅ ሪቫን ደርድረው መሸጥ ጀመሩ፡፡ ውሃው (ነብዬ የጸለየበት የተባለ) 500 ብር ፤ የተጸለየበት ዘይት ብልቃጥ 200 ብር ፤ እራፊ ጨርቁን 200 ብር ፤ የእጅ ሪቫን 100 ብር ስቲከሩ 10 ብር ወዘተ ኪሳራ የሌለበት ፤ ታክስ የማይከፈልበት ፤ በዕዳ የማይጨነቁበት መንፈሳዊ መሳይ ንግድ!

በሚሊኒየን አዳራሽ በር ላይ ንግድ እንደጦፈ የተመለከተው ‹‹ነብይ››  ቡሽሪ በአዳራሹ ውስጥ አስፈላጊውን ተጋድሎ ፈጽሞ የገባውን  ሕዝብ ‹‹ልዩ የተጸለየበት ውሃ›› እንዳለው በመንገር ለክፍያ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አስታወቀ፡፡ ‹‹ነብዩ››  ይህን ውሃ ለ20 ሰዎች ብቻ እንደሚሰጥና እነዚህም 2ሺህ የአሜሪካ ዶላር መክፈል የሚችሉ መሆን እንዳለባቸው ተናገረ፡፡ 2000 የአሜሪካ ዶላር ! በዚያች ብልቃጥ ውስጥ የሚገኝ ውሃ ምስጢሩ ምን እንደሆነ ማን ያውቃል? ብሎ የጠረጠረውና ሲጎመዥ ከከረመው ህዝብ  መካከል በርካቶች  ተንጋግተው ወጡ፡፡ አድራሻቸውን አስመዝግበው በነጋታው የተባለውን ዶላር ሲያመጡ ውሃው እንደሚሰጣቸው ተነገራቸው፡፡ ፍላጎት እያላቸው በአቅም ማነስ  ውሃውን መግዛት ላልቻሉ ደግሞ‹‹ነብዩ›› የተለየ አስተያየት ማድረግ ጀመረ፡፡  በቅድሚያ አንድ ሺህ ዶላር የሚከፍሉትን ጠርቶ ስምና አድራሻቸውን አስመዘገበ ፤ በመቀጠል 500 ዶላር የሚከፍሉትን ጠራ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ የጎመዥውንና የደነዘዘውን ሕዝብ የብልቃጡን ውሃ በዶላ የሚገዛበትን  ዋጋ አስመዝግቦ ከጨረሰ በኋላ  ደሀውና ምስኪኑ አፍጥጦ ቀረ…..

“ላለው ይጨመርለታል” የሚለው ቃል የተፈጸመ ያህል ቆጥሮ እንኳን ዶላር ፤ ብሩን በወጉ ያልያዘው ተስፈኛ ወደ ነብዩ አይኑን ሲያቁለጨልጭ “ነብዩ” በነጻ እንደሚሰጥ ነግሮት ደስታውን መለሰለት፡፡ ነገር ግን ስብሰባው አልቆ የብልቃጡን ውሃ ለማግኝት ከአዳራሹ ሲወጣ የተራወጠው ሕዝብ ተሰልፎ ሲጠባበቅ “ነብዩ” ‹‹አትስጡ ብሎ አዟል››  የሚል ሌላ ምላሽ ተሰጠውና ባዶ እጁን ተሸኝ፡፡ ከዚያ በኋለላ መሸወዱ የገባው ተስፈኛ ፤ የደነዘዘው ፤ የጎመዥው እና የደነቆረው የሀገሬ ሰው ጸያፍ ስድቡን ሌላው እርግማኑን በአጋፋሪዎቹ ላይ እያወረደ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡

“ነብዩ” ቡሽሪ በነጋታው ከሀገር ውስጦቹ ጋባዦች ጋር በሌላ ድራማ ተዘጋጀ፡፡ ወይም አዘጋጁት፡፡ የዚህ ድራማ ተካፋይ ለመሆን እጁ ተጭኖበት እንዲጸለይለት ሕዝበ አዳም 500 ብር የመግቢያ ቲኬት በመግዛት ራሱን አዘጋጀ፡፡ ይህ ፕሮግራም ለየት የሚያደርገው በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩትን ሰዎች ሁላ መጋበዝ መቻሉ ለተመለከተ ዞሮ ዞሮ የመጨረሻ አላማና ግቡን ለመረዳት ቀላል ያደርገዋል፡፡  በአቋራጭ በነብዩ ቃል ሚሊየነር ለመሆን የተዘጋዙ የጎመዡ ሰዎች ጥርቅም፡፡  ከዚህ ፕሮግራም ቀደም ብሎ 2ሺህ እና ከዘያ በታች የሆነ ዶላር እየከፈሉ ነብዩ ጸልዮበታል የተባለን ውሃ እና ዘይት ለመውሰድ የተመዘገቡት ዶላራቸውን እየመዥረጡ ከፍለው እጅ እየተጫነ ተጸለየላቸው ፤ ዘይታቸውንም ሊቀቡ ወሰዱ ፤ ውሃውንም እንደዚያው….

የነጋታው የነጋዴዎቹ ስልጠና ተብሎ 500 ብር እየከፈለ የነብዩን ቅባት ለመካፈል የተዘጋጀው ሕዝብ ወደ ሸራተን ሲያመራ  ቦታው ወደ መድህን ዲኮር ተይሯል ተባለና ሕዝቡ ተስፋ ሳይቆርጥ ወደ ቦታው አመራ፡፡በዚያ ከማለዳ ጀምሮ ሲጠብቀው የነበረው ቡሽሪ  ከቀኑ 5 ሰዓት አልፎ በቦታው ይደርሳል፡፡ ለጥቂት ደቂቃዎች ስለ ግል ሀብቱና አሁን ስለደረሰበት ከፍታ ብሎም ስለ ወደፊት ኢንቨስትመንት  ዕቅዱ ከተናገ በኋላ  ጋሻ ጃግሬዎቹ  ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ምሳ ስላለበት ወደዚያ መሄድ እንዳለበት ነገሩት ነባለ፡፡ እንደመጣ በዚያው ፍጥነት ሾልኮ  ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በረረ፡፡ የጎመዥው ሕዝብ እጅ ሳይጫንበት ፤ ውሃ እና ዘይትም ሳይሰጠው ተመለሰ፡፡

ትሞታላችሁ
“ነብዩ” ቡሽሪ ለሕዝቡ ደጋግሞ ቀጣዩ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል አሉ፡፡ “በእኔ ላይ ማናቸውንም ክፉ ነገር የጻፈ ፤ ያጻፈ ..ሁሉ ይሞታል” ማለቱ ተሰምቷል፡፡ እሱ አልተረዳውም እንጂ ሕዝቤ ከሞተ ቆየ፡፡ “ነብይ” የተባለው ስለ ራሱ ሰግቶ “ትሞታላችሁ” ይበላቸው እንጂ ሕዝቡ ለራሱ ክብር መስጠት ያቃተው ዕለት ፤ ለገንዘብ መጎምዥት ከጭቃ ላይ ጥሎ እስከማዋረድ ያደረሰ ዕለት ፤ መንፈሳዊነት ከጥንቆላ እና ሟርት ጋር የተምታታብን ዕለት ፤ የፈጣሪን ታላቅነት በሰው ሚዛን አውርደን ለሰው የተንበረከክን ዕለት  በእርግጥ በእዚያን ዕለት ሕዝቤ እኮ  ሞቷል፡፡

“ኢየሱስ ከዓሳ ሆድ ውስጥ ዲናር አላወጣምን? እኛስ ብር ብናባዛ ምን አለበት? ለሚሉን የከተማችን ‹‹ነቢያቶች›› ደግሞ መልሳችን፡- “ኢየሱስ መንፈሳዊ ኃይልና ስልጣንን ተጠቅሞ ያወጣውን ዲናር ግብር ከፈለው እንጂ እንደ እናንተ  አልበላውም” እንላቸዋልን፡፡ በመንፈሳዊነት ስም ሕዝቡን ከሚያበሉ ሳይሆን ከሚበሉ ፤ በሕዝቡ ላይ ሕይወትን ሳይሆን ሞትን ከሚያውጁ ‹‹ነብያቶች›› ጋር በአንድ ማዕድ ለምሳ መቀመጥም ነውር ነው፡፡


22 comments:

 1. ewenete new kemoten koyetenal

  ReplyDelete
 2. አቤቱ ቸሩ እግዚአብሔር ማስተዋልን ስ\ተን…. እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ የአስራት ሀገርሽን ኢትዮጵያን በምልጃሽ ጠብቂልን….

  ReplyDelete
 3. እንደዚህ ለሀገራቸው የሚቃጠሉ ሙህራን መኖራቸው በእውነት ያስደስታል.. በርታ እኛም ለመበርታት እንጥራል

  ReplyDelete
 4. ሕዝቡ ለራሱ ክብር መስጠት ያቃተው ዕለት ፤ ለገንዘብ መጎምዥት ከጭቃ ላይ ጥሎ እስከማዋረድ ያደረሰ ዕለት ፤ መንፈሳዊነት ከጥንቆላ እና ሟርት ጋር የተምታታብን ዕለት ፤ የፈጣሪን ታላቅነት በሰው ሚዛን አውርደን ለሰው የተንበረከክን ዕለት በእርግጥ በእዚያን ዕለት ሕዝቤ እኮ ሞቷል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሕዝቡ ለራሱ ክብር መስጠት ያቃተው ዕለት ፤ ለገንዘብ መጎምዥት ከጭቃ ላይ ጥሎ እስከማዋረድ ያደረሰ ዕለት ፤ መንፈሳዊነት ከጥንቆላ እና ሟርት ጋር የተምታታብን ዕለት ፤ የፈጣሪን ታላቅነት በሰው ሚዛን አውርደን ለሰው የተንበረከክን ዕለት በእርግጥ በእዚያን ዕለት ሕዝቤ እኮ ሞቷል፡፡
   Reply

   Delete
 5. Yigermal betam betam yigermal

  ReplyDelete
 6. ሕዝቡ ለራሱ ክብር መስጠት ያቃተው ዕለት ፤ ለገንዘብ መጎምዥት ከጭቃ ላይ ጥሎ እስከማዋረድ ያደረሰ ዕለት ፤ መንፈሳዊነት ከጥንቆላ እና ሟርት ጋር የተምታታብን ዕለት ፤ የፈጣሪን ታላቅነት በሰው ሚዛን አውርደን ለሰው የተንበረከክን ዕለት በእርግጥ በእዚያን ዕለት ሕዝቤ እኮ ሞቷል፡፡
  Reply

  ReplyDelete
 7. ሕዝቡ ለራሱ ክብር መስጠት ያቃተው ዕለት ፤ ለገንዘብ መጎምዥት ከጭቃ ላይ ጥሎ እስከማዋረድ ያደረሰ ዕለት ፤ መንፈሳዊነት ከጥንቆላ እና ሟርት ጋር የተምታታብን ዕለት ፤ የፈጣሪን ታላቅነት በሰው ሚዛን አውርደን ለሰው የተንበረከክን ዕለት በእርግጥ በእዚያን ዕለት ሕዝቤ እኮ ሞቷል፡፡
  Reply

  ReplyDelete
 8. ሕዝቡ ለራሱ ክብር መስጠት ያቃተው ዕለት ፤ ለገንዘብ መጎምዥት ከጭቃ ላይ ጥሎ እስከማዋረድ ያደረሰ ዕለት ፤ መንፈሳዊነት ከጥንቆላ እና ሟርት ጋር የተምታታብን ዕለት ፤ የፈጣሪን ታላቅነት በሰው ሚዛን አውርደን ለሰው የተንበረከክን ዕለት በእርግጥ በእዚያን ዕለት ሕዝቤ እኮ ሞቷል፡፡
  Reply

  ReplyDelete
 9. yigermal, be ethiopia yih hulu kale egziabher eyefesese, endih lefrd endaihonachu tselyu yemilut abatoch lezih new. betechiristian eyastemarech new jero yalew yisma, chirsotos bemiastemrbet gize enquan saiker aberkto yabelanal blew yemiketelu neberu , mecherechaw gin alamarem,silezih menafkan sirachew mesratachew aykerm behiwot metshaf yaltetsa yenesu megelgeya mehonu aykerim.egzio sewrene malet yasfelgal, ebakih wegenie bemastewal temelales.

  ReplyDelete
 10. አቤቱ ቸሩ እግዚአብሔር ማስተዋልን ስ\ተን…. እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ የአስራት ሀገርሽን ኢትዮጵያን በምልጃሽ ጠብቂልን….

  ReplyDelete

 11. betam yemigerm yemiyasazin ke endezih ayinetu kihidet ena tifat yisewuren yitebken

  ReplyDelete
 12. “ነብዩ” ቡሽሪ ለሕዝቡ ደጋግሞ ቀጣዩ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል አሉ፡፡ “በእኔ ላይ ማናቸውንም ክፉ ነገር የጻፈ ፤ ያጻፈ ..ሁሉ ይሞታል” ማለቱ ተሰምቷል፡፡ እሱ አልተረዳውም እንጂ ሕዝቤ ከሞተ ቆየ፡፡

  ReplyDelete
 13. ነብይ ቡሽሪም፡ ጆሹዋም ጠንቋዮች ናቸው!
  ጥላውን ሳይሆን አካሉን እንመልከት እግዚአብሄር የሚቀባን በጤናና ብልፅግና ሳይሆን በዘላለም ህይወት ጸጋ ነው፡፡ ስለዚህ የጤናና ብልፅግና ትንቢት ስጋዊ ነው፤ምድራዊ ነው፤ጥንቆላ ነው! የሰማይ መላእትም ቢሆኑ ጠንቆላ የተረገመ ነው! -ድንቅና ተአምራት ፈልገን ማግኘት ያለብን እውነት ሳይሆኑ ከኋላ የሚከተሉ ጥላዎች ናቸው፡ ጥላ እኛ ፈልገነው የሚመጣ ሳይሆን በራሱ ጊዜ ሊኖርም ላይኖርም የሚችል፡ከብርሃን/ከእውነት ማነስ ወይም መጉደል የተነሳ የሚከሰት ክስተት ነው -መብልና መጠጥ፡ጤናና ብልጽግና እንዲሁ በተፈጥሮ ልግስና እና በእግዚአብሄር ቸርነት የሚመጡ ወይም የምናገኛቸው የስጋ መሻት ናቸው፤እኛ(ክርስቲያኖች፡እውነትን የተቀበልን) ፈልጉ የተባልነው የእግዚአብሄርን መንግስትና የእግዚአብሄርን ጽድቅ(እውነትን) ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በመንፈስ ቅዱስ የሆነች ደስታና ሰላም ናት እንጂ መነብልና መጠጥ አይደለችም፤ሰማያዊ እንጂ ምድራዊ አይደለችም፤መንፈሳዊ እንጂ ስጋዊ መሻት አይደለችም
  -ድንቅና ተአምራት ለሚያምኑት ከኋላቸው የሚከሰት ጥላ ነው፡ለዚህ ነው ጌታም ያመኑትን በዚህ(በተአምራት) ደስ አይበላችሁ/እንዳይላችሁ ፡ሰይጣን ራሱ ከዚህም የሚበልጥ ድንቅ ነገር ሊያደርግ ይቻለዋልና ያላቸው፡፡ ለማያምኑና ለጠማሞች ግን መሻታቸው ነው፤እነሱ ስለእውነት ሳይሆን የሰውንና አለማዊ ፍላጎትን የሚከተሉ ብርሃን የሌለባቸው/ያነሳቸው የጨለማው ልጆች ናቸው -መብልና መጠጥ፡ጤናና ብልጽግና፤እንደ ሰማይ ወፎችና እንደምድር አበባ እንስሳቶችና ግኡዝ ፍጥረታትም የሚያስፈልጋቸው ነው፡፡እውነትን የሚሹና የተቀበሉት ግን አሁን ታይቶ ኋላ የሚጠፋውን ሳይሆን እውነትን ፈልጎ በማግኘት የዘላለም ህይወትን መኖር ነው፡፡ ስለዚህ
  -በቃላትና በዜማ፡በየሚዲያውና በየአደባባዩ በምናያቸው ትእይንቶች አንደነቅ፤ሙታን ከመቃብር ወጥተው ሲራመዱ ብናይ እንኳን፤ -ይህ ስጋዊና ምድራዊ የአጋንንትም ትምህርት ስለሆነ፡ምንም ተከታዮቻችን ቢበዙ፤ምንም በልተን ቢስማማን ፤ለብሰን ቢያምርብን፤ትምርትና ስብከታችን ድንቅና ተአምራት፤ጤናና ብልጽግና ከሆነ እኛ ከንቱዎች ነን፡፡ እውነት ጆሹዋና ዳዊት ሳይሆኑ የተጻፈው ክርስቶስ ብቻ ነው!

  ReplyDelete
 14. እሱ አልተረዳውም እንጂ ሕዝቤ ከሞተ ቆየ፡፡ “ነብይ” የተባለው ስለ ራሱ ሰግቶ “ትሞታላችሁ” ይበላቸው እንጂ ሕዝቡ ለራሱ ክብር መስጠት ያቃተው ዕለት ፤ ለገንዘብ መጎምዥት ከጭቃ ላይ ጥሎ እስከማዋረድ ያደረሰ ዕለት ፤ መንፈሳዊነት ከጥንቆላ እና ሟርት ጋር የተምታታብን ዕለት ፤ የፈጣሪን ታላቅነት በሰው ሚዛን አውርደን ለሰው የተንበረከክን ዕለት በእርግጥ በእዚያን ዕለት ሕዝቤ እኮ ሞቷል፡፡

  ASAFARI HIZBI; YASAZINAL
  EZZAWU BEMALAWI, WEYIM BE GANA/KONGO/TOGO/, ETC. BEHON AYIGERMIM
  BEZICH AGER, BE AGERE EGZIHABIHER- BE ETHIOPIA, MEHONU MINIGNA
  ASNEWARI NEWU?

  BE KIDUSAN AGER, LE DINGIL ASRAT TEDERGA BETESETECH AGER

  WEY ALEMETADEL

  LEZEGABIWU KALEHIWOT YASEMALIN

  ReplyDelete
 15. my Goodness! is this happened in Addis Ababa? were are we? please let us know more about this person. is he in Addis Abaa at this time? or already let ? Let me tell you something about this . the problem is ours not his. because our people have faith but they do not have enough knowledge about their faith . look! even in Ethiopia, we have many falls preachers, monks and priest ,.so, we the Ethiopian Orthodox Tewahdeo Church scholars have to stand together against this teaching in order to save our people. I deeply thank Mr. Hailegiyourgis for the information. I believe that this information will save many innocent people from this evil spirit.
  truly.

  ReplyDelete
 16. እሱ አልተረዳውም እንጂ ሕዝቤ ከሞተ ቆየ፡፡ “ነብይ” የተባለው ስለ ራሱ ሰግቶ “ትሞታላችሁ” ይበላቸው እንጂ ሕዝቡ ለራሱ ክብር መስጠት ያቃተው ዕለት ፤ ለገንዘብ መጎምዥት ከጭቃ ላይ ጥሎ እስከማዋረድ ያደረሰ ዕለት ፤ መንፈሳዊነት ከጥንቆላ እና ሟርት ጋር የተምታታብን ዕለት ፤ የፈጣሪን ታላቅነት በሰው ሚዛን አውርደን ለሰው የተንበረከክን ዕለት በእርግጥ በእዚያን ዕለት ሕዝቤ እኮ ሞቷል፡፡

  ReplyDelete
 17. ይድረስ ኦርቶዶክሳዊ ትውፊቶችን ሁሉ ተረት ለማለት ለምትፋጠኑ!!
  1. በመ/ቅዱስ ቅዱሳንን አማልዱን ማለትና ለቅዱሳን የአክብሮት ስግደት መስገድ ኃጢኣት ነው የሚል ጥቅስ ካለ አምጡልን!!ቃሉን ካላመጣችሁ ግን እናንተንም የተረት አባት አድርገን እንድናያችሁ እንገደዳለን!!በእናንንተ አነጋገር ከተመራን እነ ኤልሻዳይና እነ ኢማኑኤል ቲቪዎች የሚደሰኩሩዋቸው ዲስኩሮችም ተረት ናቸው ማለት ነው!!በተለይ ትንቢታዊ ኮንፈረንስ በሚባለው ዳንኪራችሁ የሚወራው ተረትና የነፓስተር ጆሹዋ የፈውስ ተረት ሆዴን እስኪያመኝ ያስቀኛል!!ጥንቆላ ከረባት ለብሳ በጉዋሮ በር ትምጣ!! ያሰኘኛል!!ለስንት የጠብቅናችሁ ሰዎች የወያላ ጎረምሳ ፓስተሮችና የናይጀሪያ ጠንቁዋይ ፓስተር ተብየዎች መጫወቻ ሆናችሁ አረፋችሁት እላለሁ!!
  2. በተለይ ኢ/ዊ ፓስተሮች፤ግዴለም ወደ ኦርቶዶክስነትም አትመለሱ!!ግን እባካችሁ ለእርዳታ ስትሉ ኢንተርናሽናል የሚል ታፔላ እየለጠፋችሁ ሀገሪቱን የውጭ ሚሺነሪዎች መናህሪያ አታድርጉዋት!!ቢያንስ የቸርቹ ቁልፍ በእናንተ እጅ ይሁን!!ሰዎቹ(የውጭ ፓስተሮች) ለብር ነው ቅርንጫፍ የሚከፍቱት!!ለዕምነት ከሆነማ ቸርች እንደሱቅ በደረቴ በተንሰራፋባት አዲስአበባ ብቻ በዚህ መጠን ቅርንጫፍ ከማብዛት ወጣ ብለው ወደ ገጠር ይከፍቱ ነበር!!እናንተም መኮረጁን ስለማታውቁበት ኩረጃችሁ “አሜን” የሚለውን የብዙ ብሄረሰቦች ቃል “ኤሜን” በሚለው ፈረንጅኛ ቃል ከነመሀረቡ መሆኑ በጣም ያስቀይማል!!ራሳችሁን ሁኑ!!
  3. ዘመናዮቹ አማንያን፡ ቀልባችሁን ገዝታችሁ ወደ ራሳችሁ እስክትመለሱ በታይትና በሚኒ እየዘለሉ ቅጥ በሌለው መልኩ አረፋ እየደፈቁ ለጌታ አምልኮ ነው ማለቱን ቀጥሉበት!!የእናንተ እግዜር እንደኤልዛቤል ውቃቢ ጠሪዎች ካልጮሁ እና አቡዋራው እስኪጨስ ካልተንፈራፈሩ አይሰማም አሉ!!አይዙዋችሁ!!በዚሁ ከቀጠለ ገና የመዝሙር ምሽት ቤት ይከፈታል!! እረ በአዳር ፕሮግራም ጌታን እናስመልካለን ብለው ተነስተው የመዝሙር ፓርቲ ለወጣቶች የሚሉትን አስመላኪ ተብየ ዲጄዎቻችሁን አስታግሱልን!!እኛስ ለእናንተ በተረትነት የሚታየውን ስለክርስቶስ መስክረው አክሊለ-ክብር የተቀበሉ ቅዱሳንን ገድል በጸጥታ የበረታው ቁሞ የደከመው ተቀምጦ እየሰማን ነበር!!
  4. አትሸወዱ!!ኦርቶዶክስነት ወደው ፈቅደው በፍቅር የሚይዙት ሃይማኖት እንጅ በግድ ታስረው የሚያዙበት ዕምነት ስላልሆነ በነጻነት እምነታችሁን ቀይራችሁዋል!!ግን አሁንም ኢትዮጵያዊ ናችሁ!!ታዲያ ኢ/ዊ የሆነውን ባህል ሁሉ ኦርቶዶክስን ስለሚያስታውስ እያላችሁ ስታጣጣሉትና በምእራባዊ ባህል ስትወረሩ ሳይ ወይ አለማስተዋል እላለሁ!!በዚህ ዙሪያ ገና ወደፊት የምለው ይኖረኛል!!በዚያው በምናውቀው ብሎግ እንገናኝ!!
  እስከዚያው ልብ ይስጣችሁ!!

  ReplyDelete
 18. yih neger ebakachu leabatoch asayulin. mikniatum abatoch yih eyehone yalew layawkut yichilalu , kidus sinodosm hone abatachin abune matias liyayut yigebal .endih ayinet tenakashoch betelekekubet zemen kudus sinodos yebetchristian astemhrona miemenanu betekula endayiwesdu begochun yemetebek halafinetu yenesu new, ababtoch yebetechristian kinat yalachew lijochachu atagluachew,
  t

  ReplyDelete
 19. yih neger kudus sinodosm abatachin abune matiasm liyayut yigebal ,mikniatum min eyetederege endal layawku yichilalu, Beahunu gize endih ayinet netaki tekulawoch balubet zemen abatochachin betechiristiana lemenga litebku gidetachew kesew saihone keamlakachew yetesetachew adera liasbu yigebalna , neger gin enesu chel bemalet saihon bealem yemikahedew zemenu akahed laiwkut yichilalu.

  ReplyDelete
 20. Be geza hagerachen weste yehen mayet ena mesmat yasaferal!!! Ere wegene neka bakhe! Menw Fetarin resanew???

  ReplyDelete