(አንድ
አድርገን ሰኔ 13 2006 ዓ.ም)፡-
116ኛው የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ 6ኛ በፓትርያርክነት ዘመናቸው ይቀመጡበት የነበረው በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል የሚገኝ አንድ ያረጀ ክፍል ነበር፡፡ በዚህ ክፍል ሲኖሩ አንድ የካቶሊክ መነኩሴ ሊጎበኛቸው መጣ፡፡ ፓትርያርኩን ማረፈያ ቤትና ዕቃዎቻቸውን ሲመለከት ለክብራቸው የሚመጥን ባለመሆኑ ደነገጠ፡፡ (ፓትርያርክ የሚሆኑ አባቶች በደህና ማረፊያ ሊኖሩ ይገባል ፤ ይህም ለእነርሱ ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን ክብር ሲባል ነው፡፡) መነኩሴው አቡነ ቄርሎስን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው ‹‹እባክዎን በእንዲህ ዓይነት ቤት ውስጥ መኖር ለእርስዎ የሚመጥን አይደለም፡፡ ፈቃድዎ ከሆነ እኔ ቤትዎን ላድስልዎትና ምርጥ ምርጥ ዕቃዎችን ላስገባልዎት?›› ፓትርያርኩ ይህንን ጥያቄ ሲሰሙ ፈገግ ብለው በፍቅር ዓይን ከተመከቱት በኋላ ‹‹የእኔ ልጅ እጅግ አመሰግናለሁ! እርግጥ ነው ይህ ቤት በጣም የተጎሳቆለ ነው፡፡ እንደዚህም ሆኖ ግን ጌታችን ከተወለደበት በረት ይሻላል!!›› አሉት፡፡
በእኚህ አባት እግር የተተኩት ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ደግሞ በግብፅ መንግሥት በታሰሩ ጊዜ ምእመናኑ ከእስር ቤት ወጥተው ማረፊያ ቤት እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ሰልፍ ወጥቶ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ አቡነ ሺኖዳ ለሕዝቡ ንግግር አድርገው ማረፊያ ይሰጣቸው በሚል የተወጣውን ሰልፍ እንዲበትኑ ተጠየቁ፡፡ እኚህ አባትም ሕዝቡን እንዲህ ሲሉ አረጋጉት፡፡ ‹‹ለእኔ ማረፊያ እንዲሰጠኝ ብላችሁ ሰልፍ ወጥታችኋል ፤ ነገር ግን በፍቅር ከተሞሉት ከእናንተ ልቦች የተሻለ ማረፊያ ለእኔ አያስፈልገኝም!›› አሏቸው፡፡
ከሄኖክ ኃይሌ
ይህ የሆነው በ116ኛው የኮፕት ፓትርያርክ በአቡነ ቄርሎስ እና በ117ኛው
ፓትርያርክ በአቡነ ሺኖዳ ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት አባቶችን ማየት እድለኝነትን ይጠይቃል፡፡ መንጋውን በአግባቡ
እየመሩ ከመቶ በላይ መንፈሳዊ መጻሕፍት ለእመነቱ ተከታዮች እየጻፉ ፤ በየሳምንቱ ቋሚ መርሐ ግብር በመያዝ ወንጌል እየሰበኩ ፤
አክራሪ ሙስሊሞች ቤተ ክርስቲያቱ ላይ የሚያነሱትን ችግር ተቋቁመው ከአስር በመቶ የማይበልጡ የእምነቱን ተከታዮች መንፈሳዊ ልዕልናው
ከፍ እንዲል የሚሰሩትን ሥራ መመልከት እጅግ ደስ ያሰኛል፡፡ ወደ
እኛ ቤተክርስቲያን ስንመጣ ደግሞ በርካታ ችግሮች የተጋፈጡባት ቤተ ክርስቲያን ብዙ የመነጋገሪያ አጀንዳ አንስቶ ሸክሟን ማቅለል
ሲገባ ‹‹የጳጳሳት ንብረት ውርስ››ን በሚመለከት በሲኖዶስ ደረጃ አጀንዳ ይዞ መነጋገር ያለንበትን የመንፈሳዊ ደረጃ ዝቅጠት ያሳየናል
(አንዳንድ አባቶች በአዲስ አበባ ከ500 ካሬ ሜትር በላይ የተንጣለለ ቪላ እና G+1 በስማቸው የተመዘገበ ንብረት ባለቤቶች ስለሆኑ)፡፡
‹‹በፍቅር ከተሞሉት ከእናንተ ልቦች የተሻለ ማረፊያ ለእኔ አያስፈልገኝም!›› በማለት ምንም ዓለማዊ
ሀብት ንብረት ሳያፈሩ የተሰጣቸውን ሓላፊነት በሚወጡ አባቶችን እኛ ለምን አጣን? እኛን እጅግ የሚገርመን በጥቂት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና
በግብጽ ኮፕት ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ያለው ዘርፈ ብዙ--------------------------------------------
ልዩነት ነው፡፡
ከታች እያነጹ መምጣትን ማን ከለከለ !!!!
ReplyDeleteእንዳለመታደል ሆነና አንዱን ፓትርያርክ ስንወቅስ ኖርንና የተተኩትን አወድሰን ሳንጨርስ ደግሞ የባሰ ጉድ አየንም ሰማንም፡፡ ሰሞኑን ለምንድነው ስለ ፓትርያርክ ብቻ የምንወዛገበው እያልኩ አስባለሁ፡፡
ነፍሳቸውን ይማርና በአቡነ ጳውሎስስ ዘመን ቢሆን ማዕከላዊው የቤ/ክ አስተዳደር ላይ ችግር ቢኖርም በየሀገረ ስብከታቸው ጳጳሳቱ ምን ሰሩ፤ ምንም የጠቅላይ ቤተ ክህነትን መመሪያና በጀት የማይጠይቁ ጳጳሳቱ በራሳቸው ድንበር ሕዝበ ምዕመኑን አስተባብረው ምን ቁልፍ ችግር የሚፈታ ሥራ ሠሩ፤ (የሞካከሩ እንዳሉ፣ በጸሎት የተጠመዱ እንዳሉ ሳንዘነጋ)፤
አሁንም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ዘመንስ በሀገረ ስብከታቸው ጠንክረው መሠረት የሚሆን ሥራ እንዳይሠሩ ማን ከለከለ፤ እንዲሁ እኛም አነርሱም በቅዱስ ፓትርያርክ ጉድለትና ድክመት ተሸፍነን እስከ መቼ፤
ከጳጳሳቱ በተዋረድ እስከ ደብር አለቃ፤ እንደውም እስከ ሰንበት ት/ቤት አመራር በራሳችን የሥልጣን ድንበር ድምጽ ሳናሰማ የምንሰራው፣ የበላይ ይሁንታ የማያስፈልገውና አሁን ባለው የቤ/ክ ሕግ የተደነገገልንን እንስራና ለቀሪው ፈጣሪን እንጠይቅ፡፡
ታዛቢ ዘ መሃል ሀገር
Is there any plan to visit S. Sudan refugees in Ethiopia? This is something the church needs to orginize real quick. No preaching or teaching. Just feed and let them drink the hungry and thristy, kiss their chucks, wash their legs, sit, talk, laught and cry with them. Then, when their suffering subsides, they will remember the blessings they received in Jesus name. They really need an honest help, not politically motivated one. They suffered way too long. My apologies for posting unrelated comment.
ReplyDeleteIt is extremely disappointing that you have posted the interview of "tesfaye shewaye", who is either wizard or weird person. He has so many funny stands against the Orthodox Tewahido. He can not in any way be called "orthodox". He is not a priest but claims to be a priest. ............You should have researched before bringing to your post. Such wicked personalities will lower down your blog. Think....
ReplyDeleteI don't want to see Andadirgen to entertain a low profile posts, let alone tesfaye the wicked.