- ይቅርታ የሚያስከለክሉ በሚል በረቂቅ የይቅርታ ሕጉ የተዘረዘሩት ወንጀሎች ተሰረዙ ፤ ከተሰረዙት መካከል ‹‹ግብረ ሰዶም›› ይገኝበታል፡፡በሕጉ መሰረት መንግሥት ወደፊት የግብረሰዶም ፍርደኞችን በይቅርታ ሊፈታ ይችላል፡፡
- ‹‹ግብረ ሰዶም ወንጀል ይቅርታ የማያሰጥ ተደርጎ መግባቱ ከሕገ መንግሥቱና ከሕዝብ ሞራል አንፃር ትክክል ነበር፤›› የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ
- ‹‹የተዘረዘሩት ይቅርታ የማያሰጡ ወንጀሎች እንዲወጡ የተደረገው ይቅርታ የማያሰጡ በማለት ዝርዝር ከተጀመረ መቆሚያ ስለማይኖረው ነው›› የፓርላማው የሕግ፣ የፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፍትሕ አስተዳደር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አስመላሸ ወልደ ሥላሴ
(አንድ አድርገን ግንቦት 3 2006 ዓ.ም)፡- የይቅርታ አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ ውስጥ ይቅርታ የማያሰጡ የወንጀል ዓይነቶችን የሚዘረዝረው አንቀጽ ሙሉ በሙሉ በሕግ አውጪው አካል በሕዝብ
ተወካዮች ምክር ቤት መሰረዙ ተሰማ፡፡ ሌሎች ማስተካከያዎች የተካተቱበት ይህ የይቅርታ አዋጅ ባለፈው ሳምንት ፀድቋል፡፡ የረቂቅ አዋጁ ክፍል ሦስት አንቀጽ 14 ንዑስ 1 በሕገ መንግሥቱ ይቅርታ የሚያስከለክሉ ተብለው ከተቀመጡት ወንጀሎች በተጨማሪ ይቅርታ የሚያስከለክሉ ወይም የማይጠየቅባቸው በማለት ከአሥር በላይ ወንጀሎችን ዘርዝሮ አስቀምጧል፡፡ ከእነዚህ መካከል ግብረ ሰዶም፣ ሙስና፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሽብርተኝነት መሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸም ወንጀል የመሳሰሉ ይገኙበታል፡፡ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተደረጉት ማሻሻያዎች መካከል የይቅርታ ዓላማን
የተመለከተው አንቀጽ አንዱ ነው፡፡ ‹‹የይቅርታ ዋና ዓላማ፣ የመንግሥትና የታራሚዎችን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል መንግሥት ጥፋተኞች
በጥፋታቸው የተፀፀቱና የታረሙ መሆኑን በማረጋገጥ ወደ ኅብረተሰቡ ተቀላቅለው አምራች ዜጋ እንደሆኑ ማድረግ ነው፤›› በሚል ተተክቶ
አዋጁ ጸድቋል፡፡
በዚህ መሰረት ወደፊት በአዲስ ዓመት ዋዜማም ሆነ በተለያዬ ሕዝባዊ በዓላት ወቅት መንግሥት ይቅርታ ከሚያደርግላቸው ፍርደኞች መካከል ግብረ ሰዶማውያን ፍርዳቸው እንደ ተራ ወንጀል በመቁጠር ሊለቀቁና ይቅርታም የሚደረግበት የሕግ አግባብ ሊኖር ይችላል ተብሏል፡፡ ይህ መንግሥት በግብረሰዶም ወንጀል ላይ የያዘውን አቋም ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ያመላክታል፡፡
ምንጭ ፡- ሪፖርተር
የተወካዮች ም/ቢት አባላት አብዛኛዎቹ የግብረ-ሰዶም አቀንቃኞች ስለሆኑ ነዉ ሕጉን ያሻሻሉት
ReplyDeleteሕዝቡ እራሱ ካልተነሳ መንግስት ለዚህ ጉዳይ ደንታ እንደሌለው የታወቀ ነው፡፡ እግዚአብሄር ይጠብቀን፡፡
ReplyDelete