Thursday, May 8, 2014

ድሮና ዘንድሮ ፤ ዘመነ አቡነ ጳውሎስ እና ዘመነ አቡነ ማትያስ የተጻፉ ደብዳቤዎች

(አንድ አድርገን ሚያዚያ 30 2006 ዓ.ም)፡- አቡነ ማትያስ አሜሪካ በነበሩበት ወቅት አቡነ ጳውሎስ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ በቤተክርስቲያኒቱ በተለያዩ የስልጣን ተዋረዶች የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ከ15 ገጽ ያላነሰ አቤቱታ ለብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲደርስ አድርገዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ምዕመኑ ጉዳዩን እንዲያውቀው በጊዜው ለሚታተሙ ጋዜጦች መካከል ለአንዱ በመላክ ለአንባቢያን እንዲደርስ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ የእሳቸውን አቤቱታ ፖስት ያደረገው ጋዜጣ ከአቤቱታው ብዛት የተነሳ አንኳር አንኳሩን ብቻ እንዳወጣው በጽሁፉ ላይ ገልጾ ነበር፡፡የወቅቱ የአንድ ዲያቆን አላግባብ ዝውውር የሚኮሰኩሳቸው አባት ነበሩ አሁን ላይ ግን ስለ ብዙዎች ማኅበር የቆሙበት መንገድ ብዙዎችን ግራ ያጋባ እየሆነ መጥቷል፡፡   አሁን ዘመኑ ነጉዶ አምስተኛው ፓትርያርክ አልፈው ስድስተኛ ብለን መጥራት ከጀመርን አንድ ድፍን ዓመት አለፈን ፤ አንድ አመት ቢያልፍም ቤተ ክርስቲያን ግን ሸክሟ ሲቀልላት አልተመለከትንም፡፡ ባለፉት 20 ዓመታት ቤተክርስቲያኒቱ የቆመችበትን ዓላማ እንድታሳካ ቀን ከሌት ጎንበስ ቀና የሚለው ማኀበረ ቅዱሳን ላይ ከሶስት ዓመት በፊት እና ከሦስት ዓመት በኋላ በአንድ ብዕር ፤ በአንድ አይነት ሰዎች የተጻፉ በተለያዩ አባቶች ፍቃድ አግኝቶ የወጣውን ደብዳቤ ለማየት ወደድን፡፡ ከዚህ ቀደም የአብነት መምህራን ጉባኤ እገዳ ላይ በአባ ሰረቀ ብርሃን የተረቀቀውን በአቡነ ማትያስ የጸደቀው ደብዳቤ ፤ የዛሬ ሳምንት ፓትርያርኩ የማኅበረ ቅዱሳንን የጥናት ጉባኤ ያገዱበትና በሚዲያ ያልወጡ በሁለቱ ተቋማት ብቻ የሚገኙ ደብዳቤዎች የቀድሞ ዘመን ለመመለሱ መንገድ አመላካች ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ( ብጹእ አቡነ ማትያስ ከዓመታት በፊት ለቅዱስ ሲኖዶስ የላኩትን አቤቱታ እና ጩኽት ወደፊት ፖስት እናደርገዋለን …. ‹‹ከበሮ በሰው እጅ ያምር ..ሲይዙት ያደናግር›› ይላል ያገሬ ሰው…..  

ዘመነ አቡነ ጳውሎስ 


ዘመነ አቡነ ማትያስ 11 comments:

 1. ዘደብረ ሐይማኖት መካነ ኢየሱስMay 9, 2014 at 6:42 PM

  ደብዳቤዎቹ ይዘታቸው ተመሳሳይ ቢሆንም የአቡነ ማትያሱ ቀለል ያለ ይመስላል፤ ምክንያቱም የሚያብራራውም ሆነ የሚከለክለው አንድ ጉዳይ ስለሆነ፥ መሰብሰብን። ነገር ግን የመጀመሪያው አቡነ ጳውሎስ ስልጣን ከያዙ ከ፲፯ ዓመት በኋላ የተፃፉት ሲሆን ሁለተኛው ግን አቡነ ማትያስ ስልጣን ከያዙ ከ፩ ዓመት በኋላ የተፃፉት ነው መሆኑ፤ ስለዚህ ለማወዳዳር ይከብዳል። እኔ የምፈራው፥ እድሜ ቢሰጣቸው ከ፲፭ ዓመት በኋላ ከፊተኛው የባሱ እንዳይሆኑ ነው።

  ReplyDelete
 2. ዘደብረ ሐይማኖት መካነ ኢየሱስMay 9, 2014 at 6:47 PM

  ለማንኛውም የራሳችሁን ትንታኔ ለመስጠት አለመዳዳታችሁን አደንቃለሁ፤ ፍርዱን ለአንባብያን መተዋችሁን መልካምነቱን ልገልፅላችሁ ፈልጌ ነው። ደብዳቤዎቹ ይዘታቸው ተመሳሳይ ቢሆንም የአቡነ ማትያሱ ቀለል ያለ ይመስላል፤ ምክንያቱም የሚያብራራውም ሆነ የሚከለክለው አንድ ጉዳይ ስለሆነ፥ መሰብሰብን። ነገር ግን የመጀመሪያው አቡነ ጳውሎስ ስልጣን ከያዙ ከ፲፯ ዓመት በኋላ የተፃፈ ሲሆን ሁለተኛው ግን አቡነ ማትያስ ስልጣን ከያዙ ከ፩ ዓመት በኋላ የፃፉት መሆኑ ነው፤ ስለዚህ ለማወዳዳር ይከብዳል። እኔ የምፈራው፥ እድሜ ቢሰጣቸው ከ፲፭ ዓመት በኋላ ከፊተኛው የባሱ እንዳይሆኑ ነው።

  ReplyDelete
 3. What can I say! Egziabher yifareden! YeAbatochachin Amlak yiresan zend fiqadu aydelem, gin sirawun yemiserabet yerasu gize alew!

  ReplyDelete
 4. Aba Paulos yimarun eyalin yalenibet huneta new yalew!!!

  ReplyDelete
 5. Can't believe what I am reading here.

  Is it possible that Abune Matias may be part of the Tehadisso movement?

  ReplyDelete
  Replies
  1. do you think that every body that tries to correct mkidusan is tehadiso? what kid tought!

   Delete
 6. Can't believe what I am reading here.

  Is it possible that Abune Matias may be part of the Tehadisso movement?

  ReplyDelete
 7. ይህ የሚያመለክተው ከእነዚህ አባቶች ጀርባ የአባቶችን እጅ የሚጠመዝዝ ጠንከር ያለ እጅ መኖሩን ነው፡፡ ይህ እጅ ደግሞ ከማን በኩል እንደሆነ ለመገመት አይከብድም፡፡ ይህ ደግሞ ግልጽ የሕገ-መንግስት ጥሰት ነው፡፡ አቡነ ማትያስ ለፓትርያርክነት ሲመረጡ አንድ ነገር አስቤ ነበር፤ የዕድሜ ባለጸጋ መሆናቸውን፡፡ ይህ ለሁለት ነገር ጠቃሚ ነው ብዬ አሰብኩ፤ አንደኛው፤ በሳልና አስተዋይ መሆናቸው ለቤተክርስቲያን አስተዳደር ጽኑ አቋም እንዲኖራቸው ያደርጋል፤ ሁለተኛው ደግሞ ምናልባት ከአቡነ ጳውሎስ ያልተሻሉ ወይም የባሱ ከሆኑ የዕድሜ ጣሪያ ስለሚገታቸው “ብልሹ አሰራሩ” እና ጎጠኝነቱ/ዘረኝነቱ ዕድሜም አብሮ ያጥራል የሚል ነበር፡፡ አሁን ሁለተኛውን እንዳስብ ሆኛለሁ፤ “ጌታ ሆይ ባሪያህን በቶሎ አሰናብተው” እያልንም ልንጸልይ ግድ ይለናል፡፡ ለማንኛውም “ለአባቶቻችን ረዥም ዕድሜና ጤና ይስጥልን” ብለን አምላካችንን ለመለመን እንድንችል እውነተኛ የሃይማኖት መሪ ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
 8. ለምን ይሄ ሁሉ? በእውነት ስለ ቤተክርስቲያን እድገት ስለ ስለ ወንጌል መስፋት…ተጨንቀው ይሆን??? ምነው እኔም ይገደኛል….ብሎ በነጻ አገልግሎት ለቤተክርስቲያናችን ሁለንተናዊ እድገት….የሚሰራውን ማኀበር ከመታገል ‘’በቤተ ክህነቱ’’ የተንሰራፋውን ጥቅመኝነት፣ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ቢታገሉ፡፡

  ReplyDelete
 9. እግዚአብሄር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

  ReplyDelete
 10. ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን ከፈተና ይጠብቅልን

  ReplyDelete