Wednesday, May 28, 2014

‹‹በአሁኑ ሰዓት ከራሱ ከባለቤቱ በቀር ይህቺን ሃይማኖት የሚያጸናት ፤ ይህቺንም ቤተ ክርስቲያን የሚታደጋት አካል የለም›› መምሕር ተስፋዬ

 (አንድ አድርገን ግንቦት 20 2006 ዓ.ም)፡-
ዕንቁ፡- ሁሉም ሰባኪን ወንጌል መንፈሳዊ ጥሪ ተደርልኝ  ጸጋ ተሰጥቶኝ ነው ሲሉ ይስዋላሉ፡፡ ተግባራቸው ግን ይህንን አይገልጽም ፡፡እውተኛ ጥሪና ጸጋ እንዴት ይታወቃል ?

መምሕር ተስፋዬ፡- እግዚአብሔር የሚያመሰግነው እንጂ ራሱን የሚያመሰግን ሁሉ እርሱ ተፈትኖ አይወጣም ተብሎ በመጽሐፍ ተጽፏል፡፡ የሃሳውያን መታወቂያቸው እኔ እኔ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹እኛ ከሰበክንላችሁ የእውነት የሕይወት ወንጌል ሌላ ከሰማይ መልአክም መጥቶ ቢሰብክላችሁ አትቀበሉ፡፡›› ተብሎ የተጻፈ ስላለ ምዕመን በጣም መጠንቀቅ ይገባዋል፡፡ ከፍሬያቸው ታውቋችዋላችሁ ከበለስ ወይን ሊለቀም አይችልም ተብሏል፡፡ ሃሳውያንም እውነት የላቸውም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ያብላሉ፡፡ ከእነርሱ መራቅ ያስፈልጋል፡፡ ትልቁ አላማቸው በጸሎታቸው ርዝመት እያመካኙ እመበለቲቱ ቦርሳ ጎልማሳው ኪስ መግባት ነው፡፡ይኸ ደግሞ ሥጋቸውን ብቻ ሳይሆን ነፍሳቸውንም የሚያደኽይ ነው፡፡ አሁን አሁን በቤተክርስቲያኗ አካባቢ ሁሉን በገንዘብ ማድረግ እንደ ሥርዓት እየተለመደ መጥቷል ፤ ሰውን በከፍተኛ ሁኔታ በሚያስገብዝ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ግን ደግሞ በገንዘብ መርገም መግዛት እንዳለ  ከጽድቁም ከገንዘቡም ሳይኮን ሜዳ ላይ  እንደሚያስቀር ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሀብቷ ሰው እንጂ ገንዘብ አይደለም፡፡


ዕንቁ ፡- በነገረ መለኮት ትምህር የተመረቁ ፤ በዓለማዊ ፍልስፍና የተራቀቁ ፤ በሃይማኖታዊ ርዕዮተ ዓለም የመጠቁ ምዕመናንን በሀሰተኛ ትምህርት የሚያጠቁ ወጣት ምሁራን በስፋት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ ፤ ይህንን ማስቆም የሚችለው የትኛው አካል ነው? ሲኖዶስ ፤ ቤተክህነት ወይስ መንግሥት ?

መምሕር ተስፋዬ፡- ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የሕግ ሲኖዶስ የላትም፡፡ የሕግ( dejour) ፓትርያርክ አግኝታ አታውቅም ፤ መናብርት ሲደለደሉ ለሌላው መትረፍ የማይችል የአንድ ሕጋዊ ሊቀ ጳጳስ ሀገረ ስብከት ናት፡፡ ሥልጣነ ክህነት የሚያላብስ ሊቀ-ጳጳስ አሁን በመንበር ላይ የለም ፤ ከዚህ የተረፈው የክዶ ማስካድ ፕሮጀክት ነው ፡፡ ዐመጽ ነውና ከራሱ ከባለቤቱ በቀር ይህቺን ሃይማኖት የሚያጸናት ይህቺንም ቤተክርስያን የሚታደጋት አካል የለም፡፡

ዕንቁ ፡- የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መምሕራን ከጥራት ይልቅ ብዛት ፤ ከመንፈሳዊነት ይልቅ አለማዊነት ፤ በአፍቅሮተ ነዋይ የተጠመዱበት (የተተበተቡበት) ወቅት ላይ በመሆናቸው ምዕመናን ሊታደጉ አልቻሉም የሚሉ ወገኖች ብዙ ናቸው ፤ በቤተ ክርስቲያቱ ቀኖና እና አስተምህሮ መሠረት የመምሕራንና የሰባኪያ ወንጌል አመዳደብ ወይም ሹመት እንዴት ነው ?

መምሕር ተስፋዬ ፡- እግዚአብሔር ተናግሮለት ፤ ሥነ ፍጥረት መስክሮረት ፤ ትዕቢት ርቆለት ከሆነ ያስታውቃል ፤ አፉ ባይገር ግብሩ ያስተምራል፡፡ አበባ ካለበት ንብ እንደሚቀስም ከርሱ ረብ ጥቅም ይገኛል፡፡ አሁን ባለው አሿሿም ግን መንፈስ ቅዱስ የለበትም፡፡

ዕንቁ፡- መንፈሳዊ ሹመት መገለጫው ምንድነው?
መምሕር ተስፋዬ ፡- መንፈሳዊ ሹመት መገለጫው ፍቅር ነው፡፡ ሰው የሚወድ ፤ በሰው የሚወደድ ፤ በጎ ምግባርና የቀና ሃይማት ይዞ መገኝት ነው፡፡ በመልከጼዴቅ የታየች ሥልጣነ ክህነት ጌታ እመቤታችን በጉልበቱ የነበሩትን አብርሃምን እንደ ሞተ ሰው አድርጋ ነበር ፤ ኋላም የመልጼዴቅ አምላክ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርነ መለኮትነቱን  በደብረ ታቦር በገለጸ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ከርሱም ጋር የነበሩት ሐዋርያት የሆኑት አላወቁትም፡፡ ከቅዱስ ጴጥሮስ የነበረች ሥልጣነ ክህነት ስታተርፍም ስታሳልፍም ታይታለች ፤  ሙት አንስታለች ፤ ሕያዋኑንም አሰናብታለች፡፡ መንፈሳዊት ሹመት ያደረችበት ሰውነት እንደ መስተዋት እግዚአብሔር የሚጎላባት ታደርገዋለች ፤ እርሱም ይታይባታል፡፡ ዛሬ አለች የምትባለው ግን ይኽ ሁሉ የላትም፡፡ እግዚአብሔር የተለያት ናትና፡፡

ዕንቁ ፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከሺህ ዓመታት በላይ ባስቆጠረው ታሪክ ተገዳዳሪ ፤ ተፃራሪ ያጣችበት ወቅት የለም፡፡ ለምሳሌ ፡- ፀጋና ቅባት ፤ አሁን ደግሞ ተሐድሶ  የሚባል አደጋ አንዣብቦባታል፡፡ ለዚህ እንዴት መፍትሄ ማምጣት ይቻላል?

መምሕር ተስፋዬ፡- ሕዝቡ መደንገጥ የለበትም፡፡ ከሀሳውያን ስህተት ከአላውያን ክህደት ፤ ከመናፍቃን ማታለል ለመጠበቅ እነርሱ የሚጠሉትን ማድረግ ፤ መስቀል አይወዱምና የመስቀል ምልክት በአንገት ላይ ማሰር ፤ ማማተብ ፡፡ ነገራቸው በህሊና ሲመላለስ “እግዚአብሔር ያሳፍርህ” ብሎ ማውገዝ ውዳሴ ማርያምን ፤ ተዓምረ ማርያምን ፤ ገድለ ቅዱሳንን ፤ ድርሳነ ቅዱሳንንና መላዕክትን አይወዱምና ይኽንን መድገም ፤ በአጠቃላይ ሥጋ የለበሱ መልአክት እንዳሉ ሁሉ በሥጋ ታንክ የሚዋጋ ሰይጣን ስለሆነ በሃይማኖት መቋቋም፡፡ በቡድን የሃይማት ነገር በሚወያይበት ጊዜ  ስለ ሃይማኖት ጠንቅቀው የሚያውቁ ሰዎችን ማማከር ፤ መናፍቃኑ የሞተች ወንጌላቸውን ሲያነበንቡ አለመስማት ፤ እርሷ ለሙታን ናትና፡፡ የእኛ ግን እርጥብ አመድ የምታደርግ እሳታዊት ስለሆነች ለልቡናችን ለመረዳት አይቸግራትም ፤ አታስቸግርም፡፡
እንዲህ ያለው ክፉ ጊዜ መምጣቱ አስቀድሞ ስለሚታወቅ አባቶቻችን ያቆዩልን አምስት አዕማደ ምስጢራት አሉ፡፡ እነርሱን ጠንቅቆ ማጥናትና ከልብ መሆን፡፡ ጸሎተ ሃይማኖት ሲደግሙ አስተውለው መድገም፡፡ እንደ ሰንበት ት/ቤቶች ያሉ ደግሞ  ሁል ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ግቢ ከየድርጅቱ ተከፋይ የሆኑ አወናባጆች በቋሚነት ስላሉ ሁኔታቸውን እያዬ መለየት ፤ ግብታዊ አለመሆን ፤ ሰው አለማመን (መቼ እንደሚለወጥ ስለማይታወቅ)፡፡  በተዋሕዶ አንድ የሆኑትን ማገዝ እርስ በእርስ መተጋገዝ ፤ ከጠብ ፤ ከክርክር ፤ ከወንጀል መራቅ፡፡ በዚህ ጉዳይ በአደባባይ ግልገሎችንና ጠቦቶችን  ለመጠበቅ የተሰናበተ አባት ስለሌለ ሁሉም ጠቃሽ ተኩላ ስለሆነ  ወጣቱ ባላወቀው ነገር እየተደናበረ ወደ ችግር እንዳይገባ መጠንቀቅ ፤ ራሱን መጠበቅ ይገባዋል (በሁለቱም በሥጋዊው በመንፈሳውዊም አካሄዱ፡፡) እንደ በትር ሊጠቀሙበት ከሚፈልጉ አካላት መጠንቀቅ ግድ ይለዋል፡፡

ዕንቁ ፡- ሊቅነት መንፈሳዊነት ነው ብለው ያምናሉ?
መምሕር ተስፋዬ፡-  ሊቅነት ከመንፈሳዊነት ጋር ግንኙነት የለውም ፡፡ መንፈሳዊነት ትህትናን ፤ ትዕግስን ፤ ፍቅርን ፤ ርህራሄን ፤ ደስታን ፤ ሰላምን የመንፈስ ፍሬዎች የተባሉትን ሁሉ የተላበሰ መሆን ነው፡፡ ሊቅነት ግን የዚህ ተቃራኒ ነው፡፡

ዕንቁ፡- የተዋሕዶ ሰባኪያን ወንጌልና መምሕራን ከዓለማዊ ሕዝብ የባሰ ጥል ይጣላሉ ፤ ይሸነጋገላሉ ፤ ይካሰሳሉ ፤ ከንስሓ ይልቅ “ሒስና ግለ ሒስ” ግምገማና እርማት ማለት ያበዛሉ፡፡ አንደበታቸው የሚገልጸው ፤ ሃሳባቸው የሚያስረዳው ርዕዮተ አለማዊው(Ideological) እንጂ መንፈሳዊ(Spiritual) አይደለም የሚል ወቀሳ ጎልቶ ይሰማል ፡፡ ይህን አይነት ነገር በሃይማኖት አስተምህሮ (Doctrine) እና ቀኖና እንዴት ይታያል?

መምሕር ተስፋዬ፡- ፖለቲካው ሦስት ፈርጅ ያለው ነው፡፡ አንዱ ፈርጅ መደብ ያታግለናል የሚለው ደርግ ያነሳው ነው፡፡ ሁለተኛው ብሔረሰብ ያታግለናል የሚለው ኢህአዴግ የሚለው ነው፡፡ ሦስተኛው ወገን ሃይማኖት ያታግለናል የሚለው ነው፡፡ በአጼ ኃ/ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በአራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ አንድ መነኩሴ ነበሩ፡፡ ሰባኪ ወንጌል ሆነው ብዙ ሰው እንደተከተላቸው ባዩ ጊዜ ሞቅ ሲላቸው “የሰባት ወር ሽል እንዴት ይገዛኻል” ብለው ተከታዮቻው ይዘው ወደ ኢዮቤልዩ ቤተ-መንግሥት አመሩ ፤ በመሀል የሆነው ሆነና ሰውየው ፍቼ ታሰሩ፡፡ ንጉሡ ሲወርዱ ቢፈቱም በስትሬቸር ላይ ውለው ነበር፡፡ የወታደራዊው መንግሥት መውደቂያ አካባቢ ደግሞ ከዲላና ከደብረ ብርሃን አካባቢ ተነሳን የሚሉ መሰል ባህታውያን ምድር ጠቧቸው ነበር፡፡ የዲላው ባህታዊ የደርግን ፓትርያርክ በመንበር ለማቆየት ከልማት መምሪያው በተለገሳው 75,000 የኢትዮጵያ ብር ከፍተኛ ቅስቀሳ አካሄዱ፡፡ ቅድስተ ማርያም ደውል ቤት ላይ ወጥተው ፊታቸው በጣልያኗ ሥዕል አምሳል ተሸፋፍነው ወደራሳቸው ባትሪ አብርተው ወላዲተ አምላክ ታየችኝ ብለው ተሳለቁ ፤ በጊዜው በከተማው አንድም ሰው የቀረ በማይመስል ሁኔታ ተርመስምሶ ሲያደንቅ ዋለ፡፡ እኚህኛው መመረጣቸውና የኒያኛው ቀሚሳቸውን ሰብስበው ወደ ናይሮቢ መፈርጠጣቸው ሲሰማ የባህታዊው ዘመቻ አንሶና የሽንብራ አፍንጫ አክሎ አደባባይ ኢየሱስ ላይ የሆነው ሆነ፡፡ የደብረ-ብርሃኑ ደግሞ አሁን አንድ በሕይወት የሌሉ ጳጳስ ፓትርያክ ለማድረግ በቤታቸው ሲያስፎክሩ ሰንብተው እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን አንድ መሰላቸውን ካስጣሉ በኋላ በቦብ ማርሌይ አስጎንጉነውት የነበረው ጠጉራቸው በሰው ፊት በደረቁ ተላጭቶላቸው እርፍ አለ፡፡ አሁን ላይ ባሕታዊነቱን እርግፍ አድርገው ትተው ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ያውም በሳምንት አንድ ቀን ከባለቤታው ጋር የሚተያዩ ሆነዋል ፤ ድቄም….

ቅዱስ ጴጥሮስ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ ጆሮ ከግንዱ ጥርግ አድርጎ በቆረጠ ጊዜ ባለቤቱ ጴጥሮስ ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልሰህ አስገባው ብሎታል፡፡ በሰይፍ የገደሉ በሰይፍ ይሞታሉና፡፡ መንፈሳዊን የስህተት ኃይል በሥጋ ጉልበት ማሸነፍ አይቻልም ፤ በሃይማኖት ነው፡፡

መናፍቃንን በመለፍለፍ ወይም በስለላና በዱላ ማሸነፍ አይቻልም፡፡ ያውም እነርሱ ጫማ ስር ተደፍቶ!!! የቃለ እግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ለብሶ የመንፈስ ቅዱስ ሰይፈ ታጥቆ በቀናች በተዋሕዶ ሃይማኖት  ጸንቶ በምሳሌነት በመቆም እንጂ ማንኛውም ስጋዊ ስልት ወይም ጉልበት በባለቤቱ የተወገዘ ነው፡፡ እግዚአብሔር አይፈተንም እግዚአብሔርንም ከመፈታተን የከፋ ኃጥያት የለም፡፡ አልፎ መሰጠት ያልታሰበ አደጋ ላይ መውደቅ ያስከትላል፡፡ በሰውኛ እርቅና መላቀስ መሸፋፈን በቤተክርስያኗና በሕዝበ ክርስቲያኑ ከመዘበት ተለይቶ አይታይም ፤ በነርሱ መዘላለፍ የተሰቀቀ ፤ ያዘነ ፤ ምዕመን ብዙ ነውና፡፡

ዕንቁ፡-  በተዋሕዶ እምነት መምህር የሚባለው እዴት ነው?
መምሕር ተስፋዬ፡- ሰው በመጽሐፍ ፤ በምዕራፍ ፤ በቁጥር የዘላለም ሕይወት ያለ ይመስለዋል፡፡ መጻሕፍት ግን ወልደ አብ ወልደ ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ በተዋሕዶ የባሕርይ አምላክ መሆኑን ይናገራሉ ተብሎ በዚያው በቅዱስ መጽሐፍ  ተጽፏል፡፡ ይህ ደግሞ ከኬንያ ለመጣው የክህደት እሳት ዋና ማገዶ አቅራቢ ናት ብለው ለሚያላግጡባት ይህች የኛይቱ የቀናች የተዋሕዶ ሐይማኖታችን አምልታ ፤ አስፍታ ፤ አብራርታ አስተምራለች፡፡ ከአራቱ ወንጌላት የተማረ ሌሎችንም የሥርዓት መጽሐፍት ያወቀ ፤ ከርዕይ የደረሰ ፤ ጣዕመ ጸጋ የቀመሰ ፤ መንፈሳዊ ሀብት ትምህርት ያለው ፤ ከመንፈስ ቅዱስ የተሰናበተ እንደሆነ ነገሩ ሰውን በእምነት ታጸናለችና መምህር ይሆናል፡፡ ዳግመኛም “መነኩሴ እኔ አባ ካለ ፤ ወታደር ከፎከረ ነገር ቀረ” እንደሚባለው ራሱን እኔ እኔ የሚል ሳይሆን ሥራው የሚመሰከርለት ፤ ንጽሕናውን |የጠበቀ ፤ ነገሩን እግዚአብሔር የሚያሰረዳለት  እንደሆነ እርሱ መምህር ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ምዕራና ቁጥር እያነበነበ በሕገ እዚአብሔር እያስፈራራ ሰው ከእግዚአብሔር መንገድ የሚያወጣ ሁሉ አመጸኛ ነው ፤ የሚሰሙትንም ያሳምጻል፡፡

ዕንቁ ፡- ሃይማኖተኛነትና መንፈሳዊነት ልዩነቱና አንድነቱ እንዴት ይገለጻል?
መምሕር ተስፋዬ፡- ሃይማኖተኛ ሆነ ሲባል የቅድስት ሥላሴ አንድት ሦስትነት ፤ የጌታችንና የመድኃኒታችንን የባሕርይ አምላክነት ፤ የመስቀሉን ኃያልነት አመነ ማለት ነው፡፡ መንፈሳዊነት ደግሞ ይኽው ሃይማኖቱ የሚያዘውሥርዓት ጸንቶ ኖረ ማለት ነው፡፡


ምንጭ፡- ዕንቁ መጽሔት

5 comments:

  1. በእርግጥ ቤተ-ክርስቲያናችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች አሉባት፡፡ ጽሑፉ ጥሩ ነው፡፡
    እነዚህ አባባሎች ግን ጥሩ አይመስሉኝም፡፡ ታስቦበት ይሁን፣ ዳኅፀ-ልሳን ይሁን፣ የተናጋሪው ይሁን የፀሐፊው እንጃ፡፡
    1. ሥልጣነ ክህነት የሚያላብስ ሊቀ-ጳጳስ አሁን በመንበር ላይ የለም- ማለት ምን ማለት ነው ? ታዲያ ይህ ሁሉ ካህን ስልጣን የለውም ማለት ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ እርስዎም መስቀል ይዘዋል፡፡ ስልጣኑን ከየት አገኙት ?
    ስልጣኑ አለ ወንድሜ፡፡ ችግሩ የስልጣኑ አይደለም፡፡ ጠመንጃ ይተኩሳል፤ አልሞ መመታት ግን የጠመንጃው ስራ አይደለም ፤የተኳሹ እንጂ፡፡ ኢላማውንም ጠመንጃው ሳተ አይባልም፡፡ ጠመንጃው እስካልከቸፈ ድረስ፡: ስልጣኑማ የማይከችፍ ጠመንጃ ነበር፡ ግን ማን ተኩሶ ኢላማ ይምታ፡፡ ታዲያ የተኳሹን ስሕተት ወደ ጠመንጃ ማዞር ጥሩ አይደለም፡፡
    2. ሊቅነት ከመንፈሳዊነት ተቃራኒ ነውስ እንዴት ይባላል ? ሊቅ ሁሉ መንፈሳዊ ላይሆን ይችላል ነገር ግን ሊቅ መሆን ማለት መንፈሳዊ አለመሆን ማለት አይደለም፡፡ ሊቅም መንፈሳዊም የሆኑ አባቶች አሁንም ቢሆን ስላሉ፡፡ እንዲህ ማለት እኮ ደንቆሮ መሆን መንፈሳዊነት መሆኑ ነው፡፡
    እንደዚህ አይነት ንግግሮች ደግሞ ለጸጉር ሰንጣቂዎች መንገድ መስጠት ይመስለኛል፡፡ አስተውለን ብንናገር ጥሩ ነው፡፡
    ሌላው አስተያየቴ ደግሞ መስቀሉን ስንይዝ እንደ አባቶቻችን አለባበሳችንም ቢመስል ጥሩ ነው(ቢያንስ ሜዲያ ላይ)፡፡ማንን ልንመስል ነው? ካልሆነ ከተሐድሶ የተሻልን አይመስለኝም፡፡
    ዲ/ን ፍሥሐ ነኝ - ባሕር ዳር

    ReplyDelete
  2. "ከመንፈስ ቅዱስ የተሰናበተ እንደሆነ ነገሩ ሰውን በእምነት ታጸናለችና መምህር ይሆናል።" እንዴት ነው ነገሩ መንፈስ ቅዱስ የሌለው እንዴት
    መምህር ይሆናል እንዴት በእምነት ያጸናል ።እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ።የታይፕ ስህተት ከሆነ ይታረም።የመምህር ተስፋዬ አስተያየት ከሆነ ግን በጣም ያሳዝናል የምትናገሩትን ማንን እንመን ጥሩ ጀምራችሁ ታንሻፍፉታላችሁ።

    ReplyDelete
  3. thank you so much Deacon Fisha ! you said all what I wanna say ! Thomas GMaryam too

    ReplyDelete
  4. ትክክል ነው፡፡ የሰልስቱ ምእልት ድንጋጌ ተሽሮ፣ ምህላ ተሽሮ፣ ፍትሃ ነገስቱ ቀርቶ ከሩማንያ በተቀዳ ቃለ አዋዲ ቤተክርስትያን እየተመራች ስለሆነ ሊቀ ጳጳሱም ሆነ ጳጳሱ ስልጣነ ክህነት ሊሰጥ ስልጣን የለውም፡፡ እርሱ ራሱ በሰልስቱ ምእልት ግዝት የታሰረ ነው፡፡
    ኢትዮጵያ በፍትሃ ነገስቱ የህግ ሲኖዶስ የላትም፡፡ አንድ መንበር ነው በሃገረ ስብከት ደረጃ ያላት፡፡ ለዛም መንበር ሊቀ ጳጳስ ከማርቆስ መንበር ከስክንድርያ ነው ተሾሞ የሚመጣላት፡፡ እርሱም ለራሱ ይከብራል እንጂ ሌላውን ጳጳስ አድርጎ ማክበር ስልጣን የለውም፡፡
    በዛ ላይ ሊቀ ጳጳስ ወ ፓትሪያርክ የሚል ሹመት ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ ስለዚህ ሊቀ ጳጳሱም ሆነ ጳጳሱ ስልጣነ ክህነት ሊሰጥ ስልጣን የለም የሚለው መግለጫ ትክክል ነው ብዬ እቀበላለው፡፡

    ReplyDelete