Wednesday, December 11, 2013

“ይቅርታ አድርጉልን ?” :- የቤተ ክህነቱ ተቋማዊ ድቀት ምስክሮች ስልተ ነገር


 •  ‹‹በነበረው ሒደት በተለያየ ምክንያት ለበደላችኹን ሁሉ ይቅርታ አድርገንላችኋል ፤ እናንተም ይቅርታ አድርጉ ›› በጋሻው ደሳለኝ ባለፈው እሁድ በሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳምምእመናን ያደረገው ንግግር
 • በአንድ  የቅዱስ ሲኖዱስ ምልዐት ጉባኤ ውሳኔ  ሊያበቃ የሚችልን ጉዳይ አንዲትዘማሪት›  እስክትገባ መፍቀድ  ትልቋን ቤተ ክርስቲያንን  አይመጥንም
 • ልጆቹ እኮ ምስጢረ ሥላሴን “ሥላሴ አትበሉእያሉና ምስጢረ ሥጋዌን ”…ክርሰቶስና ዲያብሎስ ቁማር ተጫወቱ…” እያሉ አላግጠው ነበር፡፡
 • የይቅርታው ሒደት ቀኖናዊ ነው የሚለው ተገቢ ቢሆንም የመንፈሳዊ እና አሰተዳደራዊ ቀውሱን ተራራ  እንደማይንደው ጥርጥር የለውም ፡፡ ቀውሱ  ይቅርታ አድርጉልንይጠልቃል ፤ ይረዝማልም ፡፡


 • እንዲህ ያለ ዜና ከሰሞኑን ሰማን፡፡ አንዱ "የበቃ" ከየት መጣ ሳይባል ድንገት ሲያውከው ሲያተራምሰው በከረመው መድረክ ብቅ ብሎ እንዲህ ተናገረ መባሉን ሰማን፡፡ "ለበደላችሁኝ ሁሉ ይቅር ብያችኋለሁ"፡፡ እንደዚህ ያለ "የበቃ" ሰው በ፳፩ኛው ክፍለ ዘመን ያላት አሮጊቷ ሣራ መሆኗም አይደል፡፡ ተበድሎ ይቅር ማለት እንዲህ ነው እንጂi  ታዲያ እንዲህ ያለውን በበር እንጂ ለምን በጓሮ ተሞከረ? ለመሆኑ ከበር በስተቀር ቤተ ክርስቲያን ሌላ መግቢያ አላት? ምነው በጓሮ ተሞከረችሳ! ….......................................................(/ አባይነህ ካሴ).......
 (በጽጌ ማርያም)
(አንድ አድርገን ታህሳስ 02 2006 ዓ.ም)፡- በቅርቡ የበጋሻው  ደሳለኝ እና የያሬድ አደመ ቀኖናዊ ያልሆነ ይቅርታ አድርጉልን ?”እግረ ጉዞ ለብዙዎች የመነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል፡፡የይቅርታ አድርጉልን ?”ሒደትም የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ እንደማይሆንም በራሳቸውይቅርታ አድርጉልን ?”በሚሉት እና ከቤተ ክርስቲያን አውጥተውእምነ ጽዮንየስደተኞች ማኀበር በሚል በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መስመርነት በሐዋሳ ከአደራጆት ቡድናቸው ጋር መከፋፈላቸውም ገላጭ እሆነ ነው፡፡ይህ ቀኖናዊ አግባቦችን  አላሟላም የሚባለው ይቅርታ አድርጉልን ?”እግረ ጉዞ   ያስከተለው መለስተኛ ውዝግብ በልጆቹ ብቻ አልተወሰነም፡፡ደዌው ተዛምቶ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆችንም አምሶ ነበር፡፡አሁንም ቢሆን ( በመሠረቱ) የጉዳዬን ማዕከላዊ ጭብጥ እና መነሻ አድበስብሶ የሚያልፍ ከመሆን የታደገው ያገኘ አይመስልም፡፡


ይቅርታ አድርጉልን ?” እግረ ጉዞ ላይ የሚነሡትን ክርክሮች ወይም አሳቦች በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ አንደኛው በይቅርታ በራሱ ተፈጥሯዊ ምንነትና ትርጉም ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ ይቅርታ ምንድ ነው? ውግዘት ምንድ ነው? በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ፣ በቀኖና ድንጋጌዎችና ትውፊትስ ያለው ቦታ ምንድ ነው? የማዉገዝ ምክንያቶች ምንድ ናቸው? መናፍቃን የሚወገዙት እንዴት ነው? እንዴትስ ይመለሳሉ? የሚሉትን ጥቄዎች በመመለስ ላይ የሚሽከረከሩ ናቸው፡፡ ይህ ክርክር ዕውቀት ሰጪነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በግልብ ምሁራዊነት (pseudo intellectualism) የተጣበበ መሆኑንም መደበቅ አይቻልም፡፡ በዚህም ምክንያት ከስልት አኳያ ዕውቀት ሰጪነቱ ጎጂ ባይሆንም በቀጥታይቅርታ አድርጉልን ?”የሚሉትን ልጆች  ወይም የሐዋሳውን አፈንጋጭ ስብስብ በአድራሻ ገላጭ አይደለም፡፡ሁለተኛው ይቅርታ አድርጉልንባዬቹ ትእምርታዊ(symbolic) ትርጉም ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ይህ ምልክታ በአብዛኛውውጫዊበተለይም ፖለትካዊ፣ ክልላዊነትና ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ዘውጌነት የሚጫነው ነው፡፡የይቅርታ አድርጉልን ውዝግብ ከጥቅስ እና ከቀኖና ክርክር ለጥጦ በመመልክት አገራዊ እና ምዕመን ዐቀፍ ገጽታ ለመስጠት በመሞከር የተሻለ ነው፡፡
ሆኖም ዞሮ ዞሮ ማጠንጠኛው በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አስተምህሮ አድራሽ ፈረስነት በአንድም ሆነ በሌላ ስማቸው በተደጋጋሚ በሚነሳው በጋሻው ደሳለኝ እና ያሬድ አደመ ግፋ ሲል ደግሞ የሐዋሳው አፈንጋጭ ቡድን ብቻ ስለሆኑ የክርክሩ መጨረሻ እየጠበበ ሔዶ የአንድ ቡድን አባላት ጉዳይ ይሆናል፡፡ክርክሮቹ  ጠፍተው ግን በተነሳኂ ልቡና ያልተመለሱትን ልጆችን ቀኖናዊ ድርጊት ከትምህርት፣ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ከቤተ ክርስቲን ታሪክ እና ሲለጥቅም ከይቅርታ መርሕ አንጻር ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ ይቅርታ ተባይን፣ይቅር ባይንና ይቅር አባባይን በጋራ ያወግዛሉ፡፡

በሁለቱም የክርክር ዘውግ የተሰለፉ ወገኖችየይቅርታ አድርጉልንእግረ ጉዞ ቢቆም የክርክራቸውን አጀንዳ ዘግተው ወደ ተለመደው ኑሮ ለመመለስ ብዙ ጊዜ አይፈጅባቸው ይሆናል፡፡ግፈ ቢል ደግሞ ሌላ የያሬድ-በጋሻው እና በዙርያቸው የተሰበሰቡ ተጧሪዘማሪያንና ሰባክያንየሚፈጽሟቸውን ነጠላ ድርጊቶች እያነሡ በተመሳሳይ የክርክር እና የውግዘት አዙሪት ይጠመዳሉ፡፡የእነዚህ ልጆች የአስተሳሰብ ተጋሪዎችም በፊናቸው’’ ከቤተ ክርሰቲያን ይልቅ ሁሉ ለእነርሱ፤ሁሉ በእነርሱበሚለው ኦርቶዶክሳዊ ባልሆነው መርሕ ስር ጉዟቸውን ይቀጥላሉ፡፡አሁን የታየውም ይኸው ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገሪቱ ማኀበረ-ፖለቲካ ታሪክ እና ባህላዊ ማንነት ውስጥ ከነበራትና ከአላት ሚና አንጻርየይቅርታ አድርጉልን ሆነ ሌላ ውዝግብ ሰፊ ትኩረት ቢስብ የሚገርም አይሆንም፡፡ሆኖም ግን ትኩረቱ በተሳሳተ ዒላማ ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ሁለቱም የአተያይ አቅጣጫዎች አንድምከይቅርታ አድርጉልንጀርባ ያለውን አስፈሪና አሳፋሪ የቤተ ክነቱን ውሰጣዊ እውነታ ለመጋፈጥ የሚያስችል ብቃት አጥተው የመከኑ ናቸው፡፡አንድም ግላዊ የገንዘብ፣የዝና፣የፖለቲካና የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ዘውጌነት ወዘተ.ፍላጉት ለሟሟላት ሰልፉን የተቀላቀሉ ናቸው፡፡

ለአለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት እና ከዚያም ለሚበልጡት ዘመናት ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሚነሡት ውዝግቦች መሠረታዊውን ችግር እያድበሰበሱ በእንጭፍጫፊ ጉዳዩች ላይ ጉልበት የሚያስጨርሱ ናቸው፡፡የዚህ አንዱ ምክንያት ችግሩን ከምንጩ እና ከምልክቱ ለይቶ የሚመለከት፤ከዚያው በመነሳትም መሠረታዊ ምላሽ ለመስጠት የሚያችል አቀራረብ መጥፋቱ ነው፡፡ቤተ ክርስቲያኒቱን በበላይነት ይመራታል የሚባለው ሲኖዶስም ሆነ እንቆረቆራለን የሚሉት ወገኖች በአብዛኛው እነዚህ ነገሮች አምታታው የሚመለከቱ ናቸው፡፡ግራ ተጋብተው ግራ የሚያጋቡ ናቸው፡፡ተቆርቋሪነትን በመግለጽ ብቻ የአደባባይ ውዳሴ ከማግበስበስ አልፈው የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረታዊ ችግር በሁለንታዊ ለመረዳትም ሆነ ለመፍታት የማይችሎ ሆነው ቆይተዋል፡፡

ይቅርታ አድርጉልንእግረ ጉዞ ምሳሌነት ቁምነገሩን እንመልከተው፡፡ በእኔ አስተያየት ቀኖናዊነት በጉደለው አግባብ እነዚህ ልጆች ይቅርታ አድርጉልንማለታቸው የሌላ ጥልቅ በሽታ ምልክት እንጂ ራሱን የቻለ በሽታ እይደለም፡፡ በቤተ ክህነቱ ሕይውት ያለው ተቋማዊ እና መንፈሳዊ ሚዛን ቢኖር ኖሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ የተያዘን የሃይማኖት ጉዳይ አንዲት ዘማሪ በወኔ ተነስታ በይቅርታ ጠይቁ ለመዳኘት ባልተነሣች ነበር፡፡ ልጆቹም ትናት በስብከታችው ፣ በመጸሐፋቸውና በመዝሙር ግጥማቸውና ዜማቸው  ያጉደፉትን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ድግሞ በይቅርታ ሽፋን ዳግም ለማጉደፍና ጉዳዬን የጭቅጭቅ  ጉዳይ ተደርጉ እንዲታይ ለማድረግ ባልደፈሩ ነበር፡ ፡ቢበዛ በአንድ የቅዱስ ሲኖዱስ ምልዐት ጉባኤ ውሳኔ ሊያበቃ የሚችልን ጉዳይ አንዲትዘማሪት›  እስክትገባ መፍቀድ  ትልቋን ቤተ ክርስቲያን አይመጥንም፡፡መቼ ይሆን ትልቋ ቤተ ክርስቲያናችን ከወይዛዝርት አተራማሾቿ ነጻ የምትሆነው ያስብላል፡፡

ይቅርታ አድርጉልንከሚለው ጥያቄ የበለጠው አሳሳቢ ሊሆን ይገባ የነበረው የቤተ ክህነቱን ሕይወት አልባ መዋቅር ታከውና በኢ ቀኖናዊ መንገድይቅርታ አድርጉልንእናይቅርታ አድርጉላቸውለማለት ያስቻሉትና ያነሳሱት መንፈሳዊ ፣ማኀበረ-ፖለቲካዊና ምጣኔ ሀብታዊ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ህልውናም አስጊው ይኸው ነው፡፡

በርግጥ ቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ፣ ማኀበራዊ/አገራዊ እና አስተዳደራዊ ሐላፊነቷን ሚዛኗን ሳትስት (ጠብቃ) እንድትጓዝ  የሚያስችላት ተቋማዊ እና ሕሊናዊ  ልጓም ከተሰባበረ ሰንብቷል፡፡ አለ ከተባለም ያለው በቅዱሳት መጻሕፍት ፣ በቀናዒ ምዕመናን ፣ በእውነተኞቹ መናንያን እና በጥቂት አገልጋዩች ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቤተ ክህነቱን ከተዘፈቀበት መንፈሳዊ እና ተቋማዊ ክስረት የማውጣት አቅምም ተልእኮም ሊሸከም የሚችል አካል አይደለም፡፡ ይህ መሆኑ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አስተሳሰብ አድራሽ ፈረስ ናቸው ለሚባሉትናይቅርታ አድርጉልንባዮች ተጋላጭነቱን አስፍቶታል፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ  ለስሙ ቤተ ክህነት  የሚባል ተቋማዊ ቅርጽ እንዳላት ከመነገሩ በቀር በሕጉና በሥርዐቱ የሚሠራ ነገር ባለመኖሩ ከሕግ አግባብ ውጪ ይቅርታ አድርጉልንእናይቅርታ አድርጉላቸውተብላ መጠየቋ አያስገርምም፡ ፡እንደውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ሕይወት መሥራት ቀርቶ መተንፈስ ከማይችልበት ደረጃ ለመድረሱ ማሳያ ሆኑ ሊያገለግል ይችል ይሆናል፡፡ ሥርዐቱ ሁሉንም ተቋማት የእርሱ ተራ ሎሌዎች እስኪሆኑ መቆጣጠር እንደሚፈልገው ሁሉ ቤተ ክህነቱን ወይ በቁም እንዲሞት ተደርጓል አለዚያም ለእንዲህ ዐይነቶቹ አፈንጋጮች ከለላ በሚሆኑ ተላላኪዎች እንዲሞላ ተደርጓል፡፡

ብዙዎችን እነዚህ ልጆች በዘማሪቷ ትከሻ ታዝለውይቅርታ አድርጉልንማለታቸው  ግራ አጋብቷል፡፡ ግን ከዚህ የባሳ ስንት ነገር መፈጸሙን እያወቅን ይቅርታ አድርጉልንጉዳይ እንደማሳያ ካልሆነ እንደ ቁልፍ ችግር ባይቀርብ በወደድኩ ነበር፡፡ ልጆቹ እኮ ምስጢረ ሥላሴን “ሥላሴ አትበሉእያሉና ምስጢረ ሥጋዌን ”…ክርሰቶስና ዲያብሎስ ቁማር ተጫወቱ…” እያሉ አላግጠው ነበር፡፡ አሁን በያዙት መንገድ ከዚህ የከፋ ኑፋቄ ሊዘሩ እንደሚችሉ መጠበቅ የበለጠ ብልህነት ነው፡፡

ስለዚህይቅርታ አድርጉልንጉዳይ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረታዊ  ችግር አስመስሎ ማቅርብም ሆነ በዚሁ ላይ ጉልበትን መጨረስ ዒላማውን የሳተ  ተኩስ ነው፡፡ ከዚያ ይለቅ የኑፋቄውን መንገድ ለመረጡት ለእነዚህ ልጆችም ሆነ የእነዚሁ የኑፋቄ ሞግዚት ለሆነው ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኮር ኀይል ወደብ ሆኑ የሚያገለግለውን  በቤተ ክህነቱ አመራረ እና በቤተ ክርስቲያኒቱ  ዙሪያ ለዘመናት የተጋገረውን የቀውስ ተራራ በድፍረት መመልከቱ ለቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ ለአገሪቱ ይጠቅማል፡፡ራስን ከመዋሸትም ያድናል፡፡የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረታዊ ችግር የመንፈሳዊ እና አስተዳደራዊ  ድቀት ነው፡፡ይህ ካልተፈታ ግን ከቀኖና ቤተ ክርስተያን ውጭ በቀላጤ ደብዳቤ ውጉዛኑን እነ ጽጌ ስጦታውን በዐውደ ምህረታችን ልናይ እንችላለን፡፡

በርግጥ አሁን ቤተ ክርስቲያኒቱን ተብትበው ያሰሯትና ሊገድሏትየሚተናነቋት ችግሮች የጊዜው የኑፋቄ አድራሽ ፈረስ የሆኑት ልጆች ወደ ዐውደ ምሕረቱ ከመምጣታቸው በፊት የነበሩ ናቸው፡፡ ከእነርሱም በኃላ ይቅጥል ይሆናል፡፡ ነገር ግን እነርሱ የተጓዙባቸው የጥፋት መንገዶችና ሌሎች ከባቢያዊ ሆኔታዎች (ፖለቲካዊ ፣ ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች) ችግሮቹን ለማመን በሚያስቸግር መጠንና ስፋት አባብሰዋቸዋል፡፡ ከ1997 . ወዲህ ቀንደኛ  የቀውሱ አካል መሆናቸው የሚያከራክር ባይሆንም ብቸኛው ተጠያቂ ማድርግ ግን አይቻልም፡፡ የይቅርታው ሒደት ቀኖናዊ ነው የሚለው ተገቢ ቢሆንም የመንፈሳዊ እና አሰተዳደራዊ ቀውሱን ተራራ  እንደማይንደው ጥርጥር የለውም ፡፡ቀውሱ ይቅርታ አድርጉልንይጠልቃል፤ ይረዝማልም፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ ካለችበት ቀውስ አንጻር  አሁን የሚያስፈልጋት ጥልቅ ራስን የምር የመፈተሸ  ቁርጠኝነት ነው፡፡የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተምህሮዎች፣ትውፊትና ታሪክ የጠበቀና የሚጠብቅ የመንፈሳዊ እና ተቋማዊ ለውጥ አብዬት ሊያመጣ የሚችል ራስን የመፈተሸ ተጋድሎ ከሰሞነኛውም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በእጅጉ ይጠበቃል ፡፡እርቅ የሚያስፈልገው ተጋድሎ እርሱ እንጂ ለስልትይቅርታ አድርጉልንከሚለው የጥፋት ኀይል ጋር አይመስለኝም ፡፡ይህ የተዳፈነው የለውጥ አብዬት ከየት ይነሣል፣እነማን ያነሡታል፣እንዴትና እንደምን ተጀምሮ በምን ይጠቃለላል ይሆን የሚሎት ጥያቄዎች ቀላል መልስ የላቸውም፡፡

እንደ እኔ እስከዚያው ግን ቢያንስ ለቤተ ክህነቱ ድቀት ምስክር ይሆኑ ዘንድ ይቅርታ አድርጉልንኀይል ባለበት ይቆይ፡፡እነዚህ ልጆች ይቅርታውን የጠየቁት ከሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ይዘውት የወጡት ጥቂት ስብስብ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መስመራዊነት ተመዝግቡ ለመንቀሳቀስ የሚያደርገው ተጨባጭ እንቅስቃሴ ይቅርታ አድርጉልንባዮቹን ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ዘውጌነት  ተጨባች ሰለሚያደርግ  እና እንዳያገለግሎ ያደረጋቸውን ዕግድ በይቅርታ ለመፍታት ብቻ ነው፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ ከአካለዊ ዕገዳ እንጂ ከመንፈስ ዕገዳ አይላቀቁም፡፡

አሁን ባለንበት ሁኔታ የልጆቹ ይቅርታ  በቀጥታ ግለሰቦችን የሚመለከት ፣ ግፋ ቢል ቤተ ክርስቲያኒቱን ከድቀት ሊታደጉ ከማይችሉ ኀይሎች ጋር የሚደረግ እርቅና ትእምርታዊ ትውስታ ከመሆን የዘለለ ፋይዳ ካለው ለመረዳት ዝግጆ ነኝ፡፡ ልጆቹ በዚህ ይቅርታ አድርጉልንሒደት ውስጥ ሆነው  እንኳን የሚያደርጓቸው ነገሮች ለይቅርታ የተገቡና የበቁ  ናቸው ለማለት የሚያስችል አይደለም፡፡ እውነተኛ ይቅርታ ለመስጠትም እንደዚያው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ይቅርታ አባባዩቹም ያሉበትን ሁኔታም መረዳት ይገባል፡፡ በቅድሚያ ምንም ቢሆን  ሙከራቸውን አልነቅፍም፤ እንዲሳካላቸውም እመኛሉ፡፡ ከዚያ ውጭ ግን እነርሱም ቢሆኑ ያለባቸው ሸክም ከባድ ነው፡፡ የይቅርታ ምክንያት ለመሆን እውነተኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ይህ ቢያስቸግር እንኳን ተደርጉ መቆጠርን ይጠይቃል፡፡ ይህ ደግሞ በተግባር እንጂ ከአሜሪካ በመምጣት ፣ ልብስን በማሳመርና ጥቅስ በመጥቀስ የሚገኘ ጸጋ አይደለም፡፡

ከዚህ አንጻር ይቅር አባባዩቹ ሰለይቅርታ አድርጉልንባዬቹ በእውነትና ያለአድሎልዎ ሲናገሩ ተሰምተው አያውቁም፡፡ስለዚህ ከመንፈስና ከሞራል ልዕልና አኳያ ካየነው በእኛ በተራዎቹ ምዕመናን ዐይን እነርሱም ይቅርታን ለማምጣት ገና የበቁ ሆነው አይታዩም፡፡እንደዚህም ሆኑ ግን ይህ ሙከራቸው  በራሱ ወደ ምንናፍቀው  የቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ አሐቲነት ደረጃ የሚሸጋገሩበት አጋጣሚ እንዲሆንላቸው እመኛለው፡፡

አጋጣሚዎቹ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተጥሏል/አልተጣሰም ውዝግብን ተከትሎ የተፈጠሩትን ቁስሎች እና መሰሎቻቸውን ማከም በተገባ ነበር ፡፡አሁንም መዋቅራዊ አሐቲነትን ለማምጣት እና መጥፎ ስሜቶችን ሊያስቀር የሚችል ኦርቶዶክሳዊ እርቅ በአባቶቻችን መካከል ማምጣት ያስፈልጋል፡፡አልረፈደም፡፡ድርጊቱ ግለሰባዊ መልክ ያለው ላይሆን ይችላል፡፡ነገር ግን በእርቅና በፍቅር መንፈስ ሊታከሙ የሚገባቸው ስሜቶች አሉ፡፡የቤት ሥራው የሁሉም ወገን ነው፡፡መንግስትንም ሆነ ተቀዋሚውንም ጭምር፡፡እርቅ ሕሊናና ልብ በአንድነት ቆርጠው ካልገቡበት እና እግረ ጉዞ ብቻ ከሆነ የማይደረስበት ልዕልና ነውና፡፡

ከዚህ አኳያም ሆነ አስቀድሚ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ለልጆቹ ይቅርታ መደረጉ የሚኖረው ፋይዳ ለመመዘን የሚያስቸግር መስሎ ይታያል፡፡በግሌ አጋጣሚው ሰለጉዳዩ እንድንነጋገር ከማድረግ አልፎ ቤተ ክርስቲያን ዐቀፍም ሆነ አገራዊ ፋይዳ ይኖረዋል ብዬ አላምንም፡፡ምክንያቱም ይቅርታው ዛሬ ባለው በቤተ ክርስቲያኒቱ ተጨባጭ ሁኔታ ላይ የሚያስከትለው ተጨባጭ ውጤት አይኖርም፡፡

ከዚህ በተረፈ እኔም ይቅርታ ቢደረግላቸው  ችግር የለብኝም፡፡ከዚህ ባለፈ ግን ይቅር ተባዬቹ፣ይቅር አባባዬቹና ይቅር ባዬቹ በተመሳሳይ የመንፈስ ደረጃ ያሉ አይመስለኝም፡፡የይቅረታ ወሬውም ከሰብአዊ አዘኔታ ባሻገር የኦርቶዶክሳዊ የይቅርታ መሠረቶችን  እና ፋይዳቸውን ገና አንስቶ አልጨረሰም፡፡እናም ለይቅርታ በተሻለ ደረጃ የተገቡ ያደርጋቸዋል የሚል ተስፋ የለኝም፡፡ከዚህ አኳያ ጉዳዩንም ሆነ ልጆቹን የቤተ ክህነቱ የተቋማዊ ለውጡ ድቀት ምስክሮች  ወቅታዊ ስልት አድርገን ብንገነዘብ እላለሁ፡፡
ምንጭ፡- ዕንቁ መጽሔት

4 comments:

 1. Hulunm yemiasmama qulf hasab hono yagegnehut: mesretawi chigirun neaw, le betekrstean beteley tenkara ye betekihnet mewakir alemenoru neaw. Yechigirochu hulu meseret:: yeh sile ene begashaw guday seta geba ketejemerebet gize jemiro le hizbu yalewn chigir lemasawek yetewesedu akahedoch, yemasawekia mengedoch, mizanawinetu,... Simet yebezaw neberna ahunm Simet libezabet gid yemilew yemeslegnal. Ke Abatoch eske Meamenu gira yagaba, eyagaba yale, yekefafele,.... Lemin? Kejimiru yeneberew mizanawinet ena erasun chilo be gilts Bete kihnet sirawn yalemesrat,.. . Hulu degafi hulu awgazz hulu sim awchi hulum... . Lelaw meseretawi chigrachin Menfesawinet: seaw yawm ende kirstianinetachin Amlakachinin kidmia adrgenew simetachinin, filagotachinin, ewketachinin.. Le Ersu asalfen kalseten endet linsmama enchilalen? ahun yemitayew emnet yalew astesaseb ena eytawoch sayhon alemawi maninet eko neaw huletu sinodos andd yehun sibal kaltewnewn endet linsmama yechalal? Hulum yemeselewn, yemisegawn, yelemedewn, yeyazewn, yeyazewn melkek( metew) ayfelgim! Metekommm bicha! Endet seaw yestekakelal? bistekakelm yemitekumbet, yemisalekibet, elh wust yemiasgebaw, yemiatatlew.. Ale! bistekakelm eyemnlewn enatalen wey?? babzagnaw agelgay simet ena agul kinatun makom yegebawal alebelezia sinodosu andach sayl ers berasachin 'menafk' 'tehadiso' 'yatfachu' 'tebye' 'maq' 'weyzero' Yeminbabal kehone nege firee silalew esun metebek neaw, Le kutr bemitakt melku yekefaflenal..yamenemnenal, lemanim aytekimim Beteley ende ene Yemahibere Kidusan abalatoch ena ye Begashaw abalatoch YEMITWERAWERUTN DINGAY AQUMU! Beminim memezegna minim honachu min ende ene chigirachu zare yemawkew aydelemna sile betekrstean bilachu beteley AGUL SIMETAWINETACHUN akumu! le ene yegebagn ye begu teretim yehnin chigr neaw yasayegn... bekfat manefnef yebka be mehal le nege yebase gize atfteru( EYANDANDACHU ENE!!! YALE ENE!!! Yemil Kinat endalachu yegebagnal yerasachu guday!...ahun ene sile bete kirsteane tekorkure wendim ena ehitochen endih lil yegebagnal tilalachu? beftsum!!!) . Ke jimiru sirat yalew(formal) awekakesochn alayehum ahunm endi aynetun wetet metebek yalseranewn endemetebek yemeslegnal. Meseretun yeminastekakilbet lay mebertatu yeteshale neaw, ke basew lemetebek yehe yalfal! kifatun ena simetawinetin anaberetata! sewochn anashemak, chigrachewn agulten nege simm lemawtat kenege besteam lememeles ena bebego lemayt endikebden ayhun, gena legena sera alew eyaln andemdim, sihtetoch alu! sihitetin bicha eyekoraretin anawta, hulum agelgay gar chigir endale ena hulum maninetu yeteleyaye endehone ye egnam eyta endemiagadil enastewl..lefird yemiaschegirewm chigiru saygeban ena Abatoch sayredut aydelem eytawochachin lay chigir silale yemeslegnal. asteyayet ena agelaletsachin sistekakel yetgnawm yebetekrstean agelgay weynm meamen ke tesasate gar ayhonm goltom yewetal. Chigir anhun derejachininm metebek ena memamarm yelmedibn kewch yalew aysalekibnm tananashochm talakakochin yakebraluna. Egziabhear yelibn yayal seaw gin... Hulun yastekakilewal, be maymesil neger hulu des yemil neger alew, liatenekiren lihon yechlalna tesfa ankuret alem lay neaw yalenew, nurowachin(tiglachin) ende tswami yehun..

  ReplyDelete
  Replies
  1. wondim or ehit kalehiwotin yasemalin endihm aynet amelekaket yalew sew kale minim anilim ...realy realy

   Delete
 2. ena yemigermegn sinodosu bicha new sew siletenagerew kerbo masredat kalchale chigr ale mallet new so............

  ReplyDelete
 3. አንድአድርጉን
  የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው፡ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
  በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል ጠብ እንዲፈጠር በመጄመሪያ ምክንያት የሆነው ፍጥረት ሰይጣን ነው። ይህ ጠብ ኋጢአትን በማድርግና ሕግጋትን በመጣስ ተጄመረ። ስለሆነም ሰዎችን ከታላቁ የቅድስና ሥፍራ የለያቸው የጠብ ግድግዳ በመካከል ቆመ። ይህም መጋረጃው ነው። ዕብ 9፡3 ይህንንም የጠብ መጋረጃ ለማውረድ በእምነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መግባት አስፈላጊ ሆኖ ተገኘ። ዕብ 10፡19 የሚያስታርቁ ሰዎች በሰውና ሰላምን ሊፈጥሩ የሚያስታርቋቸውን ሰዎች ወደ እምነትና ወደ ንሰሃ ስለሚመራችው ለጌታ ያዘጋጇቸዋል። ይህን በተመለከተ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል" በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ሰለክርስቶስ መልክተኞች ነን። ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።" 2ኛ ቆሮ 5፡18 እግዚአብሔር በንስሃ የሚመለሱትን ሲምር አይዘልፋቸውም አይሰድባቸውምም። በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 15 ውስጥ ሦስት በንስሃ የተመለሱትን ሰዎች መቀበሉን እንመለከታለን። እነዚህም ሰለጠፋውና ስለባከነው ልጅ፧ ስለጠፋው ድሪምና ስለጠፋው በግ የተገለጹት ናቸው። በምዕራፉ ውስጥ እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ እነዚህን የጠፉትን እንደፈለጋቸውና ሲመለሱም ያለ አንዳች ትግሳጽ እንዴት ባለ ደስታ እንደተቀበላቸው እናነባለን። በተመሳሳይ መልኩ ጌታ ከትንሳኤው በኋላ ስምዖን ጴጥሮስን አግኝቶት ነበር። ይሁን እንጂ "ሰውየውን አላውቀውም" በማለት የከዳውን ክህደት አንሰቶ የጴጥሮስን ሰሜት ሊጎዳበት አልወደደም። ይልቁንም ወደ ቀድመው የክህነት ማዕረጉ መልሶ "ግልገሎቼን አሰማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጎቼንም አሰማራ" አለው እንጂ ዮሐ 21፡15 አንድአድርገን ምንአለ አንድ ቢያደርገን ። ሃዋሳ ላይ የነበርውን የእርቀሰላም ሂደት በተመለከተ እውነቱ እናንተ ባላችሁት ሳይሆን ምመኑም በደስታ የተቀበሉት ሲሆን እናንተ እውነቱን ሸሻችሁ።"

  ReplyDelete