Thursday, December 5, 2013

ቤተክርስትያኗ ከሳውዲ ለተመለሱት ኢትዮጵያውያን 2 ሚሊዮን ብር እርዳታ እንደምትሰጥ ገለፀች


(ኢሬቴድ ኅዳር 25 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ከሳውዲ አረቢያ ለተመለሱት ኢትዮጵያውያን የሁለት ሚሊዮን ብር ጊዚያዊ እርዳታ እንደምትሰጥ አስታወቀች፡፡ ብፁእ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትሪያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሀይማኖት በቀጣይም ቤተ ክርስትያኗ እርዳታዋን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡
ቅዱስ ፓትሪያሪኩ ከእኛ የሚጠበቀው የእንኳን ደህና መጣቹህ ማለት ወይም በመንፈሳዊ አስተምህሮ ማፅናናትና መርዳት ብቻ ሳይሆን መልሰው እስኪቋቋሙ ድረስ መርዳት ግዴታችን ነው ብለዋል፡፡ፓትርያርኩ እንደገለፁት ይህ የወገኖቻችን እርዳታ ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ወቅታዊ አጀንዳ መሆኑን በመግለፅ እስካሁን በመንግሥት በኩል እየተደረገ ያለውን የተቀናጀ አቀባበል በአካል በመጎብኘታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው ለወደፊቱም  ተመሳይ እርዳታ ለማድረግና አባታዊ ምክር ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸው ተናግረዋል፡፡ መንግስት ብቻውን የስደተኞች ወገኖቻችን ምግብና መጠለያ አይችልም ያሉት ተሰብሳቢዎቹ ለወደፊቱ በተቀናጀ መልኩ እርዳታ በማሰባሰብ የወገኖቻችን ህይወት እንዲስተካከል ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡
 ምንጭ፡-የቤተክርስትያኗ የኮሚኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት

2 comments:

  1. Great job, at least to receive and well come by the Church the helpless Ethiopians and further rehabilitation is very important.

    ReplyDelete
  2. Yehe new kekrstiyan yemitebekew ,betam des yeilal

    ReplyDelete