Wednesday, May 8, 2013

በቡሌ ሆራ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን እንድትፈርስ መታዘዙ ቁጣን ቀሰቀሰ


(ኢትዮ-ምህዳር ጋዜጣ ሚያዚያ 29 2005 ዓ.ም)፡-  በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቦረና ዞን ቡሌ ሆራ(ሀገረ ማርያም) ከተማ የምትገኝው ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን እንድትፈርስ መታዘዙ በአካባቢዋ ቁጣ መቀስቀሱ ታወቀ፡፡ የአካባቢ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያ አማኞች  ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት “የከተማዋ ከንቲባ ኃላፊነት በጎደለው እና በማን አለብኝነት ቤተክርስቲያኑን አፍርሰው ቦታውን ለባለሀብት ለመሸጥ መወሰናቸው ለሃይማኖቱም ሆነ ለሕዝቡ ያላቸውን ንቀት ያሳዩበት ነው” ሲሉ አውግዘዋል፡፡የአካባቢው ነዋሪዎች አሁን የወሰዱት አቋም ሲገልጹ ‹‹የከተማው ከንቲባ  በድፍረት ቤተክርስያኑን አፍርሰው እንጨትና ቆርቆሮውን እንድናነሳ አዘዋል ፤ እኛም የእግዚአብሔርን ቤት አናፈርስም ፤ እሳቸው ከፈለጉ በሚፈልጉት ኃይል ሊያፈርሱ ይችላሉ  ፤ ለወረዳው አስተዳደር አመልክተን የወረዳው አስዳዳሪ በቦታው በመገኝት ተመልክተውልናል፡፡ ቤተክርስቲያ እንዳይፈርስ የሚያስችለውን ውሳኔ ይሰጣሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አስተያየት ሰጪዎቹ በመጨረሻ እንደተናገሩት በዚሁ ከተማ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ያለ ሲሆን ይህን ቤተክርስቲያን  ካለፈው መንግሥት ጀምሮ  በከተማው ማስተር ፕላን መሰረት ፍቃድና ካርታ አለው ፤ ይሁን እንጂ እኚህ የከተማው ከንቲባ ቦታውንና ከቦታው ላይ ያለውን ባሕር ዛፍ አላስረከብንም ብለው ችግር ፈጥረውብን እስከ አሁን ድረስ ችግሩ ባልተፈታበት ሁኔታ እንደገና አሁን ደግሞ ፊታቸውን ወደ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን መዞራቸው አግራሞትን ፈጥሮብናል ብለዋል፡፡ የከተማው ከንቲባ አቶ ቡሉ ገመዳ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው እና በጽ/ቤታቸው ስልክ ለማግኝት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡
ኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ ሚያዚያ 29 ቀን 2005 ዓ.ም

5 comments:

  1. The Angry Ethiopian/ቆሽቱ የበገነውMay 8, 2013 at 12:26 PM

    አንድ ሀቅ አለ። ይኼም ሀቅ ወያኔ ከገባ ጀምሮ አገሪቱን ሲገዛት የከረመው የጴንጤና የእስላም ሀይል ነው። ጴንጤው በፈረንጆቹ ዕገዛ የበለጠ በለስ ቀናው። እስላሙም ከጌታው ጋር አሁን የሻከረ ግንኙነት ያለው ቢመስልም እንዲሁ ለይስሙላ ነው። ወያኔ በዐረብ ጉያ ውስጥ ዕስካለ ድረስ ምንም አቅም የለውም። የወያኔ አቅም የኢትዮጵያኖች አንድነት ማጣት ብቻ ነው - በተለይ የአማራው። የነ ዳንኤል ክብረት አይነት አሽቃባጮች "አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም ዓይነት" ነገሮች ናቸው።

    ReplyDelete
    Replies
    1. Why Daniel here? Pls focus on the point!

      Delete
    2. Andande geza ke andebetachen yemiwetan kale benetebeke melkam new. Poletican ke Betekerestiyan atekelaklu. Sew yegelu yehone akuam linoreq yechelal. Sedebe ayegebam. Yehen sele tadeya abatochachen yakoyulen kirse siyatefu zem enebel maleta ayedelem yelekunem ende Nabuta enkume enjii. kerestiyan ena mekera ayetetatum. Enetsena ena Betekerestiyanachenen enetebeke.

      Delete
    3. The Angry Ethiopian/ቆሽቱ የበገነውMay 14, 2013 at 8:24 AM

      People who say Politics and religion does not go together, You need to wake up. Andeargen why didn't you publish my previous reply to anonymous. I'm the last person you want to block.

      Delete
  2. እነዚህ ሰዎች ዝም ብለን ካየናቸው ገና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ከሀገር ይውጣ ማለታቸው አይቀርም ስለዚህ ነገ ዛሬ ሳንል ትግልም ከሆነ መታገል አለብን የእምነት ነፃነታችን እስኪረጋገጥ::

    ReplyDelete