ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com
ከጽሁፉ የተወሰደ
- የዚህ መመሪያ ግብም እንደመመሪያው አርቃቂዎች እምነት የእምነት ተቋማቱን እግዚአብሔር (ፈጣሪ) ከሚባለው ምናባዊ ነገር እንዲራራቁና እንዲረሳሱ በማድረግ የእነሱ ጉዳይ ፈጻሚዎችና አምላኪዎች እንዲሆኑ በማድረግ ሊፈጥሯት የሚፈልጓትን ከማንነቷ ፣ከታሪኳ ፣ከመለያዎቿ ተለያየችና የተካካደች አዲስ ሀገርና ሕዝብ መፍጠር ነው፡፡
- ስናያቸው ኢትዮጵያዊያን ይመስላሉ ወይም ናቸው ምን ነው ታዲያ በገዛ ማንነታቸው ላይ የጥፋት ዘመቻ ላይ መጠመዳቸው? ምን የሚሉት በሽታ ነው ይሄ? ይሄን ሁሉ ጉድ እውን የራስ ዜጋ ያደርገዋል ብሎ ማሰብ እንዴት ይቻላል?
- የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያዊነት መገለጫ እና መለያ ናትና፡፡ የኢትዮጵያዊነት መገለጫዎችን፣እሴቶችን ጠልቶ ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት አይቻልም ፤ይህች ቤተክርስቲያን ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ከራሷ አልፋ ለመላው ዓለም የዋለችው ቁም ነገር ሁሉ እጅግ ብዙና ውለታን ለሚያስብ ኅሊናም ላለው የሰው ፍጡር ሁሉ ውለታዋ ከክብደቱ የተነሣ የሚያስጨንቅና ዕረፍት የሚነሳ ነው
- ኢትዮጵያ ሃይማኖት ከየትም አልመጣላትም፡፡ የመጣለት ነገር ቢኖር ኪዳናቱ ብቻ ናቸው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢትዮጵያ ከመቼ ጀምሮ በእግዚአብሔር እንዳመነች አልተገለጸም፡፡ የሚታወቀው ነገር ቢኖር ከቀደሙት የቀደምን መሆናችን ብቻ ነው፡፡
(አንድ አድርን ግንቦት 5
2005 ዓ.ም)፡- መሰንበቻውን የፌዴራል ጉዳዮች ሚንስቴር የእምነት ተቋማትን ለመመዝገብ (ለመቆጣጠር) አንድ መመሪያ ማውጣቱና እያነጋገረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ መመሪያ የተረቀቀውና ተግባራዊ ሊደረግ ታስቦ የነበረው በተመሳሳይ ዓላማና አንቀጾች በተለያዩ ሰብአዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሰማርተው ይሠሩ የነበሩትን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን (NGOs) ያሽመደመደው ፣ መፈናፈኛ ያሳጣውና ከአገልግሎት ውጪ ያደረገው ደንብ ወይም መመሪያ ወጥቶና ተግባራዊ ሆኖ ለዓላማቸው አመርቂ ውጤት እንዳስመዘገበላቸው ባወቁ ጊዜ ነበር፡፡ ይህንን ውጤት በማየትም በተመሳሳይ መልኩ ደንቡን ወይም መመሪያውን በሃይማኖት ተቋማትም እንዲፈጸም ቢያደርጉ የልባቸው ሊደርስ እንደሚችል እምነት አሳድረው በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ በመሀሉ ያልታሰቡ ሁለት የሞት አደጋዎች በመከሰታቸው እስከአሁን ሊቆይ ቻለ፡፡ አሁን ቀጥታ ወደ መመሪያው ዝርዝር ጉዳዮች ገብቼ ይሄ ይሄ ከማለቴ በፊት ለዚህና መሰል የቤተክርስቲያንን ጥቅም ለሚጋፉ መመሪያዎች መውጣትና መተግበር መሠረት ወደ ሆነው የተሳሳተ አስተሳሰብ ተመልሼ ጥቂት ብል ነገሩን በሚገባ ግልጽ ያደርገዋልና መለስ አድርጌ ልያዛቹህ፡፡
አንድ አሠሪ ለሠራተኛ በወር ክፍያ ሊከፍል ተዋውሎ ሥራውን ሲያሠራ ይቆያል በሥራው ላይም ተሠማርቶ በትጋት ደፋ ቀና ይል የነበረው አንድ ሠራተኛ ብቻ ነበር፡፡ የተቀሩት ሠራተኞት ነን ባዮች ወሩ ሊያልቅ ሳምንት ሲቀር በመንጠባጠብ ተቀላቀሉት፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ቀዳሚው ሠራተኛ በትጋት ሊሠሩ ይቅርና ጭራሽም ሥራቸው የተሠራውን ማፍረስና ማበላሸት ሆነ ፤ በወሩ መጨረሻ ቀን ላይ ግን አሠሪው ሰው ባልታወቀ ሁኔታ ከምኑም ነገሩ ሳይቆጥብና ሳይሳሳ በትጋት ደፋ ቀና ይል ለነበረው ሠራተኛ የተሠራውን ሲያፈርሱና ሲያበላሹ ከነበሩትና በወሩ መጨረሻ ሳምንት ላይ እየተንጠባጠቡ ከመጡት “ሠራተኞች” ጋር እኩል ከፈለው፡፡ ይህ አሠሪ ብልህና አስተዋይ አሠሪ ነው? አከፋፈሉስ ትክክለኛ ፍትሐዊና ተቀባይነት ያለው አከፋፈል ነው? በቀጣዩ ወርስ ለዚህ አሠሪ ሥራውን በትጋት የሚሠራለት ሠራተኛ ይገኛልን?
ይህ ግፍና በደል በሀገራችን አሁን በሥልጣን ላይ ባለው “መንግሥት” ተፈጽሟል እንደሚታወቀው ይሄ “መንግሥት”እንደ ሐሳቡ የዲሞክራሲያዊ (የበይነሕዝባዊ) አስተዳደር ሞዴሉ (አርዓያው) የአሜሪካ ዲሞክራሲ (በይነ ሕዝብ) ነበር፡፡ እንግዲህ ችግሩ ያለው እዚህ ላይ ነው በአሜሪካ አገባብ አውድ (Context) የሃይማኖት እኩልነት ሥርዓት መስፈኑ ትክክለኛና አማራጭ ያልነበረው ነው፡፡ ምክንያቱም በዚያች ሀገር ከሌሎቹ ተነጥሎ ቀድሞ በመገኘት ዋጋ የከፈለ ለሀገሪቱ ህልውናና ሥልጣኔ የደከመ ሃይማኖት አልነበረምና ሁሉም የገቡት በስደት በተመሳሳይ ወቅት ነውና፡፡ በመሆኑም እኩል መብት እንዲኖራቸው መዳረጉ ትክክለኛና አማራጭም ያልነበረው ውሳኔ ነበር፡፡ ወደ አውሮፓ ስንመለስ ግን ነገሩ ከዚህ የተለየ ነው፡፡ በርካቶቹ ዲሞክራሲ (በይነ ሕዝብ) የሰፈነባቸው የአውሮፓ ሀገራት ብሔራዊ ሃይማኖት ያላቸው ናቸው፡፡ በአንዳንዶቹ ኦርቶዶክስ በሌሎቹ ካቶሊክ በከፊሎቹ ፕሮቴስታንት፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በየ ሀገራቸው ቀድሞ በመገኘት ለሕዝቡና ለሀገር ህልውና የደከመ የለፋውን ምንም እንዳላደረገ ቆጥሮ ዛሬ ላይ 15 ሆነው ከሚመሠረቱት የእምነት ተቋማት ጋር እኩል መቁጠር ኢፍትሐዊነት እንደሆነ በሚገባ ያውቃሉና፡፡ የኛ ‹‹መሪዎች›› ዲሞክራሲና (በይነሕዝብና) ፍትሐዊነት ያላቸው ቁርኝትና ዝምድና የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ያህል ሊነጣጠሉ የማይችሉ መሆኑን መረዳት ስለተሳናቸው ፍትሐዊነትንና በይነ ሕዝብን (ዲሞክራሲን) ሊነጣጥሉ ቻሉ፡፡ በመሆኑም ከመጀመሪያው ቀን ጀምራ ያለማሰለስ ለዚህች ሀገርና ሕዝብ ከነጻነቷ እስከ ሥልጣኔዋ ድረስ በብቸኝነት በከፍተኛ ትጋት ጻዕርና ጋዕር ስትለፋ ስትደክም የኖረችውን የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን በሕገ መንግሥታቸው ድንጋጌ መሠረት 15 ሰዎች ሆነው የሆነ ስም ሰጥተው ዛሬና ነገም ከሚመሠረቱት የእምነት ድርጅቶች ጋር እኩል ናት፡፡በማለትና በማድረግም ከባድ የድንቁርና ሥራ ሊሠሩ ቻሉ፡፡
እምነቱ ምንም ይሁን ማሰብ የሚችል ጭንቅላት ያለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ የዚህን ድርጊት ኢፍትሐዊነት መረዳት ይቸግረዋል ብዬ አልገምትም፡፡ ፍትሕ ወይም ፍትሐዊነት የዲሞክራሲ(የበይነሕዝብ) የጀርባ አጥንት ነው፡፡ ያለ ፍትሕ ዲሞክራሲን ማሰብ ጨርሶ የሚቻልነገር አይደለም፡፡ ምንም እንኳ እያልነው ያለነው ነገር ይሄው ቢሆንም፡፡እናም ኢ-ፍትሐዊነት ኢ-ሚዛናዊነት፣ በደል የአንባገነን እንጅ የዲሞክራሲ (የበይነሕዝብ) ምሰሶዎች ሊሆኑ አይችሉም አይገባምም፡፡
እንግዲህ ይህ መሠረተ አስተሳሰብ ነው፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን 15 ሰዎች ሆነው ዛሬ ነገም ከሚመሠረቱት የቃልቻም ይሁን የባዕድ አምልኮ ወይም የሌላ በእምነት ስም ከሚቋቋሙ የእምነት ድርጅቶች፣ በሀገሪቱ ሥልጣኔና ሌሎች ጸጋዎች ላይ አስተዋጽኦ ከሌላቸውና ካልነበራቸው ከማይኖራቸውም ፣ ለሀገሪቱና ለሕዝቡ ህልውናና ነጻነት ኢምንት ዋጋ ካልከፈሉ ጋር እኩል መብትና ዕውቅና እንዲኖራት ያደረጉትና አሁን ደግሞ ተመዝግበሽ ካልተቆጣጠርሽ እንዲሉ ያበቃቸው፡፡ ልቦና ቢኖረን እውነትም ብንነጋገር ይህች ሀገር ካሏት ኩራቶች፣ የሥልጣኔ ፍሬዎች ፣ መታወቂያ መገለጫዎች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያልሆነ ምን አለ? የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከሀገራችንም አልፋ ለስንት ሀገራት ስንት ነገር እንዳበረከተች የማይታወቅ የተሰወረ ሆኖ ነውን? ይህች ቤተክርስቲያን መላው ዓለም ዛሬ ለደረሰበት የአስተሳሰብ ብስለትና የቴክኖሎጂ (የኪነብጀታ) እድገት ከፍተኛና የማይተካ አስተዋጽኦ አበርክታለች፡፡አሁን ይሄ ይሄ ብሎ መዘርዘር መጽሐፍ መጻፍ ነው የሚሆነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ይከፈለኝ ብትል አይደለም የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም መንግሥታት እንኳ ሊከፍሉ ይችላሉን? ለዚህ ሊከፈል ለማይቻለው ውለታዋስ ሊከፈላት የሚገባው ወረታ ፈጽሞ ይሄ አልነበረም፡፡ ኧረ የልብ ያለህ! እናንተ ምን ይሻላል? ስናያቸው ኢትዮጵያዊያን ይመስላሉ ወይም ናቸው ምን ነው ታዲያ በገዛ ማንነታቸው ላይ የጥፋት ዘመቻ ላይ መጠመዳቸው? ምን የሚሉት በሽታ ነው ይሄ? ይሄን ሁሉ ጉድ እውን የራስ ዜጋ ያደርገዋል ብሎ ማሰብ እንዴት ይቻላል? ይህ መመሪያ ኃላፊነት ከሚሰማውና ጥቅሙ ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም ጋር ከሚቃረን ሳይሆን ከሚስማማ ከሚጣጣም መንግሥት የወጣና ቀደምም ያለ ቢሆን ኖሮ ማንነታችንን ለማጥፋት የራሳቸውን ጥቅምና ዓላማ ለማስጠበቅ ለማስፈጸምም ከባድ ገንዘብ እያፈሰሱ ከገጠር እስከከተማ በተደራጁ በእርዳታና በማባባያ ጥቃቅን የልማት ሥራዎች እየተታለለ እምነቱንና ማንነቱን እንዲክድ የተደረገውንና በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ሩቡን የሕዝባችንን ቁጥር ያሳጣንን እምነት መሰል የምዕራባዊያንን የጥፋት ድርጅቶች የጥፋት ዘመቻን መከላከልና መቋቋምም ባስቻለን ነበር፡፡
አሁን ያለንበት ሁኔታ ግን የተበሉብንን ወይም የተማረኩብንን ዜጎች በመመሪያ የምንመልስበትና እነሱ በኢትዮጵያና በኢትየጵያዊነት ላይ የጋረጡትን አደጋ የምንቀለብስበት ሳይሆን ዋጋ የምንከፍልበት ጊዜ ነው፡፡ ልዑል እግዚአብሔር በፈቀደው መንገድ በተአምሩ ይታደገን እንጅ፡፡ ነገር ግን አስቀድመው እነዚህን ድርጅቶች ለዚህ ያበቃቸውን ምቹ ሁኔታ ከፈጠሩና ሁለት ዐሥርት ዓመታት ካለፉ በኋላ በመመሪያ ለመቆጣጠር ማሰቡ ለቡድን ህልውና በመሥጋት ካልሆነ በስተቀር ለሕዝብና ለሀገር ህልውና በመሥጋት ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም መመሪያው አግባብነት በሌለውና እንግዳ በሆነ ሁኔታ ጨርሶ ለሀገርና ለሕዝብ ህልውና ሥጋት ያልሆነችን ቤተ ክርስቲያን አካቷልና፡፡
እንደሚታወቀው በተለይ እንደዚህ ዓይነት ሥራ ሲሠራ የራሱ የሆነ ዓላማና ግብ ይኖረዋል የዚህ መመሪያ ዓላማና ግብም ፡-
1. ለቤተክርስቲያን (ለሃይማኖት) አስተምህሮዋን ጠብቃ ለመቀጠል የግድ የሚለውን የተማከለ አስተዳደር በማፈራረስ ጥንካሬ እንዳይኖራት አድርጎ ልክ በምዕራቡ ዓለም በተመሳሳይ አሠራር አንድ የነበሩት ተፈረካክሰው እንደ አሸን እንደፈሉትና በየቀኑ እንደሚፈሉት ሁሉ ቤተክርስቲያናችንንም ለመፈረካከስ ለመበታተን የታለመ ነው፡፡
2. ፓርቲው ጥቅሜ የሚለውን ነገር ለማስጠበቅ የእምነት ተቋማቱን በገዛ ገንዘባቸው ለራሱ ቀጥሮ የራሱ ቡድናዊ ጥቅም አገልጋዮች ለማድረግ፡፡
3. እዛው መመሪያው ላይ በግልጽ እንደሠፈረው የእምነት ተቋማቱ ግዴታዎች በሚለው ርእስ ሥር ዓይን ባወጣና የእምነት ተቋማቱን መንፈሳዊ ግዴታ ጨርሶ ግንዛቤ ውስጥ ባላስገባ መልኩ ፓርቲው የሕልውናዬ አደጋ ናቸው ከሚላቸው ማናቸውም ነገሮች ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳያደርጉ ከልክሎ ሃይማኖቶቹን እንደየእምነታቸው ከአምላክ የተሰጣቸውን መንፈሳዊ፣ ሞራላዊ (ግብረገባዊ)እና ሰብአዊ ግዴታዎቻቸውን እንዳይወጡ በማገድ መገልገያ እቃው ማድረግ ነው፡፡
የዚህ መመሪያ ግብም እንደመመሪያው አርቃቂዎች እምነት የእምነት ተቋማቱን እግዚአብሔር (ፈጣሪ) ከሚባለው ምናባዊ ነገር እንዲራራቁና እንዲረሳሱ በማድረግ የእነሱ ጉዳይ ፈጻሚዎችና አምላኪዎች እንዲሆኑ በማድረግ ሊፈጥሯት የሚፈልጓትን ከማንነቷ ፣ከታሪኳ ፣ከመለያዎቿ ተለያየችና የተካካደች አዲስ ሀገርና ሕዝብ መፍጠር ነው፡፡
ይህች ቤተክርስቲያን በዚህች ሀገር የተገኘችው ለዚህችም ሀገር መጣር መድከም የጀመረችው 2000 ዓመታት ብቻ አይደለም፡፡ የሀገራችንም ታሪክ የ3ሺ ዓመታት ታሪክ የሚባለውም ስሕተት ነው 3ሺ ዓመታት የሚባለው ሰሎሞናዊው ሥርዎመንግሥት ከመጀመሩ ወዲህ ያለው ዘመን ብቻ ነው ከዚያ በፊት 74 ነገሥታት ኢትዮጵያን አስተዳድረዋል፡፡ ቤተክርስቲያንም ስሟ ወደ ቤተክርስቲያንነት ከመለወጡ በፊት ቤተምኩራብ ትባል በነበረበት ጊዜና ቤተምኩራብም ከመባሏ በፊት ባጠቃላይ ከክርስቶስ ልደት በፊት ለ3300 ዓመታት በላይ ይህችን ሀገር እንደ ኦሪቱ ሥርዓት መንግሥት መሥርታ ነገሥታትን ቀብታ ከማንገሥ ጀምሮ ዜጎችን በሥነ ምግባርና በጥበብ አንፃና አስተምራ የበቃ ዜጋ እስከማድረግ ድረስ ይህችን ሀገርና ሕዝብ ስታገለግል ቆይታለች ከክርስቶስ ልደት በኋላም በሐዲሱ ኪዳን መሠረት ቤተክርስቲያን ከተባለች በኋላም ይሄው እስከ ዛሬ ለ2005 ዓመታት ያህል እያገለገለች ትገኛለች ባጠቃላይም 5305 ዓመታት በላይ አገልግሎት ስትሰጥ ኖራለች፡፡
ብዙ ጊዜ በስሕተት ሲነገር የምሰማው ነገር አለ ፤ ሃይማኖት ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ንግሥተ ሳባ ወደ ኢየሩሳሌም ከመሄዷ ጋር ተያይዞ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ነው የሚል፡፡ ኢትዮጵያ ሃይማኖት ከየትም አልመጣላትም፡፡ የመጣለት ነገር ቢኖር ኪዳናቱ ብቻ ናቸው፡፡ ሃይማኖት ማለት የእግዚአብሔርን የፈጣሪን ማንነት በትክክል ዐውቆና ተረድቶ እሱን ማምለክ ለእሱም መገዛት ማለት ነው፡፡ አምልኮተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ ተቋርጦ አያውቅም በኢትዮጵያ ያለው ሃይማኖት ከአዳም ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣና ሳይቋረጥ የኖረ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሊቀ ነቢያት ሙሴ ኢትዮጵያዊቷን ሊያገባ የቻለው፡፡ ወንድሙ አሮን እና እኅቱ ማርያምም ሙሴ ኢትዮጵያዊቷን በማግባቱ ‹‹እግዚአብሔር በእኛ ብቻ ተናግሯልን በእሱም የተናገረ አይደለምን?›› ብለው አጉረመረሙ፡፡ የእስራኤል ልጆች ከዘራቸው ውጪ ከአሕዛብ ወገን ጋር እንዳይጋቡ እንዳይዋለዱ በእግዚአብሔር ተከልክለው ነበርና፡፡ ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያዊያን እንደሌላው ሕዝብ ከአሕዛብ ወገን ሳንሆን ከሕዝብ ወገን ነንና በመሆኑም የሙሴና የሲፓራ ጋብቻ በእግዚአብሔር ዘንድ አልተጠላም አልተነቀፈም፡፡ እንዲያውም ሳይገባቸው አጉረምርመው የነበሩት እኅቱ ማርያም እና ወንድሙ አሮን በማጉረምረማቸው በእግዚአብሔር ተቀጡ ዘኁ. 12 ፤1-15 / ዘጸ. 2፣16-22 ፡፡ ወደ ኋላ ላይ ነገሩ ማለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕዝበ እግዚአብሔር መሆኑ በደንብ ግልጽ ሆኖ ተጽፏል፡፡ ለምሳሌ በትንቢተ አሞድ 9-7 ላይ እግዚአብሔር የተናገረውን ብናይ ጭራሽ እንዲያውም እኛ የኢትዮጵያ ልጆች በኩራት ነን ከሚሉት ከእስራኤል ልጆች ይልቅ በእግዚአብሔር የተወደድንና የከበርን ሆነን እናገኘዋለን፡፡ ቃሉ እንደሚለው ‹‹የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር ›› በማለት እግዚአብሔር የእስራኤል ልጆችን ልክ እንደ እኛ አድርጎ እንደሚያያቸው ከ እኛ አሳንሶ እንደማያያቸው እነሱን በማጽናናት መናገሩ ተጽፏል፡፡ እንግዲህ የእኛ ማንነት በእግዚአብሔር ፊት የተገለጸውን ያህል ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢትዮጵያ ከመቼ ጀምሮ በእግዚአብሔር እንዳመነች አልተገለጸም፡፡ የሚታወቀው ነገር ቢኖር ከቀደሙት የቀደምን መሆናችን ብቻ ነው፡፡
ሕዝበ እስራኤልን ከእግዚአብሔር ጋር ያስተዋወቃቸው አብርሃም እንደሆነ ይታወቃል፡፡ አብርሃምን የባረከውና አብርሃምም ዐሥራትን ያወጣለት የእግዚአብሔር ካህን መልከጸዴቅ ግን ኢትዮጵያዊ ነበረ ወይም ነው፡፡ የእሱ ትውልድ አልተገለጸም በምን ታወቀ ቢሉ በስሙ፡፡ የመልከጸዴቅ ስም በየትኛውም የዓለማችን ቋንቋ በተጻፈ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉ ብታዩ ተቸግረውም ቢሆን የሚያስቀምጡት ያው ራሱ መልከጸዴቅ የሚለውን ነው፡፡ ይህ ስም የግእዝ ስም ነው፡፡ ለሌሎች ቋንቋዎች ግን ይህ ቃል ወይም ስም ባዕድ ነው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ መልከጸዴቅ ሲናገር የስሙ ትርጓሜ በመጀመሪያ የጽድቅ ንጉሥ ነው፡፡ በኋላ ደግሞ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉሥ ነው ብሎ በቋንቋቸው ተርጉሞ ለወገኖቹ በመልእክቱ አስረድቷል፡፡ በተጨማሪም እናትና አባት የትምልድም ቁጥር የሉትም ብሎታል፡፡ ይህን ማለቱ ሰው አይደለም ለማለት ሳይሆን በአይሁድ መጽሐፍ ወይም የትውልድ ሃረግ ስሙ የለም አልተጠቀሰም ማለቱ እንጅ፡፡ ያልተጠቀሰበትም ምክንያት አይሁድ ባለመሆኑ ነው ይህንንም እዚያው ላይ ገልጾታል፡፡ እንጅ ሥልጣነ ካህነቱና ክብሩማ የሱን የሚያህል ማን ነበር ? እንዲያውም የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ብሎም ይጠራዋል፡፡ ለዘመኑ ጥንት ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም ሲል ሞቶ እንደሆነም የሞተበት ቀንና እድሜ አይታወቅም ማለቱ ነው፡፡ ዕብ. 7፣1-3 በመሆኑም እግዚአብሔርን በማምለክ ከእስራኤላዊያንም እንቀድማለን ማለት ነው፡፡
እናም ይህች ቤተክርስቲያን በቀጥታና በተዘዋዋሪም እስራኤላዊያንን ሕዝበ እግዚአብሔር እንዲሆኑ ከፍተኛ ሚና መጫወቷን መረዳት ይቻላል፡፡ እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ ብቻም ሳይሆን የሕዝብ አስተዳደር ሥርዓትንና ሕግንም ጭምር ለእስራኤላዊያን አስተምራለች፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ በእግዚአብሔር ተመርጦ ሕዝቡን ከግብጽ አውጥቶ እየመራ ወደ ምድረ ርሥት በሚወስድበት ወቅት ሕዝቡን ማስተዳደር መዳኘት ለሕዝቡና ለራሱም አስቸጋሪና አድካሚ ሆኖ ነበር፡፡ አማቱ ኢትዮጵያዊው ካህን ዮቶር ወይም ራጉኤል ይህ ሙሴ እያደረገ ያለው ነገር ትክክል ያልሆነና ለሕዝቡም ለራሱም አድካሚና ሥራ አስፈቺ መሆኑን አስረድቶ ከሕዝቡ የነቁ የበቁትን ሰዎች እንዲመርጥ ከእነሱም የሺ የመቶ የሃምሳ የዐሥር አለቆችን እንዲሾምላቸውና በሕዝቡ ላይ እንዲፈርዱ እንዲዳኙ አውራውንና የሚከብዳቸውን ብቻ ወደ አንተ ያምጡ ብሎ መክሮ በዚያ መሠረት በአንድ በሙሴ ብቻ ሙሉ ቀን ሥራ ፈተው ሲዋትቱ የነበሩበትን አሠራር ቀይሮ የተሳለጠና ምቹ የአስተዳደር ሥርዓት እንደሠራላቸው ይህም አሠራር ዛሬ ለመላው ዓለም ሁሉ ተዳርሶ እነሆ እየተጠቀመበት እንዳለ መረዳት ይቻላል፡፡ ዘጸ. 18፣13-27 እንግዲህ ይህች ቤተክርስቲያን ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ከራሷ አልፋ ለመላው ዓለም የዋለችው ቁም ነገር ሁሉ እጅግ ብዙና ውለታን ለሚያስብ ኅሊናም ላለው የሰው ፍጡር ሁሉ ውለታዋ ከክብደቱ የተነሣ የሚያስጨንቅና ዕረፍት የሚነሳ ነው ፡፡ ይህች ቤተክርስቲያን (ቤተምኩራብ) ለዚህች ሀገር ሁለንተና መሠረትና ባለ አደራም ናት ፡፡ በነገሥታቱ ዘመን ይሄ ታውቆላት ማንም የማይጋራት የማይጋፋት ክብርና ሞገስ እንዲሁም ካላት ሚናና አስተዋጽኦ አንጻር በቂ ባይሆንም ሲሦ መንግሥትም ሁሉ ነበራት ፡፡ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ዛሬ ላይ የድካም ዋጋዋ የነበረው ያ ሁሉ ክብርና ሞገስ ሥልጣንም ተገፎ ጭራሽ ዛሬና ነገም 15 ሰዎች ብቻ ይዞ ከሚመሠረት የምንም ዓይነት የእምነት ድርጅት ጋር እኩል ተደርጋ እንድትቆጠር ተደረገ ፡፡
በዚህ የሚደሰት የሌላ ‹‹ሃይማኖት›› ተከታይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ካለ ማስተዋል የጎደለውና ንክ እራሱን ለማጥፋት ፈንጅ የታጠቀ እንደሆነ ልነግረው እወዳለሁ ፡፡ ዛሬ በብዛት የሚርመሰመሰውና ኢትዮጵያዊያኑን የተቀራመተው የእምነት ድርጅት ሁሉ ትላንት አልነበሩም፡፡ ትላንት የነበረችው ሁሉም እንደሚያውቀው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ብቻ ናት፡፡ ዛሬ ከዚህች ቤተክርስቲያን ውጪ ሆነው የሚቃወሟት ዜጎች አባቶቻቸውና አያቶቻቸው ቆራጥ የቤተክርስቲያን ምእመን (ክርስቲያኖች) የነበሩ ናቸው፡፡ በታሪክ አጋጣሚ በተከሰቱ የጥፋት ጦርነቶች በሰይፍ እና በተለያዩ ችግሮች በተፈጠሩ ክፍተቶች ‹‹ የእሳት ልጅ አመድ እንዲሉ›› ዛሬ የነሱ ልጆች ከበረት ወጥተው ወይም ተማርከው ከባዕዳን በረት ታጉረው የማንነት መገለጫቸውን እናት ቤተክርስቲያናቸውን የገዛ ሀብታቸውን ቤታቸውን የሚፃረሩ የሚዋጉ የሚቃወሙ ለመሆን በቁ፡፡ ጥቂት መቶ ዓመታትን ብቻ ወደ ኋላ ብንመለስ ግን አይደለም አሁን ኢትዮጵያ ብለን በምንጠራው ሀገር ይቅርና ሞቃዲሾ ላይ እንኳ ከሰባት በላይ አብያተ ክርስቲያናት እና ሕዝበ ክርስቲያን የነበርን ነበርን፡፡
ስለሆነም ሌላው ሁሉ ቢቀር እምነታቸው ምንም ቢሆን በኢትዮጵያዊነታቸው ብቻ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ሊያከብሩ ሊጠብቁ ሊንከባከቡ እንጂ በጠላት ዓይን ሊያዩ ጨርሶ የሚገባ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያዊነት መገለጫ እና መለያ ናትና፡፡ የኢትዮጵያዊነት መገለጫዎችን፣እሴቶችን ጠልቶ ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት ኢትዮጵያዊነትንም መግለጽ ጨርሶ አይቻልምና፡፡ ሌሎች መገለጫዎች የሌሎች ማለትም የባዕዳን እንጂ የኛ አይደለምና፡፡ የኛ ያልሆነው ደግሞ የኢትዮጵያዊነት መገለጫና ማንነት ሊሆን አይችልምና፡፡ ከዚህ ውጪ ማንነት፣ መለያ፣ መገለጫ ሊገለጽ የሚችልበት ሌላ አማራጭ ወይም ዕድል ከቶውንም የለም፡፡ የእኛ የእኛ ነው፡፡ የሌላው ደግሞ የሌሎች ነው አለቀ፡፡ ኢትዮጵያ በዓለማችን ካሉ ጥቂት የራሳቸው ማንነት እና መገለጫ ካላቸው ሀገሮች አንዷ ናት፡፡ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መገኘት ዕድለኛነት ነው፡፡ ላወቀውና አክብሮ ለያዘው፡፡ በመሆኑም ማንም ዜጋ እምነቱ ሌላ ቢሆንም ኢትዮጵያዊነቱ ግን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምን ግዴታና ኃላፊነት እንደጣለበት ሁሉም የሌላ ‹‹ሃይማኖት›› ተከታይ የሆነ ዜጋ ሁሉ በሚገባ ሊረዳው ይገባል፡፡
በሚያሳዝን ሁኔታ ከታሪካችን እንደምንረዳው ወንድሞቻችን ይሄንን ግዴታና ኃላፊነት ሳይረዱ ቀርተው የሚከተሉት እምነትና ያ እምነት የመጣበት ሀገር በሀገራችን ላይ ያለው የጥቅም ፍላጎት ባሳደረባቸው ተጽዕኖ እነኝህ ወንድሞቻችን ለገዛ ሀገራቸው መልካም ነገር ሊመኙና ሊውሉ አልቻሉም፡፡ በሚከተሉት እምነት ምክንያት ብቻ ከጠላት ጋር አብረው ተሰልፈው የገዛ ሀገራቸውንና ወገናቸውን አመቺ ሁኔታ ባገኙ ቁጥር በተለያዩ ጊዜያት የወጉ እንዳሉ ታሪካችን ይነግረናል፡፡ ሌሎኞቹ ደግሞ እስከ አሁን ተመሳሳይ ተግባር ለመፈጸም ዕድል ባያገኙም ባጠቃላይ ግን ለኢትዮጵያዊነትና ለማንነታችን ያላቸውና የሚያራምዱት ጥላቻ በግልጽ ይታወቃል፡፡ እነዚያ ባዕዳን ሰባኪዎቻቸው ወይም የእምነቶቻቸው መሪዎች እነኝህ ወንድሞቻችንን እንዴት ባለ አዚም ወይም ምትሐት ወርቅ የሆነ የገዛ ማንነታቸውን እንዲጠሉና እንዲክዱ ከአኩሪ ማንነታቸው ጋር እንዲቆራረጡ ሊያደርጓቸው እንደቻሉ ለእኔ ሊፈታልኝ ያልቻለ የዘወትር እንቆቅልሽ ነው፡፡ እነሱን ትዝብት ላይ ከጣላቸው አጋጣሚዎች አንዱን ብጠቅስ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት በየ አዳራሾቻቸው በአንድ ድምፅ የመንፈስ መልእክት ነው እያሉ “እኛ ሀገራችን በሰማይ ነው፣ ዜግነታችን ክርስትና ነው የማንም ወገን አይደለንም ከሥጋዊያን እርሾ ተጠበቁ እንዳትተባበሩ”ወዘተ. እያሉ ተከታዮቻቸውን በመስበካቸውና በዜግነታቸው ለሀገራቸው ሊያደርጉ የሚጠበቅባቸውን ነገር ሁሉ እንዳያደርጉ በመስበካቸው በወቅቱ መንግሥትን አስቆጥቶት በእነኝህ የእምነት መሪዎች ላይ የሥነ ሥርዓት እርምጃ የወሰደበት ሁኔታ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡
እነኝህ ሁለት ታሪካዊ መረጃዎች የሚያሳዩትና የሚናገሩት ጉዳይ አለ ሰዎቹ ወይም እምነቶቹ ለዚህች ሀገርና ሕዝብ በደባል የያዙትን ዓላማና አመለካከት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ማንነታቸውን ከሃይማኖታቸው ነጥለው ማየት ባለመቻላቸውና እምነታቸው የመጣበት ሀገር ለራሱ ዓላማ መጠቀሚያ እያደረጋቸው እንደሆነ ባለመረዳታቸው ነው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከመወለዱ በፊት በእናቱ ማኅፀን እያለ ገና ሀገሩ ኢትዮጵያ ማንነቱም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ግልጽ ነው ፤ እምነት ግን ከተወለደ በኋላ ከወደደና ከፈቀደ የሚከተለው ካልፈለገ የሚተወው በመሆኑ ሰዎች እዚህ ላይ ባይሳሳቱና ቢጠነቀቁ መልካም ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜ አልፎ አልፎ ለማየት እንደቻልነው ከእነዚህ ወንድሞቻችን ውስጥ እንዳንድ የገባቸው እምነትንና ማንነትን ነጣጥለው ለማየት የቻሉና እምነታቸው ሌላ ቢሆንም ማንነታቸውንና መለያቸውን ግን በተቻላቸው መጠን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ የተዋደቁ በጣት የሚቆጠሩ ዜጎች እንዳሉ ከታሪካችን ለመረዳት ይቻላል፡፡
ወደ መመሪያው ስመለስ ሚንስቴር መ/ቤቱ ወይም “መንግሥት” ይሄንን መመሪያ ፈጽሞ ሥራ ላይ ሊያውለው ከማይችልባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች 3ቱን ብቻ ጠቅሼ ልጨርስ፡፡
ወደ መመሪያው ስመለስ ሚንስቴር መ/ቤቱ ወይም “መንግሥት” ይሄንን መመሪያ ፈጽሞ ሥራ ላይ ሊያውለው ከማይችልባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች 3ቱን ብቻ ጠቅሼ ልጨርስ፡፡
1. የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እንዳሰበው ቤተክርስቲያን ዶግማዋንና ቀኖናዋን፣ሕግና ሥርዓቷን መሠረት እድርጋ የምትሠራቸውን መንፈሳዊ ሥራዎቿንና አገልግሎቶቿን ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ሕግ መመሪያ ወይም ደንብ ጋር ማግባባት ፣ማስማማት፣ ማዋሐድ፣ ፈጽሞ የማይቻለው ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም በግልጽ ማየት እንደሚቻለው የሁለቱም ርዕዮተ ዓለም (Ideology) መሠረተ እምነት እጅግ የተለያዩ የተራራቁ የማይስማሙ የሚቃረኑም ስለሆነ፡፡ ቤተክርስቲያን እያንዳንዱን መንፈሳዊ አገልግሎት ስትሠራ ለሚያምኑ እንጂ ለማያምኑ በዓይን የማይታየውን በጆሮ የማይደመጠውን የመንፈስ ቅዱስን ፈቃድና ፈጻሚነት መሠረት አድርጋ ሲሆን ለዚህም ደግሞ ማረጋገጫ ልትሰጥ አትችልም፡፡ የሚንስትር መ/ቤቱ ደግሞ በእጅ በሚጨበጥና በሚዳሰስ ሊረዳው በሚችለው አሠራርና ክወና ነው ማረጋገጫም ይፈልጋል በመሆኑም ሁለቱን አግባብቶ አንድ ሥራ መሥራት ፈጽሞ የማይታለም ነገር ነው፡፡
2. ‹‹ሞኝ አሉ ብልጥን አሸነፈው ምን ብሎ ቢሉ እምብኝ ብሎ›› እንደተባለው የሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ የቀረቡትን መከራከሪያ ነጥቦችና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን የፍትሕ ጥያቄ ወደ ጎን ትቶ ከአቋሙ የማይመለስ ከሆነ ደንቡን ወይም መመሪያውን ከእምነት ተቋማቱ ሕግጋትና ሥርዓት ጋር የሚቻሉትን ያህል ብቻ እንኳን ለማጣጣምና ለመዳኘት ተፈጻሚ ለማድረግ ቢያንስ የየእምነት ተቋማቱን መሪዎችና ‹‹ሊቃውንት›› ያህል ስለእየ እምነቶቹ አስተምህሮ እውቀትና መረዳት ሊኖረው ግድ ይላል፡፡ በመሆኑም ከቶውንም የማይታሰብና ፈጽሞ የማይቻል ነገር ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
3. የሚንስቴር መ/ቤቱ ሊያስጠብቀው በሚፈልገው የቡድን ጥቅም ሳቢያ የዚያን ሃይማኖት አምላካዊ ተልእኮ ሲያደናቅፍና መመሪያው እንደሚለው በቀላል መዘናጋቶች በሚፈጸሙ ትናንሽ መተላለፎች የዚያን ሃይማኖት ፈቃድ ሠርዞ ያንን ሃይማኖት መዝጋት እንደሚችል ማሰቡና መዘጋጀቱ አንድ ነገርን ይጠቁማል ይህ መመሪያ የተረቀቀው በእግዚአብሔር በማያምኑና እግዚአብሔርን በማይፈሩ ሰዎች መሆኑን፡፡ እርግጥ ነው ሁሉም ሃይማኖቶች በእግዚአብሔር የተፈቀዱ ወይም ተቀባይነት ያላቸው አይደሉም መጽሐፉም እንደሚለው እግዚአብሔር የሚያውቀውና ለሰው ልጆች የሰጠው አንድ ሃይማኖትን ብቻ ነው፡፡ ኤፌ4፡5 አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የሚኒስቴር መ/ቤቱ መዝግቤ በራሴ መንገድ እመራቸዋለሁ ከሚላቸው “ሃይማኖቶች” አንዱ ብቻ እግዚአብሔር የቆመለትና በእግዚአብሔር ጥበቃ የሚደረግለት ሃይማኖት ነው፡፡
የሚንስቴር መ/ቤቱ በትናንሽ የደንብ መተላለፍ ያችን እግዚአብሔር የቆመላትን አንዲት ሃይማኖት ፈቃዷን ሠርዥ እዘጋለሁ ሲልና በቡድን ጥቅም ሳቢያ ሐዋርያዊ ተልእኮዋን ሲያደናቅፍ እንግዲህ የሚጣላው ከጠባቂዋ ከኃይሉ እግዚአብሔር ጋር መሆኑንና ለዚህም አቅም ጨርሶ ሊኖራቸው እንደማይችል በቅስፈት እንደሚጠፋም ጨርሶ አልተረዱም ካለማመናቸው የተነሣ ይመስለኛል፡፡
በመሆኑም በእነኝህ ሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች የሚንስቴር መ/ቤቱ ጨርሶ የማይታለም ነገርን እንዳለመና ሊተገብረውም እንደማይችል መረዳት እንችላለን፡፡ ተስፋ ባላደርግም የሚንስቴር መ/ቤቱ ‹‹በመንግሥት›› ጭንቅላት አስቦና መክሮ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ለዚህ መመሪያ ተገዥ እንድትሆን ማሰቡ በተሳሳተ ግንዛቤ መሆኑን ተረድቶ ውሳኔውን እንዲቀለብስ እንደ ዜጋና እንደ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምእመን እጠይቃለሁ እለምናለሁ፡፡ መቸም ቤተክርስቲያን አባሪ ተባባሪ እንጅ ለመብቷ የሚከራከር የለም አይሆንም የሚል አስተዳደር (Active alert responsible and comitted administration) አስቀድሞ እንዳይኖራት በመደረጉ በምን ተአምር ከዚህ ጣጣ ልንወጣ እንደምንችል እግዚአብሔር ይወቀው፡፡ “መንግሥት” እንደሆነ ምንም ቢያደርግ ማንም ምንም እንደማይለው የተቋውሞ ምላሽ እንደማያጋጥመው የዘመኑ ሕዝበ ክርስቲያን ለሆዱ እንጅ ለአምላኩ እንደማይገዛ በተለያየ ጊዜ በቤተክርስቲያን ላይ ባደረሰው ጥቃትና በደል ጥፋት እስከቅርብ ጊዜው በዋልድባ ገዳም ላይ ባደረሰው ግፍ ጥፋትና ውድመት አይቶ አረጋግጧልና ማንንም ፈርቶ ወደ ኋላ ይላል ብዬ አልጠብቅም፡፡
ቸሩ መድኃኔዓለም እንደ ኃጢአታችን ሳይሆን እንደ ቸርነቱ ተመልክቶ የሀገራችንንና የቤተክርስቲያናችንን ክብርና ልዕልና ይመልስ ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን ይታደገን አሜን !!!
I beg you in the name of Ethiopian church to share it to Twitter and Facebook, to Email and Blog it . thank you
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com
Legek nesh eheti wenetegochun ye'geta agelegayoch sem eyekebu seyasadedu geta zem selachew betegesu melakam eyseru besloachew neber Egziabher senesa gen manem atezewemen yekdesuan agelagelegyochu sedet ena eneba end Abel Deme yechochal eko Amelak beseraw ayezebetebetem. tatikin eyaworu sewen ke'geta meneged yaswoctu woy ensu ayegebu woy sew aysegebu. becheresachew zemen ekenan wongel endemesebek bekalu kuch belo ensu wongele selemayaweku le'betekirseteyan yekenu etmesleachew yegeta yehonuten sekesu seyasekesesu seyasadedu hezebunem gera seyagabu yenoraleu. seyetan enekna yenesun yahel wonegel sesebek ayenadedem. ensu ge keseyetan yebelet yewongelu neger yemeyamachew yegeta sem yemeyasedenegetache nachew. lemanegnawem " yemachun mot alefekdem" belalena ebakachu tmelesu asetwelu eyelaen be'Egeziabhere ereherahe enelemenalen enji hawareyaw paweles endalew wondelen enesebekalen enji anemetam" endale lebe endesetachew eyetsleyen demom begeta fikrem enemekerachewalen. tebareku masetewalen lehulachenem yeseten Amennnnnnnnnnn
ReplyDeleteAndeargen, you let pentae like Almaz post her non-sense but you block the openion of a person who see himself as 'gatekeeper'/ዘበኛ of our Church. Some of us defend this church because we have nowhere to go. Without this church our Ethiopianess is null and void. Again people who say politics and religion doesn't go together needs to wake up from mental slavery. Even your precious daniel keberet do agree with me on that one. That is why he is a woyane messenger who has been working hard in shaping people' opinion, instead of empowering people. Please read you history, you would know how this church was a thorn for all of our external enemies. They would use their internal agents and her own children to minimize her influence and eradicate her compeletly by any means necessary.
ReplyDeletetadeya ende daniel keberet ena MK adelum endi yegeta ena ye'bitekiresetan telatoch yegeta yehonutem eyasadedu seletarik yemiyaworku tarik eko talefale yemayalef tarik ye'kirstos yemadanu sera new. yanen megelet yashalem wondemi geta keo legna temotew zelalemawi endenehon new eko. tarekachenen yekyerew ke'machi nefes wod hiwot yametan esu enji. sele'hagerena sle'betikrestan keresenet maworat adelem yemiyadenew. bereget betekresteyanachew getan bemekebel kedami nat gen ahun tarekana wog wod hala melesatena gata lela asetubaten bado aderegat ena kirestan tareka woriwa ker yenen demo yemiyaderegut bezeh zemen ene danil kiberetena MK nachew geta getn sle'ewnet yeferedal ebakachu yeseun ewenet yebigletuten atasadu lenegeru betasadedachewem ayegremem ye'ewnetegna agalegay melegechaw sedet new ye'haymanotachew mereena fesami kiresetosom bezeh meder tsedal. lemanegnawem geta masetewalen yseten le'betekrestan gena besebek tensai yehunlat.
ReplyDelete