- በዋልድባ የሰራተኞች መኖሪያ የቅዱስ ሚካኤል እለት ንፋስ በቀላቀለ ንፋስ ተጠራርጎ ጠፍቷል
- በአፋር እና ትግራይ ክልል አካባቢ የሚገኘው ታሪካዊ እና እድሜ ጠገብ የመዝባ ገዳም እሳት ተለኮሰበት፣ አንድ ቤተመቅደስ ተቃጥሏል ሌሎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤
(Save Waldba) :- እለቱ ግንቦት 12 ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ነው
በዋልድባ ገዳም ዙሪያ በተለይ በዛሬማ ወንዝ አካባቢ የወልቃይት ስኳር ፋብሪካን ለመገንባት የሰፈሩት ሠራተኞች፣ መሃንዲሶች፣
የሥራ ተቋራጮች ብሎም ለዚህ ሥራ (ፕሮጀክት) ለማገዝ በአካባቢው ካምፕ ሰርተው ከሰፈሩ ወደ አንድ አመት ይጠጋቸዋል። እነዚህን
ሠራተኞች ለማስቀመጥ በርካታ ቤቶች፣ የሚመገቡበት የምግብ አዳራሽ፣ ለሥራ ተቋራጮች እና ለማሀንዲሶች ቢሮዎችን በተጨማሪ ለሥራው
የሚጠቀሙበትን መሳሪዎች የሚቀመጡበት መጋዘኖችን ጨምሮ ቦታው በርካታ ቤቶችን እና ትላልቅ መጋዘኖችን የያዘ በዛሬማ ወንዝ ሰሜን
በኩል ኮረብታ ላይ የተከተመ ቦታ ነበር። “በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም
አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሰሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” ዘጸዓት ፳፫ ፥ ፳፩ አረማውያን በየጊዜው የጌታን
ትዕዛዝ በመተላለፍ በቤቱ በድፍረት እና በትዕቢት የሚያደርሱትን በደል እየተመለከተ በቁጣው የተግሳጽ ድምፁን ሲያሰማ ቢቆይም እነርሱ ግን ሊሰሙ አልቻሉም
እግዚአብሔርም ትዕዛዛሩን በመልዕክተኞቹ በባለሙዋሎቹ እያስተላለፈ ነው ፣ ልቡ ለተሰበረ በፈጣሪ አምላካችን እምነት እና
ድህነትን ማግኘት የፈለገ የምሕረት አባት ነውና ሁሌም ይጎበኘናል ነገር ግን የፈርዖን ልጆችን በባሕረ
ቀይ ባሕር የበላ ዛሬም በየጉድባው ለሚጸልዩት አባቶቻችን መልሱን እየሰጠ ነው ፤ በለፉት አንድ አመት ብቻ መድኅኒዓለም ክርስቶስ
በርካታ ታዓምራቱን በገዳሙ አካባቢ ስኳር እናመርታለን ያሉትን እድሜ ለንሰሃ እየሰጠ ሥራቸውን ግን እንደ ባቢሎን ግንብ
እያመከነው ይገኛል ፥ ልክ
ባቢሎናውያን አምላክን እናገኘዋለን ብለው ግንብ ሲገነቡ በመጨረሻ ድፍረታቸው ስለበዛ ቋንቋቸውን ቢቀላቅልባቸው እላይ ያለው
ሲሚንቶ ሲጠይቅ አፈር ይዞለት ይመጣ ነበር ፤ በመሆኑም ሥራቸው መክኖ አምላክም ክብሩ የተገለጸበት ጊዜ እንደነበር መጽሐፍ
ቅዱሳችን ቁልጭ አድርጎ ይናገል፥ ዛሬም ፈጣሪ እለት ተእለት የሚሰለስበትን፣ የሚቀደስበትን ቅዱስ ቦታ ለማፍረስ እና ታሪክን
እና የወገን ሃብትን ለማጥፋት የተገዳደሩትን ልክ እንደ ባቢሎናውያኑ ቋንቋቸው ባይጠፋም እርስ በእርስ መግባባት
እስኪሳናቸው ድረስ ማድረግ የሚችል የሠራዊት ጌታ ዛሬም እነዚህን አረማውያን አንዴ በቁጣው ሲገስጻቸው፣ ሌላ ጊዜ ሥራውን ሊሰራ
የመጣውን ካምፓኒ ሲያበረው ተግዳሮታቸውንም በድፍረት እና በማናለብኝነት እንደቀጠሉ ነው እውን እዳር ያደርሱት ይሆን?
ከአራት ቀናት በፊት በቅዱስ ሚካኤል እለተ ቀን
ነፋስ ቀላቅሎ በዘነበው ዝናብ እና ነፋስ አማካኝነት በዛሬማ ወንዝ ኮረብታ ላይ ያሉትን ካምፕ ጠራርጎ ወደ ገደል ከቶታል፣
በእለቱም ምንም አይነት በህይወት ላይ የደረሰ አደጋ እንደሌለ ለመረዳት ችለናል። እንግዲህ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው
እግዚአብሔር አምላክ “ልብሱ እሳት፣ ቃሉ እሳት፣ እርሱ እሳት ነው ማንም ከፍጥረታት ወገን ወደ እርሱ ሊቀርብ የሚችል ማንም
የለም፥ ነገር ግን ምሕረቱ እና ቸርነቱ እሳቱን እያቀዘቀዘው በፊቱ ለመቆም ችለናል” ነበር ያለው አሁንም አረማውያኑን በእለቱ
በጊዜው ከምድረ ገጽ ማጥፋት ሲችል በምሕረቱ እና ቸርነቱ ስለበዛ እድሜ ለንሰሃ ይሰጣቸዋል (የሚመለስ ካለ) ዛሬ በንብረታቸው
በሥራቸው ያልተመለሰ ነገ ወደራሳቸው ካልተመለሱ ወየውላቸው እንላለን። ዛሬ በቅዱስ ሚካኤል እለተ ቀን የደረሰው የፈጣሪ ቁጣ
ቢማሩበት እና ከመድኅኒዓለም ቦታ ላይ (ከዋልድባ ገዳም) ዘወር ቢሉ ይሻላል እንላለን፥ እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት የቅዱስ
ሩፋኤል እለት በዛሬማ ወንዝ ላይ ሲሰራ የነበረውን ድልድይ እና የችግኝ ማፍያ የተሰራውን ግድብ በእለቱ ለበረከት የሚዘንበው
ዝናም (ጸበል) ለእነሱ መዓት ሆኖባቸው የተሰሩትን ግድብ እና ድልድይ ጠራርጎ ወስዶ ታዓምራቱን አሳይቷል፣ ሌላው ገና
የወልቃይት ሥኳር ፋብሪካ ጥናት የመጣው የመጀመሪያው ዲዛይን ኢንጂነር የዋልድባን ምድር ከመርገጡ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል፣
በተለያየ ጊዜ ከገዳሙ የሚወጡ አውሬዎች በርካታ ሰራተኞችን ለህልፈት አብቅተዋል፣ በዋልድባ ገዳም የዮርዳኖስ ጸበል ውስጥ
በድፍረት የታጠቡ የሰራዊቱ አባላት (ታጣቂዎች) በእባጭ እና ተመሳሳይ በሽታዎች ተመተዋል፣ በመነኮሳት አባቶቻችን ላይ የድፍረት
እጆቻቸውን ያነሱ ታጣቂዎች ሁለቱ ወዲያውኑ ለህልፈት ሲዳረጉ ሌሎች ደግሞ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ሆነው እስከ አሁን ድረስ
በስቃይ እንደሚገኙ ይታወቃል፥ ስለዚህ እነዚህ ሁሉ ታዓምራት ትምህርት ካልሰጧቸው እነዚህ አረማውያን ነገ ምን እንደሚሆኑ
መገመት የሚያዳግት አይመስለንም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፋር እና ትግራይ
ክልል ውስጥ የሚገኘው የሚገኘው
ታሪካው እና እድሜ ጠገቡ የመዝባ ገዳም ሆን ተብሎ የተለኮሰ የእሣት ቃጠሎ እንደደረሰበት የገዳሙ መነኮሣትና
የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል። በመነኮሳቱ ላይ ድብደባ መፈፀሙንም የVOA ዘገባ ገልጿል። ድርጊቱ ያስቆጣው በመቶዎች የሚቆጠሩ መነኮሳት እና
የአካባቢው ነዋሪዎች ሰኞ፣
ግንቦት ፲፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ወደ መቀሌ ተጉዞው በተወካዮቹ አማካኝነት ለክልሉ መንግሥት ፕሬዘዳንት ቢሮ
አቶ አባይ ወልዱ አቤቱታቸውን ማሰማታቸውን ከአካባቢው ተዘግቧል። የአባላ ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ ጉዳዩን ለማጣራት
ወደ አካባቢው የፖሊስ ኃይል መላኩን አስታውቋል።
qale hiweta yasemalna wedam
ReplyDeleteአዎ ! ቃለ ሔይወት ያሰማልን።
ReplyDelete