(ይህ ጽሁፍ በአሰበ ተፈሪ ተከስቶ የነበረውን አጥማቂ
ብቻ ይመለከታል)
(አንድ አድርገን ግንቦት 2 2005 ዓ.ም)፡- የዛሬ ሁለት ዓመት አንድ
ሰው ከሰሜኑ ክፍል ይነሳና የማጥመቅ ስራውን እያከናወነ ወደ ምስራቅ ክፍል ሐረር መንገድ አሰበ ተፈሪ ጉዞውን
ይቀጥላል፡፡ አሰበ ተፈሪ ሲደርስ የማጥመቅ ጸጋ እንዳለው ለቤተ ክርስቲያን አባቶች እና ለአካባቢው ሊቀ ጳጳስ አስረድቶ ፤
የማጥመቅ አገልግሎት እንዲሰጥ ህጋዊ ፍቃድ አግኝቶ ሰዎችን ሊያጠምቅ ስራውን በይፋ ይጀምራል፡፡ ቅዳሜ እና እሁድ ከቅዳሴ በኋላ
ስራውን ሲጀምር ለመጠመቅም ሆነ ለመመልከትም የመጡ ሰዎች እያጓሩ ፤ እየጮሁ ፤ ሌሎች እንደሚያደርጉት መውጣት ጀመሩ ፡፡
መንፈስ ተብዬው ሲለፈልም ‹‹ሟርት ነኝ›› ፤ ‹‹መተት ነኝ›› ፤ እገሌ ነኝ ማለቱን
ቀጠለ፡፡ ማነው ያደረገብህ ? ተብሎ ሲጠየቅ ፤
የሚታዘዘው መንፈስ የደብሩን አስተዳዳሪ ፤ ቄሶችን ፤ ዲያቆናትን ፤መምህራንን ስም መጥራት ተያያዘው ፡፡ እዛ ያለው ሰው ግራ
ገባው ፤ ግማሹ ‹‹ይሄ
ሰውዬ ትክክለኛ እጥማቂ አይደለም ፤ እነዚህን ዲያቆናትና ፤መምህራንን እናውቃችዋለን ንፁህ ናቸው›› ሲል
፡፡ ሌላው ክፍል ደግሞ ‹‹ያው መንፈሱ እኮ ተናገረ ፤ ከዚህ በላይ ምስክር አያሻንም›› ብለው
ስማቸው የተጠራውን ቀሳውስ ዲያቆናት ፖሊስ አስጠርተው አፍሰው እስር ቤት ከተቷቸው፡፡ ይህ ሰው መሰል ተግባሩን በተለያዬ ቦታዎች
ውስጥ እየዞረ በመስራት መሰል ነገሮች በሶስት ቤተ ክርስትያኖች ላይ ተከሰተ፡፡ ቀሳውስቱ ፤ዲያቆናቱ ሁሉም ዘብጥያ ወረዱ፡፡
ቤተ ክርስቲያን ማን ይቀድስ? ማንስ ቀድሶ ያቁርብ? ነገሩ በጣም አስቸጋሪ ሆነ ፤ የአካባቢው ምእመን እነዚህን ቀሳውስቱንና ዲያቆናቱን ደግመን ማየት አንፈልግም ስላለ የአካባቢው ሀገረ ስብከት አስተዳዳሪ ሊቀ ጳጳስ መንፈሱ መሰከረባቸው የተባሉትን አባቶች ወደመጡበት ማሰናበት እና አዲስ አገልጋዮችን በማምጣት
ሂደት ውስጥ ከአንድ ወር በላይ ቤተክርስትያኑ ተዘጋ ፤ አገልግሎቱም ተስተጓጎለ፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ይህ ሰው ብር
መሰብሰቡን ማጥመቁን የከለከለው አካል አልነበረም፡፡ አንዳንድ ቦታ ላይ እሱን ለመጋበዝ እስከ 7000 ሺህ ብር ድረስ
ከምዕመናን ይሰበሰብ እና ይጋበዝ ነበር፡፡ እዛው አካባቢ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በጧፍ እጥረት አገልግሎቱ ማከናወን
ሲገዳደራቸው እየተመለከቱ ለአንድ ህገ ወጥ አጥማቂ ግን 7000 ብር በቀናት ጊዜ ውስጥ እንዴት መሰብሰብ እንደቻሉ ለተመለከተ ይገረማል፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ ሰውየው ሌላ ቦታ ላይ ተጋብዞ ለማጥመቅ ሄደ፡፡
እዚያ ቦታ ላይ ደግሞ የተከሰተው ነገር ከአሰበ ተፈሪው የተለየ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ባልታወቀ ምክንያት ከዓመታ በፊት
ተቃጥላ ነበር ፤ የአካባቢውም ምዕመን በቻለው መጠን የበፈት ይዞታዋን ሳትለቅ እንደገና መስራት ችሎ ነበር ፡፡ ይህ ‹‹አጥማቂ››
ነኝ ባይ እዚች ቤተ ክርስቲያን ላይ እያጠመቀ ሳለ አንዱ መንፈስ የያዘው ሰው ይነሳና መለፍለፍ ይጀምራል፡፡‹‹ቤተ ክርስቲያኗን ያቃጠላት መምህሬ እገሌ ነው›› ብሎ መሰከረ፡፡ ሰው
እውነት መስሎት ያን መምህር ካልገደልነው ብሎ ተነሳ፡፡ በመሀል አንድ አባት ይነሱና እረፉ ‹‹መንፈስን ሁሉ አትመኑ›› ነው የተባለው፡፡ አንተም ማጥመቅህን አቁም ፤ ‹‹በችግር የተያዙትን እስራታቸውን
እግዚአብሔር ይፍታ ስንል አንተ ደሞ ሌላ ብጥብጥ አመጣህብን›› ብለው በሰላም ሸኙት፡፡
ለቤተ ክርስትያን መቆርቆራች ባልከፋና ጥሩ ሆኖ ሳለ እንዴት እንደምናስብላት አለማወቃችን ደግሞ ሌላ ችግር እየፈጠርን መሆኑን
ተገንዝበነው አናውቅም፡፡ አሁንም የአካባቢው ሰው አቃጠለ የተባለውን መምህር ይዘው ለፖሊስ አስረከቡ ፡፡
ፖሊስም እስኪጣራ ብሎ መምህሩን አሰረው ፤ ፖሊስ ምንም አይነት ተጨባጭ ማስረጃ ስላላገኝ መምህሩን ፈትቶ ሀገር ለቆ እንዲሄድ
ያሰናብተዋል፡፡ ህዝቡም አይንህን እንዳናይህ ቤተክርስትያናችን አቃጥለህብን ብለው ‹‹አይንህ ለአፈር›› አሉት፡፡
ይህ ሁሉ እየሆነ ማስተዋል የሚችል ሰው በመጥፋቱ በሌላ ጊዜ ፤ ሌላ
ቦታ ላይ ሰውየው መንፈስ ያወጣል ፤ ተዓምረኛ ነው ሲባል የሰሙ ምዕመኖች ይምጣልን ብለው የጠየቃቸውን ብር ከማህበረሰቡ ላይ ፤
ከሀላፊ አግዳሚው ላይ መሰብሰብ ይጀምራሉ ፡፡ አሁንም የዚህ ሰውዬ ማንነት ለማወቅ ሰው አይነ ልቦናው አልበራለትም
ነበር ፤ ራሱ መተተኛ በመተት የተያዘ ሰው እፈታለሁ ፤ ከዲያቢሎስ ቁራኛነት እገላግላችዋለሁ ብሎ ማወራቱን
ማጥመቁን ተያይዞታል ፡፡ አባቶች እዚህ ጋር ተሰብስበው መከሩ ፡፡ እንቢ አይመጣብ ቢሉ ‹‹የራሳችሁ ጉድ እንዳይወጣባችሁ›› ነው ይባላሉ ፤ ይምጣ ቢሉ ደግሞ
ቤተክርስትያኗን ፈትቶ ፤ ያሉትን ካህናት እንዲባረሩ አድርጎ ምዕመኑን ለሌላ እምነት አሳልፎ ሊሰጥ ነው፡፡ ግራ የሚገባ ነገር
ሆነ ፡፡ አባቶች ተሰብስበው መከሩ እንዲህም አሉ ፡- በሚቀጥለው ‹‹ እሁድ
ጠዋት መምጣት ይችላል ፤ ነገር ግን እኛ ለሊቱን ሙሉ የገብርኤልን ፤ የሚካኤልን ፤ ሁሉን ድርሳናት እንድገም ፤ ሙሉ ዳዊት
ደግመን ጸሎት እናድርግ ፤ መልካ መልኮችን እናድርስ ፤ ከዛ እኛ በማኅበር ሆነን ባደረግንበት ፀበል እሱ መጀመሪያ ይጠመቅ ፤
ከዛ እኛ ሁላችንም እንጠመቃለን ፤ ከዛ ምዕመኑን ያጠምቃለል ›› ብለው ቃለ ጉባኤ ይዘው ተፈራርመው
፤ ወስነው ስብሰባን ዘጉ፡፡
አጅሬ ለካ ምን እንደተባለ መንፈሱ ይንገረው ማን ይንገረው
አልታወቀም፡፡ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ በህብረት ሆነው ቃል የገቡትን አድርገው ቢጠብቁት ቢጠብቁት ሊመጣ አልቻለም፡፡ በቃ እሺ
ብለው ሌላ ቀጠሮ ያዙለት ፤ አሁንም ሊመጣ አልቻለም ፡፡ የቀረበትን ምክንያት ሲጠይቁት ተልካሻ ነገር ነገራቸው፡፡ ይገርማል
!!!! ሰዎች ቀስ እያሉ የሰውየው ማንነት ስለገባቸው ገፍተው ከአካባቢው አባረሩት፡፡ ይህ ሰው ይህን አይነት ስራ ደቡብ
አካባቢ ሲሰራ ሌባና አጭበርባሪ መሆኑ ታውቆ በእስር ቤት እንደሚገኝ ከጊዜ በኋላ ሰማን፡፡ እኛ ይህ ሰው በአንድ ቦታ ላይ ብቻ
ያደረገውን ብቻ እናውቃለን ፤ በፊት ምን ያህል ቤተ ክርስቲያን ይበትን? ፤ አሁን ምን ይስራ? ፤ በአሁኑ ሰዓት ምንም የምናውቀው
ነገር የለም፡፡
እኛ አይናችን ታውሯል ፤ እናያለን አናስተውልም ፤ እንሰማለን
አናዳምጥም ፤ በቃ እንደዚህ ነን፡፡ እነሱም እየዞሩ ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳሉ ፤ ቤቱን ይፈታሉ ፤ ተከታዮች ያፈራሉ ፤ በሲዲ
አድርገው አቀነባብረው ለኛው ይሸጡልናል ፤ እኛም ‹‹ይገርማል››
እያልን እናያለን፡፡ ስራቸው ሳይሆን የሚገርመው እኛ ነን የምንገርመው፡፡
የአካባቢው አባቶች ጠይቀን እንደተረዳነው ፡- ‹‹ይህው እሱ በዚያን ጊዜ አጠምቃለሁ ብሎ ውሀ የረጨባቸው ሰዎች አሁንም ይጥላቸዋል ፤ ምን
እንዳሰፈረባቸው እግዚአብሔር ይወቀው ፤ እሱ ሳይመጣ በፊት ጤነኞች ነበሩ ፤ እሱ ካጠመቃቸው በኋላ ግን በሽታ ላይ ጥሏቸው ሄደ
፤ አንዳንዶቹ ቤተክርስትያን እየመጡ እየተጠመቁ እየተሸላቸው ነው ፤ አንዳንዶቹ ግን አሁን በሽተኞች ናቸው›› ብለው
ነበር የነገሩን ፡፡ ይህን ሲነግሩን ያለንበት ጊዜ ምን ያህል አስቸጋሪ መሆኑን ነው የተረዳነው፡፡
በቅርብ ጊዜ ደብረ ብርሐን ቅዱስ
ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አዲስ አጥማቂ መጥቷል ተብሏል.. እስኪ ነገሩን አጣርተን እንመለሳለን
thankyou what about girma ? the same thing. no body oppose him
ReplyDeletethankyou what about girma ? the same thing. no body oppose him
ReplyDeleteTo me "እነሱም እየዞሩ ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳሉ ፤ ቤቱን ይፈታሉ ፤ ተከታዮች ያፈራሉ ፤ በሲዲ አድርገው አቀነባብረው ለኛው ይሸጡልናል ፤ እኛም ‹‹ይገርማል›› እያልን እናያለን፡፡ ስራቸው ሳይሆን የሚገርመው እኛ ነን የምንገርመው" shows beyond "ይህ ጽሁፍ በአሰበ ተፈሪ ተከስቶ የነበረውን አጥማቂ ብቻ ይመለከታል".
ReplyDeleteIf there is a slight chance that you may be suggesting a comparison of this woslata atmaki with Memhir Girma, beware that you are insulting the Holy Ghost's grace (tsega-Menfes Kidus). Be careful, be very careful. We should be able to separate the fox in sheep's clothing from the ACTUAL SHEEP!!! Fathers like Memhir Girma of Ethiopia, as well as Father Makari of Egypt NEVER for one second departed from Orthodox dogma!!! They are the grace of the Orthodox world and I duly and humbly warn you to be careful when you make implicit suggestions that mislead the herd.
ReplyDeleteየእኛ ጉድ ተዝቆ አያልቅም ጠላት በቤተክርስቲያን ላይ ብዞ ጦር ወረወረ ቤተክርስቲያን ግን አሁንም አለች መስራቿ ይጠብቃታልና ፡፡ ወገን የተዋሕዶ ልጅ እባክህ ልብ በል መጨረሻው ዘመን አስከፊ መሆኑንም ልብ በል፡፡ የተዋሕዶ ልጅ ጠላት በቤተክርስቲያን ጸንተህ በማየቱ ከቅጥሩ ሊያወጣህ ስለፈለገ አስመሳይ ሰዎችን በቤተክርስቲያን ተክሏቸዋልና እርሱ እግዚአብሔር ነቅሎ እስከሚያወጣቸው ድረሰ አንተ ከአባቶችህ ከሐዋርያት በተማርከው ሃይማኖት ትምህርት ጸንተህ ኑር፡፡ ቆላ 2፡7 የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የክፉ ትንቢት መፈጸሚያ እንዳልሆን ጠብቀኝ በለው፡፡ ይጠብቅሃል፡፡
ReplyDeleteወላዲተ አምላክ በቃል ኪዳንሽ በተዋሕዶ ሃይማኖት ጠብቂን፡፡
Egziabher libona yistachihu. meserinet yekrstian tsebay aydelem.
ReplyDeleteጽሑፋችኁን በማንበብ ላያ ሳለኁ፡ መዠመሪያ በጭንቅላቴ እንደ ዚያቆኔው ቅጭል ያቃጨለብኝ፡ እኚ ሰዎች የተወደዱ መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙን ረብ በሌለው ክታባቸው መተንኮላቸው ይኾንን ብዬ አሰብኩኝ። ያሰብኩትም አልቀረ፡ ከታች ዝቅ ብዬ፡ ሌላኛውን መልእክት ስመለከት፡ ''የደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን መምህር ግርማ ወንድሙን ከማጥመቅ ስራቸው አገደ'' የሚል ደብዳቤ አገኘኁ። እናንት ሆይ! ከአረመኔው ዲያብሎስ ጋር ማሕበር ሰርታችኁ፡ እሱን በማገልገል ላይ የምትገኙ፡ ለራሳችኁ ብላችኁ ንስሐ ግቡ!።
ReplyDeleteእግዚአብሔር ለኹላችን ማስተዋሉን ያድለን!።
At last, an individual are quenched by what you keep built, put it apart for a
ReplyDeletebit of time. This bestows on way to unquestionably the undulating sounds rushing
brook.
Also visit my web site strefa-mieszkania.com.pl
በመሠረቱ የማጥመቅ ጸጋ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋ ነው ማንም ተነስቶ ላጥምቅ ቢል አይሆንም ነገር ግን ቤተክርስቲያን የሥርዓት ቤት ናትና የማጥመቅ ጸጋው ያለው እንኳ ቢኖር ቅድሚያ የአባቶች ይሁንታ ወይም በደረጃው ያሉ የቤተክርስቲያን ኃላፊዎች ሊያውቁት ወይም ሊያውቁለት ይገባል ፡፡ አሁን እየሆነ ያው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ተብሎ በተነገረበት መድረክ ላይ የለፈለፈውን ሁሉ አምነን ካህናቱን ከመንበራቸው ካባረርን ሰይጣንስ ቢሆን ከዚህ የተለየ ምን ይሰራል፤ እኔ የማውቀውን እውነት ላካፍላችሁ ሰውየው(አጥማቂ ነኝ ባዩ) ከጎንደር እንደተነሳ ይናገራል ባህርዳር ሄዶ ማጥመቅ ጀመረ አልፎ ተርፎም የኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ልትቃጠል ነው ብሎ በዕለተ ሰንበት ሰዉን ሲያሰግድ ተገኘ ሌሎችም ተግባራትም እንዲሁ በኋላ በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ጥረት ተባረረ፡፡ ይህ ሰው አዲስ አበባ መጥቶ እንዲሁ አጥማቂ ነኝ እያለ ሲያውክ ቆይቶ ገዳመ ኢየሱስ ወደሚባለው ቤተክርስቲያን መሽጎ ማጥመቅ ጀመረ በዚያ ደግሞ ከቀድሞው የበለጠ ችግር ፈጠረ- በእግራቸው ተራምደው መጥተው የባሰ ታመው (ዕድለኞቹ ማለት ነው) ተመለሱ እንዲሁም በርካቶች ሞቱ፡ ሰውየው ቢያንስ ለሁለት ዓመት ቆይቶአል ከ10 በላይ አስከሬን ከጊቢው በፖሊስ እገዛ እንደወጣ አውቃለሁ፡ ይህ ሰው መንፈስ አወጣለሁ እያለ ነገር ግን ሰዉን አስቀዳሹን ኁሉ ሳይቀር ከቤተክርስቲያን አስቀረው፡ አልፎ ተርፎም ባለህግ ሆኖ ሳለ ከሚስቱ ጋር በቤተክርሰቲያን ቅጥር ጊቢ ውስጥ ቤት አሰርቶ ይኖር ሁሉ ነበር፡፡ ያን ሁሉ ጊዜ ሲኖር ግን ቤተመቅደስ ውስጥ ግን ከሁለት ቀን በላይ ገብቶ አያውቅም ነበረ (ለምን መግባት እንደሚፈራ ግን የሚያውቀው እሱ ብቻ ነው) ችግሩ እየባሰ ሲሄድ የደብሩም ካህናት ተማክረው እንዲባረር አደረጉት ፡፡ ይህ ሰው ከዚያ ወደ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አመራና አጥማቂ ነኝ አለ እዚያም ላልሰሙትና ያላወቁትን እንዲሁ ሲያምታታ ኖረ ነገር ግን ደብሩ ወዲያው አሰናበተው፡ ከዚያ ጉዞውን ወደ አዋሳ አድርጎ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አካባቢ ያጠምቅ እንደነበር መረጃ ነበረኝ በዚያ ስለተደረገው ነገር ብዙም አልሰማሁም ምናልባት ይህ ሰው ንሰሐ ገብቶ የሚመለስ ቢሆን ለቤተክርስቲያን እሱም ሃብተ ሊሆን ይችላልና ስሙ ከመጥቀስ እቆጠባለሁ፤ - መንፈስን ሁሉ አትመኑ የሚለውን ማስተዋል ይገባል ለዛውም በዚህ ዘመን፡፡
ReplyDeleteመንፈስን ሁሉ አትመኑ
ReplyDeleteወገኖቼ እንዲህ ያሉ የእምነት መሰናክሎች በየግዜው በሃገራችን የተከሰቱ ቢሆንም ለመሆኑ አንድ አጥማቂ ለመሆን የሚችል የአምላክ ጸጋ ያደለው እንዲሁ ተነስቶ የማጥመቅ ጸጋ ታድያለሁ በማለቱ አድርግ ተብሎ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች መስጠታቸው፡ ለየት ያለ ከበላይ የተሰጣቸው ትእዛዝ እንጂ በክህነት ግልጋሎት የሌለው ማንም ላጥምቅ በማለት የመጣ አይመስለኝም ፡ ከንባቡ የተረዳሁት ያሉትን አገልጋኦች ከምእመኑ ጋር በማጋጨት ባልሰሩትና ባልፈጸሙት ተግባር ለስርና ለመባረር እጣ ፍንታ የገጠማቸው ግለሰቦች፡ በሚስጥር የተደረገ እንጂ በእውነት አንድ ግለሰብ ሌላውን የመወንጀል የእግዚአብሔር ሰጋ አድሮበት አጥማቂ ሆነ የሚለው በእውነት ምእመኑ በእምነት ያልጸና፡ በሰው አምልኮ የተደናገረ ኃይል ያጣ፡ በዚህ ሰው ፍላጎትና መንገድ ለቁጥጥር የዋለ ለመሆኑ የሚያሳይ ከመሆኑም ባሻገር ራሱን መፈተሽ እንዳይችል የተላያየ ድንግርግር ሁነታዎች እንደፈጠረበት ያሳያል፡
ReplyDeleteየኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የሆናችሁ ሁሉ በውጭም በውስጥም ያላችሁ በነዋይ ሕሊናቸውን በሸጡ እምነትና ምንነታቸውን በዘነጉ እምነትና ታሪካዊ ቤታችንን ማሕደራችንን ለማፍረስ ለመበረዝ የተነሱበንን የቀበሮ ባሕታውያን በንቃት እንጠብቅ ከመቀበላችን በፊት ማንነታቸውንና አታላይ አንድበታቸውን በንቃት ቀንና ለሊት እንቅስቃሴያቸውን እንፈትሽ ለሁሉም ኃያሉ አምላካችን በተክርስቲያናንና ኢትዮጵያን ይጠብቅ