Thursday, October 29, 2015

‹‹መምህር›› ግርማ የተጠረጠሩበት ወንጀል ዝርዝር ይፋ ሆነአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18 2008 (ኤፍ..) ትናንት በቁጥጥር ስር የዋሉት መምህር ግርማ ወንድሙ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።መምህር ግርማ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄም ወድቅ ተደርጓል።የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፖሊስ መርማሪ ቡድን ዛሬ ግለሰቡን በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1 የወንጀል ችሎት አቅርቧቸዋል።ፖሊስ ግለሰቡ በተጠረጠሩበት የማታለል ወንጀል ቀሪ የምርመራ ስራ ስላሉብኝ ተጨማሪ 14 ቀን ይፈቀድልኝ ብሏል።

ተጠርጣሪው በራሳቸውና በጠበቃቸው በኩል ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ  በመቃወም የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል። የፖሊስ የምርመራ ቡድን በበኩሉ እሳቸው ቢለቀቁ ሌሎች ተፈላጊዎችን እና የተለያዩ ሰነዶችን ስለሚያሸሹብን ጥያቄያቸው ውድቅ ይሁን ብሏል።ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገን ክርክር መርምሮ ፖሊስ አብዛኛውን የምርመራ ስራ ያካሄደ በመሆኑ ለቀሪ የምርመራ ስራዎቹ ይረዳል በማለት ከጠየቀው 14 ቀን ጊዜ ውስጥ 7 ቀን ብቻ ፈቅዷል።ውጤቱን ለመጠባበቅም ለጥቅምት 25 2008 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።


የወንጀሉ ዝርዝር
ፖሊስ መምህር ግርማ  በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ምክንያት የሆነው ወንጀል የተፈፀመው መስከረም 2006 . ነው ብሏል። በየካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወሰን ግሮሰሪ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩት አቶ በላይነህ ከበደ በመምህር ግርማ የማታለል ወንጀል የተፈጸመባቸው ግለሰብ ናቸው። እንደ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እኚህ ግለሰብ ከትዳር አጋራቸው ጋር 400 ካሬ ሜትር ላይ ባረፈ መኖሪያ ቤታቸው ይኖሩ ነበር።
እንደ ምርመራ መዝገቡ መምህር ግርማ የግል ተበዳይን እምነት በመጠቀም የምትኖርበትን መኖሪያ ቤት እስከ ጥር 30 2006 ሽጠህ ካልወጣህ አስከሬንህ ይወጣል ይሏቸዋል። የፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚለው ልጅ ያልወለዱት ባልና ሚስት ከመሞት መሰንበት በማለት ይህንን ቤት በጣም በዝቅተኛ ዋጋ 800 ሺህ ብር ይሸጡታል። ቤቱ በዚህ ዋጋ እንዲሸጥ መምህር ግርማ በራሳቸው ሰዎች አማካኝነት ብዙ ያልተገባ ስራ ሰርተዋል ነው የሚለው የምርመራ መዝገቡ።

ከዚያም መምህር ግርማ በዚህ ብቻ ሳይመለሱ የግል ተበዳዩን ቦሌ አካባቢ በራዕይ ያየሁት ቦታ አለ እዚያ ነው ገዝተህ የምትኖረው ይሏቸውና ሌላ የማታለያ ዘዴ ቀየሱ ይላል ምርመራው። ቤቱ የተሸጠበትን 800 ሺህ ብር አምጣና እንዲበረክትልህ ልፀልይበት ብለው በመውሰድ በዚያው ውለው አደሩ፤ የግል ተበዳዩም በእርሳቸው ላይ ያላቸው እምነት ባለመጥፋቱ በትዕግስት ስልክ ቢደውሉላቸውም ስልካቸው ዝግ ሆነባቸው፤ ይባስ ብሎ ከሀገር ወጡ ተባለ የሚለውም ተጠቅሷል።

የግል ተበዳይ ሁኔታው ማታለል መሆኑን ስለተረዱ 2007 መጋቢት ወር ገደማ ለፖሊስ ያመለከቱ ሲሆን፥ እርሳቸው ከሄዱበት እስኪመለሱ ፖሊስ የግል ተበዳዩን እና የምስክሮችን ቃል ተቀብሎ ቆይቶ ተጠርጣሪው መምህር ግርማ ወንድሙን ትናንት በቁጥጥር ስር አውሏቸው ነው ዛሬ ፍርድ ቤት ያቀረባቸው። ተጠርጣሪው እኔ የተባለውን ሰው ቀይ ይሁን ጥቁር አይቼው አላውቅም፤ ሆን ተብሎ ከጀርባ የተጠነሰሰብኝ ሴራ አለ በማለት ለችሎቱ አስረድተዋል።

ጠበቃቸውም የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና የሚከለክል አይደለም፤ ፖሊስም የሚጠበቁ ምርመራዎቹን አጠናቋል፤ ደንበኛዬ የዋስትና መብታቸው ይከበርልኝ በማለት ጠይውቋል። ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጓል።

11 comments:

 1. ወይ ግርማ ?

  ReplyDelete
 2. እኔ የመምህር ግርማ ተከታይ አይደለሁም እኔ ማንንም የምከተል ሰው አይደለሁም፡፡ የምከተለው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትንና ስርዓትን በተቻለኝ አቅም መንገዴ አድርጌ ወንጌልን የሕይወቴ ህግ አድርጌ የምኖር ነኝ፡፡ ማንም ቤተክርስቲያን አውደምህረት ላይ የሚያስተምሩትን ትምህርት እሰማለሁኝ፣ እመዝናለሁኝ፡፡ ስለዚህ ይህንንም ውስጤ ከተሰማኝና እንደዜጋና በእርሷቸው በኩል የሚደረገው ተቃውሞ አንጻር ስመለከተው እንድመረምረው አስገደደኝና ነው ይህንን ህሊና ያለው ያውም በዚህ ዘመን ብዙ እንድናስብና እንድናስተው እየተደረገ ባለው ድካም፤ ብዙ ሰው ብዙ ማድረግ በሚችልበት ጊዜ እንደዚህ አይነት የፖሊስ ምርመራ ተብሎ መቅረብ አለበት? የእኛ ሀገር ፖሊሶች በዚህ አካሄድ እየሄዱ ነው ሰው የሚያስሩት፡፡ እስኪ እንመርምረው፡፡ እንደው በደፈናው ከመፍረድ እያንዳንዷ ቃላት በራሱ ብዙ ስህተቶች አሉበት፡፡ 1. መሰከረም 2ዐዐ6 የሚለው መስከረም ወር መሆኑ ቀርቶ ቀን ሆነ እንዴ? ቀኑ መገለጽ ነበረበት፡፡ 2. ይሄ ሰው በትክክል የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ከሆነና አማኝ ከሆነ እኚ አባት የቤተክርስቲያን ሰው ናቸው በግልጽ እያሰተማሩና እያገለገሉ ነው፡፡ ሁላችንም እየሄድን ተመልክተናቸዋል፡፡ ትምህርታቸውን ሰምተናል፡፡ አገልግሎታቸው በግልጽ የምንመለከተው ነው ለምን ለቤተክርስቲያን ማሳወቅና የሆነውን ነገር መግለጽ ነበረባቸው፡፡ ሰውዬው የእምነቱ ተከታይ እንዳልሆነ በዚህ ማወቅ ይቻላል፡፡ 3. ፖሊስ ሲመረምር በትክክል የቤቱን አድራሻ ለምን አልገለጸም፤ ለምን አካባቢ ብሎ ማንም የማያውቀውን ሰፈር መግለጽ አስፈለገ፡፡ ይሄ በራሱ ትልቅ ችግር እንዳለበት ያሳያል፡፡ 4. ፖሊስ መረመርኩኝ ብሎ ያቀረበው ቤቱ ተሸጠ ተብሎ የተገለጸው ግለሰብ፣ ለማን እንደሸጠው የተሸጠለት ሰውዬ ከእርሷቸው ጋር ያለው ግንኙነት ሳይገለጽ በደፈናው አልባል ነገር አድርገዋል ብሎ መግለጽ አሁን የሀገራችን ፖሊሶች ችግር እንዳለባቸው ያሳያል፡፡ 5. የብሩ መጠን ተገልጾ ልጸልይልህ አሉኝ እንዲበረክት ማለት ተበዳዩ በእውነት ክርስቲያን ነውን? እንደዚህ የሚባል የወንጌል አስተምሮስ አለን? መምህር ግርማ አደረጉ እንበል፡፡ ተበዳዩ ሰውዬ ታምራት የሚባለው ጠንቋይ እንደዚያ ሲዋረድ አልሰማም፡፡ በከተማው አልነበረም፡፡ እንደገና ስልካቸውን አጥፍተው ተሰወሩብኝ ወደ ውጪ ሄደው እያለ የሚዘባርቀው እሷቸው ወደውጪ ሲወጡ እኮ በግልጽ አሳውቀው ሲመጡ በግልጽ አሳውቀው የት አገልግሎት እንዳለ ገልጸው ነው ለምእመኑ የሚያሳውቁት እኔ በጣም በኢንተርኔት ስለምከታተላቸው ነው፡፡ በ1 ወር በፊት እንኳን መምህርን ግርማ በጽርሀ ስላሴ አገልግሎት እንዳላቸው አንዲት እህት ፀበል ቦታ ላይ አውርታኛለች፡፡ የወንጌል አገልግሎት ቅዳሜ ማታ በራድየ እያስተማሩ ነው፡፡ ይሄ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቋል ከተባለ በኋላ የዋስትና መብታቸው ሊከበር ሲል ቆይ ይቀረኛል ማለት ምን ማለት ነው፡፡ 6. ተበዳዩ ለፖሊስ ያሳወቀበት ቀን የለውም መጋቢት ወር ገዳማ ተብሎ መግለጽ ታሪካው ምርምር ለምን አስመሰለው? ቢያንስ ይህንን ቀን መግለጽ ቀኑ እርቆ ነው ነው ፖሊስ ይህ ማመለከቻ ሳያነበው ነው አልገባኝም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ክስ አለወይ? ፖሊስ ያቀረበው መረጃ ይህ ከሆነ አካሄዱ ትክክለኛና አሳማኝ አይደለም፡፡ ሌላ የተጠናከረ መረጃ አለኝ የሚል ከሆነ ወደፊት እንመልከት፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቶ /ወሮ/ወሪት ሳስባይስ ሳድቢያስ ፤ ስለ “መምህር” ግርማ እርስዎ የጠየቋቸውን ጥያቄዎች ፍርድ ቤቱ ፖሊስን ስለሚጠይቅ በቀጠሮው ቀን ወደዚያ ብቅ ቢሉ ዝርዝሩን ሊረዱ የሚችሉ ይመስለኛል ። ተከታያቸው አይደለሁም እያሉ ለምን ነገ ለሚጣራ ጉዳይ ጥብቅና እንደ ቆሙ አልገባኝም ። ሌላው ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተሠራ ወንጀል ጉዳዩን የሚያጣራው የኢትዮጵያ ፖሊስ መሆኑን የዘነጉት ይመስለኛል ። የታምራትን ወንጀል ማን ነበር ያጣራው?

   Delete
 3. እውነት ብለሃል ወዳጅ፡፡ እኔ እንካን የጠበኩት በጣም የተራቀቀ የመርመራ ስልትን የተከተለ ክስ እንጂ እንደዚህ የተምታታና የቀለለ አልነበርም፡፡ ለማንኛውም እውነት ትቀጥናለች እንጂ አትበጠስም፡፡ እውነተኞችም ዋጋ ይከፍላሉ፡፡

  ReplyDelete
 4. መቸም የሰው አመለካከት

  ReplyDelete
 5. እኔ እንኳን ያሳሰበኘኝ እስር ቤት ሆነው ሰይጣንን ቃለ መጠይቅ ያደርጉለት ይሆን?

  ReplyDelete
 6. ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሰጠች እምነት እንከተል እንጂ ሰውንማ እንዴት እንከተላለን ጊዜው ሲደርስ እንደዚህ ነው እግዚአብሔር እንደዚሁ ሌሎችን አስመሳይ ተከታዮቻቸውን ያጋልጥልን እንላለን

  ReplyDelete
 7. ለመሆኑ የሚያገለግሉበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ጉዳይ ላይ ያለው አስተያየት ምንድነው? ምግባራቸውስ እንዴት እንደነበር? እስቲ አንድ በሉን፡፡

  ReplyDelete
 8. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
  ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ።ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ።
  አዋቂነት ባነበቡት ወይም በፃፉት መፅሃፍ ብዛት ለሚመስላቸው፤ከንቱ አዋቂነት በልባቸው ስለሞላች በራሳቸው አይን ፍቅር በጎደለው አንደበታቸው ምንም የተጨበጠ ነገር ሳይዙ ሲተቹ እና ሲያሳስቱ ለሚውሉ….
  [ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።
  እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል።]
  ምክንያቱም…
  [ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።]
  ከአለማዊው ጥበብ አልፎ እንኳን ሰማያዊ ጥበብን ቢታደሉ ሰው ፍቅር ከጎደለው ከንቱ ነው
  [በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ።
  ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።]
  አብዝቸ ብመፀውት ፍቅር በጎደለው መንገድ የሰበሰብኩትን ባካፍል ብረዳበት በፍቅር ካልሆነ ከንቱ ነው
  [ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።]
  ለምንም ነገር ቢሆን
  [ ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤
  ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።
  እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።]
  ስትመረምሩም ስትናገሩም ስትፅፉም ስታስተምሩም ስትገስፁም…ሁሉ በፍቅር ይሁን
  [በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን።]
  አንደኛው ያንደኛው አገልጋይ ታናሽ እንደሆነ እራሱን ዝቅ ዝቅ አድርጎ ይታይ እንጂ በስጋ ፍርድ አንዱ አንደኛውን ሊጥለው ሊያዋርደው አይሽቀዳደም፡፡ አሁን በዘመናችን የምናየው፣ ስለፍቅር ሊሰብኩልን የሚገባቸው በየጉባዔው አብዝተው ሲኮንኑ ሲያብጠለጥሉ መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡ ሰባኪያን በመካከላቸው ፍቅር የለም ስለትህትና ብዙ ያሉን “መጋቢዎች” በመታበይ እራሳቸውን ከቅዱሳን መስመር አሰልፈዋል .. ቤተክርስቲያን ፍቅር ትህትና ከጠፉ ሰነበተ !
  [ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ።
  ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤]
  የራስ ማንነት በክፉው ተይዞ በጥላቻ አንዱ ስለሌላው በመጥፎ በስድብ እየተናገረ እየኮነነ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ስራ የሚሰራ የሚመስለው የውዳሴ ከንቱ “ሊቆች” አገልጋዮች ነን ባዮች …
  [እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።
  መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።
  እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤
  ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።]
  ወንጌል ሊያስተምሩ በምኩራብ የሚቆሙ በምኑም በምናምኑም እንደራሳቸው ፈቃድ እራሳቸውን የእግዚያሔር ወገን ሌላውን የእግዚአሔር አንጃወች እያደረጉ ከመቆጣት አልፎ መረጋገም መወቃቀስ በስጋዊ ሀሳብ መጨቃጨቅ በስጋዊ ነገር መከፋፈልና መከራከር ያች ከእግዚአብሔር ዘንድ አይደለችም፡፡ በአንድ ስርአት ካሉትም ካልሆኑትም ካመኑትም ካላመኑትም ወንድሞች ጋር ተከባብሮ ፍቅር በሰፈነበት መንገድ መተራረም ሲገባ ፣አንዱ ስለአንዱ መፀለይ እና መለመን ሲገባ፣ ለጥፋቱ ማቀድ ማደም እና ማሳደም በምንም አይነት ክርስቲያናዊ አስተምህሮት ሊሆን አይችልም፡፡
  በማንስ በምንስ ላይ ትፈርድ ዘንድ አንተ ማን ነህ ይህ የእግዚአብሔር ነው ይህ የእግዚአብሔር አይደለም ለማለት በእርግጥ አንተ ማን ነህ ወንጌልን ትሰብክ ዘንድ አንደበትህ ቢከፈት የፈራጁን ቦታ፣ የኮናኙን ቦታ ትወስድ ዘንድ በርግጥ አንተ ማን ነህ ነገርግን ምንም ቢሆን በእግዚአብሔር ከሆነ እርሱ ያውቃል ካልሆነም እርሱ ይፈርዳል እንጂ፡፡
  [ለቀደሙት። አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።
  እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።
  እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤
  እናንተ ሥጋዊ ፍርድን ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በአንድ ሰው ስንኳ አልፈርድም።
  አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ።
  ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።
  እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።]
  በእናንተ አይን በእምነቱ እንኳን የሳተ ቢመስላችሁ በፍቅር ተቀብላችሁ መማማር እንጂ ፤እንኳንስ በሱ ላይ በአሳቡም ላይ አለመፍረድን አስተመሯል፡፡
  [በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ።
  አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።
  ይህ ሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንዲሻል ያስባል፥ ያ ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደ ሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ።
  አንተም በወንድምህ ላይ ስለ ምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና።
  እኔ ሕያው ነኝ፥ ይላል ጌታ፥ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል መላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል ተብሎ ተጽፎአልና።
  እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን።
  እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በርሳችን አንፈራረድ፤ ይልቁን ግን ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይህን ቍረጡ።
  በራሱ ርኵስ የሆነ ነገር እንደ ሌለ በጌታ በኢየሱስ ሆኜ አውቄአለሁ ተረድቼአለሁም፤ ነገር ግን ምንም ርኵስ እንዲሆን ለሚቆጥር ለእርሱ ርኵስ ነው።
  አሁንም አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ።
  TCD...

  ReplyDelete
 9. CTD (3)
  በእርግጥ አጋንንትን ማውጣት ያመኑ ሰዎች የሚያደርጉት ነገር እንደሆነ ጌታ ተናግራል፡፡
  [ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ]
  ከማይከተሉትም መካከል የማይቃወሙትም አጋንንትን በስሙ ያወጡ እንደነበር በመፅሃፍ ተፅፏል
  [ዮሐንስ መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፥ስለማይከተለንም ከለከልነው አለው። ኢየሱስ ግን አለ። በስሜ ተአምር ሠርቶ በቶሎ በእኔ ላይ ክፉ መናገር የሚችል ማንም የለምና አትከልክሉት፤የማይቃወመን እርሱ ከእኛ ጋር ነውና።]
  በእናንተ ሃሳብ አይከተለንም፣ እኛን አይመስልም እንኳ ብላችሁ ብታስቡ ከጌታ ቃል ውጭ በምንስ ስልጣን እና ስለምን እናንተ ታድያ ትከለክላላችሁ?
  [ ነገር ግን አለመታደል ሆኖ እንጂ አጋንንትን ማውጣትም ትልቅነገር አልነበረም፡፡ አጋንንትን ማውጣት የስሙን ማዳን ማመንን እንጂ ፃዲቅነትን እንኳን አይጠይቅም፡፡ከሀዋሪያት አንዱ ለሆነው፣ ጌታን አሳልፎ ለሰጠው ይሁዳም ይህን ስልጣን ጌታችን ሰጦታል፡፡
  [አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው።የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ... ስምዖን ደግሞም አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።]
  አመፀኞች ሆነው እንኳ በስሙ ትንቢት እንደሚናገሩ አጋንንት እንደሚያወጡ በስሙ ብዙ ታአምራትን እንደሚያደርጉ አስተምሯል፡፡ አጋንንትስ ለወጣላቸው እና ከዛች ጊዜ በኋላ ከክፉው ሀጥያት ለራቁ መልካም ሆነላቸው፤ ነገርግን አመፀኛ ሲሆኑ ላወጡት ምን ይበጃቸዋል?
  [በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ። ]
  ይልቁንም እርኩሳንን በስሙ ለሚያስወጡ በስሙ ለሚያስገዟቸው ሰዎች በዚህ ደስ እንዳይላቸው ይልቁንም መንግስቱን እንዲመኙ ያሳስባል፡፡
  [ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው። ጌታ ሆይ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት።እንዲህም አላቸው ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ።እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም።ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ። ]
  በልባችን ሃሳብ ክፋት ተተብትበን፣ ስለስጋ ምኞት በክፉ እጂ ወድቀን፣ በክፉው መንፈስ ተይዘን፣ ፍቅር ጠፍቶ አንዱ ባንደኛው ላይ ከሰይጣንም በላይ ጠላት ሆኖ በተነሳበት የመርገምት ዘመን ደርሰን፣ አይናችንም ልቦናችንም ታውሮ ነው እንጂ…. አጋንንትን ሊያስገዛልን ስሙ ብቻ የሚበቃ ድንቅ መካር ሃያል አምላክ እንዳለን ብናውቅ ይህ ባልገረመን፡፡
  አሁን ደግሞ እምነት ጎድሎን በስሙ አምነው በስሙ ታምነው የሚያነቁ ከርኩሳን መናፍስት አገዛዝ የሚያላቁ ጥቂት አባቶችን መናከስ ከመታመምም በላይ ነው፡፡ መታጠብ ለታጣቢው እንጂ ላጣቢው እስኪ ከቶ ምን ይፈይዳል? ለነገሩ ውጊያው ከመንፈስ ጋር እንጂ ከስጋ ጋር አይደለም፡፡ታድያ በእግዚአብሔር ስራ እየገባን ይህ እንዴት ሆነ እያልን ከምናጉረመርም፣ አገልጋዮቹን ከምናሳድ፣ ፍርድን ለእግዚአብሔር ትተን ዝም ብለን የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ብናደርግ አይሻልም?
  [ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፥ ወልድንም ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፥ አብንም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር ወልድም ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በቀር የሚያውቅ የለም አለ።]
  እራሱ የስሙ ባለቤት የሀይል ሁሉ ጌታ አሳልፎ ለሰጠው ለአስቆርቱ ይሁዳ ያልነፈገውን፣ የማይከተሉትም ቢሆኑ አጋንንትን ያወጡ ዘንድ አትከልክሏቸው ያለ፣ አመፀኞችም በስሙ አጋንንትን ሲያወጡ እስከፍርዳቸው ቀን ዝም ያላቸው ምን ያህል ትውልዱ ሁሉ በክፉው መንፈስ እንደሚጠቃ ያውቃል እና ነው ፡፡
  የምንድነው እኛ ፣የሚያድነን ስሙ ሳለ ለምን ምክንያት በሆኑት ሰወች ላይ እንበረታለን? ስለምን በህዝቡ መዳን እንከፋለን?ስለምን ሳናውቀው ለክፉው መንፈስ አጋሮች እንሆናለን?
  ይልቅስ እረኞች እንደሌሏቸው በጎች ተበትነን ያለነውን ሕዝቦች አሁንም አብዝቶ ያስበን ዘንድ በብዙም አድርጎ ይጎበኝን ዘንድ ልንለምነው ሲገባ በጥቂቶቹ ላይ ከከፋን፣ እጆቻንንም ካነሳን፣ አረማችንን ሊነቅሉና ሊኮተኩቱ በተላኩት እጆች ላይ በእሾሐችን ከበረታን፣ ካረሞቻችን ጋር ከተባበርን፣ በመከሩ ጊዜ የመከሩ ጌታ ፍሬ ባጣብን ጊዜ ካረሞቹ ጋር ወደ እሳት እንጣላለን!
  [ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።
  ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።
  በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤
  እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው።]
  ሊያድነን ሊመክረን ሊገስፀን በየዋህት መንፈስ እምቢ ካልነው እንጊዳውስ …
  [ምን ትወዳላችሁ? በበትር ወይስ በፍቅርና በየውሃት መንፈስ ልምጣባችሁን?]
  ጀሮ ያለው ይስማ!!!

  ReplyDelete
 10. [እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?]
  ስለስሙ በእውነት ለሚሰደዱት ለሚገፉት ግን …
  [ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።
  ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?
  ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ።
  እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና።
  ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥ መጽናናታችሁን ተቀብላችኋልና።
  እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ፥ ትራባላችሁና። እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ፥ ታዝናላችሁና ታለቅሱማላችሁ።
  ሰዎች ሁሉ መልካም ሲናገሩላችሁ፥ ወዮላችሁ፤ አባቶቻቸው ለሐሰተኞች ነቢያት እንዲሁ ያደርጉላቸው ነበርና።
  ነገር ግን ለእናንተ ለምትሰሙ እላችኋለሁ፥ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ ለሚጠሉአችሁ መልካም አድርጉ፥
  የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ።
  ጕንጭህን ለሚመታህ ደግሞ ሁለተኛውን ስጠው፥ መጐናጸፊያህንም ለሚወስድ እጀ ጠባብህን ደግሞ አትከልክለው።
  ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፥ ገንዘብህንም የሚወስድ እንዲመልስ አትጠይቀው።
  ሰዎችም ሊያደርጉላችሁ እንደምትወዱ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው።
  የሚወዱአችሁንማ ብትወዱ፥ ምን ምስጋና አላችሁ? ኃጢአተኞች ደግሞ የሚወዱአቸውን ይወዳሉና።
  መልካምም ለሚያደርጉላችሁ መልካም ብታደርጉ፥ ምን ምስጋና አላችሁ? ኃጢአተኞች ደግሞ ያን ያደርጋሉና።
  እንድትወስዱባቸው ተስፋ ለምታደርጉአቸው ብታበድሩ፥ ምን ምስጋና አላችሁ? ኃጢአተኞች ደግሞ በትክክል እንዲቀበሉ ለኃጢአተኞች ያበድራሉ።
  ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ ምንም ተስፋ ሳታደርጉም አበድሩ፥ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፥ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፥ እርሱ ለማያመሰግኑ ለክፉዎችም ቸር ነውና።
  አባታችሁ ርኅሩኅ እንደ ሆነ ርኅሩኆች ሁኑ።
  አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ።
  ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል።
  ደቀ መዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም፤ ፈጽሞ የተማረ ሁሉ ግን እንደ መምህሩ ይሆናል።]
  እግዚአብሔር በፀጋው ስልጣን ለሰጣችሁ፣ እንዳከበራችሁ እናንተም በስራችሁ አክብሩት፣ በፍቅር ያልሆነውን ሁሉ በፍቅር መልሱት፡፡ እንዳትሸረሽራችሁ ለክፋታቸው እና ለማትረባ እጂ መንሻቸውም በልባችሁ እና በስፍራችሁ ቦታ አትተውላት ፡፡ የመከሩ ጊዜ ደርሷል እና አብዝታችሁ ለጌታ ትርፍ ታደርጉ ዘንድ ለመልካም የሾማችሁ ሰራተኞች ናችሁ እና በከንቱው አትወሰዱ!
  [ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ፦
  በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤
  ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ።
  ሄዳችሁም መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ።
  ድውዮችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ።
  ወርቅ ወይም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ፥
  ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።
  በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የሚገባው ማን እንደ ሆነ በጥንቃቄ መርምሩ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያ ተቀመጡ።
  እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።
  ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤
  ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ።
  አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤
  በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና።
  ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ ይገድሉአቸውማል።
  በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
  በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።
  ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፥ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም።
  ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!
  እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና።
  በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።
  ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።
  ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም።
  የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል።
  እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ።
  ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤
  በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።
  ለአህዛብ መጥፎ ቢመስልም እንኳን እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
  ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።
  እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
  ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
  እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?]
  እኛ ግን አቤቱ… የምናደርገውን አናውቅም እና በቸርነትህ ይቅር በለን!

  ReplyDelete