Saturday, October 31, 2015

ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት ልትጀምር ነው

  • ለሳተላይት ሥርጭቱ 12. ብር በላይ ዓመታዊ በጀት ጸድቋል
(አዲስ አድማስ ጥቅምት 20 2008 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ፣ ምእመና ድምፅዋን የምታሰማበትና መረጃ የምትሰጥበት 24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት እንድትጀምር ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡

ከጥቅምት 12 ጀምሮ የዓመቱን የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በማካሔድ ላይ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የቴሌቪዥን አገልግሎቱን ለማስጀመር 12 ሚሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ በጀት ከትላንት በስቲያ ማጽደቁ ታውቋል፡፡


በጠቅላይ ቤተ ክህነት /ቤት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብዙኃን መገናኛ ድርጅት በሚል ተዋቅሮ ሥራ አስኪያጅ በመሠየምና እስከ 22 ሠራተኞችን በመቅጠር የሚጀምረው አገልግሎቱ፤ ዝግጅቱንና ቀረጻውን በሀገር ውስጥ በማከናወን በሳተላይት እንደሚሠራጭ ተገልጿል፡፡

በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያ ተልእኮ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ የሚመራውና ዘጠኝ አባላት ያሉት የብዙኃን መገናኛ ቦርድ፣ የሳተላይት ሥርጭት አገልግሎቱን የሚሰጠው የኮሚዩኒኬሽን ኩባንያ በመምረጥ ሥራውን ለመጀመር እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡

በሚዲያ ጥቅም፣ አሠራርና የወደፊት አቅጣጫ ለምልአተ ጉባኤው አባላት ማብራሪያ የሰጡት የቦርዱ አመራሮች፤ የሳተላይት ሥርጭቱ መካከለኛው ምሥራቅን፣ ደቡብ አውሮፓን፣ ሰሜንና ምሥራቅ አፍሪቃን እንደሚያካልልና ለተቀረው ዓለም ዝግጅቱን በኢንተርኔት በመጫን እንደሚያስተላልፍ አስረድተዋል፡፡

 በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ 50 ሚሊዮን ያላነሱ አገልጋዮችና ምእመናን ያሏት ቤተ ክርስቲያኒቱ፣ ተከታዮቿን ለማስተማርና ለመጠበቅ የምትችልበት ተጨማሪ ሚዲያ ካላመቻቸች በተለይም ተረካቢውን ወጣት ትውልድ ለመድረስ እንደሚያስቸግራት፣ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡

 የሚዲያ ጥናት እና የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴውን በማስተባበርና የውጭ ተሞክሮዎችን በመዳሰስ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩት አቡነ ሳሙኤል፣ የቴሌቪዥን አገልግሎቱ ቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረተ እምነቷን፣ ሥርዐቷን፣ ትውፊቷንና ታሪኳን ለማስተማር፤ ቅዱሳት መካናቷንና ቅርሶቿን ለማስተዋወቅ፤ ለጥናትና ምርምር ለማነሣሣት፤ በየአህጉረ ስብከቱ የተሠሩ መልካም ሥራዎችን በማቅረብ የምእመኑን ድጋፍ ለማግኘት እንደሚረዳትሚዲያ እና ዓለምአቀፋዊ አስተሳሰብበሚል ርእስ ባቀረቡት ጽሑፍ አስረድተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment